Telegram Web
"እንደ ሰውነታችን ዕለት ዕለት እንበድላለን፡፡ በጥምቀት ያገኘነውን ልጅነት እናቆሽሸዋለን፡፡ አዲሱን ሰውነታችን ብሉይ እናደርገዋለን፡፡ ነገር ግን ይህን ዕለት ዕለት ማደስ ይቻላል፡፡ አንድ ቤት እያረጀ ቢሄድ እንደ አዲስ እንሠሯለን፡፡ ክዳኑን፣ ቀለሙን፣ ምንጣፉን እድሳት እናደርግለታለን፡፡ እኛም በኃጢአት ባረጀው ሰውነታችን ላይ እንዲህ ልናደርግ ይገባናል በንስሐ፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


#___ሰናይ____ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
👍117
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

[  † እንኩዋን ለአባታችን "አባ ብሶይ ዼጥሮስ" እና "ቅዱስ ዕብሎይ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †  ]

[   †   🕊  አክርጵዮስ   🕊  †   ]

በዚች ቀን የእስክንድሪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት አክርጵዮስ አረፈ። እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አስረኛ ነው። ይህም አባት እግዚአብሄርን የሚፈራ ንፁህ ቅዱስ ነው ።

በእስክንድርያ አገርም ቄስ ሆኖ የሚያገለግል ነበር ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ከላድያኖስ በአረፈ ጊዜ የእስክንድር አገር ህዝብና ኤጲስቆጶሳቱ መረጡት በወንጌላዊው ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።

ከዚህም በኃላ እንደ ሀዋሪያት መልካም ጉዞን ተጓዘ የእግዚአብሄርን ሀይማኖት ህይወት የሆነ ህጉንም እያስተማረ ቅዱሳት መፅህፍትንም እያነበበላቸውና እያስተማራቸው መንጋዎቹን ይጠብቃቸው ነበር ሁል ጊዜም ይመለከታቸዋል አንድ የብር አላድን ወይም አንድ የወርቅ ዲናርን ጥሪት አላኖረም ከእለት ምግቡ ከቁርና ከሀሩር ስጋውን ከሚሸፈንበት ልብስ በቀር ምንም አላከማቸም።

በዚህም ተጋድሎ አስራ ሁለት አመት ኑሮ ጌታችንንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

[ †  🕊  ቅዱስ ዕብሎይ  🕊  † ]

አባ ዕብሎይ በቀደመ ሕይወቱ ለ፵ [ 40 ] ዓመታት በኀጢአት የኖረ: እግዚአብሔር ለንስሃ ሲጠራው "እሺ" ብሎ : ለ፵ [ 40 ] ዓመታት በንስሃ ሕይወት ተመላልሶ በበርሃ የተጋደለ: እንባው እንደጐርፍ ይፈስ የነበረ: አጋንንትንም ድል የነሳና ለፍሬ: ለትሩፋት የበቃ ቅዱስ አባት ነው:: እግዚአብሔርም ብዙ ቃል ኪዳን ገብቶለታል::

" ባርያ ሆኖ ያለ ኀጢአት: ጌታ ሆኖ ያለ ምሕረት የለምና ይቅር በለን !! " [የአባ ዕብሎይ የንስሃ ጸሎት]

[ † 🕊 አባ ብሶይ [ዼጥሮስ] 🕊 † ]

ብሶይ [ቢሾይ] በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተለመደ
የቅዱሳን ስም ነው:: በተለይ በምድረ ግብ በዚህ ስም ሰማዕታትም : ጻድቃንም ተጠርተውበታል:: ከእነዚህ ቅዱሳን [ከገዳማውያኑ] አንዱ የሆነው አባ ብሶይም [አንዳንዴ አባ ዼጥሮስም ይባላል] የዘመነ ጻድቃን ፍሬ ነው::

ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን ቤት ናት:: ያ ማለት ራሳቸውን ለክርስቶስ የለዩ ሰዎች ይኖሩባታል:: እነዚህ ሰዎች ከተለያየ ጐዳና እና ማንነት ሊመጡ ይችላሉ:: ቢያንስ ግን በንስሃ የታጠቡ መሆናቸው ወደ ተቀደሰው አንድነት እንዲገቡ ትልቅ መሠረት ይሆናቸዋል::

