#እንዴት_ንስሓ_ልግባ_እንዴት_ልናዘዝ
የኃጢአትን ወጤት በሚገባ ካወቅክ ኃጢአትን
ትጠላለህ፤ የኃጢአትን ቅጣት ካይነትክ ኃጢአትን
መስራት ትፈራለህ ከራስህ ጋር ተነጋግረህ በደልህን
ማወቅ እና ማመን እንድትችል ለራስህ ጊዜ ስጠው
አድምጠዉ፡፡1ቆሮ11፡31ሮሜ14፡22 ንስሓ ኑዛዜ
የሚነገረው ለማንም አይደልም ለቄስ ለካህን ብቻ
ነው፡፡ማቴ 8፡4 የሚነገረውም በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ነው፡፡ ማንም በሌለበት ንስሓ አባት
የተነገረውን ሰምቶ እንዳልሰማ ቀኖና ሰጥቶ ያልፋል
እንጅ ለማንም አይናገርበትም ደግሞም አያነሳበትም
ስለዚሀ ሰሀፍረት ሰበብ ኃጢአትን መደበቅ የለበትም፡፡ ማቴ 3፡6 ዘጸ 5፡5
የንስሓ መሠረታዊ ስርዓቶች
1. ኃጢአትንም አስታውሶና መዝግቦ
በመሃፍ፡ ወይም በቃል ይዞ ምህረትን በመፈለግ
ወደ ንስሓ አባት በትህትና በመቅረብ ዝቅ ብሎ
ኃጢአቱንም ባልተንዛዛና ፀያፍ ባልሆነ ቃላት
ለንስሓ አባቱን ግልጽ በሆነ መልኩ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሉቃ15፡21
2. ንስሓ አባቱ ሰምተው አቅሙን ያገናዘበ
ቀኖናዊ ቅጣት ይሰጡታል ቀኖናውን ፈጽሞ
ጨርሶ እንዲመጣ ቀነ ቀጠሮ ሰጥተው በጸሎት ያሰናብቱታል፡፡ማቴ 3፡8
3. የታዘዘውን ሙሉ በሙሉ ሲፈጽም ቄሱ
የስርየት ጸሎት ጸልየው እግዚአብሔር ይፍታህ
በማለት ሽክሙን ያወርዱለታል፡፡ ዳግም
እንዳትበድል ተጠንቀቅም ይሉታል፡፡
መስቀል አሳልመው በሰላም ያሰናብቱታል፡፡ ማር 5፤34
#የሁላችንንም_ለንስሀ_ሞት_ያብቃን
#መልካም_ቀን🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇
@Enatachn_mareyam

❤10👍3
†
† 🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊 †
💖
[ ዓ ለ ም ን ስ ለ መ ተ ው ! ]
[ ክፍል ሦስት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ መነኵሴ በማንኛውም ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ትእዛዛተ እግዚአብሔርን ብቻ የሚይዝ ነው፡፡ መነኵሴ ዘወትር ባሕርዪውን የሚገታና ሳያቋርጥ ስሜቶቹን የሚቆጣጠር ነው፡፡ መነኵሴ ሥጋውን በቅድስና ፣ አንደበቱን በንጽሕና ፣ ሐሳቡን ብሩህ አድርጎ የሚጠብቅ ነው፡፡ መነኵሴ በሁለቱም ተኝቶም ሆነ ነቅቶ ሳለ ሳያቋርጥ በተዘክሮ ሞት ተመልቶ የሚኖር ኀዘንተኛ ነፍስ ነው፡፡ ከዓለም መለየት ማለት በፈቃድ በቁሳዊ ነገሮች መታበይን መጥላትና ከተፈጥሮ በላይ የሆነውን ለማግኘት ሲባል ተፈጥሮን መካድ ነው፡፡
በፈቃዳቸው ከዓለም ነገሮች የተለዩ ሁሉ ፣ በርግጥም ስለሚመጣው መንግሥት ፣ ወይም ስለ በዛ ኃጢአታቸው ብለው ፣ አሊያም እግዚአብሔርን ከመውደዳቸው የተነሣ ያደረጉት ነው፡፡ ከእሊህ ምክንያቶች ስለ አንዱ ብለው ያልተለዩ ሆነው ቢሆን ኖሮ ከዓለም መለየታቸው ትርጉም የለሽ ይሆን ነበር፡፡ ዳሩ ግን ተጋድሎአችንን ያዘጋጀ እግዚአብሔር የጉዞአችን ፍጻሜ ምን እንደ ሆነ ይመለከት ዘንድ ይጠብቃል፡፡
