ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር
በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship, Coaching and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?
(በውጪ ሃገር ያላችሁም በTelegram and WhatsApp ከዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ፡፡)
1. ያጋጠማችሁ ወቅታዊ አስቸጋሪ ሁኔታ ካለና በራሳችሁ ለመወጣት ስላቃታችሁ እገዛ ከፈለጋችሁ፣
2. የሕይወታችሁን ራእይ ወይም ዓላማ ባለማወቅ ከተወዛገባችሁና አቅጣጫን መያዝ ከፈለጋችሁ፣
3. ካለባችሁ አጉል ልማድ በመውጣት አዲስ ልማድን ማዳበር ካስቸገራችሁና ምክርና ድጋፍ ከፈለጋችሁ፣
4. መመለስ ያቃታችሁ የሕይወት ጥያቄዎች ከበዙባችሁና በአንድ ለአንድ ውይይት የመፍትሄ መንገድ ከፈለጋችሁ፣
5. በራሳችሁ መወጣት ያልቻላችሁት የተያዩ የስሜትና የስነ-ልቦና ጥያቄዎች ውስጥ እንዳላችሁ ከተሰማችሁና ከሁኔታው ለመውጣት ምክር ከፈለጋችሁ፣
ከግል በተጨማሪም ቁጥራችሁ ከአስር ባልበለጠ ሁኔታ በመሰባሰብ የGroup Coaching and Training ጥያቄም ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
በቴሌግራም
@DrEyobmamo
inbox በማድረግና በፌስቡክ መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን ማሳወቅ ትችላላቸሁ፡፡

❤59👍20🔥2😁1
ኃይላችሁን አታስቀሙ!
ዶ/ር ፊል (Phil McGrow) በታዋቂዋ በኦፕራ (Oprah Winfrey) የቴሌቪዢን ፕሮግራም ላይ በእንግድነት ለአመታት በተከታታይ ከቀረበ በኋላ ባተረፈው ታዋቂነት የራሱን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከመጀመሩም በላይ የተለያዩ መጽሐፍቶችን በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡ “Life Strategies” በሚል ርእስ በጻፈው መጽሐፍ ውስጥ የተለያዩ የሕይወት ሕጎችን ይነግረናል፡፡
ከእነዚህ ህጎች መካከል ዘጠነኛውን ህግ በጻፈበት ምእራፍ ውስጥ “በቁጣ የተጀመረ ነገር በሃፍረት ይፈጸማል” የሚለውን የBen Franklin ትርጉም ያለው አባባል በመግቢያነት ተጠቅሞበታል፡፡ይህ ዘጠነኛው የሕይወት ሕግ፣ “በይቅርታ ውስጥ ኃይል አለ” የተሰኘ ነው፡፡
ዶ/ር ፊል እንዲህ ሲል ይመክረናል፡-
“ቁጣና ቂመኝነት እያደረገብህ ያለውን ክፉ ነገር ለማየት አይኖችህን ክፈት፡፡ የጎዱህ ሰዎች የወሰዱብህን ጉልበት መልሰህ የራስህ አድርግ”፡፡ እንደዚህ አይነት ጠንካራ ምክር ለመለገስ የፈለገበትን ምክንያት ሲያብራራ እንዲህ ይላል፣ “ሰዎች ካላቸው ስሜቶች መካከል ጥላቻ፣ ቁጣ እና ቂም እጅግ ኃይለኛና አጥፊ የሆኑ ስሜቶች ናቸው”፡፡
ሰዎች በአንተ ላይ ከአንተው የቀሙት ኃይል እንዲኖራቸው ስትፈቅድ እየደከምክ ትሄዳለህ፡፡ ይህ የሚሆነው ደግሞ በበደሉህና በጎዱህ ሰዎች ላይ ጥላቻና ቂምን አምቀህ በመያዝ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ለመኖርና ለመሻሻል የሚያስችልህን የግልህን ጉልበት ለእነዚያው ሰዎቸ አሳልፈህ ትሰጣለህ፡፡ የመተኛትና የማረፍ፣ የመመገብ ፍላጎትና የመዝናናት ስሜትህ ከመቀማቱም ባሻገር የስሜት ቀውስ ውጤት ለሆኑ ህመሞችም ራስህን ታጋልጣለህ፡፡
