tgoop.com/Duzzl/2606
Last Update:
ሟች መሞቱን በምን ያረጋግጣል⁉️
-------------------------------------------------
✍መጀመሪያ የሞተ ሰው መሞቱን አያቅም። ሞቶ እያለ እራሱን ያያል፣ ሁለት መላኢካዎች ይመጣሉ መልካም ሰሪ ከሆነ ነፍሱን ያፅናኑለታል።
ቀባሪዎች መሬት ውስጥ አስገብተው አፈር ሲከምሩበት ግን ማልቀስ ይጀምራል ይጮኸል ግን ጩኸቱን የሚሰማው የለም፣ ሁሉም ሰው ተበትኖ ብቻውን ሲሆን አላህ ነፍሱን ይመልስለታል።
ቀብረውት ሲሄዱም ሰዎች ሲቀሩ የእርሱን ድምፅ እንስሳዎች ሳይቀሩ ይሰሙታል።
አይኖቹን ከፍቶ ይነቃል። በመጀመሪያ ደስተኛ እና አመስጋኝ ነበር ያጋጠመው ነገር ቅዠት ሆኖበት አሁን ከተኛበት ነቅቷል።
ከዚያም በጨርቅ የተጠቀለለውን ሰውነቱን ይነካካውና ምነው እዚህ ምን አየሰራሁ ነው? እሱ እየተሰማው ያለው ነገር ህልም አይደለም የምርም እንደሞተ ይረዳል።
የቻለውን ያህል ይጮኸል ዘመዶቼ ከሰሙኝ ብሎ ግና ማንም መልስ አይሰጠውም ከዚያም ተስፋው አላህ ብቻ መሆኑን ያስታውሳል።
አያለቀሰ ይቅርታ ይጠይቃል ያረብ አምላኬ ሆይ ይቅር በለኝ በህይወቱ ተሰምቶት የማያቀው አስገራሚ ፍርሃት ይዞት ይጮኸል።
መልካም ሰው ከሆነ መልካም ስራው ፈገግ እያለ ሊያፅናናው አጠገቡ ይቀመጣል።
መጥፎ ሰው ከሆነ አስቀያሚ ስራው አስቀያሚ ሆኖ መቶ ያሰቃየዋል።
አላህ ከቁጣው አድኖ ጀነት ከሚገቡት ባሮቹ ያድርገን‼️
መልክቱን ለሌሎችም እንዲደርስ ሁላችሁም ሼር ማድረግ አትርሱ ወደ መልካም ያመላከተ ሰው ያመላከትምተውን ያክል አጅር አለው‼️
:
«በየ ጊዜው የምለቃቸውን ጽሑፎች በቀላሉ ለማግኘት ይህን የቴሌግራም ቻነሌን ተቀላቀሉት»።
https://www.tgoop.com/joinchat-U4q9OHoSPqgy3teR
BY ባህረል ሙገ(غ)የባ (የሳዳቶች ስርፋ)
Share with your friend now:
tgoop.com/Duzzl/2606