tgoop.com/Dagmele19/660
Last Update:
አሰበላችብህ..........
በድሮ ጊዜ አንድ እረኛ ነበረ ታድያ ከብቶቹን ወደ መስክ ይዞ
ሲወርድ የግጦሽና የውኃ ቦታ እየራቀው እሱም እየደከመው
ሲመጣ አንዳንድ ጊዜ ከብቶቹን ሜዳ ላይ በትኖ ወደ ቤቱ
ይመለሳል።
ቤተሰቦቹ ከብቶቹስ? ሲሉት "ለቅዱስ ሚካኤል
አስጠብቄያቸዋለሁ" ብሎ በዕምነት ይናገራል። በማግስቱ ሲሄድ
ከብቶቹ አውሬ ሳይነጥቃቸው፣ ሽፍታ ሳይንዳቸው፣ ከቁጥር
ሳይጎድሉ በደሕና ያገኛቸዋል።
በዚሁ መሠረት አንድ ጊዜ ለቅዱስ ገብርኤል፣ ሌላ ጊዜ ለቅዱስ
ጊዮርጊስ በአደራ አስጠብቄያቸዋለሁ እያለ ይናገር ነበር። ታድያ
አንድ ቀን ወላጅ አባቱ "ዛሬስ ለማን አስጠበክምቸው?" ብለው
ይጠይቁታል። እሱም ኮራ ብሎ "ዛሬ ለእመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም አስጠብቄያቸዋለሁ" አለ።
ተናግረውት የማያውቁት አባት "አዬ ልጄ እሷማ አስበላችብህ
አሉት" መጠነኛ ፈገግታ እየፈገጉ። ልጁ የአባቱ ንግግር አላምር
ብሎት "እንዴት አባባ እመቤቴ የእኔን ከብቶች መጠበቅ አቅቷት
ነው የምታስበላብኝ?" ብሎ አባቱ ላይ አፈጠጠ።
አባቱም "አየኸ ልጄ እሷ ርህሪት በመሆኗ የራበው ጅብ ከመጣ
አትከለክለውም፤ ያንተን ከብት እንዲበላ ታሰናብተዋለች እንጂ"
አሉት። ልጁ ይኽን ሲያስብ "እውነትም ታስበላብኛለች" አለና ወደ
ከብቶቹ ሂደ።
በዚህ ታሪክ ማስተላለፍ የተፈለገው የእመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያምን ርህራሄና አዛኝነት እንጂ ሌላ ነገር አይደለም።
ለተጠማ ለውሻ የራራች ለጅቡም ከተራበ ለእርሱ ትራራለች
ብለው ነው። ድንግል ማርያም ኃጢአቱን ለሚያምን ሁሉ ከልጇ
ከወዳጇ ምሕረትና ይቅርታን ለምና ታሰጣለች።
ረድኤቷ፣ በረከቷ፣ ፈጣን ምልጃዋ አይለየን
BY ዳግም ምጽዓት
Share with your friend now:
tgoop.com/Dagmele19/660