tgoop.com/Ekramcalligraphy/7264
Last Update:
☞ ዝክረ ኸሚስ ( 85 )
.
« ጉረስ ያለውማ ማድ የዘረጋለት ፣
በእህል ውሃ ዲስቱ ኒካውን ጣደለት ። »
( አገሬው )
-
አውገረዴ ሆዴ ...
አብሮ ዘማች ጓዴ ፣
ኸሚስ አመሻሹ - - ኸሚስ ወደ ማታ ፣
ያርገበግበኛል የክድሚያሽ ወጋገን ክንፉን እያማታ።
.
ይሄው ...
.
ወቅቱ ላይ ደግ ሀጃ ፣
ሃጃው ላይ ውብ ሓድራ ፣
ሓድራው ላይ ጠይም ሌት ፣
አንቺን የተኳለ በቀለሜ አውሃል የሚያክለፈልፈኝ፣
ለሰንበራም ግጥም ፣
የነፍሴን ዳርቻ በኣጀቡ ለበቅ በጉድ የሚገርፈኝ ።
..
( መቼስ ...
..
እድል ባያነቅፈኝ እጣዬ ጠርጎልኝ ፣
መንገዴ ቢያሰልጠኝ ‘ርምጃ ሰልቶለልኝ ፣
ብቻየን አይሆንም ...
ውሃ ልኬ አንቺ ነሽ ፣
የመሄዴ ሚዛን ከነግ ተስፋ ፈጅር ተዋዶ ይተጋል፣
በ‘ያንዳንዱ ዳና የመድረሴ ጀንበር በሺህ ዲጂት ያድጋል።
..
ኸሚስ አመሻሹ ...
ኸሚስ ወደ ማታ ፣
ሃጃው ገድምዳሜ ፣
ሓድራው አባ ሞገድ ፣
የቀኑ ምስለኔ የለይሉ ባለሟል ጠይሞ አንቺን ሲሆን ፣
በኸሚሱ ሞደብ የቱን ቀለም ይዤ የቱን እጥል ይሆን ?!
.
( እንዲያ ሆነ እንግዲህ ... ! )
.
እድያ ነውና ...
እምቢ የማይሉት ፣
ሀቅ ያጉረበረበው ምናብ ሲጠዘጥዝ እከኩ ይነሳል፣
ጠይም ሌሊት መሀል ፣
ቀልብ የሚያለመልም ሀረግ ያፈረጠው ቅኔ ደም ይፈሳል
.
አዎ !
( አውቅሻለሁ ሌቱን ... ! )
.
በሀጃው ኸለዋ ፣
ከግርዶሹ ወዲያ አወል ቡናው ደርሶ ቀሃ ጀባ ‘ስኪባል፣
ከመከኬው ክንፈር ፣
ከፍንጭትሽ ግርጌ ፈገግታሽ ያደባል።
ሊናደፍ ...!
.
መገን ።!
.
ፈሽረክ ትይዋለሽ ...
.
መሳቅሽ አቅል ነው !
ፈገግታሽ ቀለብ ነው !
.
የመሀባ ሸውቁ ፣
የሓድራውን ዋርካ ፣
በፈገግታሽ ጠለሽ ሌቱ ላይ ያዘማል፣
ሳቅሽን አሳቦ ....
ነፍስ የሸነቆረው የሀሴት ጉድ ቀለም ፈሶብኝ ይተማል።
..
አውገረዴ ሆዴ ፣
ኸሚስ ሃላል ሳቄ ፣
ጠይም ሌት ቀለሜ ፣
ገራም ማልዶ ቢብት ፣
ለይሉ ቢገማሸር ታለ ሰው ብቻውን በዱንያ ሞደቡ፣
ቀለሙ ጥሞናን በሶብሩ ቢያረብብ ምን ቢቸር አደቡ፣
.
ቀኑ መች ሲቀናው ፣
ሌቱ መች ሲገራው ፣
ሊገጥመው ሰው ገጥሞት ፣
ከኸልቄው እዬዬ እምባ እየጨለፈ ፣
ዝጎ ላይዶለዱም ለብዕሩ ስለት ሳቅ ካላጠቀሰ ፣
ገጣሚ ፉዞ ነው ... !
ለምናቡ ንቃት ሰውነት ኮልኩሎት ካልተቀሰቀሰ ።
ገጣሚ ‘ራስ የለው ... !
ለምናብ ጎፈሬው ባብሮነቱ ሚዶ በሰው ካልነቀሰ፣
.
ኸሚስ አመሻሹ - - ኸሚስ ወደ ማታ ፣
ያርገበግበኛል የክድሚያሽ ወጋገን ክንፉን እያማታ።
..
እንግዲህ ...
እሱ ይደግሰው ፣
አይሆንም ታለ ሰው ፣!
እንኳን ሳቁ ቀርቶ ይግጠመኝ አህህ ይብለገኝ እዬዬው፣
በግጥም ላባብል በምናቤ አንቀልባ ስለ ሰው አዝዬው።
.
« አዳኝ ቁንጥር ፈርቶ -- ጭቃ ተጠይፎ ፣
አይወረወርም -- ቀስቱ ደጋን አልፎ ። »
.
እያለኝ በቅኔው አያ ሙሌ ጓዴ ፣
እንደት ሀቅ ልዘጋ ይቻለኛል እንዴ ?!
.
እሱ ይዘንልኝ ፣
ሙሾ ተቧልት ጋር ፣
እንደህል ዋጀራ በማይለይበት ፣
ዘለላ ቃል ሳልፅፍ አዝሞ እንዳይነጋ ባክኜ ‘ ንዳይፈጅር ፣
መሷረፊያ ቀለም አንዳቹን ዛር ልኮ ለፍርጃው ይጀርጅር ።
..
ታልቸረማ ምኑን ...
ከምኑ ተጋጥሞ ፣
ሌሊቱ እንደት ጥሞ ፣
ሰው ታላስባለማ በምን ወዝ ሊከተብ ሀቅ እንዳይቀበር ፣
ቅብጅር ነው ‘ንጂ ፣
ሌት ሌላ መልክ የለው ካልጠየመ በቀር ።
---
semir ami✍
@semiraklu
BY 💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡
Share with your friend now:
tgoop.com/Ekramcalligraphy/7264