የገዛ ኃጢአቱን ሸክሞች ከራሱ ላይ ለማራገፍ ብሎ ከዓለም የተለየ ሰው ፣ ክርስቶስ ደግሞ ወደ እርሱ መጥቶ ከልቡ ላይ የድንዳኔን ድንጋይ እስኪያንከባልልለት ፣ አልዓዛርን እስኪፈታው ፤ ያውም አበሳችንን ከማዕሠረ ኃጢአት እስኪፈታው ፣ አገልጋዮቹ መላእክትንም ፦ “ከሥጋ ፈቃዳት ፍቱትና ወደ መቲረ ፈቃድ፣ ይሂድ” [ዮሐ.፲፩፥፵፬] ብሎ እስኪያዝዝለት ድረስ ፤ ከከተማ በኣፍአ በመቃብራት መካከል የተቀመጡትን ሊመስል ይገባዋል ፣ ከራሱም ትኩስና የሚያቃጥሉ እንባዎችን ማመንጨትና ድምፅ አልባ የሆኑ የልብ ማቃሠቶችን ማሰማትን ማቋረጥ የለበትም፡፡ አለበለዚያ ግን አንዳች ረብ የሚያገኝ አይሆንም፡፡ ❞
[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]
🕊 💖 🕊

❤1
†
† 🕊 ዘ ወ ረ ደ 🕊 †
[ የጾምን መግባት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ትምህርት ! ]
💖
[ ክፍል አራት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ ጾምም እንደዚህ ናት ፤ ዕረፍተ ነፍስን ትሰጣለች፡፡ ለሽማግሌዎች ውበትን ታጎናጽፋቸዋለች ፤ ወጣቶችን በቀና ጎዳና ትመራቸዋለች ፤ ማስተዋልን ትለግሳቸዋለች ፤ ኹሉንም ሰው እንደ ዘውድ እንደ አክሊል ያማረ የተወደደ ታደርገዋለች፡፡
እንግዲያውስ ዛሬ ምንም ዓይነት ሁካታ አይኑር፡፡ ሁካታስ ይቅርና ምልክቱም አይኑር፡፡ የምግብ ዓይነትን ለማንጋጋት የሚራወጥ ማንም አይገኝ፡፡ ኹሉም ሰው ከእንደዚህ ዓይነት ግብር ይራቅ፡፡ ከተማችን እንደ ተወደዱ ቈነጃጅት አመለ ሸጋና የምትማርክ ትኹን፡፡
በአንድ ሌሊት ውስጥ ምን ያህል ለውጥ እንዳለ ስመለከትና የትናንቱን ጫጫታ ሳስታውሰው ጾም እንደ ምን ያለች ፍቱን መድኃኒት መኾንዋን ዐይቼ በእጅጉ እደነቃለሁ፡፡ የእያንዳንዱን ሰው አመለካከት እንደ ምን እንደምትቀይር ተመልክቼ በእጅጉ መደነቅን ይይዘኛል ፡ የገዢዎችን ብቻ ሳይኾን የተገዢዎችንም ፣ የጌቶችን ብቻ ሳይኾን የባሮችም ፣ የወንዶችን ብቻ ሳይኾን የሴቶችንም ፣ የባለፀጎችን ብቻ ሳይኾን የድኾችንም ፣ ቃለ እግዚአብሔር የሚያውቁትን ብቻ ሳይኾን የማያውቁትንም እንደ ምን ልበ ንጹሀን እንደምታደርጋቸው ተመልክቼ አብዝቼ እደነቃለሁ፡፡
የገዢዎችን ብቻ ሳይኾን የተገዢዎችንም ብዬ መናገሬስ ስለ ምንድን ነው ? ነገሥታትም ከነዘውዳቸውና ከነሙሉ ማዕርጋቸው ኾነው ራሳቸውን ለጾም ስለሚያስገዙ ነዋ ! ዛሬ በባለጸጋውና በድኻው ማዕድ ልዩነት የለውም፡፡ ኹሉም ሰው ተርታ ኑሮን የሚመራ ነው፡፡ የቅምጥልነትን ሕይወት የሚመራ የለም፡፡ ታይታን የሚፈልግ የለም፡፡ ኹሉም ሰው በቤቱ ካለው የሰባ ፍሪዳና ወይን ይልቅ እዚህ በቤተ ክርስቲያን ያለውን ሰማያዊውን ማዕድ ሽቶ የመጣ ነው። ❞
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

❤2
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
[ 🕊 † እንኩዋን ለቅዱስ "አናሲሞስ ሐዋርያ" እና ለእመቤታችን "ቅድስት ድንግል ማርያም" በዓል በሰላም አደረሳችሁ † 🕊 ]
🕊 † ድንግል ማርያም † 🕊
የአምላክ እናቱ እመ-ብርሃን ድንግል ማርያም :-
- በ፫ [3] ወገን [በሥጋ: በነፍስ: በልቡና] ድንግል
- በ፫ [3] ወገን [ከኀልዮ: ከነቢብ: ከገቢር] ንጽሕት
- ሳትጸንስ: በጸነሰች ጊዜና ከጸነሰች በሗላ ድንግል
