tgoop.com/Enatachn_mareyam/6262
Last Update:
#ከቤተ_ክርስቲያን የሚበልጥ ብርቱ (ጠንካራ) ምንም የለም። ይህችውም ከሰማይ ከፍ ያለች ከምድርም ይልቅ የሰፋች ናት። አታረጅም ነገር ግን ዘወትር ታበራለች። #ቤተ_ክርስቲያን በዘመናት ሁሉ ትሰፋለች። መታሰቢያዋም የሚጠፋ (የሚሞት) አይደለም። #ቤተ_ክርስቲያን በስንቶች ውጊያ ተደርጎባት ነበር? #አልተሸነፈችም እንጂ። የተዋጓት አላውያን፣ የጦር መሪዎች፣ ነገሥታቱስ ምን ያህል ናቸው?
የተማሩና ኃይልን የተሞሉ ጎበዞች ሐዲሲቷን #ቤተ_ክርስቲያን በብዙ ጎዳናዎች ተዋግተዋት ነበር። ሊነቅሏት ግን አልቻሉም። ነገር ግን እርሷን የተዋጉ ጥቂቶች ለዝምታና ቶሎም ለመረሳት ተላልፈው ተሰጥተዋል። የወጓት #ቤተ_ክርስቲያን ግን ከሰማይ በላይ ከፍ ከፍ ብላለች። ቤተ ክርስቲያንን ድል ከማድረግስ ፀሐይን #ማጥፋት (ማጨለም) ይቀላል። #ሰው_ሆይ! ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ኃያል ምንም የለም። ከሰው ብትጣላ ወይ ታሸንፋለህ አልያም ትሸነፋለህ። #ቤተ_ክርቲያንን ግን ብትጣላ፣ ታሸነፍ ዘንድ የሚቻልህ አይደለም። እግዚአብሔር ከሁሉ ይልቅ ኃያል ነውና። #እግዚአብሔር መስርቷታል፣ እንግዲህ ማን #ሊነቀንቃት_ይችላል? "
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#_ሰናይ_ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/6262