✍️- ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለሠምረ ጊዮርጊስ ፲፩ ልጆች ወለደችለት ከነዚህም መካከል ፱ ወንዶች፣ ፪ቱሴቶች ነበሩ።(ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘመስከረም -ቊጥር- ፲፬) ልጆቿንም ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች በክብርና በሥርዓት አሳደገቻቸው።
✍️- ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትዳሯ ሰላማዊነት፣የባሏ አክብሮትና ፍቅር፣የልጆቿ መብዛት ፣የሀብትና ንብረቷ መድለብ እየሠመረ ቢሄድም የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልብ ግን የሚያስበው ግን ምናኔ ነበር።ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ፣ከዚያም በኋላ ልብሰ ምንኲስናዋን፣ ማለትም ቆቧን፣ ቀሚሷን፣ አጽፏን፣መታጠቂያዋን፣ አዘጋጀች።
✍️ ያልተለመደ ነገር ሲደረግ የተመለከቱት ቤተሰቦቿ ለምን እንደ ምታዘጋጀው ፣ለጠየቋት ጥያቄ " #ሃይማኖት ያስተማሩኝ አባቴ ልብስ አልቆባቸዋል፣ሲሉ ሰምቼ ለእርሳቸውም ነው የማዘጋጀው ፣"አለቻቸው።
ከዚህ ላይ ሃይማኖታዊ ጥበብ ያልተከሰተላቸው አስመሳዮች ለምን የሌላ ነው አለች" ሊሉ ይችላሉ።ይህ ሥርዓት ግን ለ፪ ነገር ይጠቅማል።
፩•የምናኔ ጉዞ ገና ሳይጀመር በውዳሴ ከንቱ ላለመጠለፍ፣
፪•ይህን ርምጃዋን ዲያብሎስ በተለያዩ ሰዎች አድሮ ሊያደናቅፈው ስለሚችል ከዓላማዋ ሊገታት ስለሚችል መልካም ጥበብ ነው።በሌላ በኩል ልማደ መጻሕፍትም ነው።
-✍️ ከዕለታት አንድ ቀን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ አገልጋዮችን " ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሂድ" ብላ ይዛቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደች ።የምናኔው መጀመሪያ ነበር።
✍️- ከዚያም ቤተ ክርስቲያን ጥቂት እንደምትቆይ ለቤተሰቦቿ አንዲት ፣ሠራተኛና አንድ ሕፃን ብቻ አስቀርታ
ሌሎችን አሰናብታ ምናኔው ተጀመረ፣የወላድ መናኝ የሚያልፈውን በማያልፈው ዓለም ለመለወጥ ልጇን አዝላ እግሬ አውጭኝ ብላ ገሠገሠች።እግሮቿ በደም ታጠቡ፣የራስ ፀጒሯ ተላጭቶ ወደቀ።የገዳማውያን አለባበሷን ለብሳ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገባች።ማቴ 10÷37 በተግባር ላይ ሲተረጎም ተመለከትን።
✍️የተጋድሎ ሕይወቷ እየቀጠለ ኼዶ ከመከራዋ ብዛት ከገድሏ ጽናት ሰውነቷ ተበሳስቶ የዓሣ መመላለሻ እስኪሆን ድረስ ከባሕሩ ገብታ ወደ ግራና ቀኝ ሳትል ፲፪ ዓመት ሙሉ በጣና ባሕር ውስጥ ቆማ ትጸልይ ዘንድ ኃይለ እግዚአብሔር ተሰጣት።፲፪ ዓመት ሙሉ በባሕር ውስጥ መቆየት የሚቻለው ማነው? የሚል ጎደሎ እምነት ያለው ወገን ካለ: ባሕረ ኤርትራ እንደ ግድግዳ ቆሞላቸው እስራኤላውያን ማሻገር ይችላሉ ወይ?" ለሚያምን ሁሉ ይቻላል"(ማር 9÷22)
✍️መሴ በሲና ተራራ 40መዓልትና 40 ሌሊት ያለምግብ መቆየት ይችላል ወይ?ሠለስቱ ደቂቅ እሳት ውስጥ ገብተው ሳይቃጠሉ መውጣት ይችላሉ ወይ? ብሎ መጽሐፍ ቅዱስን መጠየቁ የተሻለ ይሆናል።
✍️" ከአቤል ጀምሮ እስከ ዛሬ የሞቱት ከዛሬም በኋላ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚሞቱትን አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው "አለችው ( ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘግንቦት -ቊጥር፲፯ )
√ የአማላጅነት ጸጋዋ:
የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ሕይወት የቅድስና ሕይወት በመሆኑ ለአማላጅነት የተመቸ ነው።
✍️ጌታ ምን አደርግልሽ ዘንድ ትሻለሽ? አላት ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ " አቤቱ ፈጣሪየ ሆይ ! ፈቃድህስ ቢሆን የአዳም ልጆችን ከሥቃይ ከኵነኔ ይድኑ ዘንድ ዲያብሎስን ይቅር ትለው ወይም ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ:የኃጥእን መመለሱን እንጂ የጥፋቱን አትወድምና አለችው ፣ የምለምንህ ወይም ማረው የምልህ ዲያብሎስን ወድጄው አይደለም ነገር ግን እሱ ከተማረ በአዳም ልጆች ላይ ሥቃይና ኵነኔ ሊኖር አይችልም ብየ በመገመት ነው እንጂ " ( ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘግንቦት -ቊጥር36 -38 )ይህን ልመና ጌታችን የሚያስደንቅ ልመና ብሎታል።ይህ መልካም ሐሳብ የሚመነጨው የእምነት ፍቅር ካላቸው ሰዎች ልብ ውስጥ ብቻ ነው።
- የዲያብሎስን ተንኮል የሚያውቅ መድኃኔዓለም የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን የአማላጅነት ነጻነት አልገደበውም።
√ የተሰጣት ቃል ኪዳን
✍"ሥጋሽን እንደ እናቴ እንደ ድንግል ማርያም ሥጋ እቀድሰዋለሁ" ማለት የእመቤታችን ሥጋ በኅሊና አምላክ የተቀደሰ ሲሆን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ሥጋ ደግሞ በገድል ፣በትሩፋት ተቀጥቅጦ ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ያመልክታል።ነሐሴ 24 የዕረፍት መታሰቢያዋ ይከበራል።
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ወርቃማዋ ፎገራ(The Golden lans scape of Fogera) በደሴተ ጓንጉት ደብረ ምሕረት ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ክብረ በዓል ዓመታዊ በዓሏ በየዓመቱ ግንቦት ፲፪ ቀን በድምቀት ይከበራል፡፡ከወረታ ከተማ በስተ ምዕራብ በኩል 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ጣና ዳር ዋገጠራ ቀበሌ ትገኛለች ፡
- የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በረከቷ ፣ረድኤቷ ፣አማላጅነቷ አይለየን!
#ምንጭ
- ሐመር መጽሔት ግንቦት /ሰኔ 1997ዓ/ም
- ነገረ ቅዱሳን -፪ ( ገጽ-68)
- ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ(በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት- 1992ዓ/ም )
- ልሳነ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ ሚያዝያ 7ቀን 1993 ቁ 53
https://www.tgoop.com/tmhrtegeeze

ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምን ያክል ያውቃሉ ❓
ክፍል ፩
ቤተክርስቲያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ዋጅቶ የመሠረታት፣ በክርስቶስ ክርስቲያን ለተባልን በሙሉ መሰብሰቢያችን የተቀደሰች ቤታችን ናት፡፡ ቤተክርስቲያን ስንልም ሕንፃ ቤተክርስቲያን፣ የክርስቲያን ወገን፣ የምእመናን አንድነት ወይንም ማኅበረ ምእመናን እንዲሁም እያንዳንዱ ምእመናን ማለታችን ነው፡፡
ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን
ቅድስት ቤተክርስቲያን አምልኮተ እግዚአብሔር የምንፈጽምባት የእግዚአብሔር ማደሪያ ናት፤ ቅድስት ቤተክርስቲያን ቅዱሳን መላእክት ፈጣሪያቸውን የሚያገለግሉባት የክብሩ መገለጫ የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ምሳሌ በመሆኗ አባቶቻችን በአሠራሯ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያደርጉ ሲሆን የሕንፃዋ ቤተክርስቲያን አሠራርም በሦስት ዓይነት ቅርጽ ሊሆን ይችላል፡፡
