tgoop.com/Dire_Tube_news/18357
Last Update:
መጭውን በዓላት ምክንያት በማድረግ 108 አማራጭ የገበያ ቦታዎች ማዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ፡፡
ቢሮዉ ቀጣዩን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ እየሰራ ካለው ስራ አንዱ ህብረተሰቡ አማራጭ እና ተደራሽ የገበያ ስፍራ እንዲያገኝና የሚፈልጋቸውን ምርቶች በቀጥታ ከአምራች ገበሬው ማግኘት እንዲችልና እየተስተዋለ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት እየሰራ መሆኑን ቢሮዉ ለጣቢያችን በላከዉ መግለጫ አሳዉቋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ 108 የመገበያያ ቦታዎችን እና ከ250 ሺህ ኩንታል በላይ ተጨማሪ የግብርና ምርት የተዘጋጀ መሆኑን ቦሮዉ ጠቁሟል፡፡
በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራ የጀመሩት መሸጫዎቹ በከተማዋ የሚስተዋለዉን የኑሮ ዉድነት በማረጋጋት በተለይም የግብርና ውጤት የሆኑ የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን እንዲሁም ለበዓል አስፈላጊ የሆኑ እንደ እንቁላል እና አይብ ያሉ የእንስሳት ተዋጽኦ አቅርቦትን ይበልጥ ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፆ እንደሚኖራቸውም ተገልጿል።
ከነዚህም ውስጥ 56 የቁም እንሰሳት የገበያ ስፍራዎች ሲሆኑ 52ቱ የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫዎች ናቸው ተብሏል፡፡አዳዲስ የግብይት ቦታዎቹ በሁሉም ክፍለ ከተሞች አገልሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን መሸጫ ስፍራዎቹ ከአርሶ አደሩ በቀጥታ ተቀብለዉ ለሸማቹ ህብረተሰብ ምርት በቀጥታ ከአርሶ አደሩ ከማቅረባቸው በተጨማሪ ምርቶቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ እንዲችሉ የተዘጋጁ አማራጭ የገበያ ስፍራዎች መሆናቸዉ ተነግሯል፡፡
Via Ethio FM
@Dire_Tube_news
@Dire_Tube_news
BY Dire Tube news
Share with your friend now:
tgoop.com/Dire_Tube_news/18357