- ጌታን ሳትወልድ : በወለደችው ጊዜና ከወለደችው በሗላ ድንግል ስትሆን እናትም ድንግልም መሆኗን አምነን እመሰክራለን::
- እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ በላይ ክብርትና ንዕድ ናት:: ሊቃውንት አበው እንዳስተማሩን በዚህ ዕለት እንዲህ ብለን እንጸልያለን::
"ረስዪ ፍና ትሕትና አእጋርየ ይሑሩ:
ትዕቢትሰ ለአምላክ ጸሩ"
[እመቤቴ ሆይ ትዕቢትን አምላክ ይጠላልና እግሮቻችን በትሕትና እንዲሔዱ አድርጊ]
🕊 † ቅዱስ አናሲሞስ ሐዋርያ † 🕊
በዘመነ ሐዋርያት ምስጉን ከነበሩ አበው አንዱ ቅዱስ አናሲሞስ ነው:: ስለ ቀና አገልግሎቱና መልካም እረኛነቱ አባቶቻችን ሐዋርያት አብዝተው በቀኖናቸው መስክረውለታል:: እርሱ ከኃጢአት ኑሮ ወደ ዘለዓለማዊ የቅድስና ሕይወት መጥቷልና::
¤ ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
በሮም ከተማ የሚኖር ፊልሞና የሚባል አንድ ባለጸጋ ነበር:: ይህ ሰው በስብከተ ቅዱስ ዻውሎስ አምኖ ከርስቲያን ሆነና በመንፈሳዊ አገልግሎት ተጠመደ:: ነገር ግን ከአገልጋዮቹ መካከል ያላመነ አንድ ሰው ነበር:: "ተጽዕኖ አላደርግበትም" ብሎ ዝም ይለዋል:: ግን ክርስትና እንዲገባው ለተልዕኮ መንፈሳዊ በሚሔድበት ሥፍራ ያስከትለው ነበር::
አገልጋዩ ግን በመለወጥ ፈንታ ሌብነትን ለመደ:: ይባስ ብሎም የአሳዳሪውን [የፊልሞናን] ገንዘብ ሠርቆ ወደ ሮም ጠፍቶ ተመለሰ:: ቅዱስ ፊልሞናም ለገንዘቡ ሳይሆን ለሕይወቱ አዘነ::
ያ ሠርቆ የጠፋው አገልጋይ ግን በሮም ከተማ ሲመላለስ ስብከተ ወንጌልን ይሰማል:: ሰባኪው ደግሞ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ነበር:: ቁጭ ብሎ ሲማርም ልቡናው በርቶለት ተጸጸተ:: ከሐዋርያውም ዘንድ ቀርቦ ኃጢአቱን ተናዞ ተጠመቀ::
ከዚያች ዕለት ጀምሮም ብርቱ ክርስቲያን ሆነ:: በጥቂት ጊዜም የተጋ ሰባኪ : ርሕሩሕ እረኛ ሆነ:: ፈጣሪውንም ደስ አሰኘ:: ነገር ግን ስለ አንድ ነገር ፈጽሞ ያዝን : ይተክዝም ነበር::
+ የድሮ አሳዳሪው ቅዱስ ፊልሞና እንዳዘነበት እያወቀ ዝም ማለት ባያስችለው ለመምህሩ ቅዱስ ዻውሎስ ነገረው:: ያን ጊዜም ሐዋርያው በእሥራትና በግርፋት ይሰቃይ ነበር:: በሮም ሳለም አጭር ክታብ [ደብዳቤን] ጽፎ ለዚህ ደቀ መዝሙሩ ሰጠውና ወደ ቀድሞ አሳዳሪው ወደ ፊልሞና ላከው::
+ ይህች ጦማር [ክታብ] ዛሬም ድረስ ከ፹፩ [81] ዱ አሥራው መጻሕፍት : ከቅዱስ ዻውሎስ ፲፬ [14] መልዕክታት አንዷ ሆና ተቆጥራ እንጠቀምባታለን:: ክታቧ እጅግ አጭር ብትሆንም ምሥጢሯ ግን ሰፊ ነው::
+ ያ የተላከ ክርስቲያንም ያችን ክታብ ወስዶ ለቅዱስ ፊልሞና [ለቀድሞ አሳዳሪው] አስረከበ:: ቅዱስ ፊልሞናም በደስታ አቅፎ ሳመው:: ቀድሞውንም ያዘነ በወጣቱ አገልጋይ የነፍስ እዳ እንጂ በገንዘቡ አልነበረምና:: ያ ተላኪ ሰውም በአካባቢው ሲያገለግል ቆይቶ ወደ ቅዱስ ዻውሎስ ተመልሷል:: ደቀ መዝሙሩ ሆኖም ብዙ አገልግሏል::
+ ቅዱስ አናሲሞስ ማለት . . . የቀድሞ የሰው አገልጋይ . . . ዛሬ የክርስቶስ ባሪያ . . . ቀድሞ ሠራቂ . . . ዛሬ ግን ለመንጋው የሚራራ ሰው የሆነው ይህ ክርስቲያን ነው::