፩.ክብ
በፊልጵስዩስ የተሠራችው የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ክብ ቅርጽ ነበራት፡፡ የሙሉ ክብነቷ ትርጓሜም የፍጹምነቷ ምልክት ነው፤ በዚህም መሠረት በአብዛኛው ቤተ ክርስቲያናት በክብ ቅርጽ ይታነጻሉ፤ የዚህ ዓይነት ሕንጻ ቤተክርስቲያንም ዙሪያው ክብ ሆኖ ውስጡ በሦስት የተከፈለ ሰሆን ሦስት በሮችም አሉት፤ ቤተ ንጉሥ ቅርጽም ይባላል፤ አንድ ጉልላት ሲኖረው ከጉልላቱም ላይ መስቀል ይኖራል፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሣሉት ቅዱሳንም ዓይንና ፊታቸው ክብ ሆኖ የሚሣለው ሃይማኖትን ከምግባር አዋሕደው የተገኙና ከሕግ በላይ የሆኑ ፍጹማን መሆናቸውን ለመግለጽ ነው፡፡
፪.ሰቀላማ ወይም ሞላላ ቅርጽ ማዕዘን ቅርጽ
የዚህ ዓይነት የቤተክርስቲያን ሕንጻ አሠራር ጠቢቡ ሰሎሞን ያሠራውን ቤተመቅደስ መሠረት ያደረገ ነው፤ ለዚህ ምሳሌ በሀገራችን የአክሱም ጽዮን፣ የጎንደሩ ደብረ ብርሃን ሥላሴ እና ደብረ ዳሞ፣ ዐፄ ዮሐንስ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ያሠሩት የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ዐሥራ ስምነት ጉልላት ያላቸውን ሰቀላማ ቅርጽ ያላቸውን አብያተ ቤተክርስቲያናትን መጥቀስ ይቻላል፤ በሞላላ ቅርጽ የታነፁ አብያተ ቤተክርስቲያናት መሠረታቸው የመስቀል ቅርጽ ያለው በመሆኑ በዚህ ቅርጽ የመታነፃቸው ምሥጢር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት በመስቀል ላይ የፈጸመውን የድኅነት ሥራ እንድናስብበት ነው፡፡ ለሰው ልጆች ሲል መከራ ተቀብሎ፣ ተሰቅሎና ሞትን ድል አድርጎ ማረጉን ያመለክታል፡፡ ከላይ የጠቀስናቸው ሰቀላማ ቅርጽ አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያንና ምስካየ ኀዙናን መድኃኔዓለም ገዳማት ለሰቀላማ ቅርጽ አብያተ ክርስቲያናት በምሳሌነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
፫. ዋሻ ቅርጽ
የዚህ ዓይነት ሕንፃ ቤተ ክርስቶያናት ሰማዕታት ከዓላማውያን ነገሥታት ሸሽተው በዋሻ ሲሸሸጉ የጀመሩት አሠራር ዓይነት ነው፡፡ አንድ በርም አለው፤ በአብዛኛውም ጊዜ በውስጡ ያሉትን ክፍሎች በመጋረጃ ይከፈላል፡፡ ሆኖም ግን ጉልላት የለውም ተራራ በመፈልፈል በዋሻ ውስጥ ሲሆን ለብቻው የቆመ ድንጋይን (አለትን) በመፈልፈል ሊሠራ ይችላል ምሳሌ፡-አቡነ ሀብተ ማርያም ገዳም፣አዳዲ ማርያም፣የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ምሳሌዎች ናቸው፡፡
አንድነታቸውና ልዩነታቸው
አንድነታቸው
ሁሉም አብያተ ቤተክርስቲያናት ቅኔ ማኅሌት፣ ቅድስትና መቅደስ አላቸው፡፡ በውስጣቸው የሚፈጸመው የቅዳሴ፣ የማኅሌት፣ የሰዓታት፣ የጸሎት ሥርዓት አንድ ዓይነት ነው
ልዩነታቸው
ሰቀላማና ክብ ቅርጽ አብያተ ቤተክርስቲያናት ጉልላት ሲኖራቸው ቅርጽ ቤተክርስቲያን ዋሻ ግን ጉልላት የለውም፡፡ ሰቀላማና ዋሻ ቅርጽ በመጋረጃና በደረጃ ሲከፈሉ ክብ ቅርጽ ግን በግድግዳ ይከፈላል፡፡ በሰቀላማና ዋሻ ቅርጽ የሴቶችና የወንዶች መቆሚያ ሲኖረው የሚከፈለውም በመጋረጃ ነው፡፡ ነገር ግን በክብ ቅርጽ ግን የተለያየ ቦታ አላቸው፡፡
የቤተ ክርስቲያን ክፍሎችና ትርጓሜያቸው
ቤተ ክርስቲያን ሦስቱ ክፍሎች ያሏት ሲሆን እነዚህም ቅኔ ማኅሌት፣ ቅድስትና መቅደስ በመባልም ይታወቃሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ክፍሎች ክፍሎቿም ጎልተው የሚታዩት በክብ ቅርጽ በታነፀ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡ የቤተክርስቲያን ክፍሎችም ሦስት የሆኑበት ምክንያት አንደኛው በሦስቱ ዓለማተ መላእክት ማለትም በኢዮር፣በራማ፣በኤረር ምሳሌ መሆኑ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ በሦስቱ መዓረጋት ክህነት ዲቁና፣ቅስና፣ኤጲስቆጶሳት ምሳሌ ሲሆን በሦስቱ ጾታ ምእመናን፡ ማለትም ካህናት፣ ወንዶች፣ ሴቶች የሦስቱ ኆኅተ ገነት (የገነት በሮች) ምሳሌም በመሆኑ ነው፡፡
አገልግሎታቸው
፩. ቅኔ ማኅሌት
በዚህ ክፍል ውስጥ መዘምራን፣ ደባትር ካህናት ማኅሌተ እግዚአብሔር ያደርሱበታል፡፡ በመስዕ (ሰሜን ምሥራቅ) ንዑሰ ማዕዘን በኩል ቀሳውስትና ዲያቆናት በመንፈቀ ሌሊት ሰዓታት በነግህ ኪዳን ያደርሱበታል፤ ለጥምቀት ለቊርባን ያልበቁ በትምህርት በንስሐ የሚፈተኑ /ንዑሰ ክርሰቲያን/ ‹‹ፃኡ ንዑሰ ክርስቲያን›› እስከሚባል ድረስ የሚቆዩበት ክፍልም ነው፤ ወንዶች ምእመናንም ቆመው ያስቀድሱበታል፤ በሌብ /ደቡብ ምሥራቅ/ ንዑስ ማእዘን በኩል የሚገኘው ቦታ የሴቶች መቆሚያ ነው፡፡ ከውጭ ወደ ቤተ መቅደስ ስንገባ የምናገኘው የመጀመሪያው ክፍል ሲሆን ሦስት በሮችም አሉት፤ የካህናት፣ የወንዶችና የሴቶች ምእመናት መግቢያዎች ናቸው፡፡
፪.ቅድስት
የቅድስት ቤተክርስቲያን ማእከላዊ ክፍል ቅድስት ይባላል፡፡ ካህናት በድርገት ጊዜ ምእመናንን የሚያቆርቡበት ክፍል ሲሆን በስብከተ ወንጌል ጊዜም መምህራን ቆመው ያስተምሩበታል ክፍል፡፡ በተክሊልና በቊርባን አንድ ለሚሆኑ ሙሽሮች ጸሎት የሚደርስበትና በካህናት እጅ የሚባረኩበት በዚህ ክፍል ውስጥ ነው፡፡ በስቅለት ዕለት ሥርዓተ ጸሎት ይፈጸምበታል፤ በምዕራብ በኩል ቆሞሳት፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስት ይቆሙበታል፤ በሰሜን መነኮሳትና የሚቈርቡ ወንዶች ምእመናን ይቆሙበታል፤ በደቡብ የሚቆሙት ደናግል መነኮሳይያት፣ የቀሳውስትና የዲያቆናት ሚስቶች ናቸው፤ በምሥራቅ በምዕራብ በሰሜንና በደቡብ ዐራት በሮች ይኖሩታል፤ ነገር ግን የማይቆርቡ ምእመናን በዚህ ክፍል ቆመው አያስቀድሱም፡፡
፫ መቅደስ
በብሉይ ኪዳን ቅድስተ ቅዱሳን በሚል ስያሜ ይጠራ የነበረው የቃል ኪዳኑ ታቦት የሚገኝበት ክፍል መቅደስ ነው፡፡ ንዋያተ ቅድሳትም ከመንበረ ታቦቱ ጋር በዚህ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በምዕራብ በሰሜንና በደቡብ ሦስት በሮች ሲኖሩት እያንዳንዱ በር በመንጦላዕት ወይም በመጋረጃ የሚጋረድ ነው፡፡ ከዲያቆናትና ሥልጣነ ክህነት ካላቸው በቀር ወደ መቅደሱ ማንም መግባት አይችልም፡፡ በዚህ ክፍል ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት ቆመው ያስቀድሱበታል፤ የጌታችን ሥጋና ደም የሚፈተተው በዚሁ ክፍል ውስጥ ነው፡፡
በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ የሚሠሩና አገልግሎት የሚሰጡ ቤቶች
ቤተልሔም፡- በቤተክርስቲያን ምሥራቅ አቅጣጫ ዲያቆናቱ ለመሥዋዕት የሚሆነውን ኅብስትና ወይን የሚያዘጋጁበት ሁለተኛ ቤት ‹ቤተ ልሔም› ይባላል፡፡ ጌታችን የተወለደበትን ቤተ ልሔም ያስታውሰናልና፤ መቅደሱ ደግሞ የቀራንዮ ምሳሌ ነው
የግብር ቤት፡– ለመሥዋዕት የሚቀርበው (መገበሪያ) የሚሰየምበት ሌላኛው ክፍል ነው፡፡ የተገነባውም በምሥረቅ አቅጣጫ ነው፡፡
ዕቃ ቤት፡– የቤተ ክርስቲያን ንዋተ ቅድሳት የሚቀመጡበት ዕቃ ቤት ይባላል፡፡ የቤተ ክርስቲያን መገልገያ የሆኑት አልባሳትም ሆነ መጻሕፍትም የሚቀመጡት በዚህ ቤት ውስጥ ነው፡፡ (ሕዝ. ፵፬፥፲፱)
ክርስትና ቤት:-- ሥርዓተ ጥምቀት የሚፈጸምበት ቤት ነው፡፡
ክፍል፪ ይቀጥላል......
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE

Telegram
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ
@EOTCY
ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት?
