tgoop.com/ETH724/13
Last Update:
በሱዳን በኩል በመግባት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሽብር ለመፍጠር እና በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ከ170 በላይ ግለሰቦች መደምሰሳቸው ተገለፀ።
ፀረ ሰላም ኃይሎች ናቸው የተባሉት ግለሰቦች መተከል ዞን ጉባ ወረዳ "አልመሃል" አከባቢ ሽብር ለመፍጠር እና በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ለማድረሰ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የክልሉ ሠላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።
ቢሮው ፥ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የሕወሃት ቡድን ከክልሉ እና ከክልሉ ወጪ ከሚንቀሳቀሱ ተባባሪዎቹ ጋር በመሆን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭት ለመፍጠር ሲሠራ ቆይቷል ያለ ሲሆን፣ በእነዚህ ኃይሎች ላይ ማያዳግም እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ገልጿል።
እስከ ትላንት ድረስም የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ ከክልሉ የጸጥታ አካላት እንዲሁም በክልሉ ከሚገኙት የደቡብ፣ የጋምቤላ እና የሲዳማ ክልሎች ልዩ ኃይል አባላት ጋር በመቀናጀት በተወሰደ እርምጃ ከ170 በላይ የሚሆኑ የጸረ ሰላም ኃይሎች ተደምስሰዋል፣ የቆሰሉና የተማረኩም አሉ ብሏል።
እነዚህ ኃይሎች በሱዳን ድንበር በኩል በመግባት በመተከል ዞን የሕዳሴ ግድብ መገኛ ጉባ ወረዳ አልመሃል ቀበሌን እንደ ማዕከል ተጠቅመው ወደ ግድቡ የሚደረገውን የእንቅስቃሴ መስመር በመቁረጥ ሥራውን ለማስተጓጎል አላማ እንደነበራቸውም ተነግሯል።
የህዳሴ ግድብ ሥራውን ከማስጓጎል ባለፈ በክልሉ ሽብር በመፍጠር በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት የማድረስ ዓላማ እንደነበራቸውም እና አልማሃልን ማዕከል በማድረግ ወደ አማራ ክልል ለመንቀሳቀስ ዝግጅት እንደነበራቸው ቢሮው ገልጿል።
በተወሰደው እርምጃ ከተደመሰሱት የጸረ-ሠላም ኃይሎች ናቸው ከተባሉት ግለሰቦች መካከል ከ16 በላይ የሚሆኑት የሕወሃት አባላት መሆናቸውን ቢሮ አሳውቋል።
@ETH724
@ETH724
BY ኢትዮ 7/24 መረጃ
Share with your friend now:
tgoop.com/ETH724/13