Telegram Web
ብንስማማስ !! ??
9👍4
ብንስማማስ !! ??

አንደኛው ምርጫች ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለን ልዩነት ላይ በማተኮር እነሱን ለማጥፋት በመታገል ራሳችንንም ለጥፋት ማጋለጥ ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫችን ግን በሚያስማማንና በአንድነታችን ላይ በማተኮር አብሮ መኖር ነው፡፡

በጥንት አፈ-ታሪክ አንደሚነገረው አንበሳና ነብር በጣም ተጠምተው በየግላቸው ውኃ ፍለጋ ወዲህና ወዲያ ሲንከራተቱ እኩል አንድ ምንጭ ጋር ይደርሳሉ፡፡ በውኃ ጥም የደከመው ማንነታቸውን ለማርካትና ለመበርታት ሁለቱም በቀጥታ ወደ ውኃው ይገሰግሳሉ፡፡ ብዙም ሳይቆዪ ትኩረታቸው ውኃውን ከመጠጣት ላይ ይነሳና በመጀመሪያ ማን ይጠጣ ወደሚለው ሃሳብ ይዞራል፡፡ በዚህ ምክንያት ጸብ ጀምረው መታገል ጀመሩ፡፡

ብዙ ከታገሉ በኋላ ሁለቱም እጅግ እየደከሙ ሲመጡ ከላይ አንድ ድምጽ ሰሙ፡፡ ሁለቱም በድንገት የሰሙት ድምጽ ምን እንደሆነ ለማየት ከጸባቸው መለስ ብለው ቀና ሲሉ አንድ ጥንብ አንሳ (አሞራ) በቅርብ ርቀት ሆኖ ያንዣብባል፡፡ ጥንብ አንሳው በጸቡ ምክንያት የሚሞተውን ጠብቆ የሟቹን ሬሳ ለመብላት ነው የሚጠብቀው፡፡

ይህንን ሁኔታ የተመለከቱ እነዚህ ጠበኞች ልክ ተነጋግረው እንደተግባቡ ያህል ወዲያው አንድ ነገር ፍንትው ብሎ በራላቸው፡፡ በዚህ ጸብ ከሁለቱ አንደኛቸው፣ ምናልባትም ደግሞ ሁለቱም እሰከሞት በሚያደርስ ጉዳት እንደሚጎዱና መጨረሻ ላይ የሚጠቀመው ይህ ጥንብ አንሳ እንደሆነ ገባቸው፡፡ ይህ ሁኔታ ከበራላቸው በኋላ ለመጀመሪ ጊዜ ለመስማማት ወሰኑ፡፡ ተለያይተው ሌላ ከሚበላቸው፣ አንድ ሆነው ከምንጩ በጋራ በመጠጣት በሕይወት ለመኖር ወሰኑ፡፡ በዚህም ስምምነታቸው መሰረት ሁለቱም የሚበቃቸውን ያህል ጠጥተው ወደየመንገዳቸው ሄዱ፡፡

ለሁላችንም የሚበቃ ስፍራና አቅርቦት በዙሪያችን እያለ ሌላውን ካልጣልን እኛ የማንቆም፣ ሌላውን ካላስራብን እኛ የማንጠግብ፣ ሌላውን ካላጠፋን እኛ የማንኖር፣ ሌላውን ካላስወጣን እኛ መኖር የማንችል ሲመስለን አጥፍተን የምንጠፋ እንሆናለን፡፡

አብረን እንኑር!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1\050816404958639/
112👍32😢1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ከጊዜ ጋር መራመድ!

ጊዜ ቆሞ አይጠብቀንም! ወይ አብረን በመራመድ ስኬታማ እንሆናለን፣ ወይም በቸልተኛነት ከስረን እንቀራለን፡፡

ጊዜያችንን በሚገባ ስንጠቀም . . .

