tgoop.com/Enatachn_mareyam/16321
Create:
Last Update:
Last Update:
🕊 💖 🕊
እንኳን ለሰማዕቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል [ ለዝርወተ ዓጽሙ ] በሰላም አደረሳችሁ።
💖
ሥለ ርትዕት ሃይማኖት ነብስህን የለወጥካት
የተዋህዶ መልካም ሽታ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ይድረስህ ሰላምታ፡፡
🕊 💖 🕊
❝ የልዳው ጊዮርጊስ ሆይ ፦ ለአንተ ሰላምታ ይገባሃል፡፡ የተወደደው የልጅዋ የኢየሱስ ክርስቶስና የድንግል ማርያም ዕውነተኛ ምስክር ሆይ ፦ ሰላምታ ይገባሃል፡፡ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ልዩ ልዩ ሥቃዮችን የታገሥህ ጊዮርጊስ ሆይ ፦ ሰላምታ ይገባሃል፡፡
ሥጋህ ለአራት ለስድስት ክፍል የተከፋፈለው ጊዮርጊስ ሆይ ፦ ናርዶስ ከሚባል የሽቱ አበባ ይልቅ መዓዛህ ይጥመኛልና ሰላምታ ይገባሃል፡፡ ❞
[ መልክአ ጊዮርጊስ ]
የሰማዕቱን ፍቅር በልቦናችን ያሳድርብን፡፡ በምልጃውና በቃል ኪዳኑ ይማረን፡፡
🕊 💖 🕊
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/16321