tgoop.com/Dire_Tube_news/18351
Last Update:
ኢትዮ ቴሌኮም ከአፍሪካ የቴሌኮም አገልግሎት ኩባንያዎች ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ መቀመጡ ተሰማ።
በአፍሪካ 195 የቴሌኮም ኦፐሬተሮች ያሉ ሲኾን፤ ኢትዮ ቴሌኮም በግዝፈት፣ በደንበኛ ቁጥር እና በአገልግሎት ደረጃ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ያለው ግሎባል ሲስተምስ ፎር ሞባይል ኮሙኒኬሽንስ ወይም በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል GSMA የተባለ ተቀማጭነቱ እንግሊዝ ሀገር የሚገኝ ተቋም ያወጣው ሪፖርት ነው።
GSMA በዓለም ዙርያ ከ750 በላይ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ተቋሞችን በአባልነት አቅፎ የያዘ እና ኩባንያዎቹን በሥራቸው ልክ ጥራት እና ደረጃ ሰፍሮ የሚናገር ዓለም አቀፍ ተቋም ነው።ይኸው ድርጅት ኢትዮ ቴሌኮምን ከአፍሪካ ሁለተኛ ከዓለም ደግሞ 28ኛ እንዳለው የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
ቻይና፣ አሜሪካ እና ሕንድ የመሳሰሉ ሀገሮች በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂ እና በሌላውም ቀዳሚ በመሆናቸው፣ በእነዚህ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች ከ1 እስከ 27ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።በዛሬው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ቀጠና ማስፋፍያ ያደረገው ኢትዮ ቴሌኮም፣ የ4G እና LTE Advanced የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራውን አጠናቆ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ አስጀምሯል።
በቀጠናው 28,000 ደንበኞች የዳታ ተጠቃሚዎች ናቸው ተብሏክል።የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበጀት አመቱ 106 ከተሞች የላቀውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ማስፋፊያ እየተሰራ ነው ብለዋል።ኢትዮ ቴሌኮም የዴታ አጠቃቀም በብርቱ በሚታይባቸው የሐገሪቱ ከተሞች የላቀውን የኢንተርኔት አገልግሎት እያስጀመረ መሆኑ ተሰምቷል።
Via Sheger FM
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
BY Dire Tube news
Share with your friend now:
tgoop.com/Dire_Tube_news/18351