+ በ፷፯ [67] ዓ/ም ቅዱስ ዻውሎስ መሰየፉን ተከትሎ እርሱንም አሳድደው : አሰቃይተው : ጭኑንም ሰብረው አሕዛብ ገድለውታል:: በሰማይም የሐዋርያነትና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጅቷል:: [ጢሞ.፬፥፮-፰ [4:6-8] , ፊልሞና.፩፥፩-፳፭] 1:1-25]
አምላከ ቅዱሳን የአናሲሞስን መመለስ : ንስሃና በረከት ያድለን::
🕊
[ † የካቲት ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አናሲሞስ ሐዋርያ [የቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ ደቀ መዝሙር ሲሆን ከ፲፬ [14] ቱ መልዕክታት አንዱ የሆነው 'ወደ ፊልሞና' የተጻፈው በዚህ ቅዱስ ምክንያት ነው:: [ፊል.፩፥፲፩ 1:11]
፪. አባ ዘካርያስ ዘሃገረ ስሃ
፫. አባ አካክዮስ ጻድቅ
፬. አባ ገብርኤል ሊቀ ዻዻሳት
፭. አባ ገብርኤል [የኢትዮዽያ ዻዻስ]
[ + ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም
፪. አበው ጎርጎርዮሳት
፫. አቡነ ምዕመነ ድንግል
፬. አቡነ አምደ ሥላሴ
፭. አባ አሮን ሶርያዊ
፮. አባ መርትያኖስ ጻድቅ
" ስለ ጽዮን ዝም አልልም . . . አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ:: የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ:: በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ:: " [ኢሳ.፷፪፥፩-፫] [62:1-3)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

#የወላዲተ_አምላክ_ቅድስት_ድንግል_ማርያም የድንግልና ሕይወት ፤ እንደ ማንኛውም ሰው ድንግልና አይደለም። ይህን የመሰለ ድንግልና፣ ንፅሕናና ቅድስና ከእርስዋ በስተቀር በሌላ በማንም አልታየም። ሌሎች ከነቢብ ከገቢር ድንግል ቢባሉ(ቢሆኑ) ፥ ከሐልዮ ወይም ከማሰብ ድንግል አይደሉምና። በወንጌል "ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል" ተብሎ እንደ ተፃፈ። እርሷ ለነበረውም ለመጪውም ትውልድ የክብር አክሊል ናት። የዘወትር ድንግል(ወትረ ድንግል) የሆነች እናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም፥ ምድራዊ ዘመኗን ሁሉ ፥ ቅድስናዋን ምንም ሳይልውጠው እንዴት መኖር ቻለች? አካላዊ ቃል በማህፀኗ ባደረ ጊዜ፣ ፈጣሪዋን ስትወልድ፣ በክንዷ ስታቅፈውና በዓይኖቿ ስታየውስ፥ ምን ተሰማት? ይህ ጥያቄ በሰው ልጅ ጥበብ የሚመልስ ወይም ሊገለጥ የሚችል አይደልም።
#_ሰናይ__ቀን🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
#_ሰናይ__ቀን🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
❤14🥰4❤🔥2🔥1
†
† 🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊 †
💖
[ ዓ ለ ም ን ስ ለ መ ተ ው ! ]
[ ክፍል አራት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
ባለ መድኃኒት የሆነ መሪ ያስፈልገናል !
