tgoop.com/EAAAresponse/181
Last Update:
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ ፣ በጣም አዛኝ በሆነው።
╔───────◎ - ◎───────╗
የሥነ-ሐዲስ ጥናት (Hadith terminology)
╚───────◎ - ◎───────╝
‹ሐዲስ› ማለት ‹ትርክት› ወይም ‹የነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ቅዱስ ንግግር› ሲሆን የነቢዩ ‹ሰሓቦች "ባልደረቦች/companions"› ፣ ‹ታቢዒዮች "ተከታዮች/adherents"› እና የታቢዒይ ታቢዒዮች የዘገቡልን ነው።
ምሑራኖቻችንም ከጥንት ጀምሮ የአንድ ‹ሙሐዲስ "ተራኪ/narrator"› ትርክት ሲተላለፍላቸው የሱን ‹መትን "ይዞታል/content"› እና ‹ኢስናድ "ዘገባ/narration"› ከነ ዘጋቢው ጭምር ‹አስ-ሲሐህ "ታእማኒነቱ/authentication"› ለማረጋገጥ እንድንችለና ሐዲሱን ‹ሰሒሕ "በጣም ትክክለኛ/authentic"› ብለን ለመቀበል ሕጎችንና መርሆችን አፅድቀዋል፡፡
🎯 የእያንዳንዱ ተራኪ ዳራ ለማወቅ ምሑራኖች -
➲ የዑስታዞቹን ምስክርነት፤
➲ የተማሪዎቹን ምስክርነት፤
➲ የባልደረቦቹን ምስክርነት እንዲሁም፤
➲ ‹‹ዒልሙር-ሪጃል›› የሚባል ስለ እያንዳንዱ ተራኪ ማንነት የሚቋጭ ሰፊ ጥናትና ምርመራ ይደረጋል።
🎯 ማንነቱም ከታወቀ በኃላ ሐዲሱ ሰሒሕ ለመባል ተራኪው -
➊ ‹‹አድል››:- ታማኝ ሰው መሆን አለበት፤
➋ ‹‹ደብጥ››:- የማስታወስ ችሎታው ከጽሑፍ ጋር፤
➌ ‹‹ሙተሲል››:- ትረካውን የተቀበለበት አያያዥ ማንነት፤
➍ ‹‹ሰነድ››:- የሐዲሱ ተራኪዎች ስም/ሰንሰለት ያልተቋረጠ፤
➎ ‹‹ሻዘህ››:- እነዚህን አራት መስፈርት አልፎ ከቀደመው ዘገባ ጋር ምንም አይነት የሐሳብ ወይም የትርጉም ግጭት እና ፍጭት ሊኖርበት አይገባም።
🎯 የሐዲስ ዓይነቶች -
⓵ «ኣሓድ(ነጠላ)»:- በሦስት ሰዎች ወይም ከዚያ በታች የተዘገበ ሐዲስ ሲሆን በሶስት ይከፈላል-
‹‹ገሪብ››:- በአንድ ሰው ብቻ የተዘገበ።
‹‹ዐዚዝ››:- በሁለት ሰዎች ብቻ የተዘበ።
‹‹መሽሁር››:- በሶስት ሰዎች የተዘገበ።
⓶ «ሙተዋቲር(ተከታታይ)»:- በአራት እና ከዚያ በላይ ሰዎች የተዘገበ ሐዲስ ነው።
🎯 የሐዲስ ይዘት -
⓵ , «መቅቡል(ተቀባይነት ያለው)»
‹‹ሰሒህ እና ሐሰን››
⓶, «መርዱድ(ተቀባይነት የሌለው)»
‹‹ዷዒፍ እና መውዱዕ››
‹‹ዷዒፍ››:- ደካማ ሲባል ሙንቀጢዕ ፣ ሙድጠሪብ ፣ ሙዕዲል ፣ መጅሁል ፣ ሙንከር ፣ ሙርሰል ፣ ሻዝ ሲሆኑ ኢንሻአላህ ከታች በምሳሌ አንድ በአንድ እንመለከታቸዋለን...
ለምሳሌ አንድ ሐዲስ -
ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ ፤ 570-633 CE)
↓
➊, ለዐሊይ (ረ.ዐ ፣ 601-661CE)
↓
➋, 👤 (640-741 CE)
↓
➌, 👤 (712-795 CE)
↓
➍, 👤 (772-847 CE)
↓
➎, ለቡኻሪይ (ረ.ላ ፤ 810-870 CE)
☞ ከላይ በተቀመጠው መልኩ ሰንሰለቱ የተሟላ ሆኖ ከተላለፈን ሐዲሱ ‹‹ሰሒሕ(በጣም ትክክለኛ)›› ይባላል፨
☞ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) በሰንሰለቱ ውስጥ ከሌለ ‹‹መውቁፍ(የቆመ)›› ይባላል፨
☞ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) እና 1ኛው(ባልደረባው) በሰንሰለቱ ውስጥ ከሌሉ ‹‹መቅጡዕ (የተቆረጠ)›› ይባላል፨
☞ 1ኛው ብቻ ከሰንሰለቱ ከተቋረጠ ‹‹ሙርሰል›› ይባላል፨
☞ 2ኛው ከሰንሰለቱ ከተቋረጠ ‹‹ዷዒፍ(ደካማ)›› ወይም ‹‹ሙዐለቅ(የተንጠለጠለ)›› ይባላል፨
☞ 3ኛው ከሰንሰለቱ ከተቋረጠ ‹‹ሙንቀጢዕ(የቋዋረጠ)›› ወይም ‹‹ሙዐለቅ(የተንጠለጠለ)›› ይባላል፨
☞ 4ኛው ከሰንሰለቱ ከተቋረጠ ‹‹ሙዐለቅ(የተንጠለጠለ)›› ይባላል፨
☞ ሁለት ወይም ከዛ በላይ ከሰንሰለቱ ከተቋረጡ ‹‹ሙዕዲል(የተምታታ)›› ይባላል፨
☞ ከአምስቱ አንዳቸው የማስታወስ ችሎታው ደካማ ከሆነ ‹‹ዷዒፍ(ደካማ)›› ይሆናል፨
☞ ከአምስቱ አንዳቸው ሐሰተኛ ከሆነ ‹‹መክዙብ(የተቀጠፈ)›› ወይም ‹‹መውዱዕ(መሰረተ-ቢስ)›› ይሆናል፨
☞ ከአምስቱ አንዳቸው ማንነቱ የማይታወቅ ከሆነ ‹‹መጅሁል(ማይታወቅ)›› ይሆናል፨
☞ በአንዱ ሐዲስ ሰንሰለት ደካማ(ቶሎ የሚረሳ) ተራኪ ኖሮ በሌላ ሐዲስ ሰንሰለትም ላይ ሌላ ደካማ ተራኪ ካለ ግን ሁለቱም ያስተላለፉት ሐዲስ ይዘቱ አንድ ከሆነ(ከተደጋገፉ) ‹‹ሐሰን(መለስተኛ ትክክለኛ)›› ይሆናል፨
☞ 1ኛው ዘጋቢ ለሦስት ተማሪዎች አስተምሮ ሁለቱ በአንድ ቃል ተስማምተው ሶስተኛው ግን ለብቻው ከተለየ የሶስተኛው ሐዲስ ‹‹ሻዝ(ኢ-መደበኛ)›› ይሆናል፨
☞ ሻዝ የሆነውን ሐዲስ ያስተላለፈው ዘጋቢ ኃሳዌ ሆኖ ከተገኘ ‹‹ሙንከር(ተቀባይነት የሌለው)›› ይሆናል፨
ወሠላሙ ዐለይኩም...✍︎
Telegram channel ~> https://www.tgoop.com/EAAAresponse
Telegram group ~> https://www.tgoop.com/A3E1response
Facebook ~> https://www.facebook.com/Ethiomuslimallegationhunters/
BY E͜͡t͜͡h͜͡i͜͡o͜͡ M͜͡. A͜͡l͜͡l͜͡e͜͡g͜͡a͜͡t͜͡i͜͡o͜͡n͜͡ H͜͡u͜͡n͜͡t͜͡e͜͡r͜͡s͜͡
❌Photos not found?❌Click here to update cache.
Share with your friend now:
tgoop.com/EAAAresponse/181