tgoop.com/Duzzl/2592
Create:
Last Update:
Last Update:
የ አሪፎች በጥበብ የተዋበ አካሔድ!
ሰይዲና ዑመር (ረዲ አሏሁ ኣንሁ) ባንድ ወቅት ከመንገድ ሲያልፉ…እሳት አንድደው ተሰብስበው የተቀመጡ ሰዎችን ተመለከቱ።
«እናንተ የመብራት ሰዎች ሆይ!» በማለት ተጣሩ። ሰይዲና ዑመር…«እናንተ የእሳት ሰዎች ሆይ!»ከማለት የታቀቡት ሰዎቹ ቃሉን ሲሰሙ ቀልባቸው እንዳይጎዳ በመስጋት ነበር።
ሰይዲና ሐሰንና ሑሰይን (ረዲ አሏሁ አንሁም) አንድን ሶሓባ በስህተት ውዱእ ሲያደርግ ተመለከቱ።እና ወደርሱ ተጠጉና እንዲህ ኣሉት።«ከሁለታችን ውዱእ አሳምሮ ማድረግ ማይችለው ማን እንደሆነ በመካከላችን እንድትፈርድ እንፈልጋለን»።ከዚያም ከፊት ለፊቱ ሆነው ውዱእ ማድረግ ጀመሩ።በዚህን ጊዜ ሶሓባው ፈገግ አለ።ሊያስተላልፉት የፈለጉትን መልዕክት ተረዳ።
«በስርዓቱ ማድረግ የማልችለው እኔው ነኝ»በማለት መልሶ ከነሱ በተማረው መልኩ ውዱዑ ማድረጉን ጀመረ።
ታላቁ ሊቀ ሊቃውንት ሰይዲ ኢማም አቡ ሓሚድ አል غዛሊ(ረዐ) ተጠየቁ።
«ያ ኢማም ሶላትን ለዘነጋ ሰው ቅጣቱ ምንድር ነው?»…… ኢማሙም መለሱ፦«ከ እኛው ጋር ወደ መስጂድ ይዘነው መሔድ ነው!»
ወደ channelu ገባ በሉ
https://www.tgoop.com/joinchat-U4q9OHoSPqgy3teR
BY ባህረል ሙገ(غ)የባ (የሳዳቶች ስርፋ)
Share with your friend now:
tgoop.com/Duzzl/2592