የየእለት ኑሮህ ከሰዎች ጋር ያገናኝሃል፡፡ በዚህ ግንኙነት ውስጥ ደግሞ ሰዎችን የመጉዳትና በሰዎች የመጎዳት ሁኔታ የማይቀር ነው፡፡ ስለሆነም፣ የጎዱህ በመሰለህ ሰዎች ላይ ልትተወው የማትፈልገውን ጠንካራ አሉታዊ ስሜት ስትይዝ አቅም እያጣህ ትሄዳለህ፡፡ ይህንን አትርሳ፣ ቂምና ጥላቻ የያዝክበት ሰው በአንተ ላይ ጉልበት ያለው ሰው ነው፡፡ እርሱ የአንተን ሁኔታ ይቆጣጠራል እንጂ አንተ የራስህን ሁኔታ የመቆጣጠር ጉልበት አይኖርህም፡፡ ሰውየው በተገኘበት ቦታ የማትገኘውና ስሙ በተጠራበት ጊዜ ሁሉ ስሜትህ የሚቃወስበት ምክንያቱ ኃይልህን ስለተቀማህ ነው፡፡
ኃይልን የማስመለስ ማንገዶች፡-
1. ይቅር ማለት ያለብንን ሰዎች ይቅር ማለት፡፡
2. ይቅርታ ካደረግን በኋላ አስፈላጊውን የቀይ መስመር በማስመር ግንኙነትን ሚዛናዊ ማድረግ፡፡
3. ትክክለኛው ምላሽ ሰዎችን ለመጉዳት ከመሞከር ይልቅ ራስን ማሻሻል እንደሆነ በማስታወስ ያንን መለማመድ፡፡
መልካም የነጻነት ቀን ይሁላችሁ!
https://www.tgoop.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1\050816404958639/

Telegram
Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
You can contact me
@DrEyobmamo
❤196👍36🔥9😁1
“ያለማሰብ ውሳኔ”
“እውነትን በራስህ አይኖች ማየትን ተማር፡፡ አንድ ሰው የነገረህን ነገር ብቻ እውነት አድርገህ በፍጹም አትቀበል”
በአሁን ሰዓት በአንድ አንተ በማታውቀው ቦታ ሁለት ሰዎች ተገናኝተው እጅግ በጣም ስሜታዊ በሆነ መልኩ ስለአንተ እየተነጋገሩ ነው እንበል፡፡ እነዚህ ሰዎች በሚነጋገሩበት ነገር ላይ ያለህን አመለካከት ወይም ስሜት ተናገር ብትባል ምን ትላለህ? ምናልባት መልስህ፣ “ምንም አመለካከት ወይም ስሜት የለኝም” የሚል ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ምክንያቱም፣ ስለሁኔታው ምንም የምታውቀው ነገር ስለሌለህ ነው፡፡
ሰዎቹ ተገናኝተው ስለአንተ አወሩ እንጂ አንተ ጋር ምንም የደረሰ ነገር የለም፡፡ በተጨማሪም፣ ስለአንተ የሚለዋወጡት ጠንካራ ስሜትን ያዘለ ንግግር መልካም ይሁን ክፉ የምታውቀው ነገር የለህም፡፡ ስለሆነም፣ በሁኔታው ላይ ምንም አይነት አመለካከትም ሆነ ስሜት ሊኖርህ አይችልም፡፡
ከዚህ እውነታ ሁለት ነገሮችን መመልከት እንችላለን፡፡
አንደኛው፣ የምትሰማቸውንና የምታያቸውን አሉታዊ ነገሮች በቀነስክ ቁጥር ጠንካራ ስሜቶችና አመለካከቶችን ትቀንሳለህ፡፡ ስለሆነም፣ ለሕይወትህ ሕልውናና እድገት አስፈላጊ ከሆኑን ነገሮች ውጪ መስማትና ማየት የማይገቡህን ነገሮች ማጣራትና አላስፈላጊውን ማስወገድ ታላቅ ጥበብ ነው፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ልታስብ የሚገባህ ጉዳይ፣ አንዳንድ ጊዜ ስለአንተ የሚባለውን ሁሉ ላለመስማት የማትችልበት ጊዜ እንዳለ ማስታወስ አለብህ፡፡ ስለዚህም፣ ልክ ከላይ እንደጠቀስነው ስለነገሮቹ ፈጽሞ በማትሰማበት ጊዜ የሚኖርህን አይነት ኃይልና አቅም እንዲኖርህ ከፈለግህ፣ በምትሰማውና በምታየው ነገር አንጻር የግድ ጠንካራ ስሜትና አመለካከት ልትይዝ እንማይገባህ ማሰብ ትችላለህ፡፡
