tgoop.com/Duzzl/2605
Last Update:
መዉሊድ ለሀገራችን፣ ለእስልምና መስፋፋትና ለሙስሊሞቹ ጥንካሬነት የተጫወተዉ ከፍተኛ ሚና 👇
💚💚💚💚💚🇪🇹🇪🇹🇪🇹💚💚💚💚💚
የነቢዩ ﷺ ልደት መታሰቢያ በሀገራችን በተደራጀ መልኩ ህዝባዊ ከሆነ ከ200 ዓመታት በላይ ሆኖታል፡፡ብሄራዊ ባዕልነቱ ከታወጀም 4 አሥርት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ በነዚህ ጊዚያት ለህዝበ ሙስሊሙ ና ለሀገራችን ያስገኘው ፋይዳ መካከል ጥቂቶቹ :-
1) የዕዉቀትና የዳዕዋ ፋይዳ አስገኝቷል
2) የመገናኛ መድረክ (ኮንፈረንስ) ሆኗል
3) መንፈሳዊ ፋይዳን አስገኝቶል
4) ኪነጥበባዊ ፋይዳ አለው
5) እስላማዊ ቁመናን የመጠበቅ ፋይዳ አለው
6) የመዝናኛ አገልግሎትን ይሰጣል
7) ኢስላማዊ ሜዲያ ይሆናል
8) የትግል ጥሪ መድረኮችን
9) የህክምና አገልግሎት መስጫ ይደረግበታል
10) ደስታና ምስጋና ለማድረስ ሰበብ ይሆናል
11) ነቢዩን ﷺ የማስታወስ ሚናው ከፍተኛ ነው
12) ነቢዩን ﷺ የማስተዋወቅሚናው ከፍተኛ ነው
13) የነቢዩን ﷺ ፍቅር የማስረጽ ሚናው እጅግ የላቀ ነው
14) መንፈስን የማደስ ሚና አለው
15) የዳዕዋና የፈትዋ መድረክ ይሆናል
16) የትዉልድ ድልድይ ይሆናል
17) 9. የታሪካችን አካል ሆኗል ፡- መዉሊድ የኢትዮጵያ እስልምና ታሪክ አካል ሆኗል፡፡ ጥልቅ ማህበራዊ መሠረት ያለዉ ባህልም ፈጥሯል፡፡የኢትዮጵያን እስልምና ከመሻኢኾች የዒልም ማዕዶች፣እነርሱንም ከመዉሊድ መድረኮቻቸዉ ነጥሎ ማየት የማይቻል ነዉ፡፡ ይህንን ማንነትና ታሪክ ሊያጠፋ ወይንም ሊያበላሽ የሚለፋ አካል ለእስልምና መዳከም ሊሰራ እንጅ ፈፅሞውንም ለእስልምና መስፋፋት ሊሰራ አይችልም ።
BY ባህረል ሙገ(غ)የባ (የሳዳቶች ስርፋ)
Share with your friend now:
tgoop.com/Duzzl/2605