tgoop.com/Enatachn_mareyam/3510
Last Update:
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን "ለመስቀሉ እሮጣለሁ" በሚል መሪ ቃል ነገ የሚካሄደው ሩጫ ከሚመለከተው አካል ሕጋዊ እውቅና ያላገኘ ነው ቢልም አስተባባሪ ኮሚቴው መርሐግብሩን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል !!!
---------------------------------------------------
በደብረ ዕንቁ ቅድስት ልደታ ለማርያም ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እና በመስቀል ፕሮጀክት አሠሪ ኮሚቴ የተዘጋጀውንና "ለመስቀሉ እሮጣለሁ" በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል የተባለው ሩጫ ከሚመለከተው አካል ሕጋዊ እውቅና ያላገኘ ነው ብሏል የአዲስ አበባ ፖሊስ፡፡
እንደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘገባ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ነገ ሚያዚያ 2 ቀን 2014 ዓ.ም "ለመስቀሉ እሮጣለሁ" በሚል ምክንያት በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሚካሄድ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል ሲል ከስሷል።
የሩጫ ውድድሩ ማሟላት የሚገባውን ሕጋዊ እውቅና ከሚመለከተው አካል አላገኘም ማለቱ ነው የተገለፀው፡፡
የመስቀል ፕሮጀክት አዘጋጅ ኮሚቴውና የሩጫ አስተባባሪ ኮሚቴው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሩጫው እንደሚካሄድ ገልጾ መላው ኦርቶዶክሳውያን ለዚሁ የሩጫ መርሐግብር እንዲዘጋጁ በማለት የአለባበስ ሥነ ሥርዓትን በተመለከተም ጭምር መግለጫ ሰጥቷል።
ፖሊስ በድንገት የጎዳና ላይ ሩጫ ለማካሄድ የሚደረግ እንቅስቃሴ በከተማው የፀጥታ ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚፈጥር መሆኑን ህብረተሰቡም ሆነ ሩጫውን አዘጋጅተናል የሚሉ አካላት መገንዘብ ይገባቸዋል ቢልም የሩጫው አስተባባሪዎች አስፈላጊውን ሕጋዊ መንገድ መሄዳቸውን ባወጡት መግለጫ ገልፀዋል ፡፡
[ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/3510