⏱️ የሕይወት ዘይቤያችን professional ስለሚሆን በራስ መተማመናችን እየጨመረ ይሄዳል፡፡

⏱️ ሰዎች የሚያምኑን፣ የሚደገፉብንና የሚቀበሉን ወደመሆን እናድጋለን፡፡

⏱️ ስራችንን በተደራጀ ሁኔታ ስለምንሰራ በኢኮኖሚ እያደግን እንሄዳለን፡፡

ጊዜን በተገቢው መንገድ አለመጠቀም . . .

⏱️ በሌሎቸ መቀደምንና ኋላ ቀርነትን ያመጣል፡፡

⏱️ የባከነው ጊዜ ከሚያመጣው የማይመለስ ክስረት የተነሳ የኋላ ኋላ ጸጸትን ያስከትላል፡፡

⏱️ ለየትኛውም የዘመኑ አሰራር የማንመጥን አይነት ሰዎች ሆነን እንድንቀር ያደርገናል፡፡

ጊዜያችሁን በሚገባ የመጠቀምን ስልት አዳብሩ! ራሳችሁ አዘምኑ!

ለዚህ የሚጠቅማችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና አያምልጣችሁ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
55👍12🔥1
ጊዜ አጠቃቀም ማለት!

⏱️ ሆን ብሎ (intentionally) መኖር ማለት ነው!

⏱️ በሚያስፈልገው ነገር ላይ በማተኮር ጉልበትን መቆጠብ ማለት ነው!

⏱️ አንድን ነገር አቅዶ መጀመርና ከጀመሩ ደግሞ እስከሚጨርሱ መቀጠል ማለት ነው!

⏱️ ለዘመኑ የሚመጥን professional ሕይወት መምራት ማለት ነው!

ምንም ነገር ከማዳበራችሁ በፊት ትክክለኛ የጊዜ አጠቃቀም ጥበብን አዳብሩ!

ይህንን ልምምድ ለማዳበር የሚያግዝ ስልጠኛ ተዘጋጅቶላችኋልና ተጠቀሙበት!

የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
52👍4
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የነጋችሁ የሚጀምረው ዛሬ ነው!

ለወጣቶች እና ለጎልማሶች!!!

የዛሬውን ሕይወታችሁን እጅ በእጅ ከምታገኙት ትርፍና ጥቅም አንጻር ብቻ መገምገም አቁሙና ለነገ ከምትዘሩት ዘር አንጻር መገምገም ጀምሩ፡፡ እስከዛሬ ከኖራችኋቸው አመታት ይልቅ በፈታችሁ ያሉት አመታት ብዙ ስለሆኑ ሊያሳስባችሁ የሚገባው ነገር ዛሬ የምታገኙት ነገር ብቻ መሆን አይገባውም፡፡ ከዚያ በተቃራኒ ዛሬ ዘርታችሁ ነገ የሚበቅልላችሁ ነገር ላይ በጥብቅ ማሰብ መጀመር አስፈላጊ ነው፡፡

እስካሁን የኖራችሁት ኑሮ በአብዛኛው ሌሎች ሰዎቸ በዘሩት ዘር ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ ቤተሰብ፣ ሕብረተሰብ፣ መሪዎችና የመሳሰሉት ሰዎች የዘሩትን ስታጭዱ ኖራችሁ ይሆናል፡፡ አሁን ግን ለነገ የምትዘሩበት እድሜ፣ አመለካከትና ብርታት ላይ ነው ያላችሁትና ተጠቀሙበት፡፡

ሌሎች ሰዎች ያደረጉባችሁና ያላደረጉላችሁ ነገር ሰለባ ላለመሆን ወስኑ፡፡

ትናንትና የሆነውን መለወጥ በትችሉም የነጋችሁን ግን መለወጥ እንደምትችሉ አስታውሱ፡፡

ዛሬ ያልዘራችሁት ነገ እንደማይበቅል በመገንዘብ ነቃ በሉ፣ አቅዱ፣ ዘርን ዝሩ፣ ተንቀሳቀሱ፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
74👍20🎉1🤩1
“ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች”
(Effective Time Management Strategies)

አዲስ እና ለስኬታማነታችን ወሳኝ የሆነ ስልጠና፡፡

መረጃውን በፖስተሩ ላይ ይመልከቱ፡፡

ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡
22👍7
የምንኖርባት ዓለም!