ቅዱሳንም አንዳንዶቹ ከእናታቸው ማኅጸን ሲመረጡ : ሌሎቹ ደግሞ ከኃጢአት ሕይወት የተመለሱ ሆነው ይታያሉ:: ደስ የሚለው ደግሞ በንስሃ ከታጠቡ በሁዋላ በፍጹም ልባቸው በመጋደላቸው እነሆ በሰማያዊ አክሊል ተከልለዋል::

አባ ብሶይ ዼጥሮስም ከኃጢአት ተመልሰው ለቅድስና ከበቁ ቀደምት አበው አንዱ ነው:: ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ምድረ ግብጽ የታወቀ ሽፍታ : ዝሙተኛና ክፋቱ የተገለጠ ሰው ነበር:: ለብዙ ዘመናት በእንዲህ ካለ ግብሩ መላቀቅ ባይችል እግዚአብሔር ጥሪውን ላከለት::

የአምላካችን የጥሪ መንገዱ ብዙ ነውና ለእርሱ ደዌን ላከለት:: መቼም ወደድንም ጠላንም በሽታ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ ጥሩ ፈሊጥ [አጋጣሚ] ነው:: ዛሬም ቢሆን ዘለን : ዘለን ስንሰበርና የሐኪም መፍትሔ ሲጠፋ የግዳችን ወደ እግዚአብሔር ቤት [ወደ ጸበሉ] እንቀርባለንና:: አምላካችን ስለዚህ ጥበቡ ይክበር ይመስገን::

ቅዱስ አባት ብሶይም በሽፍትነትና በኃጢአት ኑሮ ሳለ ለሞት የሚያበቃ ደዌ ደርሶበት የአልጋ ቁራኛ ሆነ:: ኃይሉም ደከመ:: በእንዲህ እያለም በራዕዩ ያየው ነገር ፍጹም አስደነገጠው::

መላእክት ነፍሱን ወስደው መካነ ኩነኔን ካሳዩት በሁዋላ አለቀሰ::

ይልቁን ሌቦችና ዝሙተኞችን ከ፬ [4] ሲቆራርጣቸው ስላየ ፈጽሞ አዘነ : ተጸጸተ:: ፈጣሪውንም ዕድሜ ለንስሃ እንዲሰጠው ተማጸነ:: ጌታንም "አምላኬ ሆይ! ከበሽታየ ብታድነኝ : ዳግመኛ አልበድልህም:: ዓለምን ሁሉም ንቄ አገለግልሃለሁ" ሲል ተማጸነው::

እግዚአብሔርም ሰምቶት ፈጥኖ ፈወሰው:: አባ ብሶይም እንደ ቃሉ በፍጹም ልቡ ንስሃ ገብቶ መነነ:: በገዳመ አስቄጥስ [ግብጽ] ለ፴፰ [38] ዓመታት ሲኖር የላመ የጣመ በልቶ : ከሞቀ መኝታ ተኝቶ አያውቅም::

ሰውነቱን ይቀጣት ዘንድም እስከ ፴ [30] ቀን ያለ እህል ውሃ ይጾም ነበር:: በዘመኑ ሁሉም የሴት መልክን አላየም:: ንስሃን የሚወድ ጌታም ጸጋውን አብዝቶለት ብዙ ድርሳናትን ጽፏል:: የሚገርመው ደግሞ ከትህትናውና ቅድስናው የተነሳ የእያንዳንዱ ሰው ኃጢአት ተገልጦ ይታየው ነበር::

ቅዱሱ አባታችን ብሶይ ዼጥሮስ በንስሃና በቅድስና ሕይወት እንዲህ ተመላልሶ በዚህች ቀን ዐርፎ በገዳሙ ተቀብሯል:: የድካሙን ዋጋም አድልዎ ከሌለበት : ከእውነተኛው ፈራጅ ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀብሏል::

አምላከ ቅዱሳን ዕድሜ ለንስሃ : ዘመን ለፍስሐ
አይንሳን:: ከክብረ ቅዱሳንም ያካፍለን . . . አሜን !!