❝ ከግብፅ ወጥተን ለመሄድ ፣ ከፈርዖንም አገዛዝ ለማምለጥ የምንመኝ ሁሉ ፣ በርግጥም ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያማልድ [ መካከለኛ የሚሆን ] ና የእግዚአብሔር ወገን የሆነ በተግባርና በመንፈሳዊ ተከስቶ መካከል ቆሞ ፣ ስለ እኛ ብሎ እጆቹን ወደ እግዚአብሔር ለጸሎት በማንሣት ፣ በፈቃዳተ ሥጋ አማሌቅ ድል ከመነሣት መርቶ ባሕረ ኃጢአትን የሚያሻግረን እንደ ሙሴ ያለ ሰው ያሻናል [ዘጸ.፲፯ ]፡፡
ለዚህ ነው ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አሳልፈው የሰጡ መሪ እንደ ማያሻቸው ሲያስቡ ራሳቸውን ያታለሉ የሚሆኑት፡፡ ከግብፅ የወጡ ሁሉ እንደ መሪ ሆኖ ሙሴ ነበራቸው ፣ ከሰዶም ያመለጡም መልአክ ነበራቸው [ዘፍ.፲፱ ]፡፡ የመጀመሪያዎቹ በሐኪሞች ክብካቤ ከነፍስ ምኞቶች የተፈወሱትን የሚመስሉ ናቸው ፤ እነዚህም ከግብፅ የወጡ ናቸው፡፡ የኋለኞቹ ንጹሕ ያልሆነውን የተዋረደ ሰውነት አውልቆ ለመጣል እንደ ሚናፍቁ ናቸው፡፡ ለዚህ ነው እንደ መልአክ የሚናገር ወይም ይልቅ ከመልአክ ጋር የሚተካከል እንደ መልአክ ያለ ረዳት የሚያስፈልጋቸው፡፡ እንደየ ቍስሎቻችን መበስበስ መጠን በእውነት ብልህ አዋቂና ባለ መድኃኒት የሆነ መሪ ያስፈልገናል፡፡
ሰውነታቸውን ወደ ሰማይ ከፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ፣ በተለይም ገና ዓለምን በተዉበት ጊዜ ፣ ተድላ ወዳድ የሆኑ ጠባዮቻችንና የማይጸጸቱ ልቦቻችን ፍቅረ እግዚአብሔርንና ንጽሕናን ገንዘብ እስኪያደርጉ እንዲሁም ኀዘንን እስኪያሳዩ ድረስ ፣ በእውነት ኃይለኛና የማያቋርጥ መከራን መቀበል ያስገልጋቸዋል [ማቴ.፲፩፥፲፪]፡፡ ❞

❤6👍1
†
† 🕊 ዘ ወ ረ ደ 🕊 †
[ የጾምን መግባት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ትምህርት ! ]
[ ክፍል አምስት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ ተወዳጆች ሆይ ! ድኅነተ ሥጋን ድኅነተ ነፍስን እናገኝ ዘንድ ራስን አለመግዛትን ከእኛ ዘንድ እናርቀው ፤ ጾምንና ከእርስዋ ጋር ያሉትን ሌሎች በጎ ምግባራትን እንውደዳቸው ፤ ከዛሬ አንሥተን አዲስ ኑሮን እንጀምር ፤ ዕለት ዕለት በጎ ምግባራትን መሥራትም የሚያስደስተን እንኹን፡፡
እንዲህ መንፈሳዊ ተግባራትን የምንፈጽምና የበጎ ምግባር ሀብትን አከማችተን ጾሙን የምናሳልፍ ከኾንንም ወደ ጌታ ቀን ለመድረስ የተገባን እንኾናለን ፤ ወደዚያ ወደ አስደናቂው ማዕድ [ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ] መቅረብ ይቻለናል።
በጌታችን ቸርነትና ሰው ወዳጁ አምላካችን ክርስቶስን ደስ ባሰኙ ቅዱሳን ጸሎትና ምልጃም ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንወርሳለን፡፡
ከእርሱም ጋር ለባሕርይ አባቱ ለአብ ፣ ለባሕርይ ሕይወቱ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ፣ ኃይልና ጌትነት ይኹን ፤ ዛሬም ዘወትርም እስከ ትውልደ ትውልድ ድረስ አሜን፡፡ ❞

❤4🥰1