➢ የተለያዩ ትምህርቶችን
➢ መጣጥፎችን
➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን
➢ ተከታታይ ትምህርቶችን
➢ ብሒለ አበው
➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን
አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 1 ቀን 2015ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት እና መንፈሳዊ ዕድገት ትኩረት በመስጠት ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም ጉልላት እንደመሆኗ ሰላም መሠረታዊ ተልእኮዋ ነው፡፡ ስለዚህ ወቅታዊውን ችግር ታሳቢ በማድረግ በመላው አገራችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ካሉ ተቋማት ጋራ የሚሠራ፣ በሀገሪቱ መንግሥትም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የሚኖረው የሰላም ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
2. በትግራይ ክልል በሚገኙት አህጉረ ስብከት ተቋርጦ የነበረው መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ግንኙነትን በተመለከተ ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ ተሠይሞ በሥራ ላይ የሚገኘው ልዑክ የጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲቀጥል የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትን በማነጋገር ተልዕኮውን እንዲፈጽም ምልዓተ ጉባኤው መመሪያ ሰጥቷል፡፡
3. በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል የሚገኙ ወገኖቻችን ያሉበትን ከፍተኛ ችግር ታሳቢ በማድረግ አስቸኳይ የሆነ ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ሃያ ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4. በወቅታዊ ችግር ምክንያት በመላው ሀገራችን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ሁሉ በአጠቃላይ ችግሮቹን በጥናት በመለየት፣ ቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን ልጆቿን በማስተባበር ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ድጋፍ፣ የማጽናናትና የመጎብኘት መርሐ-ግብሮች እንዲደረጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
5. መቀሌ የሚገኘው የቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የሠራተኞችን ደመወዝና የሥራ ማስኬጃ በጀት እንዲለቀቅና በ2016 በጀት ዓመት ተማሪዎችን በመቀበል መደበኛ የሆነ የመማር ማስተማሩ የሥራ ሂደት እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
6. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጪው ዐሥር ዓመታት የመንፈሳዊ እና ዘላቂ ልማት ግብ መሪ ዕቅድ በማጽደቅ በሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅሮች ተግባራዊ እንዲደረግ ጉባኤው ወስኗል፡፡
7. የቤተ ክርስቲያናችን ቀደምት አበው በቅድስት ሀገረ ኢየሩሳሌም ገዳማት እንዲስፋፉ ሁሉ የነሱን አሰረ ፍኖት በመከተል በቅርቡ በሰሜን አሜሪካ ካልፎርኒያ ግዛት የተቋቋመው ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም እንዲጠናከር፤ በተጨማሪም በጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የአስተዳደር፣ የጽሙና፣ የትምህርትና የምርምር ማዕከል እንዲመሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ አስተላልፏል፡፡
8. በኦሮምያ ክልል በሚገኙ አህጉረ ስብከት ተፈጥሮ በነበረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በአህጉረ ስብከትና በአብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት ስለተቋረጠ፣ በርካታ ምእመናንና ካህናት በእስርና እንግልት ላይ ስለሚገኙ በዚሁ መነሻነት ችግሮች እንዲቀረፉና ወደ መደበኛው የአሠራር መዋቅር እንዲመለስ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን በመሠየም ከፌዴራልና ከኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመወያየት ችግሮች እንዲፈቱ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
9. የመንፈሳዊ ኮሌጆች መከፈት እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማጠናከር በተመለከተ በኢሉ አባቦራ የመቱ ፈለገ ሕይወት የነገረ መለኮት መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲከፈት የተፈቀደ ሲሆን በሌሎች አህጉረ ስብከት ሊከፈቱ የታሰቡ ኮሌጆችን እና የአብነት ት/ቤቶችን መሠረታዊ ጥናት ተደርጎ ለ2016 ዓ.ም. የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
10. ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትን በተመለከተ ክፍት በሆኑና በተደራቢነት በተያዙ፣ ጉልህና አንገብጋቢ ችግር ባለባቸው በኦሮምያ ክልልና በደቡብ ክልል ባሉ አህጉረ ስብከት ላይ 9 ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስመራጭ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡ ወደፊትም ተደርበው በተያዙና አስፈላጊ በሆኑ አህጉረ ስብከት እንደአስፈላጊነቱ በመንበረ ፓትርያርክ ተጠንቶ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በመጨረሻም በሀገራችን በአንዳንድ ቦታዎች የሚታዩትን አላስፈላጊ ግጭቶች የዜጐች መፈናቀል፣ ስደት ተወግዶ ሁሉም ዜጋ በሀገሩ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በአንድነት እንዲኖር፤ ለማድረግ ግጭቶችና አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡
እንዲሁም በመላው ዓለም ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ ሰላም እና ዕርቅ እንዲሰፍን በመመኘት እና በመጸለይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ሲያካሂድ የቆየውን ጉባኤ በጸሎት አጠናቋል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

ትምህርተ ኦርቶዶክስ
ውድ የ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ቻናል ተከታዮች በሙሉ በዚህ ቻናል ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን በቻ የምንለጥፍ መሆኑን ለመግለፅ እነዳለሁ ለሌሎችም በማጋራት (ሼር ) አገልግሎቱን ይደግፉ
እግዱ ተነሳ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ፤ በማህበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ጥሎት የነበረውን #ጊዜያዊ እግድ ዛሬ ማንሳቱን አሳውቋል።

# ETHIOPIA | የሚደንቅ! ... ስንቶቻችን እናውቃለን?
* እነሆ ትርጉማቸው ...
ሀ ማለት ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ማለት ነው፡፡
ሐ ማለት ሐመ ወሞተ በእንቲአነ ማለት ነው፡፡
ኀ ማለት ኀብአ ርእሶ ማለት ነው፡፡
ሁ ማለት ኪያሁ ተወከሉ ማለት ነው፡፡
ሑ ማለት ሰብሑ ለሥመ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኁ ማለት እኁዝ አቅርንቲሁ ማለት ነው፡፡
ሂ ማለት አስተይዎ ብሂዐ ማለት ነው፡፡
ሒ ማለት መንጽሒ ማለት ነው፡፡
ኂ ማለት ዘልማዱ ኂሩት ማለት ነው፡፡
ሃ ማለት ሃሌ ሉያ ማለት ነው፡፡
ሓ ማለት መፍቀሬ ንስሓ ማለት ነው፡፡
ኃ ማለት ኃያል በኃይሉ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሄ ማለት በኵለሄ ሀሎ ማለት ነው፡፡
ሔ ማለት ሔት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኄ ማለት ኄር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ህ ማለት ህልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሕ ማለት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኅ ማለት ኅብስት ለርኁባን ማለት ነው፡፡
ሆ ማለት ኦሆ ይቤ ወመጽአ ማለት ነው፡፡
ሖ ማለት ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኆ ማለት ኆኅተ ገነት ወልድ ማለት ነው፡፡
ኈ ማለት ኈለቈ አዕፅምትየ ማለት ነው፡፡
ኋ ማለት ሰንኋቲ ሥጋ ሰብእ ማለት ነው፡፡
ኌ ማለት ይኌልቍ አሥዕርተ ማለት ነው፡፡
ኊ ማለት በኊበኊ ሥጋ አዳም ማለት ነው፡፡
ኍ ማለት ዑጽፍት ወኍብርት ማለት ነው፡፡
ለ ማለት ለብሰ ሥጋ ዚአነ ማለት ነው፡፡
ሉ ማለት ሣህሉ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሊ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ላ ማለት ላሜድ ልዑል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሌ ማለት መቅለሌ ዕጹብ ማለት ነው፡፡
ል ማለት መስቀል ዘወልደ አብ ማለት ነው፡፡
ሎ ማለት ዘሀሎ እምቅድም ማለት ነው፡፡
መ ማለት መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሙ ማለት ሙፃአ ሕግ ማለት ነው፡፡
ሚ ማለት ዓለመ ኀታሚ ማለት ነው፡፡
ማ ማለት ፌማ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሜ ማለት ሜም ምዑዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ም ማለት አምላከ ሰላም ማለት ነው፡፡
ሞ ማለት ሞተ በሥጋ ማለት ነው፡፡
ሰ ማለት ሰብአ ኮነ ከማነ ማለት ነው፡፡
ሠ ማለት ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ማለት ነው፡፡
ሱ ማለት ፋሲልያሱ ማለት ነው፡፡
ሡ ማለት መንበረ ንግሡ ማለት ነው፡፡
ሲ ማለት ዘይሴሲ ለኲሉ ዘሥጋ ማለት ነው፡፡
ሢ ማለት ሢመተ መላእክት ማለት ነው፡፡
ሳ ማለት ሳምኬት ስቡሕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሣ ማለት ሣህል ወርትዕ ማለት ነው፡፡
ሴ ማለት ለባሴ ሥጋ ማለት ነው፡፡
ሤ ማለት ሤሞሙ ለካህናት ማለት ነው፡፡
ስ ማለት ልብስ ለዕሩቃን ማለት ነው፡፡
ሥ ማለት ንጉሥ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሶ ማለት መርሶ ለአሕማር ማለት ነው፡፡
ሦ ማለት አንገሦ ለአዳም ማለት ነው፡፡
ረ ማለት ረግዓ ሰማይ ወምድር በጥበቡ ማለት ነው፡፡
ሩ ማለት በኵሩ ለአብ ማለት ነው፡፡
ሪ ማለት ዘይሰሪ አበሳ ማለት ነው፡፡
ራ ማለት ጌራ መድኃኒት ማለት ነው፡፡
ሬ ማለት ሬስ ርኡስ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ር ማለት ርግብ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሮ ማለት ፈጠሮ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቀ ማለት ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል ወውእቱ ቃል ኀበ
እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቁ ማለት ጽድቁ ለኃጥእ ማለት ነው፡፡
ቂ ማለት ፈራቂሁ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቃ ማለት ቃልየ አጽምዕ ማለት ነው፡፡
ቄ ማለት ሰዋቄ ኃጥአን ማለት ነው፡፡
ቅ ማለት ጻድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቆ ማለት ቆፍ ቅሩብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቈ ማለት ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን ማለት ነው፡፡
ቊ ማለት ቊርባነ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ቍ ማለት ቍየጺሁ አዕማደ ባላቅ ማለት ነው፡፡
ቌ ማለት ቀነተ ሐቌሁ ለኀጺበ እግረ አርዳኢሁ ማለት
ነው፡፡
በ ማለት በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኵሉ ዓለም ማለት ነው፡፡
ቡ ማለት ጥበቡ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቢ ማለት ረቢ ነአምን ብከ ማለት ነው፡፡
ባ ማለት ባዕድ እምአምአማልክተ ሐሰት ማለት ነው፡፡
ቤ ማለት ቤት ባዕል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ብ ማለት ብርሃነ ቅዱሳን ፍጹማን ማለት ነው፡፡
ቦ ማለት አልቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌሁ ማለት ነው፡፡
ተ ማለት ተሰብአ ወተሠገወ እማርያም እምቅድስት
ድንግል ማለት ነው፡፡
ቱ ማለት መዝራዕቱ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቲ ማለት ተአኳቲ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ታ ማለት ታው ትጉህ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቴ ማለት ከሣቴ ብርሃን ማለት ነው፡፡
ት ማለት ትፍሥሕት ወሐሤት ማለት ነው፡፡
ቶ ማለት ነአምን ልደቶ ለክርስቶስ ማለት ነው፡፡
ነ ማለት ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ማለት ነው፡፡
ኑ ማለት ዛኅኑ ለባሕር ማለት ነው፡፡
ኒ ማለት ኰናኒ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ና ማለት መና እስራኤል ማለት ነው፡፡
ኔ ማለት ወጣኔ ኵሉ ማለት ነው፡፡
ን ማለት መኰንን እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኖ ማለት ኖላዊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
አ ማለት አአኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዐ ማለት ዐቢይ እግዚአብሔር ወብዙኅ አኮቴቱ ማለት
ነው፡፡
ኡ ማለት ሙጻኡ ለቃል ማለት ነው፡፡
ዑ ማለት ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኢ ማለት ለሊሁ ተንሣኢ ወለሊሁ አንሣኢ ማለት ነው፡፡
ዒ ማለት ለሊሁ ሠዋዒ ወለሊሁ ተሠዋዒ ማለት ነው፡፡
ኣ ማለት ኣሌፍ ፈጣሬ ኵሉ ዓለም ቀዳማይ ወደኃራዊ
ማለት ነው፡፡
ዓ ማለት ዓይነ ኵሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ ማለት ነው፡፡
ኤ ማለት አምጻኤ ዓለማት ማለት ነው፡፡
ዔ ማለት ዔ ዐቢይ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
እ ማለት እግዚአብሔር እግዚእ ማለት ነው፡፡
ዕ ማለት ብፁዕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኦ ማለት እግዚኦ ማለት ነው፡፡
ዖ ማለት ሞዖ ለሞት ወተንሥአ ማለት ነው፡፡
ከ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኩ ማለት ዐርኩ ለመርዓዊ ማለት ነው፡፡
ኪ ማለት ኪያሁ ንሰብክ ማለት ነው፡፡
ካ ማለት ካፍ ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኬ ማለት ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማእከለ አኃው ማለት
ነው፡፡
ክ ማለት ክብሮሙ ለመላእክት ማለት ነው፡፡
ኮ ማለት ዘረዳእኮ ለአብርሃም ማለት ነው፡፡
ኳ ማለት ኳሄላ አይሁድ ወልድ ማለት ነው፡፡
ኰ ማለት ኰናኔ ዓለም ማለት ነው፡፡
ኵ ማለት ኵርጓኔ ቅዱሳን ማለት ነው፡፡
ኲ ማለት ኲናተ ጌዴዎን ዘቈልቈለ ላዕለ ስሳ ምዕት ሐራ
በምዕር ማለት ነው፡፡
ኴ ማለት ወይኴንን እምባሕር እስከ ባሕር ማለት ነው፡፡
ወ ማለት ወረደ እምሰማያት ማለት ነው፡፡
ዉ ማለት ጼዉ ለምድር ማለት ነው፡፡
ዊ ማለት ናዝራዊ ሐዊ ማለት ነው፡፡
ዋ ማለት ዋው ዋሕድ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዌ ማለት ዜናዌ ትፍሥሕት ማለት ነው፡፡
ው ማለት ሥግው ቃል ማለት ነው፡፡
ዎ ማለት ቤዘዎ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ዘ ማለት ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዙ ማለት ምርጒዙ ለሐንካሳ ማለት ነው፡፡
ዚ ማለት ናዛዚ ማለት ነው፡፡
ዛ ማለት ዛይ ዝኲር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዜ ማለት አኃዜ ዓለም በእራኁ ማለት ነው፡፡
ዝ ማለት ሐዋዝ ሕገ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዞ ማለት አግአዞ ለአዳም ማለት ነው፡፡
የ ማለት የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኀይለ ማለት ነው፡፡
ዩ ማለት ዕበዩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
* እነሆ ትርጉማቸው ...
ሀ ማለት ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ማለት ነው፡፡
ሐ ማለት ሐመ ወሞተ በእንቲአነ ማለት ነው፡፡
ኀ ማለት ኀብአ ርእሶ ማለት ነው፡፡
ሁ ማለት ኪያሁ ተወከሉ ማለት ነው፡፡
ሑ ማለት ሰብሑ ለሥመ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኁ ማለት እኁዝ አቅርንቲሁ ማለት ነው፡፡
ሂ ማለት አስተይዎ ብሂዐ ማለት ነው፡፡
ሒ ማለት መንጽሒ ማለት ነው፡፡
ኂ ማለት ዘልማዱ ኂሩት ማለት ነው፡፡
ሃ ማለት ሃሌ ሉያ ማለት ነው፡፡
ሓ ማለት መፍቀሬ ንስሓ ማለት ነው፡፡
ኃ ማለት ኃያል በኃይሉ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሄ ማለት በኵለሄ ሀሎ ማለት ነው፡፡
ሔ ማለት ሔት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኄ ማለት ኄር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ህ ማለት ህልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሕ ማለት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኅ ማለት ኅብስት ለርኁባን ማለት ነው፡፡
ሆ ማለት ኦሆ ይቤ ወመጽአ ማለት ነው፡፡
ሖ ማለት ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኆ ማለት ኆኅተ ገነት ወልድ ማለት ነው፡፡
ኈ ማለት ኈለቈ አዕፅምትየ ማለት ነው፡፡
ኋ ማለት ሰንኋቲ ሥጋ ሰብእ ማለት ነው፡፡
ኌ ማለት ይኌልቍ አሥዕርተ ማለት ነው፡፡
ኊ ማለት በኊበኊ ሥጋ አዳም ማለት ነው፡፡
ኍ ማለት ዑጽፍት ወኍብርት ማለት ነው፡፡
ለ ማለት ለብሰ ሥጋ ዚአነ ማለት ነው፡፡
ሉ ማለት ሣህሉ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሊ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ላ ማለት ላሜድ ልዑል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሌ ማለት መቅለሌ ዕጹብ ማለት ነው፡፡
ል ማለት መስቀል ዘወልደ አብ ማለት ነው፡፡
ሎ ማለት ዘሀሎ እምቅድም ማለት ነው፡፡
መ ማለት መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሙ ማለት ሙፃአ ሕግ ማለት ነው፡፡
ሚ ማለት ዓለመ ኀታሚ ማለት ነው፡፡
ማ ማለት ፌማ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሜ ማለት ሜም ምዑዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ም ማለት አምላከ ሰላም ማለት ነው፡፡
ሞ ማለት ሞተ በሥጋ ማለት ነው፡፡
ሰ ማለት ሰብአ ኮነ ከማነ ማለት ነው፡፡
ሠ ማለት ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ማለት ነው፡፡
ሱ ማለት ፋሲልያሱ ማለት ነው፡፡
ሡ ማለት መንበረ ንግሡ ማለት ነው፡፡
ሲ ማለት ዘይሴሲ ለኲሉ ዘሥጋ ማለት ነው፡፡
ሢ ማለት ሢመተ መላእክት ማለት ነው፡፡
ሳ ማለት ሳምኬት ስቡሕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሣ ማለት ሣህል ወርትዕ ማለት ነው፡፡
ሴ ማለት ለባሴ ሥጋ ማለት ነው፡፡
ሤ ማለት ሤሞሙ ለካህናት ማለት ነው፡፡
ስ ማለት ልብስ ለዕሩቃን ማለት ነው፡፡
ሥ ማለት ንጉሥ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሶ ማለት መርሶ ለአሕማር ማለት ነው፡፡
ሦ ማለት አንገሦ ለአዳም ማለት ነው፡፡
ረ ማለት ረግዓ ሰማይ ወምድር በጥበቡ ማለት ነው፡፡
ሩ ማለት በኵሩ ለአብ ማለት ነው፡፡
ሪ ማለት ዘይሰሪ አበሳ ማለት ነው፡፡
ራ ማለት ጌራ መድኃኒት ማለት ነው፡፡
ሬ ማለት ሬስ ርኡስ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ር ማለት ርግብ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሮ ማለት ፈጠሮ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቀ ማለት ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል ወውእቱ ቃል ኀበ
እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቁ ማለት ጽድቁ ለኃጥእ ማለት ነው፡፡
ቂ ማለት ፈራቂሁ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቃ ማለት ቃልየ አጽምዕ ማለት ነው፡፡
ቄ ማለት ሰዋቄ ኃጥአን ማለት ነው፡፡
ቅ ማለት ጻድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቆ ማለት ቆፍ ቅሩብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቈ ማለት ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን ማለት ነው፡፡
ቊ ማለት ቊርባነ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ቍ ማለት ቍየጺሁ አዕማደ ባላቅ ማለት ነው፡፡
ቌ ማለት ቀነተ ሐቌሁ ለኀጺበ እግረ አርዳኢሁ ማለት
ነው፡፡
በ ማለት በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኵሉ ዓለም ማለት ነው፡፡
ቡ ማለት ጥበቡ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቢ ማለት ረቢ ነአምን ብከ ማለት ነው፡፡
ባ ማለት ባዕድ እምአምአማልክተ ሐሰት ማለት ነው፡፡
ቤ ማለት ቤት ባዕል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ብ ማለት ብርሃነ ቅዱሳን ፍጹማን ማለት ነው፡፡
ቦ ማለት አልቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌሁ ማለት ነው፡፡
ተ ማለት ተሰብአ ወተሠገወ እማርያም እምቅድስት
ድንግል ማለት ነው፡፡
ቱ ማለት መዝራዕቱ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቲ ማለት ተአኳቲ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ታ ማለት ታው ትጉህ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቴ ማለት ከሣቴ ብርሃን ማለት ነው፡፡
ት ማለት ትፍሥሕት ወሐሤት ማለት ነው፡፡
ቶ ማለት ነአምን ልደቶ ለክርስቶስ ማለት ነው፡፡
ነ ማለት ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ማለት ነው፡፡
ኑ ማለት ዛኅኑ ለባሕር ማለት ነው፡፡
ኒ ማለት ኰናኒ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ና ማለት መና እስራኤል ማለት ነው፡፡
ኔ ማለት ወጣኔ ኵሉ ማለት ነው፡፡
ን ማለት መኰንን እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኖ ማለት ኖላዊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
አ ማለት አአኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዐ ማለት ዐቢይ እግዚአብሔር ወብዙኅ አኮቴቱ ማለት
ነው፡፡
ኡ ማለት ሙጻኡ ለቃል ማለት ነው፡፡
ዑ ማለት ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኢ ማለት ለሊሁ ተንሣኢ ወለሊሁ አንሣኢ ማለት ነው፡፡
ዒ ማለት ለሊሁ ሠዋዒ ወለሊሁ ተሠዋዒ ማለት ነው፡፡
ኣ ማለት ኣሌፍ ፈጣሬ ኵሉ ዓለም ቀዳማይ ወደኃራዊ
ማለት ነው፡፡
ዓ ማለት ዓይነ ኵሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ ማለት ነው፡፡
ኤ ማለት አምጻኤ ዓለማት ማለት ነው፡፡
ዔ ማለት ዔ ዐቢይ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
እ ማለት እግዚአብሔር እግዚእ ማለት ነው፡፡
ዕ ማለት ብፁዕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኦ ማለት እግዚኦ ማለት ነው፡፡
ዖ ማለት ሞዖ ለሞት ወተንሥአ ማለት ነው፡፡
ከ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኩ ማለት ዐርኩ ለመርዓዊ ማለት ነው፡፡
ኪ ማለት ኪያሁ ንሰብክ ማለት ነው፡፡
ካ ማለት ካፍ ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኬ ማለት ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማእከለ አኃው ማለት
ነው፡፡
ክ ማለት ክብሮሙ ለመላእክት ማለት ነው፡፡
ኮ ማለት ዘረዳእኮ ለአብርሃም ማለት ነው፡፡
ኳ ማለት ኳሄላ አይሁድ ወልድ ማለት ነው፡፡
ኰ ማለት ኰናኔ ዓለም ማለት ነው፡፡
ኵ ማለት ኵርጓኔ ቅዱሳን ማለት ነው፡፡
ኲ ማለት ኲናተ ጌዴዎን ዘቈልቈለ ላዕለ ስሳ ምዕት ሐራ
በምዕር ማለት ነው፡፡
ኴ ማለት ወይኴንን እምባሕር እስከ ባሕር ማለት ነው፡፡
ወ ማለት ወረደ እምሰማያት ማለት ነው፡፡
ዉ ማለት ጼዉ ለምድር ማለት ነው፡፡
ዊ ማለት ናዝራዊ ሐዊ ማለት ነው፡፡
ዋ ማለት ዋው ዋሕድ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዌ ማለት ዜናዌ ትፍሥሕት ማለት ነው፡፡
ው ማለት ሥግው ቃል ማለት ነው፡፡
ዎ ማለት ቤዘዎ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ዘ ማለት ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዙ ማለት ምርጒዙ ለሐንካሳ ማለት ነው፡፡
ዚ ማለት ናዛዚ ማለት ነው፡፡
ዛ ማለት ዛይ ዝኲር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዜ ማለት አኃዜ ዓለም በእራኁ ማለት ነው፡፡
ዝ ማለት ሐዋዝ ሕገ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዞ ማለት አግአዞ ለአዳም ማለት ነው፡፡
የ ማለት የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኀይለ ማለት ነው፡፡
ዩ ማለት ዕበዩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዪ ማለት መስተሥርዪ ማለት ነው፡፡
ያ ማለት አንተ ኬንያሁ ማለት ነው፡፡
ዬ ማለት ዐሣዬ ሕይወት ማለት ነው፡፡
ይ ማለት ሲሳይ ለርኁባን ማለት ነው፡፡
ዮ ማለት ዮድ የማነ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ደ ማለት ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ ወሥጋነ ምስለ
መለኮቱ ማለት ነው፡፡
ዱ ማለት ፈዋሴ ዱያን ማለት ነው፡፡
ዲ ማለት ቃለ ዐዋዲ ማለት ነው፡፡
ዳ ማለት ዳሌጥ ድልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዴ ማለት ዐማዴ ሰማይ ወምድር ማለት ነው፡፡
ድ ማለት ወልድ ዋሕድ ማለት ነው፡፡
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ያ ማለት አንተ ኬንያሁ ማለት ነው፡፡
ዬ ማለት ዐሣዬ ሕይወት ማለት ነው፡፡
ይ ማለት ሲሳይ ለርኁባን ማለት ነው፡፡
ዮ ማለት ዮድ የማነ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ደ ማለት ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ ወሥጋነ ምስለ
መለኮቱ ማለት ነው፡፡
ዱ ማለት ፈዋሴ ዱያን ማለት ነው፡፡
ዲ ማለት ቃለ ዐዋዲ ማለት ነው፡፡
ዳ ማለት ዳሌጥ ድልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዴ ማለት ዐማዴ ሰማይ ወምድር ማለት ነው፡፡
ድ ማለት ወልድ ዋሕድ ማለት ነው፡፡
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
Telegram
ትምህርተ ኦርቶዶክስ
ውድ የ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ቻናል ተከታዮች በሙሉ በዚህ ቻናል ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን በቻ የምንለጥፍ መሆኑን ለመግለፅ እነዳለሁ ለሌሎችም በማጋራት (ሼር ) አገልግሎቱን ይደግፉ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ዐረብ ኤምሬትስ አቀኑ!
ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ )
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ከሌሎች ልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ዛሬ ጧት ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ,ም ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ዐረብ ኢምሬቶች አቅንተዋል።
https://www.tgoop.com/tmhrtegeeze
ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ )
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ከሌሎች ልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ዛሬ ጧት ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ,ም ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ዐረብ ኢምሬቶች አቅንተዋል።
https://www.tgoop.com/tmhrtegeeze
Telegram
✝️(ትምህርተ ግዕዝ)✝️
በዚህ ቻናልየተለያዩ ትምህርቶች ያገኛሉ
ከነዚህም ውስጥ ✝️የግዕዝ ትምህርት
✝️የተለያዩመፅሐፉን
✝️ የተለያዮ መንፈሳዊ ስብከቶች ✝️መንፈሳዊፊ ልሞች ወ.ዘ.ተ ያገኛሉ።

12ኛው ዓለም አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች ቀን እና ጠቅላላ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ እየተከናወነ ይገኛል !
ግንቦት 26 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዓለም አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤውን ማከናወን ጀምሯል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዓለም አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እና የሰንበት ት/ቤቶችን ቀን ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዎርክ ሀገረ ስብከህ ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በመንበረ ፓትርያርክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤የተዋሕዶ ሚድያ ማዕከልና የኢቲ አርት ሚዲያ የበላይ ጠባቂ ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በመንበረ ፓትርያርክ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ሊቀ ጳጳስ ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ፣ የየአህጉረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተወካዮች በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።
ጠቅላላ ጉባኤውም የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን በሚከበርበት በበዓለ ጰራቅሊጦስ ዕለት ጉባኤውን የሚያጠናቅቅ ሲሆን በጉባኤው ማጠቃለያ ላይም መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ጾመ ሐዋርያት
በወርኃ ሰኔ የሚጾም በመሆኑ ይህ ጾም በተለምዶ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ ጾመ ሐዋርያትን ለመጀመሪያ ጊዜ የጾሙት ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ የጾሙበትም ዋና ምክንያት በሃምሳኛው ቀን ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ስለተቀበሉና እግዚአብሔር ስላደረገላቸው መልካም ነገር ለማዘከር ነው፡፡
ጾመ ሐዋርያት በዓለ ጰራቅሊጦስ በመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፬) ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡ ‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ ያንጊዜም ይጾማሉ፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፭)
በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ ያደረው ጸጋ መንፈስ ቅዱስና ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ እንዲያድር፣ ከቅዱሳን ሐዋርያቱ በረከት እንድንሳተፍ፣ አገልግሎታችን በስኬት እንዲቃና እና ወርኃ ክረምቱ በሰላም ያልፍልን ዘንድ ጾመ ሐዋርያትን መጾም አስፈላጊ ነው፡፡ ከጸሎትና ምጽዋትን መንፈሳዊ እድገትን በጾም አስምረን ከራሳችን እና ከእግዚአብሔር አምላካችን ጋር የምንታረቅበት እንዲሆንልን የቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በረከትና ጸሎትም አይለየን፡፡
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የቅድስት ድንግል ማርያም እና የቅዱሳን ሐዋርያት አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን!
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
በወርኃ ሰኔ የሚጾም በመሆኑ ይህ ጾም በተለምዶ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ ጾመ ሐዋርያትን ለመጀመሪያ ጊዜ የጾሙት ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ የጾሙበትም ዋና ምክንያት በሃምሳኛው ቀን ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ስለተቀበሉና እግዚአብሔር ስላደረገላቸው መልካም ነገር ለማዘከር ነው፡፡
ጾመ ሐዋርያት በዓለ ጰራቅሊጦስ በመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፬) ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡ ‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ ያንጊዜም ይጾማሉ፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፭)
በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ ያደረው ጸጋ መንፈስ ቅዱስና ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ እንዲያድር፣ ከቅዱሳን ሐዋርያቱ በረከት እንድንሳተፍ፣ አገልግሎታችን በስኬት እንዲቃና እና ወርኃ ክረምቱ በሰላም ያልፍልን ዘንድ ጾመ ሐዋርያትን መጾም አስፈላጊ ነው፡፡ ከጸሎትና ምጽዋትን መንፈሳዊ እድገትን በጾም አስምረን ከራሳችን እና ከእግዚአብሔር አምላካችን ጋር የምንታረቅበት እንዲሆንልን የቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በረከትና ጸሎትም አይለየን፡፡
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የቅድስት ድንግል ማርያም እና የቅዱሳን ሐዋርያት አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን!
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
Telegram
ትምህርተ ኦርቶዶክስ
ውድ የ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ቻናል ተከታዮች በሙሉ በዚህ ቻናል ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን በቻ የምንለጥፍ መሆኑን ለመግለፅ እነዳለሁ ለሌሎችም በማጋራት (ሼር ) አገልግሎቱን ይደግፉ
#መልካም_ዜና
መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ከእስር ተፈተዋል።
ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ባሕር ዳር ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ተይዘው በአዲስ አበባ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ውስጥ በእስር ላይ የነበሩት መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ከእስር መለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸው ለማኅበረ ቅዱሳን ቴቪ ገልጸዋል።

#ንስሐ_ምንድን_ነው?
ንስሐ ማለት አንድ ሰው በሠራው ጥፋት፣ ባደረገው ስህተት፣ በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑ፣ መፀፀቱ፣ ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው። በአጭሩ ንስሐ ማለት ትርጉሙ ይህ ሲሆን፤ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስገነዝበን ቀጥሎ የተጠቀሱትን ፍችዎች ያጠቃለለ ሆኖ እናገኘዋለን።
➙ ንስሐ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው። ሚልኪያስ 3፥7
➙ ንስሐ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ነው። 2 ቆሮንቶስ 6፥19
➙ ንስሐ ከኃጢአት እንቅልፍ መንቃት ነው። ሮሜ 13፥11
➙ ንስሐ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ነው። ኤፌሶን 5፥14
➙ ንስሐ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ እግዚአብሔርን የሚያስወድድ ከንጹህ ልብ የሚመነጭ ጸጋ ነው። ሕዝቅኤል 36፥25-27
➙ ንስሐ ከኃጢአትና ከዲያቢሎስ ባርነት ነጻ መውጣት ነው። ዮሐንስ 8፥34-36
➙ ንስሐ ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ስለ ቅድስና ብሎ ኃጢአትን መተው ነው። ምሳሌ 28 ፥13
➙ ንስሐ ኃጢአትን ከተዉ በኋላ በፍጹም መልሶ አለመስራት ነው።
➙ ንስሐ ስለ አለፈው ስህተት አብዝቶ ማልቀስ፤ ያለፈውን የኃጢአት ኑሮ ማውገዝና መኮነን ነው። ኢዩኤል 2፥12
➙ ንስሐ ፍጹም የሆነ የሕይወት ለውጥ እንጂ ጊዜያዊ ስሜት አይደለም፤ ሮሜ 12፥2
➙ ንስሐ ኃጢአትን ሲሠሩ ከመኖር ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር መኖርን መሻት ነው። መዝሙር 73፥28
➙ ንስሐ የአዕምሮ መታደስ ነው። ሮሜ 12፥2
➙ ንስሐ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የሚያስችል ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር የሚያስገባ ቁልፍ ነው። ማቴዎስ 25፥1-13
➙ ንስሐ በቀራንዮ መስቀል ላይ እኛን ለማዳንና ከኃጢአት ባርነት ነጻ ለማውጣት የፈሰሰልንን የክርስቶስን ደም እንድናስብ የሚያደርግ መንፈሳዊ ሃብት ነው።
➙ ንስሐ ከኃጢአት የሚያነጻ ሱራፌል ከመንበረ ሥላሴ የወሰዱት የእሳት ፍም ነው። ኢሳያስ 6፥4
➙ ንስሐ ከሚመጣው የመጨረሻ መከራና ሃዘን መዳኛ ወይም ማምለጫ መንገድ ነው። ዮናስ 3፥10
➙ ንስሐ እግዚአብሔር የሰውን ኃጢአት ይቅር የሚልበትና ከኃጢአት ውጤት የሚያድንበት መሳርያ ነው።
➙ ንስሐ ከሰዎች ጋር ለመታረቅ የተዘረጋ የእግዚአብሔር እጅ ነው። መዝሙር 50/51
➙ ንስሐ እግዚአብሔር ወደ ሰው የሚጣራውን ጥሪ ሰምቶ ወደ እርሱ መመለስ ነው። ዮሐንስ 7፥51። ኤፈሶን 4፥30
➙ ንስሐ ስለ አለፈው ኃጢአት ከመፀፀት የተነሳ የተሰበረ ልብ ነው። መዝሙር 50/51፥17
➙ ንስሐ ሰዎች ስለ ኃጢአታቸው ተፀፅተው ከእግዚአብሔር ጋር እንዳይታረቁ በብርቱ በሚጥረው ሰይጣን ላይ የተገኘ ድል ነው። መዝሙር 123/124፥ 6-7::
ወስብሃት ለእግዚአብሔር !
(የንስሐ ሕይወት)
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

ትምህርተ ኦርቶዶክስ pinned «#ንስሐ_ምንድን_ነው? ንስሐ ማለት አንድ ሰው በሠራው ጥፋት፣ ባደረገው ስህተት፣ በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑ፣ መፀፀቱ፣ ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው። በአጭሩ ንስሐ ማለት ትርጉሙ ይህ ሲሆን፤ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስገነዝበን ቀጥሎ የተጠቀሱትን ፍችዎች ያጠቃለለ ሆኖ እናገኘዋለን። ➙ ንስሐ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው። ሚልኪያስ 3፥7 ➙ ንስሐ…»
በክልል ትግራይ ካሉ ብፁዓን አባቶች ጋር የተፈጠረውን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ የሰላም ልዑኩ ገለጸ !
ሰኔ 6 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የሰላምና የስምምነት ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የካቲት 7 ቀን 2015 ዓ.ም በቅዱስነታቸው ፊርማ ባወጣው ደብዳቤ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ በካህናት ፣ በምእመናን ፣ በገዳማትና በአድባራት ላይ ስለደረሰው ጉዳት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን በይፋ መግለጹ ይታወሳል።
በግንቦት ወር ባካሄደው የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤም በክልል ትግራይ የሚገኙ አባቶቻችን የሚያነሱትን ቅሬታ በተመለከተ ጉዳዩ በውይይትና በህግ የሚፈታበት መንገድ እንዲፈጠር ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰየመው ኮሚቴ ሥራውን እንዲቀጥል መመሪያ ሰጥቶ ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ውሳኔ አስተላልፏል።
የተቋቋመው ኮሚቴም ችግሩ በሰላማዊ መንገድና በስምምነት መቋጨት የሚችልበትን አቅጣጫ በመቀየስ በርካታ የቅድመ ውይይት ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።ወደፊትም የቅዱስ ሲኖዶስን መመሪያ በመቀበል ችግሩ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በተከተለ አግባብ መፍትሔ እንዲያገኝ ለማድረግ የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ደፋ ቀና እያለ ይገኛል።
በክልል ትግራይ የሚገኙ ብፁዓን አባቶቻችን የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ሁሉ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በተከተለ አግባብ ለመፍታት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን የምታደርገውን የእናትነት እንቅስቃሴ በማዛባት ልዩነት እንዲሰፋና የቤተክርስቲያናችን ተቋማዊ አንድነት እንዲናጋ ሌት ተቀን የሚጥሩ አንዳንድ የሚዲያ ተቋማትም ችግሩ ዘለቄታዊ መፍትሔ እንዳያገኝ ሆን ብለው እየሠሩ እንደሚገኙ እንገነዘባለን።
ይሁንና ችግሩ የሚፈታው በእልህና በቁጣ ልዩነትን በማስፋትና በመራራቅ ሳይሆን በሰከነ መንገድ በሰለጠነ አስተሳሰብና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መሠረት ባደረገ በግልጽ ውይይት መሆኑን በመገንዘብ የችግሩ መነሻዎችን አሁን ያሉበትን ደረጃና ወደፊት ሊደረግ የሚገባ የሚባሉ ነጥቦችን በመለየት በውይይት መፍታትና በመጨረሻ ጉዳዩን በእርቀ ሰላም ማጠቃለል እንደሚገባም ኮሚቴው በጽኑ ያምናል።
ስለሆነም በክልል ትግራይ የሚገኙ ብፁዓን አባቶቻችን ቀደምት አባቶቻችን ለሃይማኖታቸው አንድነትና መስፋፋት እንዲሁም ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ የከፈሉትን መስዋዕትነት መሠረት በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችሁ አንድነትና ሉዓላዊነት በጽናት በመቆም ተፈጠሩ የሚባሉ ችግሮችን ሁሉ በዝርዝር ለማቅረብ ለውይይት ዝግጁ እንድትሆኑ መልእክታችንን እያስተላለፍን የምታቀርቧቸውን የውይይት ነጥቦች መሠረት በማድረግ ችግሮቹን በስምምነት ለመፍታት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ዝግጁ መሆኗን እንወዳለን። በዚህም የውይይትና የሰላም መልእክታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያስተላለፈችውን ጥሪ በመቀበል በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውይይትና ለስምምነት ዝግጁ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እያስተላለፍን በቅርብ ቀናት ውስጥ የሰላም ልዑኩ ለውይይት ወደ ክልል ትግራይ መቀሌ ከተማ ስለሚጓዝ በጋራ በምናደርጋቸው ቦታና ጊዜ የውይይትና የስምምነት ጉባኤ የሚደረግ ይሆናል።
የፌዴራል መንግሥትና የክልል ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርም ችግሩ በሰላማዊ መንገድና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ የሚደረገውን ጥረት ሁሉ በመደገፍና ለውይይቱ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግልን በዚሁ አጋጣሚ መልእክታችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን።
አምላካችን እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንንና ሕዝባችንን ይባርክ !
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና የስምምነት ኮሚቴ
ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

♥ ቅዱስ ሚካኤል ♥
* ሚካኤል ማለት የስሙ ትርጓሜ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው ማለት ነው። የመላእክት አለቃ ነው። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጠባቂ መልአክ ነበር። በብሉይ ዘመን በግብጽ ባርነት ስር የነበሩ ሕዝበ እስራኤልን ቀን በደመና እየጋረደ፣ በሲና በረሀ እየመገበ ማር እና ወተት ወደምታፈሰው ከነዓን ያገባቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው። በሐዲስ ኪዳንም ቢሆን የባሕራንን የሞት ደብዳቤ የሰረዘ፤ አፎምያን ከሰይጣን እጅ ያዳነ፤ በሕይወቷ ዘመን ሁሉ የረዳት ይህ ቅዱስ ሚካኤል ነው።
ሕዳር 12 እስራኤላውያንን ባሕረ ኤርትራን እንዲያልፉ የረዳበት ዕለት ሲሆን ሰኔ 12 ቀን ደግሞ አፎምያን የረዳበት ዕለት በመሆኑ በድምቀት ይከበራል። ቅዱሳን ነቢያትን፣ ቅዱሳን ሊቃውንትን፣ ከእግዚአብሔር በተሰጠው የመርዳት ጸጋ በተለያየ መንገድ ይረዳቸው እንደነበር ተጽፏል። እኛም የመልአኩን ረድኤት ለማግኘት በወር በወር በ12 በ12 እናከብረዋለን::
የመልአኩ ረድኤት አይለየን።
አሜን
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
* ሚካኤል ማለት የስሙ ትርጓሜ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው ማለት ነው። የመላእክት አለቃ ነው። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጠባቂ መልአክ ነበር። በብሉይ ዘመን በግብጽ ባርነት ስር የነበሩ ሕዝበ እስራኤልን ቀን በደመና እየጋረደ፣ በሲና በረሀ እየመገበ ማር እና ወተት ወደምታፈሰው ከነዓን ያገባቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው። በሐዲስ ኪዳንም ቢሆን የባሕራንን የሞት ደብዳቤ የሰረዘ፤ አፎምያን ከሰይጣን እጅ ያዳነ፤ በሕይወቷ ዘመን ሁሉ የረዳት ይህ ቅዱስ ሚካኤል ነው።
ሕዳር 12 እስራኤላውያንን ባሕረ ኤርትራን እንዲያልፉ የረዳበት ዕለት ሲሆን ሰኔ 12 ቀን ደግሞ አፎምያን የረዳበት ዕለት በመሆኑ በድምቀት ይከበራል። ቅዱሳን ነቢያትን፣ ቅዱሳን ሊቃውንትን፣ ከእግዚአብሔር በተሰጠው የመርዳት ጸጋ በተለያየ መንገድ ይረዳቸው እንደነበር ተጽፏል። እኛም የመልአኩን ረድኤት ለማግኘት በወር በወር በ12 በ12 እናከብረዋለን::
የመልአኩ ረድኤት አይለየን።
አሜን
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
Telegram
ትምህርተ ኦርቶዶክስ
ውድ የ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ቻናል ተከታዮች በሙሉ በዚህ ቻናል ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን በቻ የምንለጥፍ መሆኑን ለመግለፅ እነዳለሁ ለሌሎችም በማጋራት (ሼር ) አገልግሎቱን ይደግፉ
#ኦርቶዶክሳዊ_ሊያውቃቸው_የሚገቡ...
፩👉 እግዚአብሔር ስራውን ሰርቶ በ 7ኛው ቀን ፈፅሟል'
፪👉7ቱ ሊቃነ መላእክት የሚባሉት
1 ቅዱስ ሚካኤል
2 ቅዱስ ገብርኤል
3 ቅዱስ ኡራኤል
4 ቅዱስ እራጉኤል
5 ቅዱስ እሩፍኤል
6 ቅዱስ ፍኑኤል
7ቅዱስ ሳቁኤል
፫👉 7ቱ ኪዳናት የሚባሉት
1 ኪዳነ አዳም
2ኪዳነ ኖህ
3 ኪዳነ መልከ ፀድቅ
4 ኪዳነ አብረሀም
5ኪዳነ ሙሴ
6ኪዳነ ዳዊት
7ኪዳነ ምህረት ናቸው
፬👉 7ቱ አፆማት የሚባሉት
1 የአብይ ፆም
2 የሀዋርያት ፆም
3 የፍልሰታ ፆም
4 ፆመ ነብያት
5 ፆመ ገሀድ
6 ፆመ ነነዎይ
7 ፆመ ድህነትናቸው
፭👉7ቱ የፀሎት ጊዜያት
1 ነገ ወይምጧት ወይም 12ሰአት
2 ሰለስቱ ሰአት ወይም ጧት 3ሰአት
3 6 ሰአት ወይም እኩለቀን
4 ከሰአት ወይም ከቀኑ 9 ሰአት
5 ሰርክ ወይም ከምሽቱ 11ሰአት
6 ንዋም ወይም ከምሽቱ 3 ሰአት
7 መንፈቀ ሌሊት ወይም ከሌሊቱ 6ሰአት
፮👉7ቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን የሚባሉት
1ሚስጥረ ጥምቀት
2ሚስጥረ ሜሮን
3ሚስጥረ ቁርባን
4ሚስጥረ ክህነት
5ሚስጥረ ተክሊል
6ሚስጥረ ንሰሀ
7ሚስጥረ ቀንድል ናቸው
፯👉7ቱ ሰማያት የሚባሉት
1 ድህረ አርያ /ከሰማያት ሰማያት
2 መንበረ መንግስት /መንበረ ብረሀን መንበረ ፀባዎት መንበረ ስበሀት
3 ሰማይ ውድድ /መንበረ መንግስት የተዘረጋበት
4 እየሩ ሳለም ሰማያዊት መንግስተ ሰማያት
5 እዮር
6 እራማ
7 ኤረር /የመላእክት ከተሞች ናቸው
፰👉7ቱ አባቶች የሚባሉት
1የሰይምና የምድርም አባት ልኡል እግዚአብሔር
2 የንሰሀ አባት/የነፍስ አባት
3 ወላጅ አባት
4 የክርስትና አባት
5 የጡት አባትማለትም /ያልወለደውን እንደልጅ የሚያሳድግ
6 የስልጣን አባት /የአገር መሪ
7 የቀለም አባት በመንፈሳዊይም/ ሆነ በአለማዊ የሚያስተምር ናቸው
፱👉7ቱ እኔ ነኝ
1 የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ_ ዮሐንስ 6÷35
2 እኔ የአለም ብረሀን ነኝ____ ዮሐንስ 8÷12
3 በሩ እኔነኝ____ ዮሐንስ 10÷ 9
4 መልካም እረኛ እኔነኝ_ ዮሐንስ 10÷11
5 የትንሳኤ ህይወት እኔ ነኝ____ ዮሐንስ 11÷25
6 እኔ መንገድ እውነት ህይወት ነኝ_ ዮሐንስ 14÷ 6
7 እውነት የህይወት ግንድ እኔነኝ ዮሐንስ 15÷1
፲👉7ቱ ጌታችን በመስቀል ላይ የተናገራቸው
1 አምላኬ አምላኬ ለን ተውከኝ ማቴ 27÷46
2 አባቶይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው_ ሉቃ 23÷34
3 እውነት እውነት እላችሆለሁ ዛሬ በገነት ከኔ ጋር ነህ። _ሉቃ 23÷43
4 አንችሴት እነሆት ልጅሽ እነሆት እናትህ_ ዮሐንድ 19÷26--27
5 ተጠማሁ____ ዮሐንስ 19÷30
6 አባቶይ ነፍሴን በእጅህ ስጥቻለሁ____ ሉቃ 23÷46 ና
7 ተፈፀሙ _ዮንሐስ 19÷30
፲፩👉7ቱ የክርስቶስ ማንነት የሚመሰክሩ
1። የባህሪ አባት ምስክርነት ዮሐ 5=34÷37 8÷18
2 እራሱ ወልድ የክርስቶስ ምስክርነት_ ዮሐ 8 ~18~58
3 የመንፈስ ቅዱስ ምስክርምነት____ ዮሐ 15፦ 26 ÷16 ÷12
4 የሰራተኞቹ ምስክርነት____ ዮሐ 5÷36--10-- 25
5 የመፅሀፍ የቅዱ ምስክርነት____ ዮሐ 5÷39 ~46
6 የመጥምቁ ዮሀንስ ምስክርነት_ ዮሐ 1 ÷7--5--33
7 የተማሪዎቹ ምስክርነት ዮሐ 15÷27~ 19~35ናቸው
፲፪👉7ቱተአምራት ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ
1 ፀሀይ ጨለመ
2 ጨረቃ ደም ለበሰ
3 ከዋከብት እረገፋ
4 አለቶች ተሰነጣጠቁ
5 መቀብሮች ተከፈቱ
6 ሙታን ተነሱ
7 የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ
፲፫👉7ቱ የሚጠሉ ነገሮች
1 ትቢተኛ አይን
2 ሀሰተኛ ምላስ
3 የንፁሀን ደም የምታፈስእጅ
4 ክፍ ሀሳብ የሚያፈልቅ ልብ
5 ወዴ ክፍ ነገር የምትሮጥ እግር
6 በሀሰተኛ የምትመሰክር ሀሰተኛ ምላስ
7 በወንድም አማቾች መካከል ፀብን የሚፈጥር
፲፬👉7 ቱ አብያተ ክርስቲያናት
1 የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
2 የሰርሚኒልስ ቤተክርስቲያን
3 የኤርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
4 የትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን
5 የሰርድስ ቤተ ክርስቲያን
6 የፌልጵልያስ ቤተክርስቲያን
7 የሎዶቂያ ቤተክርስቲያን
፲፭👉7ቱ እራሶች የሚባሉ
1 ሀሳቢመሲህ
2 ኢራቅ
3ግሪክ
4 ሜዶና
5 ግብፅ
6ጣሊያን
7 እስራኤል
፲፮👉12 የድንግል ማርያም ስሞች
1 ወላድተ አምላክ-------ማቴ 1÷21
3 የአምላክ እናት------ሉቃ 1÷40
4 ዘላለዉዊ ድንግል-----ህዝቄ 40÷2
5 ብሩክት----ሉቃ 1÷42
6 ብፅዕት---- ሉቃ 1÷49
7 የሁሉ እመቤት----መዝ 44÷9
8 የአለም ንግስት-------መዝ44÷9
9 የሰው ሁሉናት----------መዝ86 ÷5
10አማላጅ---------'ዮሐንስ 2
12 የድህነት አምላክ ናት-------መዝ 59÷4 ኢሳ 7÷1።
፲፯👉7 የአደጋ ጊዜ የሚነበቡ
1 ሲከፍዎት ዮሐንስ 14
2 ሀጢአትሲሰሩ መዝሙር 51
3 ሲጨነቁ መቴወስ 6 19÷34
4 አደጋ ሲያጋጥመወት መዝሙር 19
5 እረፍትና ሰላም ሲያሻወት ማቴ 11 ÷25--30
6 ኪሰዎ ባዶ ሲሆንመዝሙር 37
7 ብቸኝነት ሲሰማዎት መዝሙር 23
፲፰👉 6 ቱ ቃላተ ወንጌል
1 በወንድሙ ላይ በከንቱ የተቆጣ ሁሉ በፍርድ። ይፈረድበታል
2 ወዴ ሴት አይቶ የተመኛት በልቡ አመነዘረባት
3 ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ የተፈታችውንም የሚያገባ አመነዘረ
4 ፈፅማችሁ አትማሉ
5 ክፍውን በክፍ አትቃወሙ
6 ጠላታችሁን ውደዱ
፲፱👉 4ቱ ወንጌላት የሚባሉት
1 የማቴዎስ
2 የማርቆስ
3 የሉቃስ
4 የዮሐንስ ናቸው
፳👉5 የኦሪት ህግ የሚባሉት
1 ኦሪት ዘፍጥረት
2 ኦሪት ዘለላውያን
3 ኦሪት ዘፀአት
4 ኦሪት ዘውልቁ
5 ኦሪት ዘዳግም ናቸው
፳፩👉 5 ቱ አእማደ ሚስጥራት የሚልሉት
