tgoop.com/EOTCmahlet/7826
Last Update:
<<ዘርፍ>>
ዐቢይ ትምህርት ዘልሳነ ግእዝ
በግእዝ ቋንቋ ዘርፍ ትልቅ ቦታ አለው ። አንድ ቃልና ሌላ ቃል ከተናበቡ በሗላ ከሗላ ተናቦ የሚመጣው ቃል <ዘርፍ> ይባላል ።
ምሳሌ
አምላከ ሰማይ የሚለው ቃል ላይ <አምላክ> እና <ሰማይ> የሚሉ ሁለት ቃላት ሲናበቡ የሚያመጣው ቃል ነው ።በዚህ ቃል ውስጥ <ሰማይ> የሚለው ዘርፍ ይባላል ።
ዘርፍ በሚተረጎምበት ጊዜ <የ> የሚል ፊደል በራሱ ጨምሮ ከቀኝ ወደ ግራ ይተረጎማል ።
ለምሳሌ
አምላከ ሰማይ = የሰማይ አምላክ
መስፍነ ኀይል = የኀይል ገዢ
መላእክተ ሰማይ = የሰማይ መላእክት
ሀገረ ኢትዮጵያ = የኢትዮጵያ ሀገር
ነበልባለ እሳት = የእሳት ነበልባል
ቅዳሴ ሐዋርያት = የሐዋርያት ቅዳሴ
እየተባለ ከቀኝ ወደ ግራ <የ> የሚል ፊደል እየጨመረ ይተረጎማል ። ከላይ በተሰጡት ምሳሌዎች ውስጥ ሰማይ ፣ ኀይል፣ኢትዮጵያ፣እሳት ፣ ሐዋርያት የሚሉት ቃላት ዘርፍ ይባላሉ ።
እስኪ እናንተም ሦስት ሦስት ተናባባቢ ቃላትን በተሰጠው ምሳሌ መሠረት ከነ ትርጉማቸው እና የትኛው ቃል ዘርፍ ሆኖ እንደገባ በመናገር ተሳተፉ ።
ይህንን ቻናል መቀላቀል የእውነት አለባችሁ ስለ ግእዝ ሙሉውን ነገር ነው የሚያሳውቃችሁ መምህሩም በጣም ጎበዝ ነው ያው ለምሳሌ ያህል አንድ ጊዜ በጠቆምናችሁ የጎንጅ ቅኔ ጉባኤ ቤት አስነጋሪ ነው ። ትምህርቱንም በዘመናዊና በተቀላጠፈ መንገድ ነው የሚያስተምረው ገብታችሁ ስለግእዝ የፈለጋችሁትን መጠየቅ ትችላላችሁ ተቀላቀሉ ብዙ ታተርፉበታላችሁ 🙏
https://www.tgoop.com/geeZzlekulu
BY ያሬዳውያን
Share with your friend now:
tgoop.com/EOTCmahlet/7826