tgoop.com/Enatachn_mareyam/16317
Last Update:
እንኳን ለሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።
#ጥር_18_ቅዱስ_ጊዮርጊስ_የአመት_ነው
#አጥንቱ_የተበተነበት_ደሙ_የፈሰሰበት
70 ነገስታት ያፈሩበት እለት ነው
ጥር 18 " ዝርወተ ዓጽሙ " ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት ይህቺ ዕለት ለሰማዕቱ #ዝርወተ_አጽሙ' ትባላለች በቁሙ 'አጥንቱ የተበተነበት' እንደ ማለት ነው
#ቅዱስ_ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው 70 ነገሥታትን ከነ ሠራዊታቸው ከማሳፈሩ ባሻገርም በርካታ (በመቶ ሺ የሚቆጠሩ) አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ በዚህ የተበሳጨ ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ ወታደሮቹም ቅዱሱን ቆራርጠው በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት ያለ ርሕራሔም አካሉን አሳረሩት ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት በአካባቢው ወደ ነበረው ትልቅ ተራራ ጫፍ (ደብረ ይድራስ) ወጥተውም በነፋስ በተኑት እነርሱ ይህንን ፈጽመው ዘወር ሲሉ ግን የቅዱሱ ዓጽም ባረፈባቸው ዛፎች ቅጠሎችና ድንጋዮች ሁሉ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕታት የሚል ጽሑፍ ተገኘ ስለዚህም ይሕቺ ዕለት ቅዱሱ አለቅነትን የተሾመባት ናት ማለት ነው ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸውና #በክርስቶስ እመኑ ብሎ አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው 70ው ነገሥታት ግን አፈሩ የሊቀ ሰማዕታት ቅ/ጊዮርጊስ በረከቱ ይደርብን 🙏🙏🙏
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ ፈጥኖ ደራሹ በመከራ ግዜ ፈጥኖ ይድረስልን
አጥንታችንን ለመፍጨት ደማችንን ለማፍሰስ የተነሱትን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያፍዝዝልን ሀገራችንን ሰላም ያርግልን
#መልካም__በዓል🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16317