tgoop.com/EOTC2921/5299
Last Update:
🌾•✞ ላንዴ እስከወዲያኛው ✞•🌾
ላንዴ እስከወዲያኛው
ያንን ሰው ባረገኝ ያችንም ሴት በሆንኩ
ላልወጣ ገብቼ ላልመለስ በሄድኩ
ምነው እሱን በሆንኩ ያን የቀኝ ወንበዴ
ብመስለው ለአንድ ቀን ባየው በመንገዴ
ለመስረቅ አይደለም ንብረት ለመቀማት አልያም ለመዝረፍ ህይወትን ለማጥፋት
በዚያ መንገድማ
ከሱስ ብበልጥ እንጂ መች ከእርሱ አንስና
እኔን ታውቀኝ የለ
የወንበዴ አለቃ የኀጢኣተኞች ዋና
ያ ጸጸት ያዘለ
በዚያች የጭንቅ ሠዓት "አስበኝ" እያለ
ከመስቀልህ ጥላ ከሥር ስለዋለ
ከአዳም ቀድሞ ገባ ምሕረት ተቀበለ /፪/
እኔም እንደ ጥጦስ ማታዬ እንዲያምር
ብትለኝ ምን አለ
"ከገነት ተጠለል ዛሬን ከኔ እደር" /፪/
#አዝ•••✞•••
ደግሞ ይህን ተመኘሁ ለንጊኖስን በሆንኩ
ያቺን ዕለተ አርብ ቀራንዮ በዋልኩ
ለአመጽ አይደለም ከአይሁድ ለማበር
አልያም ለመውጋት ያንተን ጎን በጦር
በዚያ መንገድማ
አንተን ለማሳመም ማን እኔን መሰለ
ስንቴ እንዳቆሰልኩህ
እኔን ታውቀኝ የለ ስንቴ እንዳቆሰልኩህ
ያ ጲላጦስ ጭፍራ
በመስቀል ላይ ሳለህ በሞት በመከራ
በጦሩ ቢወጋህ ሴያዝን ሳይራራ
ከቀኝ ጎን አፍስሰህ ውኃን ከደም ጋራ
በፍቅርህ ስታስረው ዐይኑን ስታበራ
ትዕግስትህን ጎትቶት ባንተ እንደ ተጠራ
ምናለ እንደው እኔንም
ላንተ ብቻ እንዳድር ልቤ ብታበራ
ምናለ እንደው እኔንም ላንተ ብቻ እንዳድር
ልቤ ብታበራ ላንተ ብቻ እንዲያድር
•••✞•••✞•••✞•••
ላንዴ እስከወዲያኛው
ያንን ሰው ባረገኝ ያችንም ሴት በሆንኩ
ላልወጣ ገብቼ ላልመለስ በሄድኩ
ምነው በመስልኳት ያቺን ከመንዝራ
እንደርሷ ለአንድ ቀን ከፊትህ ብጠራ
ለዝሙት አይደለም ነፍሴን ለማሳደፍ
አልያም ለመርከስ መቅደስክን ለማጉደፍ
በዚያ መንገድማ
ነውርን በመሸከም መች ከእርሷ አንሳለሁ
ሕግህን በማፍረስ
እኔን ታውቀኝ የለ ምን እነግርሃለሁ
ያቺን... ድኩም ዘማ
በኃጢአቷ ቆስላ በበደሏ ታማ
ዓለም ተሰብስቦ ሕይወቷን ሊቀማ
እንዲወግሯት ሳትፈርድ ቸርነትህ ቀድማ
መሬቱን ስትጭር ድምጽህ ሳይሰማ
ነውሯን እንደቀበርክ በከሳሽ ፊት ቆማ
ዳግም አትበድዪ በፍቅር ሂጅ እንዳልካት
እንደው የእኔንም ነፍስ
ምናለ መልሰህ እንዲያ በማረካት /፪/
#አዝ•••✞•••
BY የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
Share with your friend now:
tgoop.com/EOTC2921/5299