[  † የካቲት ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
፪. ቅዱስ አባ ብሶይ ጻድቅ
፫. አባ አክርዽዮስ
፬. ፵፱ "49" አረጋውያን ሰማዕታት [ፍልሠታቸው]
፭. ቅዱስ አሞኒና ሚስቱ ቅድስት ሙስያ [የታላቁ ዕብሎይ ወላጆች]
፮. አባ ኖብ ጻድቅ : መነሳንሱ ዘወርቅ

[   †  ወርሐዊ በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
፫. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
፬. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
፭. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ

አምላክ በበረከታቸው ይባርከን::

" መቶ በግ ያለው : ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ 'የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።" [ሉቃ.፲፭፥፫-፯] (15:3-7)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
2
🥰3
#አልጠቅምም__አትበል"

ስለ ሌሎች መዳን ከማይጨነቅ ክርስቲያን በላይ ሰነፍ ሰው የለም፡፡
#ወዳጄ “እኔ ድኻ ነኝና ይህን ማድረግ አልችልም” የምትል አትኹን፤ ባለ ኹለት #ዲናሯ_ሴት ትወቅስሃለችና፡፡ ዳግመኛም “ወርቅም ብርም የለኝም” ብሎ የተናገረ #ጴጥሮስ ይወቅሰሃልና፡፡

#ምናምንቴ_ነኝ አትበል፤ እንዲህ ስትል ምናምንቴዎቹ #ሐዋርያት እንዳይሰሙህ! "እኔ በሽተኛ ነኝ" አትበል፤ በሽተኛው #ጢሞቲዎስ ይታዘብሃልና፡፡ ፈጽመህ “እኔ ሌሎች ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ማምጣት አይሆንልኝም” አትበል፡፡ በእውነት ክርስቲያን ከኾንክ ይህን ከማድረግ ይልቅ አለማድረጉ ይከብዳልና፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ እንድትኾን አድርጎ ፈጥሮሃልና ተፈጥሮህን መካድ አይቻልህም፡፡ #ክርስቲያን በጨለማ ውስጥ ለሚኖሩ ወንድሞቹ ብርሃኑን ከሚከለክል ይልቅ ፀሐይ ብርሃኗን ብትከለክል ይቀላልና ስለዚህ አልጠቅምም አትበል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#__ሰናይ__ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
8👍3👏3😢1
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

[  † እንኩዋን ለእናታችን "ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት" እና "ቅዱስ አቡሊዲስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †  ]


[ †  🕊  ቅድስት ማርያም  🕊  † ]

ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለን በስምዖን ቤት የመድኃኔ ዓለምን እግር በእንባዋ አጥባለች:: በፀጉሯም አብሳ የ300 ብር ሽቱ ቀብታዋለች:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የቀደመ ኀጢአቷን ይቅር ብሎ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ደምሯታል:: [ሉቃ.፯፥፴፮-፶] (7:36-50)

+ ስለዚህች ቅድስት ሙሉ ታሪክ :-

፩. ትርጉዋሜ ወንጌልን
፪. ተአምረ ኢየሱስን
፫. ስንክሳርን እና
፬. መጽሐፈ ግንዘትን በማንበብ ማግኘት ይቻላል::

እንት ዕፍረት [ባለ ሽቱዋ ማለት ነው] ማርያም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን [በዘመነ ስብከቱ] የነበረችና ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ሴት ነበረች:: ግን መልክ የመልካም ነገሮች ምንጭ ሲሆን አይታይም::

በመልካቸው ማማር የጠፉና ያጠፉ ብዙ ሴቶችን ዓለማችን አስተናግዳለች:: ከክሊዎፓትራ እስከ ዘመናችን "ሞዴል" ነን ባዮች : እግዚአብሔር የሰጣቸውን ጸጋ የሰይጣን መደሰቻ : የገሃነም መንገድ አድርገውት ማየት [መስማት] እጅግ ያሳዝናል::

በአንጻሩ ደግሞ ብዙዎችን ያስደመመ መልካቸውን ንቀው : ሰማያዊ ሙሽርነትን የመረጡትን ቅዱሳቱን:- አርሴማን : ቴክላን : ጤቅላን : መሪናን : ጣጡስን : ሔራኒን : ኢራኒን : አትናስያን : ሶፍያን : ኢላርያን . . . ስናስብ ደስ ይለናል:: ዛሬም ጌታ በሚያውቀው ብዙ እናቶቻችን [እህቶቻችንም] ተመሳሳዩን በጐ ጐዳና መርጠው እየተጉዋዙ መሆኑን እናውቃለን::

