tgoop.com/EliasGebru/575
Last Update:
ከልብ የተሰጠ ሥጦታ በብር አይተመንም።
በቅርቡ የማላውቀው የቤት ስልክ ቁጥት ሞባይሌ ላይ ደወለ__ አነሳሁት፣
"ሄሎ"
"ሄሎ፣ ዶ/ር ኤልያስ ነህ?"
"አዎን ማን ልበል?"
"ከቃሊቲ እስር ቤት ነው የምደውልልህ!.."
"እሺ"
"... ግን የአርምሞ መጽሐፍ ደራሲው ዶ/ር ኤልያስ ነህ አይደል?"
በውስጤ ቃሊቲ ማረምያ ቤት ደሞ ለምን ፈለጉኝ እያልኩኝ፣ "አዎ እኔ ነኝ" አልኹት፤
"እግዚአብሔር ይመስገን፣ በጣም አክባሪክ ነኝ፣ በድምፅም ቢሆን ስላገኘሁ በጣም ደስ ብሎኛል!" ... ሲለኝ ደዋዩ መጽሐፌን አንብቦ እንደሆነ ገመትኩኝ።
"አመሰግናለሁ ወንድሜ፣ አንተንስ ማን ልበል?" ስል ጠየቅኩት፤
"ሙሉጌታ እባላለሁ፣ በቃሊቲ እስር ቤት ለአመታት ያቆየሁ ታራሚ ነኝ ፤ አርምሞ መጽሐፍህ ውስጤ ላይ ትልቅ ተስፋን ስላበራልኝ ነው ላመሰግንህ የደወልኩት... ያው ታራሚ ነኝ፣ ምንም ላንተ የማደርግልህ ነገር የለም... የገንዘብም አቅም የለኝም ግን ድሮ የለመድኳት የእጅ ጥበብ አለች፤ በሷ አንድ ብእር በእጆቼ ሰርቼልሃለሁ፣ በቅርቡ ይደርስሃል" አለኝ።
(ከዚያም ከመጽሐፉ ጋር የተያያዙ ብዙ ጨዋታዎችን ተጫወትን)
እውነት ለመናገር ስጋው እንጂ ነፍሱ ያልታሰረች አስተዋይ ሰው ነው። ያው የላከው መልእክተኛም ይሄንን የሚያምር ብእር ከደብዳቤ ጋር ቢሮ ለፀሐፊያችን አቀበላት። በህይወቴ ሰዎች ከሰጡኝ ትልቅ ስጦታዎች አንዱ ነው።
የሥጦታ ውዱ ከልብ የተሰጠ ነው።
(ደራሲ፣ ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ)
@EliasGebru
BY ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ ወጎች ግጥሞች እና ቁም ነገሮች
Share with your friend now:
tgoop.com/EliasGebru/575