1 ሚስጥረ ስላሴ
2 ሚስጥረ ስጋዊ
3 ሚስጥረ ጥምቀት
4 ሚስጥረ ቁርባን
5 ሚስጥረ ትንሳኤ ሙታን
፳፪👉5ቱ ቅንዋተ መስቀል
1 ሳዶር
2 እላዶር
3 ዳናት
4 አደራ
5 ሮዳስ ናቸው
፳፫👉 8ቱ የአብይ ፆም ሳምንት የሚባሉት
1 ዘወረዴ 5 ደብረ ዘይት
2 ቅድስት_ 6 ገብርሄር
3 ምኩራብ _ 7 ኒቆድሞስ
4 መፃጉኡ 8 ሆሳእና ትንሳኤ ፍሲካናቸው
፳፬👉8ቱማርያሞች የሚባሉት
1 የአሮን እህት ማርያም----- ዘፀአት 15 ÷20--21
2 የማርታ እህት ማርያም-----ሉቃስ 10÷ 38--39
3 የያእቆብ የዮሳ እህት ማርያም------ማርቶስ 15 ÷40--41--47
4 7 አጋንት የወጣላት መቅደላዊት ማርያም ----ሉቃስ 8 ÷2
5 የቅሎጳ ሚስት ማርያም ዮሐ ----19÷25
6 የዮሀንስ እናት ማርያም የሀዋርት ----ስራ12÷12
7 የሮሟ ክርስቲያን ማርያም----- ሮሜ 16÷16
8 የኖቴር ልጅ ማርያም ------1ኛ ዜና መዋእል 4÷17
፳፭👉12ቱ ሀዋርያት
1 ጴጥሮ ስ--------- 7 ማቴወስ
2 እንድሪያስ------ 8 ቶማስ
3 ያእቆብ--------- 9 የእልፌወስ ልጅ ያእቆብ
4 ዮሐንስ----------- 10 ስሞኦን
5 ፌሊፓስ-------- 11 የያእቆብ ወንድም ይሁዳ
6 በርተለሚወስ------- 12 አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ
፳፮👉#10ቱ ትዕዛዛት
1ከኔ በቀር ሌሎች አማልግት አታምልክ
2የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አትጥራ
3 የስንበትን ቀን አክብር
4 አባትህንና እናትህን አክብር
5 አትግደል
6 አታመንዝር
7 አትስረቅ
8 በሐሰት አትመስክር
9 የባልንጀራህን ገንዘብ አትመኝ
10 ባልጀራህን እንደራስህ ውደድ

ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
#ሰኔ_20_እና_21
👉 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።
ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።
ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።
ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።
የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።
ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!
https://www.tgoop.com/tmhrteorthodox

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስታውቋል።
ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የወሰነውን የአዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሢመት በተመለከተ በምልዓተ ጉባኤው የተሰየሙት የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ሥራቸውን ያጠናቀቁ መሆኑን በመግለጻቸው ኮሚቴው አዘጋጅቶ ባቀረበው የሢመተ ኤጲስቆጶሳት ምርጫ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ለማስተላለፍ ይችል ዘንድ የተጠራ ስብሰባ ነው።
ምልዓተ ጉባኤው ከሰኔ 15 ቀን ጀምሮ ጉባኤውን እስከሚያጠናቅቅበት ቀን ድረስ ለቀናት የሚቆይ ሲሆን ከዋናው አጀንዳ በተጨማሪ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል ።
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስታውቋል።
ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የወሰነውን የአዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሢመት በተመለከተ በምልዓተ ጉባኤው የተሰየሙት የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ሥራቸውን ያጠናቀቁ መሆኑን በመግለጻቸው ኮሚቴው አዘጋጅቶ ባቀረበው የሢመተ ኤጲስቆጶሳት ምርጫ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ለማስተላለፍ ይችል ዘንድ የተጠራ ስብሰባ ነው።
ምልዓተ ጉባኤው ከሰኔ 15 ቀን ጀምሮ ጉባኤውን እስከሚያጠናቅቅበት ቀን ድረስ ለቀናት የሚቆይ ሲሆን ከዋናው አጀንዳ በተጨማሪ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል ።
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
Telegram
ትምህርተ ኦርቶዶክስ
ውድ የ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ቻናል ተከታዮች በሙሉ በዚህ ቻናል ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን በቻ የምንለጥፍ መሆኑን ለመግለፅ እነዳለሁ ለሌሎችም በማጋራት (ሼር ) አገልግሎቱን ይደግፉ
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የሚመራ የልዑካን ቡድን ወደ ትግራይ ክልል መቀሌ እንደሚጓዝ ተገለጸ !
ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም (ቲ.ኤም.ሲ/አዲስ አበባ)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ዓርብ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሔደው መደበኛ ስብሰባ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ የልዑካን ቡድን በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ክልል ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቀለ እንዲጓዝ ውሳኔ አስተላልፏል።
ልዑካን ቡድኑ ወደ መቐለ የሚጓዘው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለትግራይ ክልል እንዲሰጥ የተወሰነውን የሰብአዋ ድጋፍ ለማድረስና በትግራይ ከሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር መሆኑ ታውቋል።
ወደ መቐለ በሚደረገው ጉዞ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው የሰላምና አቀራራቢ ኮሚቴ አባላት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር አብረው እንደሚጓዙ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል።
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane

✝️ስርዓተ ቤተክርስቲያን መመሪያ ✝️
እንኳን ወደዚህ ቻናል በሰላም መጡ
የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሊቀላቀለዉ የሚገባ ስለ ሀይማኖቱ ስርአት ስለ ቤተክርስቲያን መመሪያ ህግጋት ደንብ የምናስተምርበት ቻናል ነው ።
share share share

ቅዱስ ሲኖዶስ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫን ያካሄደ ሲሆን በሕገወጥ መልኩ ተሹመው የነበሩ መነኮሳት መካተታቸው ተስተውሏል !
ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው ልዩ ስብሰባ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች በተደራቢነት ተይዘው ለቆዩ ክፍት በኾኑና አንገብጋቢ ችግር ባለባቸው ዘጠኝ አህጉረ ስብከት ላይ የሚመደቡ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጰሳትን ምርጫ ማካሄዱ ተረጋግጧል፡፡
በዚህም መሠረት፡- ለኦሮሚያ ክልል 7 አህጉረ ስብከት
1. አባ ሣህለ ማርያም ቶላ - ምዕራብ አርሲ - (ሻሸመኔ) ሀገረ ስብከት
2. አባ ወልደ ገብርኤል አበበ - ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
3. አባ ጥላሁን ወርቁ - ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
4. አባ ዓምደ ሚካኤል ኀይሌ - ሆሮ ጉድሩ ወለጋ - ሻምቡ ሀገረ ስብከት
5. አባ ኀይለ ማርያም ጌታቸው - ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
6. አባ ዘተክለ ሃይማኖት ገብሬ - ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
7. አባ እስጢፋኖስ ገብሬ - ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
ለደቡብ ኢትዮጵያ 2 አህጉረ ስብከት፤
8. አባ ክፍለ ገብርኤል ተክለ ሐዋርያት - ጌዴኦ አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት
9. አባ ስብሐት ለአብ ወልደ ማርያም - ዳውሮ እና ኮንታ ሀገረ ስብከት ሆነው መመረጣቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከእነዚህ ተመራጮች መካከል 3ቱ በጥር 14ቱ ሕገወጥ "ሢመት" የተሳተፉ መሆናቸው ምዕመናንንና ካህናትን ያላስደሰተ መሆኑን ተ.ሚ.ማ ያነጋገራቸው ኦርቶዶክሳውያን ገልጸዋል።