ቅድስት ማርያምም ከፈጣሪዋ በተሰጣት ቁንጅና ክፋትን ትሠራ ዘንድ ሰይጣን ሲያገብራት "እሺ" ብላ የእሱ ወጥመድ ልትሆን ተራመደች:: ለዘመናትም ዓይነ-ዘማ : ልበ-ስስ የሆኑ ወንዶችን ወደ ኃጢአት ጐዳና ማረከች::

ለመልኩዋ ከነበራች ስስት የተነሳም ቶሎ ቶሎ ራሷን በመጽሔት [መስታውት ማለት ነው] ትመለከት ነበር:: መቼም አምላካችን ለሁሉም የመዳን ቀን ጥሪ አለውና [የሚያስተውለው ቢገኝ] ለማርያም ጥሪውን ላከላት:: ጥሪው ግን በስብከት : በመዝሙር : በመጽሐፍ . . . አልነበረም::

እንዳስለመደች ውበቷን ለመመልከት መስታውት ፊት ቆማ የራሷን ጸጉር : ግንባር : ዐይን : አፍንጫ : ጥርስ . . . እየተመለከተች ተደመመች:: ወዲያው ግን ይህ አካል አፈር እንደሚበላው የሚያስብ ልቡና መንፈስ ቅዱስ አምጥቶባት በጣም አዘነች:: የመኖር ተስፋዋ እንዳይቆረጥ ደግሞ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ዜና ሰማች::

መወሰን ነበረባትና ከሞት ወደ ሕይወት : ከጨለማ ወደ ብርሃን ልትሔድ ቆረጠች:: በአምላኩዋ ፊት የሚቀርቡም 3 ስጦታዎችን አዘጋጀች:: ሰይጣን ሊያጣት አልፈለገምና ወደ ክርስቶስ እንዳትደርስስ ብዙ መሰናክልን ፈጠረባት:: ግን ውሳኔዋ የእውነት ነበርና እያሳፈረችው ወደ አምላኩዋ ገሰገሰች::

የስምዖን ዘለምጽ በረኞችም ሊያስቀሰሯት አልተቻላቸውም:: ወደ ውስጥ ዘልቃ የያዘችውን ሁሉ ለመድኃኒታችን ሰዋች::

፩. ከውስጧ እንባዋን:
፪. ከአካሏ ጸጉሯን:
፫. ከንብረቷ ውድ የሆነውን ሽቱ አቀረበች::

ብዙ ወዳለችና ብዙ ኃጢአቷ ተሠርዮ ቅድስት እናታችን ሆነች:: ብዙ አዝማናትን ከሐዋርያት ጋር አገልግላም በዚህች ቀን ዐርፋለች::

" ቅዱስ አቡሊዲስ መምህረ ኩሉ ዓለም "

+ የዓለም ሁሉ መምህር:

¤ ባለ ብዙ ድርሳንና ተግሣጽ:
¤ የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ:
¤ ፴፰ [38] ሕግጋትን የደነገገ:
¤ ስለ ቀናች እምነት የተጋደለ:
¤ መራራ ሞትን በደስታ የተቀበለ:
¤ የቀደመችዋ ሮም ሊቀ ዻዻሳት የነበረና:
¤ ሐዋርያትን የመሰለ አባት ነው::

+በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ያበራው ይሀን ኮከብ ካቶሊካውያን ክደውታል:: እነርሱ "አቡሊዲስ የሚባል ዻዻስ አልነበረም" ቢሉም ምክንያታቸው ግን ከሰይጣን ነው:: ሃይማኖታቸውን ከመለወጣቸው 250 ዓመታት በፊት ስለተናገረባቸውና አንድ ባሕርይን ስላስተማረ መሆኑን ዓለም ያውቃል::

አባታችን ቅዱስ አቡሊዲስ የተገደለ የካቲት ፭ [5] ሲሆን የካቲት ፮ [6] ሥጋው የተገኘበት ነው::