ይህቺ ዓለም አንዳንድ ጊዜ ጨከን ትላለች፡፡

የማንጠብቃቸውን የተፈጥሮ ገጠመኞች ፊታችን እያመጣች ከዓላማችን ታስተጓጉለናለች፡፡

ይህቺ ዓለም በውስጧ ጨከን የሚሉ ሰዎችንም በበቂ ሁኔታ ይዛለች፡፡

እነዚህ ሰዎች ወደ ላይ የሚወጣ ሰው ካለ ጎትቶ ከማውረድ፣ የሚያድግ ሰው ካለ ከማሳነስ፣ ወደ ፊት የሚገሰግስ ሰው ካለ ወደ ኋላ ከመጎተት፣ አንድን መልካም ዓላማ ይዞ የሚጀምር ሰው ካለ በተጀመረው ነገር ላይ ክፉ ወሬን በማውራት ከማቋረጥ ውጪ ሌለ ስራ ያላቸውም አይመስሉም፡፡

በሰዎች ላይ የሚናገሩት ንግግርና የሚያደርጉት ነገር በሰዎቹ ላይ ምን ያህል ጉዳት እንደሚያስከትል ፈጽሞ ያለማሰብ ጨካኝነት አላቸው፡፡

በዚህች ጨከን ባለችና ጨከን የሚሉ ሰዎች በያዘች ዓለም ውስጥ ለመኖር ጠንከር ማለትን ይጠይቃል፡፡

ይህ ጠንካራነት . . .


• ወደዚህች ዓለም ባመጣን ፈጣሪያችን ላይ ወደመደገፍ ማድላትን ይጠይቃል፡፡

• ምንም እንካን ሰዎችን ብናምናቸውም፣ ከዚያው ጋር ራሳችንን መጠበቅን አብሮ መያዝን ይጠይቃል፡፡

• ሰዎች ከፋቸውም አልከፋቸውም ያመንንበትንም ሆነ ያላመንንበትን ትክክለኛ ነገር በግልጽነት መናገርንና በአቋም መጽናትን ይጠይቃል፡፡

• ሰዎች ቅን የሆነውን የውስጥ አመለካከታችንን ሳይሆን ውጫችንን እና ተግባራችንን ብቻ አይተው እንደሚፈርዱብን በማወቅ ራስን ማበርታት ይጠይቃል፡፡

• እውነተኛና ፈጽሞ የማይለወጥ ሰዎች ማግኘት ማለት የትም የማይገኝ ስጦታ እንደሆነ በማወቅ እነዚህን ሰዎች በሚገባ መያዝን ይጠይቃል፡፡

መልካም እሁድ የምወዳችሁና ሁል ጊዜ መልካሙን የምመኝላችሁ የሃገሬ ሰዎች!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623
61👍47
የማፈራረቅ (juggling ) ጥበብ!

እድሜያችን እየጨመረ ሲሄድ ከዚያው ጋር እድሎቻችንና ሃላፊነቶቻችን እየተበራከቱ ይሄዳሉ፡፡ እነዚህ እድሎችና ሃላፊነቶች ደግሞ አንዱን አንስተን ሌላውን የማንጥልበትን ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡ ይህ ሲሆን ነው እንግዲህ የማፈራረቅ ጥበብን የማዳበር ግዴታ የሚመጣብን፡፡

በአጭሩ፣ ማፈራረቅ ማለት የተለያዩ ሃላፊነቶቻችንን በተሳካለት ሁኔታ በየተራ መያዝ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የትምህርት፣ የስራ፣ የቤተሰብ እና የመሳሰሉትን ፈጽሞ ችላ ሊባሉ የማይገባቸውን ሁኔታዎች በተሳካለት ሁኔታ በየተራቸው መያዝና ማሳካት እንደማለት ነው፡፡

ይህንን ልምምድ ተግባራዊ ለማድረግ ጊዜያችንን በሚገባ የመጠቀምን ብቃት ይጠይቃል፡፡ ለዚህ የሚጠቅማችሁ ስልጠና ተዘጋጅቷልና መስፈርቱን በማሟላት መመዝገብና መሰልጠን ትችላላችሁ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
53👍12🤩1
የምዝገባ መረጃ:-

ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡
15👍1
ኃይል (ስልጣን) እና ራስን መግዛት
1👍1
ኃይል (ስልጣን) እና ራስን መግዛት

“የመጨረሻው ሰው ለማግኘት ሊጣጣር የሚገባው ኃይል (ስልጣን) ራስን የመግዛት ኃይል (ስልጣን) ሊሆን ይገባዋል” - Elie Weisel

“ሌሎችን መግዛት ጥንካሬ ነው፣ ራስን መግዛት ግን እውነተኛ ኃይል ነው” ይላል የሰነበተ የሩቅ ምስራቆች አባባል፡፡

ሰው ሰፊ ቤተሰብ፣ ግዙፍ ድርጅት፣ ከዚያም አልፎ አገር እያስተዳደረ ራሱን በቅጡ ላያስተዳድር ይችላል፡፡

ቤተሰብ ለማስተዳደር ምናልባት በቂ ገንዘብን ማቅረብ ሊጠይቅ ይችላል (ሁኔታውን በዚያ ጎኑ ብቻ ለማየት ከወሰንን)፡፡ ድርጅትና ሃገርን ማስተዳደር ምናልባት እውቀትንና ሹመትን ይጠይቅ ይሆናል፡፡ ራስን ለማስተዳደር ግን ይህ ነው የማይባል ራስን የመግዛት ዲሲፕሊን ይጠይቃል፡፡

ባለን ገንዘብ ሰዎችን ስናስተዳድር በእኛ ላይ የተደገፉትን ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ እናኖራቸዋለን፡፡ በጨዋነትና በዲሲፕሊን ራሳችንን ስናስተዳድር ግን ለራሳችንም ሆነ ለእነሱ ለረጅም ጊዜ እንኖራለን፡፡

ባካበትነው ገንዘብ፣ በቀሰምነው እውቀትም ሆነ በሌሎች ነገሮች አማካኝነት በእጃችን በገባው ኃይልና ስልጣን ተጠቅመን ትክክለኛውን ነገር ማድረግ የምንችለው፣ በእሱ ተጠቅመን በአካባቢያችን የሚገኙትን ሰዎች አንቀጥቅጠን ስለገዛናቸው ሳይሆን ራሳችንን በመግዛት ለእውነት ስንኖር ነው፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ፣ “ኃይል የሚያስፈልግህ ሰዎችን የሚጎዳ ነገር ለማድረግ ስትፈልግ ብቻ ነው፡፡ አለዚያ፣ ማንኛውንም ነገር ለማከናወን ፍቅር በቂ ነው”፣ ይለናል Charles Chaplin፡፡

በቤተሰብ ውስጥ ካላችሁ የበላይነት ተነስታችሁ እስከ ትምህርት፣ ስራና ማሕበራዊ ተቋሞች ድረስ የተሰማራችሁበትን መስክ ተመልከቱት!

በማን ላይ ምን ያህል ኃይልና ስልጣን አላችሁ? ይህንን ኃይልና ስልጣናችሁን ሰዎች ሲያስቡ ምን እንዲሰማቸው እያደረጋችሁ ይመስላችኋል?