ያም ሆነ ይህ የምታንሸራሽራቸው ስሜቶችና ለመግለጽ የምትፈልጋቸው አመለካከቶች በተበራከቱ ቁጥር ያንን ለማድረግ ለዋናው ዓላማህ ሊውል ከሚገባው ጉልበትና ጊዜ ላይ መቀናነስ እንደሚገባህ አትዘንጋ፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ በአይኖችህ ካላየህና በማስረጃ ካላረጋጋጥክ በስተቀር መረጃን በጆሮህ ሰምተህ ብቻ ከማመን ተጠበቅ፡፡ በተጨማሪም፣ በውስጥ በአይኖችህ አይተህ ሙሉ ለሙሉ ያላመንክበትን ነገር በአንደበትህ በመናገር ከማስተጋባትም ራስህን ጠብቅ፡፡
“የጥበብ መንገድ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተቀነጨበ፡፡

❤90👍29🔥3
ጥያቄ፡-
ተቋማዊ ዝምታ (Organizational Silence)
በአንድ ተቋም ውስጥ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ዝምምምም የሚሉ ሰዎች ተቋምን በመግደልም በማዳናንም ያላቸውን ድርሻ ካለህ ልምድ አንፃር ሀሳብ ብታካፍለን ወደድሁ። እኛ ሀገር የሚገራርሙ ተቋማት ይጀመሩና በኋላፊው፣ በባለሙያው፣ በሚቆጣጠረው ዝምታ ምክንያት ሞተዋል። አመሠግናለሁ ዶር፡፡
መልስ፡-
ይህ የገለጽከው አይነት “የአመራር ዝምታ” ከተለያዩ ሁኔታዎች ሊከሰት ይችላል፡፡ ለምሳሌ፣ መሪው ብቃት እንደሌለው ሲያስብ፣ አቋም ከያዘ ይገጥመኛል ብሎ የሚያስበውን ነገር መፍራትና የመሳሰሉት፡፡ መነሻው ያም ሆነ ይህ ይህ የዝምታ አመራር መጠሪያ ስም አለው፡- ሌሰፌር (Laissez-faire) አመራር - ልቅ የአመራር “ስልት” በመባል ይታወቃል፡፡
ይህ ስልት ጥንታዊ ከሚባሉት ሶስት አመራር ስልቶች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ (ስልቶቹ አሁን ከ10 በላይ ደርሰዋል)፡፡
እነዚህ ሶስቱ ስልቶች የሚከተሉት ናቸው፡-
1. አውቶክራቲክ (Autocratic) አመራር - ገደብ የለሽ ስልጣን ያለው የአመራር ስልት
2. ዴሞክራቲክ (Democratic) አመራር - መብት ሰጪ የአመራር ስልት
3. ሌሰፌር (Laissez-faire) አመራር - ልቅ የአመራር “ስልት”
አሁን ባለንበት ዘመን የቤተሰብን አመራር፣ የተቋምን አመራር፣ የሕብረተሰብ (የሃገር) አመራር እየሞገተ ያለው ሁኔታ መሪዎች ሌሰፌር (Laissez-faire) የአመራር ስልትን እንዲከተሉ ሲያወርዳቸው ማየት የተለመደ ነው፡፡
ሌሰፌር (Laissez-faire) የአመራር ስልት ማለት ልቅ የአመራር “ስልት” ማለት ነው፡፡
ሌሰፌር የሚለው ቃል በፈረንሳይኛ፣ “ነገሮች በራሳቸው እንዲንከባለሉና እንዲሆኑ መልቀቅ” የሚለውን ሃሳብ የያዘ ነው፡፡ ይህ አይቱን የአመራር ስልት የሚከተል መሪ ተከታዮች፣ ሰራተኞች ወይም ሕዝቡ ካለምንም መታየትና ቁጥጥር በራሳቸው ስራውን እንዲያንቀሳቅሱ የሚለቅቅ መሪ ነው፡፡
የሌሰፌር አመራር፣ “አመራር-አልባ” የአመራር ስልት በመባልም ይታወቃል፡፡ ይህ አይነቱ አመራር ዘይቤ በባህሪያቸው፣ በዲሲፕሊናቸውና በብቃታቸው የተመሰከረላቸው ሰዎችን ለመምራት የሚጠቅም ሊሆን ይችላል፡፡
ከስሙ ትርጓሜ እንደምንረዳው ግን አመራሩ ልቅነትን፣ እንደፈለጉ መሆንንና ከቁጥጥር ውጪ የሆነን የመሪ-ተመሪ ግንኙነትን ስለሚያንጸባርቅ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡
• ሌሰፌር (Laissez-faire) ወይም ልቅ የአመራር “ስልት” የሚከተል ቤተሰብ በስነ-ምግባር ብልሹ የሆኑ ልጆችን ያፈራል፡፡
• ሌሰፌር (Laissez-faire) ወይም ልቅ የአመራር “ስልት” የሚከተል የተቋም መሪ ሰርአት የሌለው ስራ ሂደትና የሰራተኞች ባህሪይን ይፈለፍላል፡፡
• ሌሰፌር (Laissez-faire) ወይም ልቅ የአመራር “ስልት” የሚከተል የሕብረተሰብ (የሃገር) መሪ ለሕግ የማይገዛና ጋጥ-ወጥ ዜጋ ይፈጥራል፡፡
የበሰለ መሪ ምንም እንኳን ጨዋና ለስላሳ በመሆን ቢያምንም ከዚያም ጋር ግን አቅጣጫን የሚያሳይ፣ ስርአትንና ህግን በማስቀመጥ በትክክል መከበሩን የሚከታተልና ጠንካራ መሆን ሲገባው በጥንካሬው የሚታወቅ ሊሆን ይገባዋል፡፡

❤84👍25🔥3
የሚሳካልንና የማይሳካልን
የሚሳካልኝንና የማይሳካልኝን መለየት ማለት ብርቱ ጎኔን በሚገባ ለይቶ ማወቅ ማለት ነው፡፡
ማንኛውም ሰው ወደዚህች አለም ሲመጣ ቢያንስ ከአንድ ዝንባሌንና ስጦታን ጋር ነው የሚመጣው፡፡ ይህንን ዝንባሌ ወይም ስጦታ በመለየት እነሱ ላይ ማተኮር አስፈላጊ የስኬት ቁልፍ ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች በብዙውን ጊዜአቸውን የሚያሳልፉት ፈጽሞ ዝንባሌአቸው ያልሆነውን ነገር ለማዳበር በመታገል ነው፡፡ አስተዋዮችን ዝንባሌአቸውና ስጦታቸው የቀደደላቸውን ፈር በመከተል ከስኬት ወደ ስኬት ይሸጋገራሉ፡፡
በሚሳካልኝና በማይሳካልኝ መካከል ለመለየት መውሰድ የምችላቸው እርምጃዎች፡-
1. ሁሉን ነገር እንደማልችል አምኖ መቀበል
ምንም ብንታገል የማንችላቸው ነገሮች እንዳሉ በማመን መቀበልና ራስን ማረጋጋት የብስለት ምልክት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የማይችሉትን አምኖ መቀበልን እንደ ሽንፈት ስለሚቆጥሩት ካልተሰጣቸው ነገር ጋር ሲታገሉ ራሳቸውን ያደክማሉ፡፡
2. የሚያታግለንን ነገር መልቀቅ
ስናደርገው የሚያታግለኝንና ውስጣችንን የማያጓጓውን ነገር በመለየት ቀስ በቀስ መልቀቅ የአስተዋይነት ምልክት ነው፡፡ የማይሳካልን ነገር ላይ ብዙ ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ስንሰዋ የሚሳካልንን ነገር እየጣልነው እንደሆነ ማስታወስ አለብን፡፡
3. የሚሳካልንን ነገር ማሳደግ
ስናደርገው የሚሳካልንንና ውስጣችንን የሚያነሳሳውን ነገር በመለየት የበለጠ ጊዜን በመስጠት ማሳደግ ታላቅ የስኬት ቁልፍ ነው፡፡ ምንም አደረግን ምንም፣ በብርታታችን ላይ እንጂ በድካማችን ላይ በፍጹም አንገንባ፡፡

❤90👍30🎉2🔥1
አዲስ የስልጠና እድል!
የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡
እናመሰግናለን!

❤49👍11
ጊዜ እያለን ልክ እንደሌለን!
ጊዜ እያለን ልክ እንደሌለው የምንኖረው፣ ያንን ያለንን ጊዜ በሚገባ የማንጠቀምበት ከሆነ ነው፡፡
ጊዜያችን ሲባክን ደግሞ ባለን ጊዜ ሰርተን ማግኘት የሚገባንን ገንዘብም ሆነ ሌሎች የገንዘብ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች አብረው ይባክናሉ፡፡ ስለሆነም፣ ጊዜ ባከነ ማለት ሁሉም ነገር ባከነ ማለት ነው፡፡ ጊዜ አተረፍን ማለት ደግሞ ብዙ ነገር አተረፍን ማለት ነው፡፡
ማንኛውንም ነገር የምናተርፈው በቅድሚያ ጊዜያችንን ስናተርፍ ነው፡፡ አንድ ሰው ጊዜውን በትክክል ሲጠቀምና ጊዜ ሲተርፈው፣ ተጨማሪ ገንዘዝን ለማትረፍ የማሰቢያ እና የመስሪያ ጊዜ ያገኛል፡፡
የብዙ ነገራችን መዘባረቅ መነሻው ጊዜያችንን በትክክል ስለማንጠቀም ይሆን?
ጊዜያችሁን በውጤታማነት እንድትጠቀሙ የሚያግዛችሁ ወሳኝ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና አያምልጣችሁ፡፡

❤49👍13🔥5
ስራ ፈላጊ ነዎት እንግዲያውስ እቤትዎ ሆነው በቀላሉ በያዙት ስልክ እና ኢንተርኔት በመጠቀም ያለምንም መነሻ ካፒታል መስራት
የሚችሉት መልካም እድል ይዘንልዎ መተናል
በተለዬ ሴቶችን ያበረታታል ።
አብራችሁን መስራት የምትፈልጉ 👇
ለበለጠ መረጃ፥ https://www.tgoop.com/mercipo
ስልክ ☎️ 0943140757
ስልክ ☎️ 0910967521
ይፍጠኑ ይጀምሩ ለማገዝ ዝግጁ ነን!
የሚችሉት መልካም እድል ይዘንልዎ መተናል
በተለዬ ሴቶችን ያበረታታል ።
አብራችሁን መስራት የምትፈልጉ 👇
ለበለጠ መረጃ፥ https://www.tgoop.com/mercipo
ስልክ ☎️ 0943140757
ስልክ ☎️ 0910967521
ይፍጠኑ ይጀምሩ ለማገዝ ዝግጁ ነን!
❤18👍8
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ነገራችን ወሬ ብቻ እንዳይሆን!
“ስለ አንድ ነገር የምታወሩ ከሆነ ነገሩ ህልም ይባላል፣ ስለነገሩ በሚገባ ማሰብ ስትጀምሩ ነገሩ ወደመቻል ይሸጋገራል ማለት ነው፣ ለነገሩ የጊዜ ሰሌዳ ካዘጋጃችሁለት ግን ነገሩ እውን ወደመሆን ይመጣል” - ANTHONY ROBBINS
• ቁጭ ብላችሁ ወደማሰብና ስለነገሩ ወደማሰላሰል ያልደረሰ እስካሁን በወሬ ብቻ የቀረውን ነገር እስቲ ለማስታወስ ሞክሩ!
• ካሰባችሁና ካሰላሰላችሁት በኋላ ወደ እርምጃ እና ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት የጊዜ ገደብና ሰሌዳ ያላስቀመጣችሁለትንም ነገር እስቲ አስቡት!
ነገሮቻችሁ ከወሬ አልፈው ሃሳባችሁን እንዲገዙት፣ ከሃሳብ አልፈው ደግሞ ወደ እውነታ እንዲመጡ ከፈለጋችሁ ይህንን መርህ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡
ንግግራችን ረገብ፣ ሃሳባችሁን ሰፋ፣ እቅዳችሁ ደግሞ ተግባራዊ በማድረግ ልቃችሁ ተገኙ!
https://www.tgoop.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

❤39👍16😱1😢1
ሰዎች ስኬታማ የሚሆኑት!
አንዳንዶች እደዚህ ሲሉ ይደመጣሉ፡- “ስኬታማና ቢዚ ስሆን ጊዜዬን በሚገባ የማደረጃትን ስልት አዳብራለሁ”፡፡
ሁኔታው ግን የዚያ ተቃራኒ ነው፡፡ ስኬታማና ቢዚ የሆኑ ሰዎች እንደዚያ የሆኑት ጊዜያቸውን በትክክል መጠቀም ስጀመሩ ነው እንጂ ቢዜ ስለሆኑ አይደለም ጊዜያቸውን በትክክል መጠቀም የጀመሩት፡፡
የእነዚህን ሁለት ነገሮች ቅደም ተከተል ማዛባት፣ ፈጽሞ የማይመጣን ነገር ስንጠብቅ ጊዜያችንን እንድናባክን ያደርገናል፡፡
ጊዜያችሁን በሚገባ መጠቀም ስትጀምሩ ስኬታማ እየሆናችሁና ቢዚ እየሆናችሁ መሄዳችሁ አይቀርም፡፡ ስለዚህ፣ ጊዜያችሁን በሚገባ በማደራጀት አሁኑኑ ጀምሩ፣ የቀረው ተከትሎ ይመጣል፡፡
ይህንን ልምምድ ለማዳበር አቅጣጫ የሚያሳያችሁ ስልጠና ስለተዘጋጀ ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ ሰልጥኑ፡፡
የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡
እናመሰግናለን!
አንዳንዶች እደዚህ ሲሉ ይደመጣሉ፡- “ስኬታማና ቢዚ ስሆን ጊዜዬን በሚገባ የማደረጃትን ስልት አዳብራለሁ”፡፡
ሁኔታው ግን የዚያ ተቃራኒ ነው፡፡ ስኬታማና ቢዚ የሆኑ ሰዎች እንደዚያ የሆኑት ጊዜያቸውን በትክክል መጠቀም ስጀመሩ ነው እንጂ ቢዜ ስለሆኑ አይደለም ጊዜያቸውን በትክክል መጠቀም የጀመሩት፡፡
የእነዚህን ሁለት ነገሮች ቅደም ተከተል ማዛባት፣ ፈጽሞ የማይመጣን ነገር ስንጠብቅ ጊዜያችንን እንድናባክን ያደርገናል፡፡
ጊዜያችሁን በሚገባ መጠቀም ስትጀምሩ ስኬታማ እየሆናችሁና ቢዚ እየሆናችሁ መሄዳችሁ አይቀርም፡፡ ስለዚህ፣ ጊዜያችሁን በሚገባ በማደራጀት አሁኑኑ ጀምሩ፣ የቀረው ተከትሎ ይመጣል፡፡
ይህንን ልምምድ ለማዳበር አቅጣጫ የሚያሳያችሁ ስልጠና ስለተዘጋጀ ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ ሰልጥኑ፡፡
የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡
እናመሰግናለን!
❤22👍9🎉3
አስገራሚ ሰዎች ናችሁ!
You are amazing!
እስካሁን ከደረሳችሁበት ደረጃ የላቀ ደረጃ ባለመድረሳችሁ ከሚሰማችሁ የቅሬታ ስሜት በበለጠ ሁኔታ እንዲያውም ያሳለፋችሁትን ሁሉ ትግል አልፋችሁ እዚህ ደረጃ መድረስ በመቻላችሁ ያላችሁ ደስታ ሚዛን ካልደፋ የወደፊታችሁ ሊያሳስባችሁ ይገባል፡፡
የወቅቱን የአለም ሁኔታ፣ በሃገራችን ያለውን የመሰናክል ብዛት፣ የሰዎችን አስመሳይነትና አስቸጋሪነት፣ የራሳችሁን የስሜት ውጣ ውረድ፣ ብዙውን ነገር ካለምንም ደጋፊ ለብቻችሁ የመጋፈጣችሁን ሁኔታ . . . አልፋችሁ አሁን ያላችሁበት ደረጃ መድረሳችሁ በራሱ አስገራሚ ሰው የመሆናችሁ ማስረጃ ነው፡፡
እናንተ ባለፋችሁበት ሁኔታ ቢያልፉና ተጋፍጣችሁ የመጣችኋቸውን ነገሮች ቢጋፈጡ ኖሮ እናንተ አሁን ያላችሁበት ደረጃ ለመድረስ ቀርቶ የህልውናቸው ጉዳይ እንኳን የሚያጠራጥር አይነት ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ እናንተ ግን ብዙ ታግላችሁ ሳትበገሩ፣ ወላውላችሁ ተስፋ ሳትቆርጡ፣ ወድቃችሁ ውዳቂ ሆናችሁ ሳትቀሩ . . . እዚህ ደርሳችኋል፡፡
አስገራሚ ሰዎች ናችሁና በዚሁ ግፉበት!
https://www.tgoop.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
You are amazing!
እስካሁን ከደረሳችሁበት ደረጃ የላቀ ደረጃ ባለመድረሳችሁ ከሚሰማችሁ የቅሬታ ስሜት በበለጠ ሁኔታ እንዲያውም ያሳለፋችሁትን ሁሉ ትግል አልፋችሁ እዚህ ደረጃ መድረስ በመቻላችሁ ያላችሁ ደስታ ሚዛን ካልደፋ የወደፊታችሁ ሊያሳስባችሁ ይገባል፡፡
የወቅቱን የአለም ሁኔታ፣ በሃገራችን ያለውን የመሰናክል ብዛት፣ የሰዎችን አስመሳይነትና አስቸጋሪነት፣ የራሳችሁን የስሜት ውጣ ውረድ፣ ብዙውን ነገር ካለምንም ደጋፊ ለብቻችሁ የመጋፈጣችሁን ሁኔታ . . . አልፋችሁ አሁን ያላችሁበት ደረጃ መድረሳችሁ በራሱ አስገራሚ ሰው የመሆናችሁ ማስረጃ ነው፡፡
እናንተ ባለፋችሁበት ሁኔታ ቢያልፉና ተጋፍጣችሁ የመጣችኋቸውን ነገሮች ቢጋፈጡ ኖሮ እናንተ አሁን ያላችሁበት ደረጃ ለመድረስ ቀርቶ የህልውናቸው ጉዳይ እንኳን የሚያጠራጥር አይነት ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ እናንተ ግን ብዙ ታግላችሁ ሳትበገሩ፣ ወላውላችሁ ተስፋ ሳትቆርጡ፣ ወድቃችሁ ውዳቂ ሆናችሁ ሳትቀሩ . . . እዚህ ደርሳችኋል፡፡
አስገራሚ ሰዎች ናችሁና በዚሁ ግፉበት!
https://www.tgoop.com/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
❤87👍19🔥5🤩5
በጩኸት የተበከለ አመለካከት!
• ጠዋት ገና ስነቃ፣ ስልኬን ከፍቼ፣ የጆሮ ማዳመጫውን ጆሮዬ ላይ ሰክቼ የምሰማው ጩኸት!
• ከቤት ስወጣ መንገድ ላይ የምሰማው የሰውና የመኪና ጡሩምባው ጩኸት!
• ስራ ቦታ ያለው ሰራተኛ ቀስ ብሎ ስለማይነጋገር ጩኸት!
• ለምሳ ስንወጣ ምግብ ቤቱ ያለው ሰው ወዳጆቹ አጠገቡ እያሉ እንከኳን ንግግሩ ጩኸት!
• በምግብ ቤቱ ያለው ሙዚቃ ያለው ጩኸት!
• ከስራ ወጥቼ ከጓደኞቼ ጋር ካፌ ስንገናኝ በካፌው ውስጥ ያሉ ሰራተኞችም ሆኑ ተጠቃሚዎች ጩኸት!
ዝምታ ከሌለ እንዴት አስባለሁ? . . . ካላሰብኩስ እንዴት አዳዲስ ነገሮችን አፈልቃለሁ? . . . አዳዲስ ነገሮችን ካላፈለቅኩስ እንዴት አድጋለሁ?
ምናልባት እኔም ሆንኩ አንዳንዱ ጸጥታን ያልተለማመደው የሕብረተሰብ ክፍል የማይረጋጋው፣ አዲስ ነገር የማይፈጥረውና የማያድገው፣ ከዚህ ሁኔታ የተነሳ ይሆን?

❤69👍27😢5🔥2
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የጊዜ አጠቃቀማችን ጉዳይ!
የየቀኑ ሩጫና መጨናነቅ ቀኑ እንደ አንድ ደቂቃ ታጥፎ የሄደ እስኪመስል ድረስ ያዋክበናል፡፡ ያለን ምርጫ አንድ ነው፣ ሰዓትን በአግባቡ የመጠቀምን ጥበብ ማዳበር!
ሰዓታችንን በአግባብ በመጠቀም ሁኔታዎችን ካልመራናቸው ሁኔታዎች ራሳቸው እኛን ይመሩናል፡፡ በሰዎችም በቀላሉ የምንመራና የምንነዳ ሰው እንሆናለና፡፡ ውጤቱም የምርታማነትና የስኬታማነት መቀነስ ነው፡፡ ጊዜያችንን በአግባብ የመጠቀም
ብቃት እንደጎደለን ለማወቅ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራሳችንን መጠየቅ እንችላለን፡-
• አንድን የጊዜ ገደብ ያለውን ስራ ለመጨረስ ዘወትር በመጨረሻው ሰዓት የመሯሯጥ ባህሪ አለኝ?
• አብዛኛውን ጊዜ ለቀጠሮም ሆነ ለሌላ የጊዜ ገደብ የመዘግየት ዝንባሌ አለኝ?
• በተመሳሳይ ጊዜ ከአንድ በላይ ቀጠሮ ወይም ፕሮግራም በመያዝ ግራ የመጋባት ባህሪይ ያጠቃኛል?
• ሳምንታት፣ ወራትና አመታት ባለፉ ቁጥር እኔ የማከናውናቸው ተግባሮች ግን እንዳልተሻሻሉ ይሰማኛል?
እነዚህና መሰል ከጊዜ አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች ከታዩብን፣ የተዘጋጀው ስልጠና ጠቃሚ ነው፡፡
የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡
እናመሰግናለን!
የየቀኑ ሩጫና መጨናነቅ ቀኑ እንደ አንድ ደቂቃ ታጥፎ የሄደ እስኪመስል ድረስ ያዋክበናል፡፡ ያለን ምርጫ አንድ ነው፣ ሰዓትን በአግባቡ የመጠቀምን ጥበብ ማዳበር!
ሰዓታችንን በአግባብ በመጠቀም ሁኔታዎችን ካልመራናቸው ሁኔታዎች ራሳቸው እኛን ይመሩናል፡፡ በሰዎችም በቀላሉ የምንመራና የምንነዳ ሰው እንሆናለና፡፡ ውጤቱም የምርታማነትና የስኬታማነት መቀነስ ነው፡፡ ጊዜያችንን በአግባብ የመጠቀም
ብቃት እንደጎደለን ለማወቅ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራሳችንን መጠየቅ እንችላለን፡-
• አንድን የጊዜ ገደብ ያለውን ስራ ለመጨረስ ዘወትር በመጨረሻው ሰዓት የመሯሯጥ ባህሪ አለኝ?
• አብዛኛውን ጊዜ ለቀጠሮም ሆነ ለሌላ የጊዜ ገደብ የመዘግየት ዝንባሌ አለኝ?
• በተመሳሳይ ጊዜ ከአንድ በላይ ቀጠሮ ወይም ፕሮግራም በመያዝ ግራ የመጋባት ባህሪይ ያጠቃኛል?
• ሳምንታት፣ ወራትና አመታት ባለፉ ቁጥር እኔ የማከናውናቸው ተግባሮች ግን እንዳልተሻሻሉ ይሰማኛል?
እነዚህና መሰል ከጊዜ አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች ከታዩብን፣ የተዘጋጀው ስልጠና ጠቃሚ ነው፡፡
የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡
እናመሰግናለን!
❤51👍5🎉3
ከጊዜ ጋር መራመድ!
ጊዜ ቆሞ አይጠብቀንም! ወይ አብረን በመራመድ ስኬታማ እንሆናለን፣ ወይም በቸልተኛነት ከስረን እንቀራለን፡፡
ጊዜያችንን በሚገባ ስንጠቀም . . .
⏱️ የሕይወት ዘይቤያችን professional ስለሚሆን በራስ መተማመናችን እየጨመረ ይሄዳል፡፡
⏱️ ሰዎች የሚያምኑን፣ የሚደገፉብንና የሚቀበሉን ወደመሆን እናድጋለን፡፡
⏱️ ስራችንን በተደራጀ ሁኔታ ስለምንሰራ በኢኮኖሚ እያደግን እንሄዳለን፡፡
ጊዜን በተገቢው መንገድ አለመጠቀም . . .
⏱️ በሌሎቸ መቀደምንና ኋላ ቀርነትን ያመጣል፡፡
⏱️ የባከነው ጊዜ ከሚያመጣው የማይመለስ ክስረት የተነሳ የኋላ ኋላ ጸጸትን ያስከትላል፡፡
⏱️ ለየትኛውም የዘመኑ አሰራር የማንመጥን አይነት ሰዎች ሆነን እንድንቀር ያደርገናል፡፡
ጊዜያችሁን በሚገባ የመጠቀምን ስልት አዳብሩ! ራሳችሁ አዘምኑ!
ለዚህ የሚጠቅማችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና አያምልጣችሁ፡፡

❤55👍10🔥1
ጊዜያችን በከንቱ እንዳያልፍ!
እያንዳንዱ የእድሜ ደረጃ የራሱ የሆነ ውበት አለው፡፡ ከልጅነት እስከ ወጣትነት፣ አልፎም እስከ አዋቂነት!
እነዚህ የእድሜ ደረጃዎች ያላቸው ውበት የሚወጣው ግን ለዚያ እድሜ የሚመጥን የጊዜ አጠቃቀም ብቃት ስናዳብርና ስንጠቀምበት ነው፡፡
ይህ የሚዳብረው . . .
⏱️ ጊዜያችንን የምንሰጠውን ዓላማ ስናውቅ፣
⏱️ ጊዜያችንን በትክክል ለመጠቀም የሚያስችል ዲሲፕሊን ሲኖረን እና
⏱️ የጊዜ አጠቃቀም ክህሎት ስናዳብር ነው፡፡
ይህ አንዴ ካለፈ የማይመለሰውን ጊዜዬን ምን ላይ ላውለው? ጊዜዬን በሚገባ ለመጠቀምስ የሚያስፈልገኝ ዲሲፕሊን ምን አይነት ነው? ጊዜዬን በስኬታማነት ለማዋቀርስ ምን አይነት ችሎታና ክህሎት ነው የሚያስፈልገኝ?
እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን በሚገባ የሚያመላክታችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል!

❤60👍8