አምላከ ቅዱሳን ከቅድስት ማርያም ንስሃዋን : ከአባ አቡሊዲስ ምሥጢረ ቅድስናውን ያድለን::

[  † የካቲት ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት
፪. የዓለም ኁሉ መምሕር ቅዱስ አቡሊዲስ [ብዙ መንፈሳዊ ድርሳናትን የደረሰ ሊቀ ዻዻስና ሰማዕት]
፫. ቅዱሳን አቡቂርና ዮሐንስ [ሰማዕታት]
፬. ቅድስት አትናስያና ፫ [3] ቱ ሰማዕታት ልጆቿ [ቴዎድራ : ቴዎፍናና ቴዎዶክስያ]

[    † ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
፪. አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
፫. አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
፬. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
፭. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፮. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
፯. ቅድስት ሰሎሜ
፰. አባ አርከ ሥሉስ
፱. አባ ጽጌ ድንግል
፲. ቅድስት አርሴማ ድንግል

ከበረከተ ቅዱሳን ይክፈለን::

" . . . አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም:: እርሷ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች:: ስለዚህ እልሃለሁ : እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአቷ ተሰርዮላታል:: ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል:: እርስዋንም:- 'ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል' አላት:: ከእርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩት በልባቸው:- 'ኃጢአትን እንኩዋ የሚያስተሰርይ ይህ ማነው' ይሉ ጀመር:: ሴቲቱንም:- 'እምነትሽ አድኖሻል: በሰላም ሒጂ' አላት::" [ሉቃ.፯፥፳፮] (7:46)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
👍21
Audio
2🥰2
5🥰1
#_______ወዳጆቼ_______???

#የክርስቶስን አካል ልታከብሩት ትወዳላችሁን? መልሳችሁ አዎ ከሆነ #ራቁቱን ሆኖ እያያችሁት አትለፉት፣ በየመንገዱ ራቁቱን ሆኖ በብርድ እየተሰቃየ አለና፤ #ራቁቱን ሆኖ በብርድ እየተሰቃየ አልፋችሁት መጥታችሁ እዚህ #ከቤተ_መቅደስ በብርና በወርቅ ላስጊጥህ አትበሉት፡፡ "ይህ ሥጋዬ ነው" ብሎ የተናገረው #ክርስቶስ ራሱ "ተርቤ አይታችሁኝ አላበላችሁኝም" ያለው እንዲሁም "ከእነዚህ ከታናናሾች ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችት ለእኔ አደረጋችሁት" ያለውም ያው እርሱ ራሱ ነውና፡፡ #ወንድምህ_በረሃብ እየተሰቃየና እየሞተ ቅዱስ ደሙ የሚቀዳበት ጽዋ በወርቅ ቢለበጥና ቢንቆጠቆጥ ጥቅሙ ምን ላይ ነው? አስቀድመህ የወንድምህን ረሃብ በማጥገብና ጥሙን በማርካት ጀመር፤ ከዚያ በኋላ በተረፈህ ገንዘብ ቤተ መቅደሱንና ንዋያተ ቅድሳትን እንዲህ ማስጌጥ ትችላለህ፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#___ሰናይ____ቀን 🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
7🙏3❤‍🔥1😢1
🕊

[  † እንኳን ለጻድቁ አባታችን አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

[  † 🕊 አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ 🕊 †  ]

† ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆኑ በበርሃ ሰው ሳያዩ ለ፸ [70] ዓመታት በቅድስና ኑረዋል:: በጊዜውም እግዚአብሔር አባ አብዱልማዎስን ወደ አባ ዕብሎይ ልኳቸው ነበር:: ሁለቱ ተገናኝተው አብረው ለ፫ [3] ቀናት ሲቆዩ ቅዱስ መልአክ እየተገለጸ አጽናንቷቸዋል:: ከሥውራን ማኅበርም ተቀላቅለው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለዋል::

† አባ ዕብሎይ ሲያርፍ አንበሶች እያገዟቸው ቀብረዋቸዋል:: እርሳቸውም "እኔን የሚቀብረኝ ስጠኝ" ብለው ጸልየው ነበርና ፫ [3] ገዳማውያን መጥተውላቸዋል:: የካቲት ፭ [5] ቀን አባ ዕብሎይን ገንዘው ቀብረው በ ፫ [3] ኛው ቀን አርፈዋል::

