tgoop.com/EAAAresponse/253
Last Update:
⚪️ ❝ቁርኣን ዘላለማዊው ተዓምር❞ [𝟒]
በሥነ ጠፈር(Spaceology) ዙርያ አስትሮኖመሮች ወደ ጠፈር ጉዞ ሲያደርጉ (space blindness or VIIP) የሚባል ቅምረ ህመም በእይታቸው ላይ የዓይን እክልነትን/ስውርነትን አስከተሏል። እዛ ስበተ ቁስ(gravity) ስለሌለ በአንጎል እና በአይን ጀርባቸዉ ላይ ጫና ተፈጥሮ ነው ተብሎም ይታሰባል።
➛ ‘Julie Robinson’ እንዳለችው :- ‹ባለፉት 10 አመታት ውስጥ ከደረስንባቸው ነገራቶች አንዱ የተወሰኑ ጠፈርተኞች ወደ ህዋ ሲሄዱ ዓይናቸው ጠፋ...ጥቂቶቹ ወደ ምድር ሲመለሱ የማይቀለበስ ቋሚ የእይታ እጦት ደረሰባቸው።”›
[🔗 https://m.lasvegassun.com/news/2017/dec/02/space-blindness-must-be-solved-before-mission-to-m/]
➛ አንዳንዶችም እንደ ‘Scott Kelly’ እና ‘John Phillips’ ከጠፈር ጉዞ ከተመለሱ በኃላ በአጭር ጊዜ ውስጥ እይታቸው ላይ ችግር እንደተፈጠረ ታውጇል።
[🔗 https://www.sciencealert.com/we-finally-know-why-astronauts-lose-their-vision-in-space-and-it-s-bad-news-for-mars-missions]
🎯 አላህ ﷻ በቅዱስ ቃሉ ቁርአንን ያስተባበሉ ከሃድያን የሰማይን ደጃፍ (ozone layer) ከፍቶላቸው ወደ ላይ ቢያርጉ ኖሮ ‘space blindness’ ያጋጥማቸው እንደነበር ወደዚህ አስደናቂ ክስተት አስቀደሞ ጠቁሞናል—
۞ «በእነርሱም ላይ ከሰማይ ደጃፍን በከፈትንላቸውና በእርሱ ሲወጡ በዋሉ ኖሮ»
۞ «#የተዘጉት_ዓይኖቻችን_ናቸው፡፡ እንዲያውም እኛ የተደገመብን ሰዎች ነን» ባሉ ነበር፡፡»
— አል-ሒጅር 15÷14-15
ሰደቀሏሁል ዐዚም...✍︎
https://www.tgoop.com/EAAAresponse
BY E͜͡t͜͡h͜͡i͜͡o͜͡ M͜͡. A͜͡l͜͡l͜͡e͜͡g͜͡a͜͡t͜͡i͜͡o͜͡n͜͡ H͜͡u͜͡n͜͡t͜͡e͜͡r͜͡s͜͡

❌Photos not found?❌Click here to update cache.
Share with your friend now:
tgoop.com/EAAAresponse/253