tgoop.com/EAAAresponse/106
Last Update:
🔖 ባይብል እና ብርዛት
በአሏህ ስም እጅግ በጣም እሩህ እሩህ ፣ በጣም አዛኝ በሆነው።
فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ الْكِتَابَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ اللَّهِ لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ فَوَيْلٌ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ
ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት) ወዮላቸው፡፡
[📖 ሱረህ አል-በቀራህ; 2፥79]ዮሐንስ 7:8
- 'የኢየሱስ ውሸት ወይስ የጸሐፊ ብርዝት ?'
🎯 የሥነ-መለኮት ባለሙያ 'Caspar Rene Gregory' ይህን ጥቅስ አስመልክቶ እንዲህ ይለናል -
🔎 {There are a few cases in the New Testament in which, as we may see, for example, in John 7:8, changes have been made for a definite purpose which we might call dogmatical or even apologetical. In the verse mentioned Jesus says : “I go not up to this feast,” using the phrase which was rendered in Greek by ouk anabainw. Some good Christian in early times, reading this and finding two verses later that Jesus actually did go up to that feast, said to himself apparently : “That cannot be. Jesus cannot have said that He was not going up to the feast. He can only have said that He did not intend to go at that moment. He must have left room open for His later going up to Jerusalem.” And therefore this Christian wrote over the ouk or on the margin beside ouk the word oupw, “not yet,” and caused Jesus to say : ” I am not going up to this feast yet.”}
🔦 ‹‹በአዲስ ኪዳን ውስጥ ጥቂት አሉ ፣ ለምሳሌ እንደምናየው ፣ በዮሐንስ 7÷8 ላይ ለተለያየ ዓላማ ሲባል ለሥነ-መለኮታዊ ወይንም እቅበተ እምነት ማለት እንችላለን በአንዳንድ ጥቅሶች ላይ ለውጦች ተደርገዋል፡፡
በዚህ ጥቅስ ላይ ኢየሱስ :- "ወደዚህ በዓል አልወጣም" በማለት በግሪክኛ የተተረጎመውን ሐረግ 'ουκ αναβαινω/ ኦክ አናባይንው' ስለተጠቀመ በጥንት ጊዜያት አንድ ጥሩ ክርስቲያን ፣
ይህን አንብቦ በኋላ ግን ኢየሱስ ወደዚያ በዓል እንደሄደ ከሁለት ጥቅሶች ቀጥሎ ስላገኘ እንደሚታየው ይህ ሰው በውስጡ
"ያ ሊሆን አይችልም፡፡ ኢየሱስ ወደ በዓሉ አልሄድም ማለት አይችልም፡፡ ምን አልባት በዚያ ሰዓት ወደ በዓሉ ለመሄድ አላሰበም ብሎ ይሆናል፡፡ በኋላ ግን ወደ ኢየሩሳሌም የመሄድ እድሉን ክፍት እንደተወ ጥርጥር የለውም።" በማለት
ይህ ክርስቲያን በ(οὐκ/ኦክ) ወይም በኅዳጉ ላይ ከ'ኦክ' አጠገብ (οὔπω/ኦፖው) "ገና” የሚል ቃል በመጻፍ ኢየሱስን “ወደዚህ በዓል ገና አልወጣም” እንዲል አደረገው፡፡››
[📙 Caspar R. Gregory: Canon And Text Of The NT – Page 504]
🎯 ሌሎች ወደ አራተኛው እና አምስተኛው ክፍለዘመን ሚመለሱ የጥንት እደ-ክታባት እና ጽሑፎች ግን ከ(ουκ) ወደ (οὔπω) የተቀየረውን ስህተት ቁልጭ አርገው በማጋለጥ (οὔπω) የምትለዋን ቃል አሽቀንጥረው በመጣል (ουκ) ወደ ቦታዋ መልሷታል።
☞︎︎ Codex Sinaiticus & Codex Bezea (ከታች ፎቶው አለ)
☞︎︎︎ Nestle-Aland. (27. Aufl., rev.) Page 269 Stuttgart.
☞︎︎︎ UBS4. Revised Edition (Jn 7:8) Page 342.
☞︎︎︎ Tischendorf. Novum Testamentum graece. 1869-94
☞︎︎︎ Griesbach. Greek Text Of J. J. Griesbach – Page 191
🎯 ይህ የቃላት መለዋወጥም ያስፈለገው ኢየሱስን ውሸታም ላለማስመሰል እንደሆነ 'Bruce Terry' ይነግረናል -
🔎 {Looking past verse 9 (“he remained in Galilee”) to verse 10 (“he also went up”), several copyists apparently changed “not” to “not yet” to remove what they thought would have been a lie told by Jesus. If “not yet” was original, there would have been no reason for it to have been changed to “not” in so many manuscripts.}
🔦 "ያለፈውን ቁጥር 9 (“በገሊላ ቀረ”) እስከ ቁጥር 10 (“እሱ ደግሞ ወጣ”) ስንመለከት ፣ ኢየሱስ የተናገረው ውሸት ነበር የሚለውን ሐሳብ ለማስወገድ ብዙ ጸሐፊዎች “not” ወደ “not yet(ገና)” በማለት ቃሉን ለውጠዋል፡፡ “ገና(not yet)” የሚለው ትክክለኛ ቢሆን ኖሮ በብዙ የብራና ጽሑፎች ውስጥ ወደ “not” የሚያስቀይር ምንም ምክንያት አይኖርም ነበር።"
[📙 Bruce Terry: A Student’s Guide to New Testament Textual Variants – John 7:8]
🎯 በተጨማሪም
🔎 {The reading οὔπω was introduced at an early date (it is attested by P66, 75) in order to alleviate the inconsistency between ver. 8 and ver. 10.”}
🔦 ‹‹ 'οὔπω' የሚለው ንባብ የተዋወቀው ቀደም ባለ ዘመን ሲሆን (በ P66 ፣ 75 ደንገል) በቁጥር 8 እና 10 መካከል ያለውን የአውድ አለመጣጣምን ለማቃለል ነው።››
[📙 Bruce M. Metzger, A Textual Commentary on The Greek New Testament, Second Edition (Stuttgart, Germany: Deutsche Bibelgesellschaft/United Bible Societies, 1994), p. 184.]
✋️ ጥያቄ -
--›› ይህ ጥሩ ክርስትያን ደስ ያለውን ጥቅስ በማስተካከል ውለታ ከሰራላችሁ ከሱ በኃላም ሌሎች ጥሩ ክርስትያኖች አለመጨመርና አለመቀነሳቸውን በምን እርግጠኞች ሆናችሁ ?
ምሑራን እና ምንጮቻችሁም የቃላት መለዋወጥ እንዳለ እየመሰከሩ እንዴት እምነታችሁን በዚህ መጽሐፍ ላይ ትመስርታላችሁ ?
☕︎ ይቀጥላል ኢንሻአላህ...✍︎
Facebook page
https://www.facebook.com/Ethiomuslimallegationhunters/
BY E͜͡t͜͡h͜͡i͜͡o͜͡ M͜͡. A͜͡l͜͡l͜͡e͜͡g͜͡a͜͡t͜͡i͜͡o͜͡n͜͡ H͜͡u͜͡n͜͡t͜͡e͜͡r͜͡s͜͡
Share with your friend now:
tgoop.com/EAAAresponse/106