tgoop.com/Dire_Tube_news/18317
Last Update:
የአዲስ አበባ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን ሊከስ መሆኑ ተሰማ።
በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አማካኝነት እየፈረሱ የሚገኙት በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶች ጉዳይ አሳስቦኛል ያለው የአ.አ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኮርፖሬሽኑን ልከስ ነው ብሏል።
በቅርስነት የተመዘገበው የራስሃይሉ ተክለሃይማኖት መኖሪያ ቤት ያፈረሰው ወደ ፍርድቤት ለመውሰድ በሂደት ላይ መሆኑንም የአ.አ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።
ቤተእምነቶችን፤ ድልድዮችና ሃውልቶችን ጨምሮ በከተማዋ ከ440 በላይ ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን 316 የሚሆኑ ቤቶችን በቅርስነት መዝግቦ የቅርስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ለመስጠት በሂደት ላይ መሆኑንም ነው ቢሮው የገለጸው፡፡
ከነዚህም መካከል ፒያሳ ሰባራ ባቡር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የራስሃይሉ ተክለሃይማኖት መኖሪያ ቤት ተጠቃሽ ነው፡፡
ነገርግን በቅርስነት የተመዘገበው ይህ ታሪካዊ መኖሪያ ቤት ከቢሮው እውቅና ውጪ በቤቶች ኮርፖሬሽን ሙሉ ለሙሉ መፍረሱን በቢሮው የቅርስና ጥገና እንክብካቤ ዳይሬክተር ደረጀ ስዩም ለባላገሩ ቴሌቭዥን ተናግረዋል፡፡
ባላገሪ ቴሌቭዥን በስፍራው ተገኝቶ እንዳረጋገጠው ይህ ታሪካዊ መኖሪያ ቤት ሙሉ ለሙሉ የፈረሰ ሲሆን ዙሪያውም ታጥሮ ተመልክተናል፡፡
እንደ ራስሃይሉ ተ/ሃይማኖት ያሉ አብዛኞቹ ቅርሶች ጉዳት የሚደርስባቸው በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አማካኝነት መሆኑን የገለጹት አቶ ደረጀ፤ ተቋሙ ቤቶቹን በባለቤትነት የማስተዳድረው እኔ ነኝ በማለት ቅርሱ እሴቱን እንዲያጣ የማድረግ ዝንባሌ መኖሩንም አንስተዋል፡፡
በአሰራርጥበቡ፤ የተሰራበት ጊዜና ቁስን መሰል መስፈርቶችን አሟልቶ መኖሪያ ቤቱ በቅርስነት መመዝገቡን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ አሁን ግን መፍረሱን ተከትሎ ቢሮው ጉዳዩን ወደ ፍርድቤት ለመውሰድ በሂደት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ለቀጣይ የተመዘገቡት ቅርሶች በፕላን ውስጥ የማካተት ስራ እየተሰራ መሆኑን በማንሳት ቅርሶችን መጠበቅ የሁሉም ሃላፊነት ሊሆን እንደሚገባም አቶ ደረጀ ተናግረዋል ጨምረው ተናግረዋል፡፡
#ባላገሩዜና
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
BY Dire Tube news
Share with your friend now:
tgoop.com/Dire_Tube_news/18317