ኃይልና ስልጣናችሁን ተጠቅችሁ የምትገዷቸው ይመስላቸዋል ወይስ የምትጠብቋቸው?

ይህንን ስሜት ከምን የተነሳ ያዳበሩት ይመስላችኋል?

በኃይልና በስልጣናችን ተፈሪነት ሳይሆን ፍሬ ማፍራት እንዲሆንልን እንስራ!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
63👍7
እንደ ግለሰቡ የእድሜና የመሳሰሉት ሁኔታዎችና እንደ ሕብረተሰቡ ባህል ቢለያይም፣ በአማካኝ ሲታሰብ ሰዎች ጊዜ የሰጣቸውን አንድን 24 ሰዓታት ያለውን ቀን በሚከተሉት ሁኔታዎች ያሳልፋል ተብሎ ይታመናል፡፡

• 8.5 ሰዓታት በእንቅልፍ

• 1 ሰዓት ራስን በመንከባከብ

• 2.5 ሰዓታት እንደ ጽዳት አይነት የቤት ውስጥ ስራን በመስራት

• 8.5 ሰዓታት በስራ ወይም በትምህርት ቤት

• 3 ሰዓታት ለወዳጆቻቸው እንክብካቤን በመስጠት

ከላይ የተጻፈውን ጥናታዊ መረጃ ስታነቡ ስለራሳችሁ ጊዜ ምን ሃሳብ መጣላችሁ?

የእናንተ ጊዜ እብዴት ነው የሚያልፈው?

ስለጊዜ አጠቃቀማችሁ አስፈላጊነት አስባችሁ ታውቃላችሁ?

የጊዜ አጠቃቀማችሁ በስኬታማነታችሁ ላይ ወሳኝ ቦታ እንዳለውስ ታውቃላችሁ?

በዚህ ጉዳይ ላይ ጠቃሚ ሃሳቦችን የሚሰጣችሁ ስልጠና ተዘጋጅቷልና መረጃው ከፖተሩ ላይ ይመልከቱ!

ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡
38👍6🎉3
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ሌላውን ከመምራታችሁ በፊት!

ለመሪዎች . . .

ቤተሰብን፣ ድርጅትን፣ ተቋምን፣ ሕዝብንም ሆነ ሃገርን ከመምራታችን በፊት በመጀመሪያ መምራት ያለብን ራሳችንን ነው፡፡ ራሱን በሚገባ ሳይመራ ሌላውን ሰው ለመምራት የሚሞክር ማንኛውም መሪ በአመራር ሂደቱ ውስጥ ትልቅ ክፍተት ያለበት መሪ ነው፡፡

ራሳችንን ባልመራንበት ነገር ላይ ሌላውን ለመምራት መሞከር፣ እኛው አስቀድመን ያላመንንበትን ነገር ሰዎችን ለማሳመን እንደመሞከር ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአመራሩን ስፍራ የመያዛችንን የመነሻ ሃሳብ (Motive) አጠያያቂ ያደርገዋል፡፡

እኛ የማናደርገውን ነገር ሰዎች እንዲያደርጉ፣ እኛ ያልተከተልነውን መርህ ሌሎች እንዲከተሉት . . . ለማድረግ የምንሞክረው ያንን በማድረጋችን ምክንያት ጥቅማ-ጥቅም ስለምናገኝ መሆኑንም ጠቋሚ ነው፡፡

መሪዎች፡- ሰዎች ስልጣናችሁን ስለፈሩ ሳይሆን የእናንተ ዲሲፕሊን መልካም ተጽእኖ ስላሳደረባቸው እንዲከተሏችሁ ከፈለጋችሁ በመጀመሪያ ራሳችሁን በመምራት የምሳሌ ሰዎች ሁኑ፡፡

ሌላውን ሰው ለመምራት የመጀመሪያው ብቃት ራስን መምራት ነው፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
75👍10😢3🔥2
ልቀቁት!

ሁላችንም የምናውቀው ደቡብ አፍሪካዊው የጥቁሮች መብት ተሟጋች ኔልሰን ማንዴላ (Nelson Mandela) በእስር ቤት 27 አሰቃቂ አመታትን ካሳለፈ በኋላ ሲፈታ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣

“እነዚህ የእስር ቤት በሮች ተከፍተው ነጻነቴን ለማግኘት ከዚህ እስር ቤት ወጥቼ ስሄድ መራራነቴንና ንዴቴን እዚሁ ትቼው ነው የምወጣው፡፡ ያንን ካላደረኩኝ ግን ምንም እንኳን ከዚህ ብወጣም፣ አሁንም በእስር ቤት ውስጥ መኖሬን እቀጥላለሁ”፡፡

ምንም ያህል ከባድ ቢሆንም፣ ሰዎች ያደረጉባችሁን አስከፊ ነገር ለራሳችሁ ስትሉ ልቀቁትና በነጻነት ኑሩ!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
115👍27😢1🎉1
ሁሉንም ሰው የማስደሰት ሱስ
👍6
ሁሉንም ሰው የማስደሰት ሱስ

ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ልንሰራቸው ከምንችላቸው ስህተቶች መካከል ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የመሞከር ስህተት አንዱ ነው፡፡

ይህንን ሁኔታ ስህተት ነው ከምንልበት ምክንያት ዋነኛው፣ ምንም ያህል ሰዎችን ሁሉ ለማስደሰት ብንጣጣር እንኳ ሁኔታው የማይቻል በመሆኑ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሰዎችን ሁሉ ለማስደሰት መሞከርና በማንኛውም ጊዜ በሁሉም ሰው ተቀባይነትን ለማግኘት መሯሯጥ እጅግ አድካሚና ለጉዳት የሚዳርግ በመሆኑ ነው፡፡

በአካባቢው የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ ለማስደሰት የሚታገል ሰው የመነሻ ሃሳቡ የተቀባይነትና በሁሉ የመወደድ ፍላጎት ነው፡፡ ከዚህ ነጥብ በመነሳት ከሚያደርጋቸውና ከሚናገራቸው ነገሮች የተነሳ ለጊዜው ሰዎች ሊደሰቱበት ቢችሉም፣ ብዙም ሳይቆይ የመገፋትና የባዶነት ስሜት ይጫጫነዋል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ሰው እርሱን በመቀበልና በሁኔታው በመደሰት እንደማይዘልቅ ቀስ በቀስ ስለሚደርስበት ነው፡፡

ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ትታገላለህ?

1. ሌሎች ሰዎች ስለተሰማቸው ስሜት አንተ ሃላፊነት ይሰማሃል?

2. አንድ ሰው በአንተ ላይ እንደተበሳጨ ወይም እንዳዘነ ስታውቅ ከልክ ባለፈ ሁኔታ በስሜትህ ላይ ጫና ያስከትልብሃል?

3. ሰዎች እንደፈለጉ ወዲህና ወዲያ የሚያደርጉህ አይነት ሰው እንደሆንክ ይሰማሃል?

4. በአንድ ጉዳይ ላይ ከሌሎች ሰዎች ተቃራኒ ሃሳብ እያለህ እንኳን ተቀባይነት አጣለሁ በሚል ሰበብ ያንን ሃሳብህን ከመናገር ይልቅ መተባበር ይቀልሃል?

5. ብዙ ጊዜ ግልጽ የሆነ ጥፋት እንዳልሰራህ እያወከው እንኳን ይቅርታ የመጠየቅ ዝንባሌ አለህ?

6. አለመግባባት እንዳይፈጠር ለማድረግ ከአቅምህ በላይ ስትታገል ራስህን ታገኘዋለህ?

7. ሰዎች ስሜትህን ሲጎዱት ስለሁኔታው ለሰዎቹ በግልጽ ማውራት ይከብድሃል?

8. ሰዎች አንድን ነገር እንድታደርግላቸው ሲጠይቁህ ማድረግ ባትፈልግም እንኳን ካለብህ የመገደድ ስሜት የተነሳ እሺ የማለት ዝንባሌ አለህ?

9. ሌሎች ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር ስታይ ከዚያ በመነሳት እነሱን ለማስደሰት ስትል ሁኔታህን፣ ተግባርህንና ባህሪህን ትለዋውጣለህ?

10. ሰዎች በአንተ ላይ ያላቸው አመለካከት ጥሩ እንዲሆን ብዙ ስትሯሯጥ ራስህን ታገኘዋለህ?

ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ ምናልባት ከመስመር ያለፈ ሌሎች ሰዎች ለማስደሰት የመታገል ዝንባሌ ሊኖርህ ስለሚችል በሚገባ አስብበት፡፡

በነገራች ላይ፣ በእርግጥም ሰዎች ደስ እንዲላቸው ከራሳችን ምቾት ወጥተን ረጅም ርቀት ልንሄድ የሚገባን ጊዜ ሊኖር ይችላል፣ ሆኖም፣ ሰዎችን ለማስደሰት የማደርገው ጥረት የራሴንና የቤተሰቤን ሕልውና ወደመንካት ክልል ውስጥ የሚያስገባኝ ከሆነ ሁኔታውን በሚገባ ላስብበት ይገባኛል፡፡

በነገው ፖስቴ የመፍትሄ ሃሳቦችን አቀርባለሁ::

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1\050816404958639/
73👍31🎉1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
አዲስ የስልጠና እድል!

የስልጠናው ርእስ፡-
“ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
22👍4
ሰዎችን አስደሳች የመሆንን ዝንባሌ መገንዘብ (የመፍትሄ ሃሳቦች)
👍4
ሰዎችን አስደሳች የመሆንን ዝንባሌ መገንዘብ (የመፍትሄ ሃሳቦች)

በትናንትናው ፖስቴ ላቀረብኩት ሰውን ለማስደሰት የመታገል ችግር መፍትሄ የሚሆኑ የተወሰኑ መመሪያዎችን አቀርለሁ፡፡

ለምንድን ነው ሰዎችን ለማስደሰት የምንታገለው?

1. ሰዎች ለሚሰማቸው ስሜት እኛ ሃላፊነት የመውሰድ ዝንባሌ

• ይህ ዝንባሌ እያየንና እየሰማን ካደግነው ባህላዊ ሁኔታ ወይም ከእምነት አስተምህሮ ሊመጣ ይችላል፡፡

• ሰዎች የሚሰማቸው ስሜት መንስኤው እኛ ሆንም አልሆንም ለራሳቸው ስሜት ሃላፊነት መውሰድ ያለባቸው እነሱ ናቸው፡፡

• የእኛ ሃላፊነት ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ሚዛናዊ መሆንና ስህተት ሲከሰት የእርማት እርምጃዎችን መውሰድ ነው፡፡

2. ከአንድ ከራሳችን ሁኔታ አንጻርና ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሚመጣ የዝቅተኝነት ስሜት

• ይህ ዝንባሌ የእኛን አመጣጥም ሆነ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ሰዎች ያስባሉ ብለን ከምንገምተውና ከምናስበው ሊመጣ ይችላል፡፡

• ሰዎች ምንም አሰቡ ምንም፣ ዋናውና ወሳኙ ነገር እኛ በራሳችን ላይ ያለንን አመለካከት የማስተካከካላችን ጉዳይ ነው፡፡

• መለወጥ የምንፈልገውንና የምንችለውን መለወጥ፣ የማንችለውን ነገር ደግሞ ተቀብሎ መኖር አስፈላጊ ነው፡፡

3. ማንም ሰው በእኔ ሊከፋ አይገባውም የሚል ምልከታና ፍርሃት

• ይህ ዝንባሌ “ባለስልጣኑ” ብዙ በሆነበት ቤት ውስጥ ከማደግና ሁሉም ለሚያሳየን ኃይለኛነትና ትእዛዝ ትክክለኛውን ምላሽ ለመስጠት ሲታገሉ ከማደግ ሊመጣ ይችላል፡፡

• ለህልውናችን በሌሎ ሰዎች ላይ የተደገፍንባቸው አመታት እያለፉ ሲመጡ ራሳችንን በመቻል ያመንንበትን ነገር ማድረግ እንደምንችል ራሳችን ወደማሳመን ማደግ አስፈላጊ ነው፡፡

• ሰዎች በእኛ ሲከፉ ሊያደርጉብን ወይም ሊከለክሉን ከሚችሏቸው ነገሮች ይልቅ እኛ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የምናደርገው ጥረት የበለጠ ጎጂ እንደሆነ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡

4. ከዚህ በፊት ከደረብን የመገፋት ህመም ለመውጣት አለመፈለግ ወይም አለመቻል

• ይህ ዝንባሌ ለደረሰብን የመገፋት ስብራት ትክክለኛው መፍትሄ ምን እንደሆነ ካለማወቅ ሊመጣ ይችላል፡፡

• ሰዎች ከሚያደርሱበትን ማንኛውም አይነት ከአቅማችን በላይ የሆነ ጉዳትና ችግር ለመውጣት ሊያግዘን የሚችል ሌላ ሰው ማግኘት ጠቃሚ ነው፡፡

• ካለፈው መማር፣ ሰዎችን ይቅር ማለትና መለወጥ እንደምንችል አምኖ መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነው፡፡

5. የግል የቀይ መስመር (personal boundary) በማስመር ደረጃ በእውቀት አለመኖር

• ይህ ዝንባሌ የሚመጣው በስሜት እና በማሕበራዊ ብልህነት ካለመብሰል ነው፡፡

• ከሰዎች ጋር የምናደርጋቸው የግንኙነት ልውውጦች አንድ ወጥ ስሌት እንደሌላቸውና ሁኔታዊ እንደሆኑ ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡

• ይህንን ሁኔታ መስመር ለማስያዝ የራስን ስሜት መገንዘብና አያያዙን ማወቅ፣ እንዲሁም የሌላውን ሰው ስሜት መገንዘብና አያያዙን ማወቅን ይጠይቃል፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
61👍14🤩2
“ሰባቱ ማሕበራዊ ኃጢያቶች”

በፈረንጆቹ አቆጣጠር በOctober 22, 1925 ጋንዲ (Mohandas Gandhi) በየሳምንቱ በሚያሳትመው Young India በተሰኘው የዜና መጽሔቱ ላይ “ሰባቱ ማሕበራዊ ኃጢያቶች” (The Seven Social Sins) የተሰኘን ጽሑፍ አስፍሮ ነበር፡፡

እነዚህ ዘመን-ዘለል እውነታዎች የግላችንንና የሕብረተሰባችንን ወቅታዊ ልምምድ በመገምገም ለማስተካከል ድጋፍ እንደሚያደርጉልን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

1. ስራ የሌለው ብልጽግና (Wealth without work)

2. ሕሊና የሌለው ደስታ (Pleasure without conscience)

3. ባህሪይ የሌለው እውቀት (Knowledge without character)

4. ግብረ-ገብ የሌለው ንግድ (Commerce without morality)

5. ሰብዓዊ ርህራሄ የሌለው ሳይንስ (Science without humanity)

6. መስዋእትነት የሌለው ኃይማኖት (Religion without sacrifice)

7. መርህ የሌለው ፖለቲካ (Politics without principles)

መለስ እንበል!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
3
2025/10/09 02:19:41
Back to Top
HTML Embed Code: