tgoop.com/EOTC2921/5286
Last Update:
🌾 መቼ ይሆን? 🌾
አምላኬ ሆይ አባቴ ሆይ እረኛዬ
የማትረሳ የማት'ተወኝ ጌታዬ
አንተ ቅዱስ ቤትህ ቅዱስ
ስምህ አዳኝ የሚፈውስ
የመሸብኝ ካንተ ርቄ
የነጋብኝ በኔው ስቄ
ባንተው ስራ ታየውብህ
ተከበርኩኝ ሰፋውብህ
ከፍ አረከኝ ኮራሁብህ
እየኝማ አባቴ ሆይ
ተመልከተኝ ወዳጄ ሆይ
ፈካ ብዬ ተጠቅልዬ በነጠላ
ከልለኸው ጉድፍ መልኬ እንዳይጎላ
ካንተ ውጪ የዋልኩበት
አንተን ትቼ ያደርኩበት
ባይመችም አለሁ እዛው
መቼ ይሆን የምትመጣው?
ዛሬ ይሆን የምትመጣው?
ለስጋ ሀሳብ እየተጋው
ውስጤን ነፍሴን እንደጎዳው
ማታ ይሆን የምትመጣው?
እየሰከርኩ እየጠጣሁ?
መሸታ ቤት እያነጋሁ
በራቀ ድምፅ
በቄሱ ድምፅ
ሳህታቱን
ኪዳንህን
ገድላትህን እየሰማሁ
በሙዚቃ ጭፈራዬን እያስነካሁ
ያኔ ይሆን የምትመጣው ?
መቼ ይሆን የምትመጣው?
ማታ መቼም ባትመጣ
በባለ 50ም ባትመጣ
ቅዳሜ ቀን ባትመጣ
ካንተ ስርቅ ባትመጣ
አታየኝም ታጣኛለህ
ሳትለየኝ ትሄዳለህ
ሌላ ሆኜ ታልፈኛለህ
የሞኝ ሀሳብ የምመኘው
ሀጥያቴን እንደመተው
ካንተም ከኔም እንድሆነው
በኩዳዴ በፆሙ ና
አርብ እና ሮብ ወይ በገና
ባስራ ስድስት በነሀሴ
ወይም እሁድ በቅዳሴ
ማታ አዳሬን እየወቀስኩ
ፊትህ ቆሜ እያለቀስኩ
ለንሰሀ እንደበቃሁ
ለማስቀደስ እንደገባሁ
ያን ግዜ ና ቤትህ አግኘኝ
እንዳልወጣ ቤትህ አስቀረኝ
ታምሚያለሁ አንተ አክመኝ
ልብ ስጠኝ አንተን ልበል
ያንተው ሆኜ ባንተ ልማል
ልታዘዝህ ቤትህ ልዋል::
ከቤቱ አያርቀን በምህረቱ ይመልከተን🙏
✍️ ቸርነት ፍቃዱ
BY የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
Share with your friend now:
tgoop.com/EOTC2921/5286