tgoop.com/EAAAresponse/71
Last Update:
ክፍል ሁለት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው
-------------------------------------------------------------------------------
🎯 በክፍል 1 የተለያዩ የመገናኛ ሚዲያዎች እና ጭፍን ተከታዬች ኢስላም ላይ የሚቀጥፉትን ውሸት ና የሚለጥፉትን የውሸትና የማታለያ ስሞች በአላህ ፍቃድ ውድቅ እንደሆነ የተለያዩ ነጥቦችን ከማስረጃ ጋር በማስደገፍ ለማየት ሞክረናል ። በክፍል ሁለት በአላህ ፍቃድ በ ሌላ እምነት ተከታዬች ( በተለይ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች ) አንስተው ከሚሞግቱበት ሀሳብ እየተነሳን ምላሽ እንሰጣለን ።
-----------------------------------------------------------------------------------
📖 2 እኩል እውቀትን የማግኘት መብት 📖
🔮 ወንዶችም ሆነ ሴቶች እኩል በሆነ መልኩ እውቀትን እንዲፈልጉ ይበረታታሉ ። ለዚህም ነው ነብዩ ( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ) " እውቀትን መፈለግ በሁሉም ሙስሊም ( ወንድም ይሁን ሴት ) ላይ ግዴታ ነው ። " ያሉት ።
🎈 እንዲሁም ታላላቅ ሙስሊም ሴት ምሁራኖች በ ነብዩ ( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በነበሩበት ጊዜና ቦታም ነበሩ ። አንዳንዶቹ ከሳቸው ቤተሰቦች ውስጥ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ባልደረቦቻቸው ሴት ልጆች ነበሩ ። ከነዚህም መሀከል ስሟ ጎልቶ የሚጠራው የነብዩ ሙሀመድ ( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ) ሚስት አዒሻ ( ረዲየላሁ ዐንሃ ) በሷም አንድ አራተኛው የሚሆን የኢስላም ህግጋቶች የተላለፉባት ነች ።
📚 ሌሎች ሴቶች ታላላቅ የህግ ምሁራን ሲሆኑ ከስራቸውም ታዋቂ ወንድ ምሁራኖች በ ተማሪነት ማፍራት የቻሉ ነበሩ ።
🏆 3 እኩል የትዳር አጋርን የመምረጥ መብት
💡 እስልምና ሴቶችን የትዳር አጋር የመምረጥ እና አንዴ ከተጋቡ በኋላ የቀድሞውን የቤተሰብ ስያሜ የመያዝ መብት በመስጠት አክብሯቸዋል ፡፡ በተጨማሪም ብዙ የ ኢስላም ነቃፊዎች ወላጆች ሴቶች ልጆቻቸውን እንዲያገቡ ያስገድዳሉ የሚል አመለካከት አላቸው ፡፡
ይህ ባህላዊ የሆነ ድርጊት ነው ፣ በእስልምናም መሠረት የለውም ፡፡ በእርግጥም የተከለከለ ነው ፡፡
⚜ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወቅት አንዲት ሴት ወደ እሳቸው መጥታ “አባቴ በ ማህበራዊ ያለውን ደረጃው ከፍ ለማድረግ የአጎቴን ልጅ እንዳገባ ድሮኛል እና በዚህ እኔ ተገድጃለሁ አለቻቸው ፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደ ሴቷ ልጅ አባት ላኩ ከዚያም እሱ ባለበት ሁለት አማራጭን አቀረቡላት ወይ በትዳር እንድትቀጥል ወይም ጋብቻውን ማፍረስ ፡፡ እሷም “የአላህ መልእክተኛ ሆይ አባቴ ያደረገውን ተቀብያለሁ ግን ሌሎች ሴቶችን (ወደ ትዳር ሲገቡ መገደድ እንደማይችሉ ( እንደሌለባቸው ) ) ለማሳየት በመፈለግ ነው ” ብላ መለሰች ፡፡
..................................................................................
🖇 በ ኢስላም ሴቶችና ወንዶች ያሏቸውን መብት ለአብነት ከጠቀስን ከዚህ ቀጥሎ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች የሚያነሷቸውን ሙግቶች ነጥብ በነጥብ እናያለን ።
1 ብዙ ሚስት
🔗 « በኢስላም ለወንድ ልጅ እስከ 4 ሚስትን ማግባት ሲፈቅድ በተቃራኒው ደግሞ ሴቶችን ከ አንድ በላይ ባል ማግባትን ከልክሎዋል ይሄ ደግሞ በ ኢስላም ወንድ እና ሴት በ እኩል እንደማይታዩ ያሳያል ⁉ » የሚል አመለካከትን ያነገቡ ጥቂት የማይባሉ የሌሎች እምነት ተከታዬች መኖራቸው ይስተዉላል ።
🔮 በመጀመርያ አላህ የፈቀደውን ነገር ክልክል ማድረግ የከለከለውን ደግሞ መፍቀድ ትልቅ ክስረት ነው ። አላህ የፈቀደው ሆኖ ሳለ ከ ስሜታችን ጋር ቢገጥምም ባይገጥምም መቀበል ግዴታችን ነው ።
📌 ሀሳቡን ለመግለፅ ያክል ግን ወንድ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ስለተፈቀደለት ሴት በተቃራኒው መከልከሏ እኩልነት አልሰፈነም ለማለት አያስችልም ።
☞ ረሱል(ሰዐወ) ሊሞቱ ሲሉ ለሰሃቦቻቸው ሰብስበው ካደረጉት ከመጨረሻ ንግግራቸው ውስጥ አንዱ:-
☞ “#በሴቶቻችሁ ላይ አላህን ፍሩ (እንዳትበድሏቸው) #በሴቶቻችሁ መልካምን እንድትውሉ እመክራቹሀለው “።
⛓ «polygamy» ማለት ለ አንድ ሰው ከአንድ በላይ የትዳር አጋር ሲኖረው ማለት ነው ። ይሄ « polygamy» ሁለት አይነት ነው ፦
📕 አንደኛው « polygyny » - ማለት አንድ ወንድ ከአንድ በላይ ሚስት ሲኖረው ነው ሲሆን
📔 ሁለተኛው « polyandry » - ማለት አንድ ሴት ከ አንድ በላይ ባል ሲኖራት ማለት ነው ።
ኢስላሚ ገደብ ያለውን « polygyny » ( ከ አንድ በላይ ሚስት ለ አንድ ወንድ ) ሲፈቅድ በተቃራኒው ደግሞ « polyandry » ( ከ አንድ በላይ ባል ለ አንድ ሴት ) ከልክሎዋል ።
ነጥብ አንድ
📓 ቁርአን « አንድን ሚስት ብቻ አግባ » የሚል ትዕዛዝን አጠቃሎ የሚይዝ ብቸኛው የ ሀይማኖት መፅሀፍ ነው ። ምድር ላይ የትኛው የሀይማኖት መፅሀፍ ነው የሚሉት መፅሀፍ (ልክ እንደ ቬዳስ ፣ ራማያን ፣ መሀብሃርት እና ባይብል ) ውስጣቸው ቢፈተሽ « አንድ ብቻ አግብ » ብሎ አይገድብም ።
------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
*ሱራህ 4, አያህ 3*
وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا۟ فِى ٱلْيَتَٰمَىٰ فَٱنكِحُوا۟ مَا طَابَ لَكُم مِّنَ ٱلنِّسَآءِ مَثْنَىٰ وَثُلَٰثَ وَرُبَٰعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا۟ فَوَٰحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُمْ ۚ
ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَلَّا تَعُولُوا۟
በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ)፡፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ #አንዲትን #ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡
------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ነጥብ ሁለት
💾 ኢስላም በ ሚስቶቹ መሀከል ማስተካከልን ለማይችል ( ፍትሐዊ በሆነ መልኩ መያዝ በማይችል ) ሰው አራት ማግባትን አይፈቅድም ። « .. አለማስተካከልንም ብትፈሩ #አንዲትን #ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡..» (4:3)
🔰 ምንም እንኳን ኢስላም ለ አንድ ወንድ እስከ አራት የማግባትን ፍቃድ ቢሰጥም ፤ ብዙ ጥናቶች እንደሚያስነብቡት ከሆነ ይሄ ከ አንድ በላይ ማግባት በአብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ ዘንድ 2% አቅራቢያ በሚባል ደረጃ ብቻ ተግባራዊ እንደሚሆን ነው [ 1]
BY E͜͡t͜͡h͜͡i͜͡o͜͡ M͜͡. A͜͡l͜͡l͜͡e͜͡g͜͡a͜͡t͜͡i͜͡o͜͡n͜͡ H͜͡u͜͡n͜͡t͜͡e͜͡r͜͡s͜͡
Share with your friend now:
tgoop.com/EAAAresponse/71