† የጻድቁ ክብር ይደርብን።

🕊 † የካቲት ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

1.አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ
2.አባ ቴዎድሮስ ሊቀ ጳጳሳት
3.አባ እለ እስክንድሮስ ሊቀ ጳጳሳት
4.ቅዱስ አባዲር

🕊 † ወርኀዊ በዓላት  🕊 ]

፩. ሥሉስ ቅዱስ [አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ]
፪. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
፫. አባ ሲኖዳ [የባሕታውያን አለቃ]
፬. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
፭. አባ ባውላ ገዳማዊ
፮. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
፯. ቅዱስ አግናጥዮስ

† የአብ በረከት: የወልድ ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስ አንድነት: የድንግል ማርያም ምልጃ: የቅዱሳኑ ፀጋ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::

"ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዷችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ::" † [ማቴ. ፭፥፲]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2👍2
5
#ሥላሴ_ኃይሌ መመኪያዬ ነው
በሥላሴ ስም ጠላቴ ሰይጣንን እክድዋለሁ
እግዚአብሔር ከዓለም በፊት በመንግሥቱ ነበረ እግዚአብሔር #በሦስትነቱ እግዚአብሔር በመለኮቱ አለ ከጎኅና ከጽባሕ ከብርሃናት መመላለስም በፊት እግዚአብሔር በመንግስቱ ነበረ፡፡

{ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ}

#ሥላሴ_ማለት ሠለሰ ሦስት አደረገ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተወሰደ ሲሆን ትርጓሜውም #ሦስትነት ማለት ነው፡፡ #ሥሉስ_ቅዱስ ማለት ደግሞ ልዩ ሦስት ማለት ነው፡፡ #አብ ፍጹም መልክእ ፍጹም ገጽ ፍጹም አካል አለው፣# ወልድም ፍጹም መልክእ ፍጹም ገጽ ፍጹም አካል አለው፣ #መንፈስቅዱስም ፍጹም መልክእ ፍጹም ገጽ ፍጹም አካል አለው።
#የእግዚአብሔር የአንድነትና የሦስትነት ባለቤት ስለሆነ #ሥላሴ ይባላል ።

#የአብረሃሙ_ስላሴ ከክፉ ይጠብቀን
ሀሳብ ምኞታችን ተሳክቶ በደስታ እንድንኖር ይርዳን አሜን

#መልካም_ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
13❤‍🔥2🙏2
🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

[  የካቲት ፰ [ 8 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

[  † 🕊  በዓለ ስምዖን  🕊 †  ]

ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን ጌታ በተወለደ በ፵ [40] ቀኑ ራሱ የሠራውን ሕግ ይፈፅም ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቷል:: እንደ ሥርዓቱም እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምና አገልጋዩዋ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ የርግብ ግልገሎችና ዋኖስ አቅርበዋል::

ለ፪፻፹፬ [284] ዓመታት የአዳኙን [የመሢሁን] መምጣት ይጠብቅ የነበረው አረጋዊው ስምዖን በዚህች ዕለት ስላየውና ስለታቀፈው ዕለቱ በዓለ ስምዖን ይባላል:: [ሉቃ.፪፥፳፪] (2:22) ከዘጠኙ የጌታ ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው::

ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

ከዓለም ፍጥረት በ፭ ሺህ ፪ መቶ [5,200] ዓመታት [ማለትም ከክርስቶስ ልደት ፫፻ [300] ዓመታት በፊት] በጥሊሞስ የሚሉት ንጉሥ በግሪክ ነገሠ::

በጊዜውም በኃይለኝነቱ ሁሉን አስገብሮት ነበርና "ዓለሙን እንደ ሰም አቅልጬ: እንደ ገል ቀጥቅጬ ገዛሁት:: ምን የቀረኝ ነገር አለ?" ሲል ተናገረ:: ባሮቹም "አንድ ነገር ቀርቶሃል:: በምድረ እሥራኤል ጥበብን የተሞሉ ፵፮ [46] መጻሕፍት አሉ:: እነርሱን አስተርጉም" አሉት::

ያን ጊዜ እሥራኤላውያንን አስገብሯቸው ነበርና ፵፮ [46] ቱን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከ፸፪ [72] ምሑራን [ተርጉዋሚዎች] ጋር እንዲያመጡለት አዛዦቹን ላከ:: እነርሱም ፵፮ [46] ቱን መጻሕፍተ ብሉይ ኪዳን ከ፸፪ [72] ምሑራን ጋር አመጡለት::

አይሁድ ክፋተኞች መሆናቸውን ሰምቷልና ፴፮ [36] ድንኩዋን አዘጋጅቶ: ጥንድ ጥንድ ሆነው እንዲሠሩ: ሲተረጉሙ እንዳይመካከሩ ፴፮ [36] ጠባቂዎችን ሾመባቸው:: ይህ ነገር ለጊዜው ከንጉሡ ቢመስልም ጥበቡ ግን ከእግዚአብሔር ነው::

ምንያቱም በጊዜ ሒደት መጻሕፍተ ብሉያት በአደጋ እንደሚጠፉ ያውቃልና ሳይበረዙ ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ለእኛ እንዲደርሱ ነው:: ስለዚህም ከክርስቶስ ልደት ፪፻፹፬ [284] ዓመት በፊት ፵፮ [46] ቱም ሁሉም መጻሕፍት [ብሉያት] ከእብራይስጥ ወደ ጽርዕ ልሳን በ፸ [70] ው ሊቃናት አማካኝነት ተተረጐሙ:: [በእርግጥ ከዚያ አስቀድሞ መጻሕፍት [ብሉያት] ወደ ሃገራችን መምጣቸውና ወደ ግዕዝ ልሳን መተርጐማቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው]

ወደ ዋናው ጉዳያችን ስንመለስ ከ፸ [70] ው ሊቃናት መካከል በእድሜው አረጋዊ የሆነ [እንደ ትውፊቱ ከሆነ ፪፻፲፮ [216] ዓመት የሆነው] ስምዖን የሚሉት ምሑረ ኦሪት ነበር:: በፈቃደ እግዚአብሔር ለእርሱ መጽሐፈ ትንቢተ ኢሳይያስ ደርሶት እየተረጐመ ምዕራፍ ፯ [7] ላይ ደረሰ::

ቁጥር ፯ [ 7 ] ላይ ሲደርስ ግን "ናሁ ድንግል ትጸንስ: ወትወልድ ወልደ" የሚል አይቶ "አሁን እንኳን የአሕዛብ ንጉሥ የእሥራኤልስ ቢሆን ድንግል በድንግልና ጸንሳ ትወልዳለች ብለው እንዴት ያምነኛል!" ሲል አሰበ:: "በዚያውስ ላይ ኢሳይያስ በምናሴ የተገደለው ስለዚህ አይደል!" ብሎ ቃሉን ሊለውጠው ወሰነ::

አመሻሽ ላይም 'ድንግል' የሚለውን 'ወለት-ሴት ልጅ' ብሎ ቀየረው:: እርሱ ሲያንቀላፋ ቅዱስ መልአክ ወርዶ 'ድንግል' ብሎ አስተካከለው:: ከእንቅልፉ ሲነቃ ግራ ተጋብቶ እንደ ገና ፍቆ ቀየረው::

አሁንም መልአኩ 'ድንግል' ሲል ቀየረበት:: ፫ [3] ጊዜ እንዲህ ከሆነ በኋላ ግን መልአኩ ተገልጦ ገሰጸው:: በዚያውም ላይ "ይህችን ድንግልና መሲሑን ልጇን ሳታየውና ሳትታቀፈው ሞትን አታይም" ብሎት ተሰወረው:: አረጋዊ ስምዖን ከዚያች ዕለት በኋላ የመድኅን ክርስቶስን መምጣት ሲጠብቅ ለ፪፻፹፬ [284] ዓመታት የአልጋ ቁራኛ ሁኖ ኖረ:: አካሉም አለቀ::

ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው በሆነበት በዚያ ሰሞን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ::

ሕግን የሠራ ጌታ እርሱ 'ፈጻሜ ሕግ' ይባል ዘንድ የርግብ ግልገሎችን [ዋኖሶችን] ይዘው በተወለደ በ ፵ [40] ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ አስገቡት:: በዚህች ቀንም ቅዱስ መልአክ መጥቶ ቅዱስ ስምዖንን ከአልጋው ቀሰቀሰው:: ተስፋ የሚያደርገው አዳኙ [መሲሑ] እንደ መጣም ነገረው::

ይህን ጊዜ አረጋዊው አካሉ ታድሶ እንደ ፪ [30] ዓመት ወጣት እመር ብሎ ከአልጋው ተነሳ:: እንደ በቅሎ እየሠገረም ወደ መቅደስ ወጣ:: በዚያ መሲሑን [ፈጣሪውን] ሲመለከት እንደ እንቦሳ ዘለለ:: ቀረብ ብሎም ሕጻን ጌታን ከድንግል እናቱ እጅ ተቀበለው::

ከደስታው ብዛት የተነሳም "ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ: በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው" ሲል ጸለየ:: ትንቢትንም ተናገረ:: በዚያችው ዕለትም ዐርፎ ተቀበረ::

[   †  🕊  ሐና ነቢይት  🕊  †  ]

ዳግመኛ በዚህች ቀን አረጋዊቷን ነቢይት ቅድስት ሐናን እናስባለን:: ይህች ቅድስት ትውልዷ ከነገደ አሴር ሲሆን አባቷ ፋኑኤል ይባላል:: በትውፊት ትምሕርት ሐና የተዳረችው በልጅነቷ [በ፲፪ [12] /፲፭ [15] / ዓመቷ] ነው:: ለ፯ [7] ዓመታት ከልጅነት ባሏ ጋር ኖራ ዕድሜዋ ፲፱ [19] ፳፪ [22] ሲደርስ ሞተባት::

እንደ እሥራኤል ልማድ ሌላ እንድታገባ ብትጠየቅም 'እንቢ' ብላ መበለት ሆነች:: ራሷንም ለእግዚአብሔር አሳልፋ ሰጠች:: በቤተ መቅደስም ለ፹፬ [84] ዓመታት ለፈጣሪዋ ተገዛች:: ፈጽማ ትጸልይና ትጾም ነበርና በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ውጪውን አልተመለከተችም::

ለእርሷ ፻፫ [103] ፻፮ [106] ዓመት ሲሆን መድኃኒታችን ተወለደ:: በዚህች ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ተመልክታም ጌታን ባረከች:: ደስ እያላትም ትንቢትን ተናገረች:: ወደ ቤቷ ገብታም ነፍሷን ሰጠች:: [ሉቃ.፪፥፴፮-፴፰] [2:36-38)

ቸሩ መድኃኒታችን ተርፎ ከሚቀረው ዘመን ዕድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍሥሐ አይንሳን:: ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::

[  † የካቲት ፰ [ 8 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ስምዖን አረጋዊ
፪. ቅድስት ሐና ነቢይት [የፋኑኤል ልጅ]
፫. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ እግዝእት
፬. አባ ኤልያስ ገዳማዊ [በትህትና ያጌጠ ቅዱስ ሰው]

[  †  ወርሐዊ በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
፪. ኪሩቤል [ አርባዕቱ እንስሳ ]
፫. አባ ብሶይ [ ቢሾይ ]
፬. አቡነ ኪሮስ
፭. አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
፮. ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ [ ከ፲፪ [12]ቱ ሐዋርያት ]

አረጋዊ ስምዖንን ከድካም አልጋ ያነሳ አምላከ ቅዱሳን እኛንም ድካመ ነፍስን ከሚያመጣ የበደል ምኝታ በቸርነቱ ያንሳን::

" እንደ ሕጉ ልማድ ያደርጉለት ዘንድ ሕጻኑን ጌታ ኢየሱስን በአስገቡት ጊዜ እርሱ ደግሞ ተቀብሎ አቀፈው:: እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ :- 'ጌታ ሆይ! አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ:: ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና:: ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን: ለሕዝብሕም ለእስራኤል ክብር ነው:: 'ዮሴፍና እናቱም ስለ እርሱ በተባለው ነገር ይደነቁ ነበር::" [ሉቃ.፪፥፳፯] (2:27)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
3👍1
2025/07/09 22:01:55
Back to Top
HTML Embed Code: