†
🕊 እ ን ኳ ን አ ደ ረ ሳ ች ሁ 🕊
▬🌼▬▬▬ 🌼 ▬▬▬🌼▬
❝ ሚ ሠናይ ከመ ጼና ጽጌ ልሑይ ፣
በኲሉ ጊዜ ምሒረ ነዳይ ፣
በእንተ ኪዳንኪ ድንግል ለበላዔ ሰብእ ጊጉይ ፣
ሶበ ዐብየ እምኀጢአቱ ክበደ መድሎቱ ለማይ ፣
ለተአምርኪ በሰማይ ተገብረ ግናይ ❞
❝ አንቲ ውእቱ ለእግዚአብሔር አትሮኑሱ
ለአዳም ክብረ ሞገሱ
በኪዳንኪ ኃጥኣን መንግሥተ ሰማያት ይወርሱ ❞
🕊
[ ኹል ጊዜ ለደኻ መራራት መመጽወት እንደ ለመለመ አበባ ያማረ ነው [ ምን ያምር ? ] ድንግል በቃል ኪዳንሽ ምክንያት ከበላዔ ሰብእ ኀጢአት የውሃ ሚዛን በልጦ በመታየቱ ለተአምርሽ በሰማይ ምስጋና ኾነ። ]
[ የእግዚአብሔር አትሮንሱ [ ዙፋኑ ] የአዳም የግርማው ክብር አንቺ ነሽ ፤ ኃጥኣንም በቃል ኪዳንሽ መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ። ]
[ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ]
[ 🕊 ክብርት ሰንበት 🕊 ]
🕊 💖 🕊

❤4
እንኳን ለእናታችን ለንፅህተ ንፁሀን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ለኪዳነምህረት የምሕረት ቃል ኪዳን የተገባላት አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🙏🙏
#የሮማን_ክፋይ_ኪዳነምህረት♥16
#ሰላም_ነሽ_ለኔ_ፍቅር_በረከት
#ስምሽ_ሞገሴ_ክብርሽ_ማዕረጌ
#ምን_ብዬ_ልጥራሽ_ድንግል_እናቴ..
#የቃል_ኪዳኗ_እመቤት_ሆይ_አንቺ_እኮ
#የመለኮት__ዙፋን_የአለም_እናት
#ለታመሙት__ፈውስ
#ለተራቡት__ምግብን
#ለታመሙት__እርካታን
#ለተሰደዱ__ጥንካሬን
#ላዘኑ_ዕምነትን
#ለሞቱ_የነፍስ_እረፍትን፡
#ለአለማችን ሰላምን የምትሰጪ የጭንቅ አማላጅ እናቴ እመቤቴ ቅድስት #ኪዳነምህረት_ሆይ ልጅሽ በገባልሽ ቃል ኪዳን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ስውሪን ሀገራችንን #ኢትዮጵያን አንቺ በቃል ኪዳንሽ ከውጭም ከሀገር ውስጥ ጠላት ከክፉ ነገር አንቺ ጠብቂልን
#የእናታችን_የቅድስት_ኪዳነምህረት እረድኤት በረከት ምልጃ ፀሎት ልመናዋ ጥበቃ እኛን ህዝበ ክርስትያንን አይለየን/አይለያችሁ አሜን፫ 🙏🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇
@Enatachn_mareyam

❤13❤🔥1🙏1
†
[ የድኅነት ምክንያት ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ ! ]
🕊 💖 🕊
[ ለጥፋት የቀረበ ሰው ለድንግል በተሰጣት ኪዳን ፤ ብርሃኗ በማይጨልም በመንግሥተ ሰማይ ዕረፍትና ጤንነትን ያገኛል። ]
[ በብር የተሠራች የርግብ ክንፍ ጐኖቿ በወርቅ ዐመልማሎ የተሸለመች አንቺ በምሥራቅ ስትመሰዪ ልጅሽ የእውነት ፀሐይ ነው፡፡ በእውነት ቃል ኪዳንሽ አያልቅም፡፡ ]
[ ቅዱስ ያሬድ ]
🕊 💖 🕊
"ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ ፈለገ እሳት ወደይን እም አሰጠመ ኩሎ ፤
[ የድኅነት ምክንያት የሆነው ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የጥፋት እሳት ፣ መርገም [ኀጢአት] ባጠፋን ነበር ] "
[ አባ ጽጌ ድንግል ]

❤🔥3
#ድንግል_ሆይ ! በአፍና በመጽሐፍ ያይደል ፤ በልቤና በሕይወቴ ውስጥ #የእናትነት_ፍቅርሽን አውቀዋለሁ። ስለዚህም አንችን በእናትነት የሰጠኝን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ። በፊትሽ ያፈሰሱኩት እንባ ያልታበሰበት ጊዜ የለም። #ለነፍሴ_ነፍሷ ነሽ ብያለሁ ...
#የእመቤታችንን ፍቅሯን በልባችን ፣ ውዳሴዋን በአንደበታችን ያብዛልን።
በእመብርሃን ፣ በእመሕይዎት
ቃልኪዳን ይጠብቀን ፤ አሜን። 🙏🙏🙏🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
#የእመቤታችንን ፍቅሯን በልባችን ፣ ውዳሴዋን በአንደበታችን ያብዛልን።
በእመብርሃን ፣ በእመሕይዎት
ቃልኪዳን ይጠብቀን ፤ አሜን። 🙏🙏🙏🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
❤12👍2
†
[ 🕊 የዐቢይ ጾም ሳምንታት 🕊 ]
💖
ዐቢይ ጾም በያዘው በ፶፭ ቀኑ ውስጥ ሰባት ቅዳሜና ስምንት እሑዶቸን ይዟል ፤ የእነዚህ የስምንቱ እሑዶች የተለያየ ስያሜ አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም የሰጣቸው የቤተ ክርስቲያናችን የዜማው ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ዘወረደ ፣ ቅድስት ፣ ምኩራብ ፣ ደብረዘይት ፣ ገብረ ኄር ፣ ኒቆዲሞስ ፣ መፃጉዕ ፣ ሆሣዕና ናቸው፡፡
🕊 💖 🕊
[ ፩ ኛ. ዘወረደ ፦ ]
በመጀመርያው ሳምንት ዘወረደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማያት መውረዱን ፣ ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን እና እኛን ማዳኑን በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚወሳበትና የሚዘከርበት ወቅት ሲሆን ይህንንም የሚዘክሩ መዝሙሮች ይቀርባሉ ፤ ትምህርቶች ይሰጣሉ ፤ ይህንንም እያሰብን ጾሙን እንጾማለን፡፡
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፥ ለሐዋርያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን በሥርዓቱ ጹመን እንዲንጠቀም እርዳን ፤ አሜን !
† † †

❤4👍1
ኪዳነ ምህረት
#መታሰቢያዬን_ለሚያደርጉ
#በስሜ_አቢያተ_ክርስቲያን_ለሚሠሩ
#የተራቆተውን_ለሚያለብሱ
#የተራበውን_ለሚያጠግቡ
#የተጠማውንም_ለሚያጠጡ
#የታመመውን_ለሚጐበኙ
#ያዘነውን_ለሚያረጋጉ
#የተከዘውንም_ደስ_ለሚያሰኙ
#ምስጋናዬን_ለሚጽፉ
#ልጆቹንም_በስሜ_ለሚሰይም
#በበዓሌም_ቀን_በማኅሌት_ለሚያመሰግን
#አቤቱ_ዐይን_ያላየውን_ጆሮ_ያልሰማውን_በሰውም_ልቡና_ያልታሰበውን_በጎ_ዋጋ_ስጣቸው
#በአማላጅነቴም የሚታመነውን ሁሉ
ከሲኦል ነጻ አድርገው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን
ረኃቡንና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ አለችው
#ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ
#የሰጠሁሽም_ቃል_ኪዳን እንዳይታበል በራሴ ማልኩልሽ አላት ።
#የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል_ማርያም
ጣዕሟን በአንደበታችን ፤ ፍቅሯን በልባችን ያሳድርልን
ጽኑ ቃል ኪዳኗ በአማላጅነቷ ከምናምን ከህዝበ ክርስቲያን ጋር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር 🙏🙏🙏
ለአመቱ በሰላም ያድርሰን 🙏

❤18❤🔥1👍1
🕊
[ † እንኩዋን ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
🕊 † ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት † 🕊
ቅዱሳን ነቢያት እጅግ ብዙ ናቸው:: ከፈጣሪያቸው የተቀበሉት ጸጋም ብዙና ልዩ ልዩ ነው:: ያም ሆኖ ከሁሉም ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ይበልጣል:: መጽሐፍ እንደሚል ከእርሱም በፊት ቢሆን ከእርሱ በሁዋላ እንደ እርሱ ያለ ነቢይ አልተነሳምና:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ዓለም በተፈጠረ በ ፫ ሺህ ፮ መቶ [ 3,600 ] ዓመት እሥራኤል በረሃብ ምክንያት ፸፭ [ 75 ] ራሱን ወደ ምድረ ግብፅ ወረደ:: በዚያም ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ለ፪ መቶ ፲፭ [ 215 ] ዓመታት ተከብረው: ለ፪ መቶ ፲፭ [ 215 ] ዓመታት ደግሞ በባርነት: በድምሩ ለ፬ መቶ ፴ [ 430 ] ዓመታት በምድረ ግብፅ ኑረዋል::
- በባርነት ዘመናቸውም 'ራምሴና ጋምሴ' የሚባሉ ፪ [2] ከተሞችን [ዛሬ ፒራሚዶች የምንላቸውን] ገንብተዋል:: ግፋቸው እየበዛ ሲሔድ ግን ጩኸታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ:: ያድናቸውም ዘንድ አንድ ቅዱስ ሰው እንዲወለድ አደረገ:: ይኽም ሰው ሙሴ ይባላል::
- ወላጆቹ መታመናቸውን በፈጣሪያቸው ያደረጉ 'እንበረም'ና 'ዮካብድ' ሲሆኑ ከሌዊ ነገድ ናቸው:: ከሙሴ ውጪም አሮንና ማርያምን ወልደዋል:: ቅዱስ ሙሴ በተወለደበት ወራት ወንድ የእሥራኤል ሕጻናት ይፈጁ ነበር:: ጌታ ግን በገዳዮቹ ልቡና ርሕራሔን አምጥቶ አትርፎታል::
- በሁዋላም በ፫ [ 3 ] ወሩ ዓባይ ወንዝ ላይ ጥለውት ተርሙት [የፈርኦን ልጅ ናት] ወስዳ በቤተ መንግስት አሳድጋዋለች:: 'ሙሴ' ያለችውም እርሷ ናት:: 'ዕጉዋለ ማይ / እማይ ዘረከብክዎ' [ከውሃ የተገኘ] ለማለት ነው:: ወላጆቹ ያወጡለት ስም ግን 'ምልክአም' ይባላል:: ገና ሲወለድ ፊቱ እንደ መልአክ ያበራ ነበርና::
- ቅዱስ ሙሴ ፭ [ 5 ] ዓመት በሆነው ጊዜ ፈርኦንን በጥፊ በመማታቱ ለፍርድ ቀርቦ እሳትን በመብላቱ አንደበቱ ኮልታፋ ሆኖ ቀርቷል:: እናቱ ዮካብድ ሞግዚት ሆና ስላሳደገችው ፵ [40] ዓመት በሆነው ጊዜ የፈርኦንን ቤት ምቾትና የንጉሥ ልጅ መባልን ናቀ:: ቅዱስ ዻውሎስ እንደሚለው በአሕዛብ ቤት ካለ ምቾት ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን ሊቀበል ወዷልና:: [ዕብ.፲፩፥፳፬] [11:24]
- አንድ ቀንም ለዕብራዊ ወገኑ ተበቅሎ ግብጻዊውን ገድሎት ወደ ምድያም ሸሸ:: በዚያም ለ፵ [40] ዓመታት የካህኑን ዮቶርን በጐች እየጠበቀ: ኢትዮዽያዊቱን ሲፓራን አግብቶ ኖረ:: ልጆንም አፈራ:: ፹ [80] ዓመት በሞላው ጊዜ እግዚአብሔር በደብረ ሲና ተናገረው:: ሕዝቡንም ከባርነት ቀንበር እንዲታደግ ላከው::
- ቅዱስ ሙሴም ከወንድሙ አሮንና ከአውሴ [ኢያሱ] ጋር ግብጻውያንን በ፱ [9] መቅሰፍት: በ፲ [10] ኛ ሞተ በኩር መታ:: እሥራኤልንም ነጻ አወጣ:: ሊቀ ነቢያት የሠራቸው ሥራዎች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም::
- እርሱ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ ሕዝቡን በደረቅ አሻግሯል::
- ግብጻውያንን ከነሠረገሎቻቸው በባሕር ውስጥ አስጥሟል::
- ለሕዝቡ መና ከደመና አውርዷል::
- ውሃን ከጨንጫ [ከዓለት] ላይ አፍልቁዋል::
- በብርሃን ምሰሶ መርቷቸዋል::
- በ፯ [7] ደመና ጋርዷቸዋል::
- ጠላቶቻቸውን ሁሉ ድል ነስቶላቸዋል::
- ስለዚህ ፈንታ ግን ወገኖቹ ብዙ አሰቃይተውታል:: እርሱ ግን ደግ: ቅንና የዋህ ሰው ነውና ብዙ ጊዜ ራሱን ለእነሱ አሳልፎ ሰጥቷል:: "ሙሴሰ የዋህ እምኩሎሙ ደቂቀ እሥራኤል" እንዲል:: [ዘኁ.፲፪፥፫] [12:3] ቅዱስ ሙሴ ለ፵ [40] ዓመታት ሕዝቡን ሲመራ ከእግዚአብሔር ጋር ለ፭ መቶ ፸ [570] ጊዜ ተነጋግሯል::
- ከጸጋው ብዛትም ፊቱ ብርሃን ስለ ነበር ሰዎች እርሱን ማየት አይችሉም ነበር:: ታቦተ ጽዮንንና 10ሩ ቃላትን ተቀብሎ ጽላቱ ቢሰበሩ ራሱ ሠርቶ በጌታ እጅ ቃላቱ ተጽፈውለታል:: "የቀረው የቅዱሱ ሕይወት በመጻሕፍተ ኦሪት [በብሔረ ኦሪት] ውስጥ የተጻፉ አይደሉምን?"
- እኔ ግን ደካማ ነኝና ይህቺ ትብቃኝ:: ቅዱስ: ክቡር: ታላቅ: ጻድቅ: ነቢይና ደግ ሰው ቅዱስ ሙሴ በ፻፳ [120] ዓመቱ ዐርፎ በደብረ ናባው ሊቃነ መላእክት ቅዱሳን ሚካኤል: ገብርኤልና ሳቁኤል ቀብረውታል:: መቃብሩንም ሠውረዋል:: [ይሁዳ.፩፥፱] [1:9]
አምላከ ሊቀ ነቢያት ደግነቱን አስቦ ከግራ ቁመት: ከገሃነመ እሳት ይሰውረን:: በረከቱንም አብዝቶ ያድለን::
🕊
[ † የካቲት ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት [በ፻፳ [120] ዓመቱ ደብረ ናባው ላይ ተቀብሯል]
፪. ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ [ኁለተኛው]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት [ቀዳሜ ሰማዕት]
፪. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ ዘብዴዎስ]
፫. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዘቆዽሮስ
፬. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
፭. አባ ገሪማ ዘመደራ
፮. አባ ዸላሞን ፈላሢ
፯. አባ ለትጹን የዋህ
† " ሙሴ ካደገ በሁዋላ የፈርኦን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ:: ከግብጽም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለጠግነት እንዲሆን አስቧልና:: ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ:: ብድራቱን ትኩር ብሎ ተመልክቷልና::" † [ዕብ.፲፩፥፳፬] [11:24]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

❤2👍2
ዘወረደ
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡
የዘወረደ መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ
ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፣ ለእርሱም መገዛት ደስ ይበላችሁ። እግዚአብሔር ቸር ምሕረቱም ለዘላለም፣ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና። እኛስ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን፤ ወደ ደጁ በመገዛት፣ ወደ አደባባዮችም በምስጋና ግቡ፤ ጾምን እንጹም፤ ጓደኞቻችንን እናፍቅር፤ እርስ በርሳችንም እንፋቀር። ሰንበት ስለሰው ተሠርታለችና ሰንበትን እናክብር። እውነትንም እንሥራ፤ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ፤ እዘምራለሁ፤ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ።
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው
#መልካም_ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

❤17👍1