Telegram Web
የአዲስ አመት ውሳኔዎች!

አንድ ሰው አንዲህ ሲል ሞጋች ሃሳብ ይናገራል . . .

“መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ ቦርሳ በእጄ ይዤ በውስጡ መቶ ብር ብቻ ከሚኖረኝ፣ የመቶ ብር የላስቲክ ቦርሳ ይዤ በውስጡ መቶ ሺህ ብር ቢኖኝ ይሻለኛል” . . .

“በውጪ ውድና ዘመናዊ ልብስ ለብሼ በውስጤ ግን ያረጀ አመለካከት ከሚኖረኝ ይልቅ፣ የተለመደና አመካኝ ልብስን ለብሼ ውስጤ የከበረና የታደሰ አመለካከት ቢኖረኝ ይሻለኛል” . . .

“በእጄ ላይ ውድ የተባለ ሰዓት አስሬ ለዘመኑ የማይመጥን የጊዜ አጠቃቀም ከሚኖረኝ፣ አማካኝ ዋጋ ያለው ሰዓት አስሬ ጊዜውን በሚገባ የሚጠቀምና የተደራጀ ሕይወት የሚመራ ሰው መሆን ይሻለኛል” . . .

“የዘመነና ለማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ምቹ የሆነ ስልክ ይዤ፣ የተበላሸ ማሕበራዊ ግንኙነት ከሚኖረኝ፣ የተለመደ ስልክ ይዤ ከሕብረተሰቡ ጋር አብሮ ለመኖር የሚያስችለኝን የባህሪይ ልዕልና ማዳበር ይሻለኛል” . . .

የቀረውን ጨምሩበት!

መልካም የአዲስ አመት ዋዜማ!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
219👍55🔥12🎉8🤩5
መልካም አዲስ አመት!

ለመላው የቻናሌ ተከታታዮች እንዲሁም ለውድ ቤተሰባችሁና ወዳጆቻቻችሁ!

እንኳን ለ2018 ዓ/ም በሰላም አደረሳችሁ!

 ባለፈው አመት ስኬት ላይ የመገንባት ተስፋን ይዘን እንሻገር!

 ካለፈውን አመት ስህተት በመማር አዲስ ጎዳና ይዘን እንሻገር!

 ያለፈውን አመት አስቸጋሪ ሁኔታ እንድናልፍ ያገዙንን ሰዎች በማስታወስ እንሻገር!

 ከሁም በላይ ለዚህ ያደረሰንን ፈጣሪ በማመስገን እንሻገር!

Dr. Eyob Mamo

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
193👍60🎉6🔥2😢2😱1
ጤናማ እምቢታ!
👍2215
ጤናማ እምቢታ!

አንዱ ምርጫህ ሰዎችና ሁኔታዎች “እንዲህ ነህ” ብለው የሰጡህን ስምና ማንነት ተቀብለህ አቀርቅሮ መኖር ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን ያልሆንከውን ማንነትና የማይመጥንህ ስምና ሕይወት ላለመቀበል የሚያስፈልገውን መስዋእትነት መክፈል ነው፡፡ በሕይወትህ እሺ የምትላቸው መልካም ሰዎችና መልካም ነገሮች እንዳሉህ ሁሉ እምቢ ልትላቸው የሚገባህ ሰዎችና ጤና-ቢስ ሁኔታዎች ሊኖሩ የግድ ነው!

ሄንሪ (Henry Brown) በሰዎችም ሆነ በታሪክ የሚታወቀው “ቦክስ” ከሚል ቅጽል ስም ጋር ነው (Henry “Box” Brown)፡፡ በሰሜን አሜሪካ በቪርጂንያ ግዛት ውስጥ በ1815 ዓ/ም በባርነት ነው የተወለደው፡፡ በ15 ዓመቱ በትንባሆ እርሻ የጉልበት ስራ እንዲሰራ፡፡ እድሜው ደርሶ የሚወዳትን ሴት ቢያገባም፣ የባርነት ዘመን አሰራር ናንሲ (Nancy) ከምትባለዋ የትዳሩ ጓደኛው ለይቶት ነበር፡፡ ናንሲ ባሪያዎችን በመሸጥና በመግዛት ስራ የተሰማራ የአንድ ጌታ ንብረት ሆና በአቅራቢያው በሚገኝ እርሻ ጉልበት ስራ ትሰራለች፡፡ አራተኛ ልጇን ለመውለድ ደርሳ ነበር፡፡

አንድ ቀን ሄንሪ አንድ አሳዛኝ ዜና ደረሰው፡፡ ዓመተ ምህረቱ 1848 ነው፡፡ ናንሲና ልጆቿ ወደ ሌላ ግዛት በሽያጭ ሊጋዙ ነው፡፡ በመንገድ ላይ ቆሞ እንባ ከአይኖቹ እየፈሰሱ 350 ሃምሳ የሚሆኑ ባሪዎች በሰንሰለት ታስረው ሲወሰዱ ተመለከተ፡፡ በዚያ መካከል ነፍሰ-ጡር የሆነችው ሚስቱና ልጆቹ ይገኙበታል፡፡ ሁኔታውን ለመለወጥ ምንም አቅም አልነበረውም፡፡

በተከሰተው ሁኔታ እጅግ ያዘነው ሄንሪ ከባርነት ለማምለጥ ቁርጥ ውሳኔ አደረገ፡፡ ፊላደልፊያ በተሰኘች ከተማ ውስጥ የጥቁር ባርነትን ስርዓት የሚቃወም አንድ ነጭ እንደነበረ ስለሰማ ወደ እርሱ ለመድረስ ወሰነ፡፡ ከአንድ ጄምስ (James) ከሚባል በጊዜው ከባርነት ነጻ ከሆነ ወዳጁ ጋር በመማከር ራሱን በሳጥን ውስጥ ከደበቀ በኋላ ይህ ጓደኛው አድራሻ በሳጥኑ ላይ በመጻፍና ወደ ፖስታ ቤት በመውሰድ በፖስታ እንዲልከው ተማከረ፡፡

ሄንሪ የተደበቀበትን ሳጥን ወደ ነጻ አውጪው ሳሙኤል (Samuel Alexander Smith) ወደተሰኘው ነጭ እንዲልከው ከጓደኛው ከጄምስ ጋር ተማክሯል፡፡ እቅዱ ጥሩ የፈጠራ ብቃትን የሚያሳይ ቢሆንም፣ እጅግ አደገኛ ውሳኔ ነበር፡፡ በእቅዳቸውም መሰረት ማርች 23፣ 1849 ዓ/ም ሄንሪ ራሱን የደበቀበትን ሳጥን ጓደኛው ጄምስ በፖስታ ቤት ላከው፡፡

ሄንሪ አየር እንዲያገኝ ያህል ሳጥኑ ላይ ትንሽ ቀዳዳ ፈጥረዋል፡፡ ከውኃና ከጥቂት ብስኩት በስተቀር የያዘው ነገር የለም፡፡ ጉዞው በጋሪ፣ በባቡርና በጀልባ ነበር፡፡ በመጨረሻም በፊላደልፊያ (Philadelphia) በሚገኘው የጸረ-ባርነት ማሕበር አድራሻ ሳጥኑ ደረሰ፡፡ በዚህ 27 ሰዓታት በፈጀ ጉዞ ሄንሪ የተደበቀበት ሳጥን በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፏል፡፡

ያለፈበትን ሁኔታ ሄንሪ ሲገልጽ፣ “አይኖቼ አብጠው ሊፈነዱ ጥቂት ቀርቷቸው ነበር፡፡ በጭንቅላቴ ላይ ከነበረው ውጥረት የተነሳ የደም ስሮቼ ተወጥረው ነበር፡፡” በአንድ ወቅት ሳጥኑ ተዘቅዝቆ በነበረበት ጊዜ ሄንሪ ከነበረበት ሁኔታ የተነሳ የሚሞትም መስሎት ነበር፡፡ ሁለት ሰዎች የሚቀመጡበት ስፍራ ሲፈልጉ በሳጥኑ ላይ ለመቀመጥ ሲሉ ገለበጡትና ለሄንሪ ጥሩ ገጠመኝ ሆነለት፡፡

በመጨረሻም ሄንሪ ተደብቆበት የነበረው ሳጥን ዊልያም፣ ጃምስ፣ ፕሮፌሰር ሲዲ እና ልዊስ ወደተሰኙ ሰዎች እጅ ገባ፡፡ ሳጥኑም ሲከፈት ሄንሪ፣ “እንደምን አላችሁ፣ ክቡራን?” በማለት ከሳጥኑ ውስጥ ብቅ አለ፡፡ በዚህም ውሳኔው በፍጹም ሊቀበለው ከማይችለው የባርነት ሕይወት ወደ ነጻነት ተሸጋገረ፡፡

አንድ ሰው መሆንና ማድረግ ከሚፈልገው መልካም ነገር የሚገታውን ነገር ለማሸነፍ እስካልተነሳ ድረስ ሙሉ ሰው መሆን ያስቸግረዋል፡፡ እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ደግሞ ከራሱ አልፎ ለትውልድ የሚተርፍ መዘዝ አለው፡፡ ሰው ጤና ቢስ ለሆነው ነገር “እምቢ” ማለት ሲጀምር ለብዙዎች ከእርሱ በኋላ ለሚመጡ ሰዎችም ሳይቀር የነጻነትን ፈር ይቀዳል፡፡

የሰው ዘር ከፈጣሪው ከተቀበላቸው ስጦታዎች አንዱ የምርጫ ስጦታ ነው፡፡ ለማንነቱ የማይመጥነውን ነገር ለይቶ በማወቅ በምርጫ ሲኖር ያንን ነጻነቱን መለማመድ ይጀምራል፡፡ ሆኖም፣ “እምቢ” ማለት የሚገባንን ማወቅ ቀላል፣ ያንን ማድረግ ግን ከባድ ነው፡፡

መመለስ ያለባቸው ጥያቄዎች . . .

• ከማንነቴ በታች ለመኖር ራሴን የሰጠሁበት ሁኔታና ልማድ ምንድን ነው?

• ከማንነቴ በታች እንድኖር እያስገደደኝ ያለ ሰው ማን ነው?

• ከማንነቴ በታች እንድኖር የሚጎትተኝ ያለፈ ታሪኬ ምንድ ነው?

• ከማንነቴ በታች እንድኖር የሚጎትተኝ ፍርሃት ምንድ ነው?

• አንድን ነገር ከፍላጎቴ ውጪ እንዳደርግ እያስገደደኝ ያለ ሰው ማን ነው?

መልካም ቀን!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
152👍20🤩5😁2🎉1
አዲስ መጽሐፍ! በቅርብ ቀን ይጠብቁ!

“የመኖር አቅም”
ከመትረፍ ወደ መትረፍረፍ

"Power for Living"
From Surviving to Thriving

ይህ መጽሐፍ 30 ምእራፎችን ያቀፈ ሲሆን፣ በቀን አንድ ምእራፍ በማንበብ በ30 ቀናት ውስጥ አቅማችሁን የማስመለስ ጎዳና እንድትጀምሩ አቅጣጫ የሚያሳያችሁ መጽሐፍ ነው፡፡

Dr. Eyob
👍278131🔥11🤩7🎉4😱3
የዝለት (Burnout) ምልክቶች
16👍5
የዝለት (Burnout) ምልክቶች

ያለፈው ዓመት ከነበራችሁ የስራ፣ የንግድ፣ የፍቅር ግንኙትና መሰል ማሕበራዊ ሂደቶች የተነሳ አድካሚ ጊዜ ከነበራችሁና ነገሩ ወደ ዝለት ደረጃ ደርሶ ከሆነ፣ በያዝነው ዓመት ሁኔታውን እንድታስካክሉ ትመከራላችሁ፡፡

አንድ ሰው በዝለት ስሜት ተጽእኖ ውስጥ በሚወድቅበት ጊዜ የተለያዩ ምልክቶችን ማየት ይጀምራል፡፡ እነዚህ ምልክቶች በቀናት ውስጥ የሚከሰቱ አይደሉም፡፡ ቀስ በቀስና ሰውየው ሳያውቀው ስር የሚሰዱና በመጨረሻ ወደ ፊት መቀጠል ሲያቅተው የሚታወቁ ስሜቶች ናቸው፡፡

የመዛል ምልክቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡-

• ቀድሞ እንጓጓበት በነበረ ነገር አለመጓጓት፡፡

• አቅም የማጣት ስሜት፡፡

• ተስፋ ቢስ ስሜት፡፡

• የባዶነት ስሜት፡፡

• ከሰዎች የመለየት ስሜት፡፡

• የድብርት ስሜት፡፡

• የአሉታዊ (ጨለምተኛ) ስሜት፡፡

• የጭንቀት ስሜት፡፡

• የመነጫነጭና የቁጣ ስሜት፡፡

• እንቅልፍ ማጣት፡፡

ባለፈው ዓመት ከእነዚህ ምልክቶች የተወሰኑትን ተለማምዳችሁ ከነበረ ሁኔታው የዝለት (Burnout) ምልክት ስለሚሆን አስፈላጊውን ለውጥ አደርጉ፡፡

አንድ ሰው በተቻለው መጠን ለዝለት ከሚያጋልጡ ሁኔታዎች ቅድመ-ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ሆኖም፣ አንዴ ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ግን ራስን ለማረጋጋትና ከከፋ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚከተሉትን እርምጃዎች እንዲወስድ ይመከራል፡፡

1. ጸሎትን ልማድ ማድረግ፡፡

2. በቂ የእረፍትና የመዝናኛ ጊዜ መውሰድ፡፡

3. በቂ እንቅልፍ ማግኘት፡፡

4. ትክክለኛ አመጋገብን መከተል፡፡

5. በቂ የአካል እንቅስቃሴ (ስፖርት) ማድረግ፡፡

6. ጊዜንና ሰዓትን በአግባቡና በልኩ መጠቀም መልመድ፡፡

7. ከቅርብ ቤተሰብና ወዳጆች ጋር በቂ ጊዜን ማሳለፍ፡፡

8. መቆጣጠርና መለወጥ የማይችለውን ነገር በመልቀቅ፣ መለወጥ በሚችለው ላይ ብቻ ማተኮር፡፡

መልካም አዲስ ጅማሬ!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
260👍85🎉5🔥4
ሃላፊነት መውሰድ!
17👍7
ሃላፊነት መውሰድ!

ማንም ሰው ... ቤተሰባችን፣ ዘመዶቻችን፣ ጓደኞቻችን ሆኑ ሌሎች የሕብረተሰቡ ክፍሎች ለእኛ እዳ እንደሌለባቸው በማሰብና የእኛን ሕይወት አስመልክቶ ሁሉም ነገር የእኛ ሃላፊነት እንደሆነ አምኖ በመቀበል መኖር አስገራናሚ ልምምድ ውስጥ ይከተናል፡፡

ሰዎች ለእኛ እዳ እንዳለባቸው ማሰብ ማለት፣ የሚያስፈልገንንና ሊሟላልን ይገባል የምንለውን ነገር ሰዎች ሊሰጡን ይገባል ብሎ ማሰብና መጠባበቅ ማለት ነው፡፡

ማንም ሰው እኛን ማክበር፣ ማፍቀር፣ ገንዘብ መስጠት፣ በተገቢው መንገድ ማስተናገድና የመሳሰሉትን ነገሮች የማድረግ እዳ የለበትም፡፡

ሰዎች እነዚህና የመሳሰሉት ነገሮች አስመልክቶ ልክ እዳ እንዳለባቸው ማሰብ ስንጀምር ለተለያዩ ቀውሶች ራሳችንን እናጋልጣለን፡፡

1. የመገፋትና ያለመወደድ ስሜት ያጠቃናል፣

2. ሰዎች ጨካኞች እንደሆኑ በማሰብ መራራነትን እንዳብራለን፣

3. ቁጭ ብለን ሰዎችን ስንጠብቅ ጊዜያችንን እናባክናለን፡፡

ከእነሱ እናገኘዋለን ብለን የምንጠብቀውን ነገር ሰዎች የማያሟሉበት የተለያዩ ምክንቶች አሉ፡፡

1. አንዳንድ ሰዎች እንኳን ለእኛ ሊተርፉ የራሳቸው የሆነ የማያልቅ ጣጣ አለባቸው፡፡

2. አንዳንድ ሰዎች ራስ ወዳድ ስለሆኑ ለሰው ግድም አይሰጣቸው፡፡

3. አንዳንድ ሰዎች ፍላጎቱም አቅምም እያላቸው ችግራችንን ግን ስለማያዩት ችላ ይሉናል፡

ከመብተኝነትና ሰዎች በእኛ ላይ እዳ እንዳለባቸው ከማሰብ መጠበቅ ብዙ ጠቀሜታ አለው፡

1. በፊቱኑ ያልጠበቅነውን መልካም ነገር ካደረጉልን እንደ እድል ስለምንቆጥረው አመስጋኝ እንሆናለን፣

2. በሁኔታዎች ላይ አዎንታዊ አመለካከት ይኖረናል፡፡

3. ሰውን ከመውቀስ እንድናለን፣

4. ከመብተኝነት ስሜት ነጻ በመውጣት ጠንካራ ሰራተኞች እንሆናለን፡፡

5. ራሳችንን ለማሻሻል እቅድ ማውጣት እንጀምራለን፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
179👍57🤩6🔥4🎉3
ያለፈው ስኬተ-ቢስነት ጉዳይ!

ባለፈው ዓመት ደጋግማችሁ ሞክራችሁ ያቃታችሁና ያልተሳካ ነገር ካለ ሙከራውን ያለማቆማችሁ ትጋት እንደተጠበቀ ሆኖ በያዝነው ዓመት እንደገና ከመሞከራችሁ በፊት በሁኔታው ላይ በሚገባ አስቡበት፡፡

ያልተሳካን ነገር የምንቀርብበት መንገድ ሁለት ነው፡- 1) ዝም ብሎ እየደጋገሙ መሞከር፤ ወይም 2) የምንከተለውን መንገድ ማጤን፡፡

አንድ ያልተሳካ ነገር ዝም ብሎ መደጋገም የጽንአትን ሁኔታ ቢያመለክትም፣ ተሸንፎ ላለመታየት የመፈለግንም ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ሊጠቁም ስለሚልች ሙሉ ለሙሉ አስተማማኝ መንገድ አይደለም፡፡ ከዚያ የተሸለው አስተማማኝ መንገድ ግን ተረጋግቶ ራስንና ሁኔታዎችን መመርመር ነው፡፡

ራስንና ሁኔታውን ለመመርመር፡-

1. የሁኔታው ትክክለኛነት

እየሞከር ያለሁት ነገር ትክክለኛና ከእኔ ፍላጎት ጋር የሚሄድ ነገር መሆኑን ማረጋገጥ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ አንዳድ ጊዜ የምንሞክራቸው ነገሮች ከሰው ግፊት ለማምለጥ ወይም ከወቅቱ ሁኔታችን ለመውጣት ብቻ ይሆንና ግለቱን እናጣዋለን፡፡

2. የምከተለው መንገድ ትክክለኛነት

እየሞከር ያለሁትን ነገር እየሞከርኩ ያለሁት በትክክለኛው መንገድ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ምንም እንኳን አንድ ቦታ ለመድረስ ብርቱ ፍላጎት ቢኖረኝም ትክክለኛውን አቅጣጫና ጎዳና ካልተከተልኩኝ ውጤቱ ድካም ብቻ ነው፡፡

3. የጊዜው ትክክለኛነት

እየሞከርኩ ያለሁትን ነገር እየሞከርኩ ያለሁት በትክክለኛው ጊዜ መሆኑን ማረጋገጥ ጠቃሚ ነው፡፡ ወቅቱ ያልደረሰ አትክልት ምንም ያህል ብንኮተኩተውና በየቀኑ ብንጠባበቀው ፍሬን እንደማይሰጠን ሁሉ ጊዜው ያልደረሰ ወይም ጊዜው ያለፈበት ነገር እንዲሁ ነው፡፡

Like & Share, Please!

https://www.tgoop.com/Dreyob
👍9687
ሶስቱ የሚያሙ እውነታዎች!

1. ለረጅም ጊዜ ትክክልና እውነት እንደሆነ ያመንነውና የተከተልነው አመለካከት ስህተት እንደሆነ ወደማወቅ መምጣት … ያማል!፡፡

2. ለረጅም ጊዜ እንደሚወደንና እንደሚቀበለን አምነን የነበረው ሰው እንደማይወደንና እንደማይቀበለን ወደማወቅ መምጣት … ያማል!፡፡

3. ለረጅም ጊዜ ገንዘባችንን፣ ጊዜያችንንና ስሜታችንን በማስተባበር የሰራንለት ነገር እንደማያዋጣና እንደማያዛልቅ ወደማወቅ መምጣ … ያማል!፡፡

እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ሁለንተናችንን እንዳባከኑብን፣ ከሁኔታዎቹና ከሰዎቹ አንጻር የዘረጋነው የወደፊት እቅድ ገደል እንደገባ እና ሕይወታችን ባዶ እንደሆነ ሊሰማን ይችላል፡፡

ማድረግ የምንችለው . . .

1. መረጋጋትና ስሜትን ረገብ ማድረግ፡፡

2. እውነታውን ለመቀበል ራስን ማዘጋጀትና በክህደት አለም ውስጥ አለቆየት፡፡

3. ለሁኔታው ምን አይነት ምላሽ መስጠት እንዳለብንና የወደፊታችንን እንዴት ማቀድ እንዳብን በሚገባ ማሰብና የሰዎችን እገዛ መቀበል፡፡

አይዟችሁ! ሁሉም ነገር ያልፋል! ሁሉም ነገር የታለፋል!

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
176👍34😢19🔥6🎉1
ሕይወት ብዙ መንገዶች አሏት!

የ12ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ፣ ጥሩ ውጤት ለማምጣት የቻልኩትን ያህል አጥንቼና ታግዬ ነበር፡፡ ሆኖም ውጤቴ በጣም ዝቅተኛ ከሚባሉት ውስጥ ነበር፡፡

የነበረብኝ ችግር . . .

• ቤተሰቦቼ ከእኔ የሚጠብቁትን ውጤት ባለማግኘቴ አዝኜ ነበር

• ውጤት የመጣላቸው ተማሪዎች አልፈውኝ እንደሄዱ ተሰምቶኝ ነበር

• ሰነፍ እንደሆንኩኝ ማሰብ ጀምሬ ነበር

• ወደ ፊት ምንም ተስፋ እንደሌለኝ በማሰብ ጨልሞብኝ ነበር

ይህም ሆኖ ግን፣ ከብዙ የሃሳብ ውጣ ውረድ በኋላ፣ ፈተና ወደኩኝ እንጂ እኔ እንዳልወደኩኝ ወደመገንዘብ መጣሁ፡፡

መማርና ጥሩ ውጤት በማምጣት አልፎ መቀጠል ወሳኝነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የጠበቅነው ውጤት አልመጣም ማለት ግን የወደፊታችን ተስፋ የለውም ማለት አይደለም፡፡

ፈተና ወደቃችሁ ማለት እናንተ ውዳቂ ናቸሁ ማለት አይደለም፡፡ ሕይወት ብዙ መንገድና አቅጣጫ አላት፡፡

ፈተና ከመውደቅ ባሻገር አልፋችሁ ለመሄድ የሚከተሉትን እውታዎች አስታውሱ፡-

1. ራሳችሁን በፍጹም ከሌላ ሰው ጋር አታወዳድሩ

2. የሕይወታችሁን ዋና ዓላማ ያዙና እሱን ተከተሉ

3. ሰው ስለሚያስበውና ስለሚናገረው ነገር በፍጹም አትጨነቁ

በአለም ዙሪያ ፈተና ካለፉትም ሆነ ከወደቁት ውስጥ ስኬታማም የሚሆኑ ስኬተ-ቢስም የሚሆኑ ሰዎች ሞልተዋል፡፡ ዋናው ነገር ለሁኔታው የሰጣችሁት ምላሽ ነውና በርቱ!

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ ነኝ
224👍56🎉7🔥6😢3😱2
ይህ ሕይወት የሚባለው ነገር
17👍3
ይህ ሕይወት የሚባለው ነገር

Dr. Cherie Carter-Scott “አስሩ ሰው የመሆን ሕጎች” በሚል ሃሳብ ስር ካቀረበቻቸው ነጥቦች መካከል የመጀመሪያዎቹ አምስቱ የሕይወት ትምህርትን ከማግኘት አንጻር እጅግ ጠቃሚና ተግባራዊ ሆነው ስላገኘኋቸው ላጋራችሁ (ምንጭ፡-authentic-self.com)፡፡

1ኛ ሕግ - አካልን ትቀበላለህ!

ይህንን አካልህን ልትወደው ወይመ ልትጠላው ትችላለህ፣ ነገር ግን በዚህ ምድር ላይ እስካለህበት እድሜ ድረስ የአንተው አካል ነው፡፡ ከፈጣሪ የተቀበልከውን አካል ተቀበለው!

2ኛ ሕግ - በየጊዜው ትምህርት ይሰጥሃል!

“ሕይወት” በተሰኘ ከመደበኛ ውጪ የሆነ ትምህርት ቤት ውስጥ ተመዝግበሃል፡፡ በዚህ ትምህርት ቤት ውስጥ በየቀኑ ትምህርትን የማግኘት እድል አለህ፡፡ እነዚህን ትምህርቶች ልትወዳቸውም ላትወዳቸውም ትችላለህ፡፡ በሚገባ ከተጠቀምክባቸው ግን ወደሚቀጥለው ደረጃ ታልፋለህ፡፡ የምታልፍቸውን አስተማሪ ሁኔታዎች ተጠቀምባቸው፡፡

3ኛ ሕግ - ስህተት የሚባል ነገር የለም፣ ያለው ትምህርት የሚባል ነገር ነው፡፡

እድገት ማለት የፍተሻ ፣ የተከታታይ ሙከራ፣ የስህተቶችና የአንዳንዴም የድሎች ሂደት ነው፡፡ ያልተሳኩት ሙከራዎችህ ልክ የተሳኩት ሙከራዎችን ያህል የሂደቱ አካል ናቸው፡፡ በምታልፍባቸው ሁኔታዎች ተስፋ አትቁረጥ፡፡

4ኛ ሕግ - አንድ ትምህርት እስኪገባህ ድረስ ይደጋገማል!

ትምህርቱ እስኪገባህ ድረስ በተለያየ መልኩ ይደጋገምልሃል፡፡ ትምህርትህን ካገኘህ በኋላ ወደሚቀጥለው ትምህርት ትሸጋገራለህ፡፡ ተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ራስህን ካገኘኸው ትምህርትህን አላገኘህም ማለት ነው፡፡ ከስህተትህ በመማር ስህተትህን ሳትደጋግም ወደፊት አልፈህ ሂድ፡፡

5ኛ ሕግ - ትምህርት ማለቂያ የለውም!

ትምህርትን ያላቀፈ የሕይወት ዘርፍ የለም፡፡ በሕይወት እስካለህ ድረስ የምትማራቸው ትምህርቶች አሉ፡፡ ሁልጊዜ ልቦናህን ለትምህርት ክፍት አድርግ፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1\050816404958639/
143👍43🔥12😱1
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship, Coaching and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?


(በውጪ ሃገር ያላችሁም በTelegram and WhatsApp ከዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ፡፡)

1. ያጋጠማችሁ ወቅታዊ አስቸጋሪ ሁኔታ ካለና በራሳችሁ ለመወጣት ስላቃታችሁ እገዛ ከፈለጋችሁ፣

2. የሕይወታችሁን ራእይ ወይም ዓላማ ባለማወቅ ከተወዛገባችሁና አቅጣጫን መያዝ ከፈለጋችሁ፣

3. ካለባችሁ አጉል ልማድ በመውጣት አዲስ ልማድን ማዳበር ካስቸገራችሁና ምክርና ድጋፍ ከፈለጋችሁ፣

4. መመለስ ያቃታችሁ የሕይወት ጥያቄዎች ከበዙባችሁና በአንድ ለአንድ ውይይት የመፍትሄ መንገድ ከፈለጋችሁ፣

5. በራሳችሁ መወጣት ያልቻላችሁት የተያዩ የስሜትና የስነ-ልቦና ጥያቄዎች ውስጥ እንዳላችሁ ከተሰማችሁና ከሁኔታው ለመውጣት ምክር ከፈለጋችሁ፣

ከግል በተጨማሪም ቁጥራችሁ ከአስር ባልበለጠ ሁኔታ በመሰባሰብ የGroup Coaching and Training ጥያቄም ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡

በቴሌግራም

@DrEyobmamo

inbox በማድረግና በፌስቡክ መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን ማሳወቅ ትችላላቸሁ፡፡
65👍18😁2😢2🤩2
ችግሮቻችን!

በሕይወት እስካለን ድረስ የተለያዩ ችግሮች እንጋፈጣለን፡፡ ከእነዚህ ችግሮች የአንዳንዶቹ መነሻ “ውጫዊ” ሲሆን፣ የሌሎቹ መነሻ ደግሞ “ውስጣዊ” ነው፡፡

“ውጫዊ” መነሻ ማለት የኑሮ ችግር ሲያጋጥመን፣ ሁኔታዎች በጠበቅናቸው መልኩ አልሄድ ሲሉን፣ ያልጠበቅናቸው ነገሮች ሲከሰቱና የመሳሰሉትን የሚያጠቃልል ሃሳብ ነው፡፡

“ውስጣዊ” መነሻ ማለት በውስጣችን ካለን አመለካከትና የስነ-ልቦናም ሆነ የስሜት ቀውስ የሚነሳ ችግርን አለመልካች ነው፡፡

እነዚህ የችግር መነሻዎች ይወራረሳሉ፡፡ ይህ ማለት፣ የውጪ ችግር ሲኖርብንና በሚገባ ካልያዝነው የውስጥ ችግር ማስነሳቱ አይቀርም፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የውስጥ ችግር ካለብንና ተገቢውን ትኩረት ካልሰጠነው ነገሮችን አያያዝ ላይ ቀውስ ስለሚፈጥር ውጫዊ ችግር ማስከተሉ አይቀርም፡፡

ችግር መጋፈጥ ሰው ሁሉ የሚለማመደው ሁኔታ ነው፡፡ ችግር ግን በሚገባ ካልተያዘ ወደ ቀውስ ያልፋል፡፡
ችግር ወደ ቀውስ ደረጃ ሲደርስ፣ ግራ መጋባት፣ ድብርት፣ በአንድ ነገር ላይ ማተኮር አለመቻል፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ጉጉትን ማጣት፣ “ምን ሆኜ ነው?” የሚል ስሜትና የመሳሰሉትን ምልክቶች ልናይ ችንችላለን፡፡

ችግሮቻችን ወደ ቀውስ ደረጃ የሚደርሱት

1. ችግሮች በራሳቸው ይሄዳሉ ብለን ችላ ስላቸው . . .

2. እርዳታን ለመጠየቅ ማፈር ወይም አለመፈለግ . . .

3. የሰውን ድጋፍ በሚጠይቁና በማይጠይቁ ሁኔታዎች መለየት አለመቻል እና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ችግራችሁ ወደ ቀውስ ደረጃ ሳያልፍ የምክር አገልግሎትን አግኙ፡፡

ለምክር አገልግሎት ዶ/ር ኢዮብም ለማግኘት
በዚህ 👉🏽 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ inbox በማድረግ ወይም በፌስቡክ መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን ማሳወቅ ትችላላቸሁ፡፡
107👍36
አስተሳሰብን የመቆጣጠር ወሳኝነት!
31👍3🤩3
አስተሳሰብን የመቆጣጠር ወሳኝነት!

“አስተሳሰብን መቆጣጠር” ማለት ወደ እኛ የሚመጣውን ወይም በውስጣችን የሚፈጠረውን ሃሳብ በማጣራት ማስተናገድ ማለት ነው፡፡

አስተሳሰባችንን ሳንለውጥ ሕይወታችንንም ሆነ ሁኔታችንን መለወጥ አንችልም፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የሁሉ ነገር መጀመሪያ አስተሳሰብ ስለሆነና አስተሳሰባችን የማንነታችን “ማምረቻ” በመሆኑ ነው፡፡

በመጀመሪያ አንድ ሃሳብ ወደ አእምሮአችን ይገባል፡፡ በመቀጠልም ይህ ሃሳብ በውስጣችን ይብላላና በንግግርና በተግባር መገለጥ ይጀምራል፡፡ ይህ ተግባር ወደ ልማድ ከተለወጠ በኋላ ፍጻሜአችንን የመለወጥና የመቅረጽ ጉልበት ይኖረዋል፡፡ ይህ ሃሳብ ጤናማም ሆነ ጤና ቢስ ሂደቱ ያው አንድ ነው፡፡

አስተሳሰባችንን ለመቆጣጠር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ አሰቸጋሪ ዘመን ላይ ነው ያለነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት በማሕበራዊ ሚዲያ አማካኝነት እኛው ድረስ እንዲመጡ የምንፈቅድላቸው መረጃዎች ስለሚሞሉን፡፡

አእምሯችን ማንሸራሸርና ማጣራት ከሚችለው በላይ መረጃን ስለምንቀበል፣ አእምሯችን እንደሰራ ውሎ፣ ማታም እንቅልፍ መውሰድ እስኪያቅተን ድረስ እንደሰራ ያመሻል፡፡ አንዳድ ጊዜ አንቀላፍተንም አያርፍም፡፡

ይህንን ሁኔታ ለመቆጣጠር፡-

1. የምናያቸውንና የምንሰማቸውን ሃሳቦች ማጣራት

ለማንነታችንና ለአላማችን የሚመጥኑ ሃሳቦች ምን እንደሆኑ ለይተን ማወቅ አለብን፡፡ ይህንን ለይተን ስናውቅ፣ በቀረቡልን ነገሮች መካከል መለየትንና የትኛውን ማስተናገድ እንዳለብን ጥርት ባለ መልኩ እንድናውቅ ይረዳናል፡፡

2. ጤና ቢስ አስተሳሰቦችን አለማስተናገድ

የመጣ ሃሳብ ሁሉ በአእምሯችን ስፍራ ማግኘት የለበትም፡፡ ለጤናማ አመለካከታችንና ላስቀመጥነው የሕይወት ከፍታና ደረጃ የማይመጥነውን ተራ ሃሳብ በመጣበት ፍጥነት እንዲወጣ የማድረግ ግዴታ አለብን፡፡

3. ጤና ቢሱን አስተሳሰብ በጤናማው መቀየር

ከዚህ በፊት በውስጣችን ያስተናገድናቸውን ጤና ቢስ ሃሳቦች መልካምና ስኬታማ በሆኑ ጤናማ ሃሳቦች መለወጥ መጀመር የግድ ነው፡፡ ከአእምሯችን ክፉውን ሃሳብ አስወጥተን በጤናማው ካልተካነው ሌላ ተጨማሪ ክፉ ሃሳብ መሙላቱ አይቀርም፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1\050816404958639/
153👍34🔥7
የዲሲፕሊን ስኬታማነት
25👍3
የዲሲፕሊን ስኬታማነት

ዲሲፕሊን ሁለት ገጽታ አለው፡-

1. አንድን ማድረግ ያለብኝን ነገር ስሜቴ ቢፈቅድም ባይፈቅድም መደረግ ስላለበት ብቻ ማድረግ፣

2. አንድን መደረግ የሌለበትን ነገር ምንም ያህል ብፈልገውም አለማድረግ፡፡

እነዚህን ሁለት የዲሲፕሊን ገጽታዎች መለማመድም ሆነ አለመለማመድ የሚከተሉትን ሁለት ውጤቶች ያስከትላል፡-

1. ዲሲፕሊን ከማዳበራችን የተነሳ መልካም ልምምዶችን ስንለማመድ ያልተጠበቀ አስገራሚ ውጤቶችን እናገኛለን፡፡

2. ዲሲፕሊን ከመጉደሉ የተነሳ ጤና-ቢስ ነገሮችን ስንለማመድ ደግሞ ያለተጠበቁ አጉል ውጤቶችን እናጭዳለን፡፡

ማንኛውም ችሎታና ብቃት ከዲሲፕሊን ውጪ ከንቱ ነው፡፡ ምክንያቱም ዲሲፕሊን ከሌለኝ ምንም እንኳ የማድረጉ ብቃት ቢኖረኝና በነገሩ ባምንበትም ያንን ነገር ማድረግ ያስቸግረኛል፡፡ በሌላ አባባል ዲሲፕሊን ከሌለኝ መልካም ልማድን ለማዳበር ፈጽሞ አልችልም፡፡ ሕይወቴን በዲሲፕሊን ካልመራሁ የምተገብረውን ነገር የሚወስንልኝ ያመንኩበት መርህ ሳይሆን የእለቱ “ሙድ” ይሆናል፡፡ ይህ እንዳይሆን ራሳችንን ለመምራት ጤናማ የሆነን ዲሲፕሊን ማዳበር የግድ ነው፡፡

ዲሲፕሊንን ለመለማመድ መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-

1. ለማግኘት የምንፈልገውን ውጤት ማወቅ

ማከናወን የምንፈልገውንና ጊዜያችንን ልንሰዋለት የሚገባንን ተግባር በግልጽ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ቀዳሚና እጅግ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ ማንነታችን የሚፈልገውን በሚገባ ሳናውቅ ማንነታችንንን ለመምራት መሞከር ጊዜን ማባከን ነው፡፡

2. ለፈለግነው ውጤት የሚመጥነውን ዲሲፕሊን ለይተን ማወቅ

እያንዳንዱ ለማዳበር የምንፈልገው ነገር የራሱ የሆነ ባህሪይ አለው፡፡ ለዚያ ለማዳበር ለምንፈልገው ነገር ምን አይነት ዲሲፕሊንና ልማድ ብናዳብር ስኬታማ እንደምንሆን ማወቁ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡

3. እንጀምር፣ ከጀመርን ደግሞ አናቁም

ለማዳበር የምንፈልገውን ነገር ለነገ ሳናስተላልፍ መተግበር እንጀምር፡፡ ሆኖም መጀመር ብቻ በቂ እንዳልሆነም እናስታውስ፡፡ የጀመርነውን ነገር ለማቆም ምንም አይነት ምክንያት አንስጥ፡፡ ውጤት እስከምናገኝ ድረስ እንቀጥል፣ ስናቆመውም እንደገና እንጀምር፡፡

https://www.tgoop.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1\050816404958639/
121👍21🔥13
2025/10/12 18:05:32
Back to Top
HTML Embed Code: