🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። †
🕊 † ታላቁ አባ መርትያኖስ † 🕊
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ዕለት የተጋዳይ መነኰስ የአባ መርትያኖስ ሥጋው ከአቴና አገር ወደ አንጾኪያ የፈለሰበት ሆነ። እርሱም ሽንግላ በኃጢያት ልትጥለው በወደደች ጊዜ ከአመንዝራ ሴት ከተፈተነ በኋላ እርሱ ግን መንኵሳ በገድል እስከ ተጸመደች ድረስ ስቦ ወደ ንስሓ መልሷታል።
ከዚህም በኋላ መኖሪያውን ትቶላት ከሀገር ወደ ሀገር የሚዞር ሆነ ከአቴና አገርም ደርሶ በዚያ ጥቂት ቀን ኖረ ጥቂትም ታመመና በሰላም አገፈ ዜናው በግንቦት በሃያ አንድ ቀን እንደተጻፈ።
የከበረ ቴዎድሮስም ለአንጾኪያ ሀገር በከሀዲው የፋርስ ንጉሥ ዘመን ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ይህ አባት የካህናት አለቆችንና ምእመናንን ልኮ ሥጋውን ከአቴና አፍልሰው ወደ አንጾኪያ ከተማ አመጡት በምስጋናም እየዘመሩ አክብረው ተቀበሉት ሊቀ ጳጳሳቱም ተሳለመው በሣጥንም አድርጐ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖረው። በዚችም ዕለት በዓልን አደረጉለት።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
[ † የካቲት ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ታላቁ አባ መርትያኖስ [በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ
፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
" . . . በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ:: በመጋዝ ተሰነጠቁ:: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ::" [ዕብ.፲፩፥፴፮]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

❤1👍1
#_እየጾሙ__አለመጾም ??
#ተወዳጆች_ሆይ! እየጾሙ የጾምን ፍሬ ፃማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደሆነም፦
#ከምግበ_ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኃጢአት ያልተከለከልን እንደ ሆነ፣
#ከጥሉላት_ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ሆነ፣
#ወይን_ከመጠጣት ታቅበን በክፉ መሻት ከመስከር ያልራቅን እንደ ሆነ፣
#ጀምበር_እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውኃ ርቀን በዓይናችን መልካም ያልሆኑ መመልከት
#ትዕይንቶችን ከማየት ያልጦምን እንደሆነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ #እየጾሙ እንዲህ #አለመጾም እንዳለ ዕወቁ፤ ተረዱም፡፡
#አምላከ_ቅዱሳን_እየጾሙ_ካለመጾም_ይሰውረን!
#መልካም_ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam

❤14👍7🔥2
†
† 🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊 †
💖
[ ዓ ለ ም ን ስ ለ መ ተ ው ! ]
[ ክፍል ሁለት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ እግዚአብሔር ለነጻ ፍጥረታት ሁሉ ገንዘባቸው ነው፡፡ እርሱ የሁሉ ሕይወት ነው ፣ የሁሉ ድኅነት ነው ይኸውም የአማንያንና የኢአማንያን ፣ የኃጥና የጻድቅ ፣ የበጎና በጎ ያልሆነ ፣ በፈቃደ ሥጋ የሚመላለስና በፈቃደ ነፍስ የሚመላለስ ፣ የመነኮሳትና የምእመናን ፣ የጠቢብና ያልተማረ ፣ የጤነኛና የታማሚ ፣ የወጣትና የሽማግሌ እርሱ ለሰው ሁሉ ያለ ልዩነት በተመሳሳይ እንደሚፈስስ ብርሃን ፣ ፀሐይን እንደ መመልከት ፣ ወይም እንደ ወቅቶች መፈራረቅ ነው ፤ እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያደላምና፡፡ [ሮሜ.፪፥፲፩]
ሃይማኖት አልባ ሰው ከገዛ ነጻ ፈቃዱ የተነሣ ለሕይወት ጀርባውን የሰጠና ዘላለም ሕያው ሆኖ የሚኖር የፈጣሪውን ህልውና እንደ ሌለው የሚያስብ ፣ በአዋቂ ባሕርይ ያለ ሙት ፍጥረት ነው፡፡ ሕግ ተላላፊ ደግሞ የእግዚአብሔርን ሕግ ፣ ከክፉ ጠባዩ ኋላ የሚይዝና በእግዚአብሔር ማመንን ቀጥታ ተቃራኒ ከሆነው ከኑፋቄ ጋር አጣምሮ ለመያዝ የሚያስብ ሰው ነው፡፡ [ሮሜ.፩፥፲፰]
ክርስቲያን ለሰው አቅም እስከሚቻለው ድረስ በርቱዕና ያለ ነቀፋ ሆኖ በሥላሴ በማመን ፣ በሐሳቡ ፣ በንግግሩና በድርጊቱ ክርስቶስን የሚመስል ነው፡፡ የእግዚአብሔር ወዳጅ በእውነትና ከበደል ርቆ በተቻለው ሁሉ መልካም ከሆነው አንድም ቸል ሳይል ከሁሉ ጋር ተስማምቶ በአንድነት የሚኖር ነው፡፡ ራስን በመግዛት የሚኖር ሰው በፈተናዎች ፣ በወጥመዶችና በሁከቶች መካከል እየኖረ ሳለ በመላ ኃይሉ ከሁከት ነጻ ወጥተው የሚኖሩትን ይመስላቸው ዘንድ የሚጓጓ ነው፡፡ ገዳማዊ ሕይወት በምድራዊና በመሬታዊ ሰውነት የሚደረስበት መልአካዊ የሆነ ሥርዓትና ደረጃ ነው፡፡፡ ❞
[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]
🕊 💖 🕊

👍1🙏1
†
† 🕊 ዘ ወ ረ ደ 🕊 †
[ የጾምን መግባት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ትምህርት ! ]
[ ክፍል ሦስት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ የዛሬው ንግግሬ ለአንዳንዶቻችሁ አዲስና እንግዳ እንደሚሆንባችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ነገር ግን በዓላማ [ ድኅነትን ለማግኘት ብለን ] እንጹም እንጂ እንዲሁ የልማድ ባርያዎች አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡
በየቀኑ ከልክ በላይ በመብላትና በሆዳምነት የምታገኙት ጥቅም ምንድነው ? ጥቅምስ ይቅርና ጭራሽ የከፋ ጉዳትን የሚያመጣባችሁ ነው፡፡ ተመልከቱ ከልክ በላይ በመጠጣትና በመስከር የማስተዋል ልቡና ሲታወር የጾም ጥቅምዋም ምንም ምልክትን ሳያስቀር ያጠፋዋል፡፡
እስኪ ልጠይቃችሁ ፦ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ብዙ ወይንን ከሚጠጡ በየመሸታ ቤቱ አድረው ፀሐይ ከምትወጣባቸው ፣ ለሚያገኛቸው ሰው ኹሉ ደስ ከማያሰኙ ፣ ለቤተ ሰቦቻቸው ግድ ከሌላቸው ፤ ሕፃን ዐዋቂው ከሚሳለቅባቸው ፣ ራሳቸውን ባለመግዛታቸውና ያለጊዜው በኾነ ደስታ ደስ በመሰኘታቸው ምክንያት ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን ካጡ ከእነዚህ ሰዎች በላይ ማን ጎስቋላ ሰው አለ?
ቅዱስ መጽሐፍስ እንዲህ የሚል አይደለምን ? ፦ “ሰካሮች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም” [ ፩ኛ ቆሮ.፮፥፲ ]፡፡ ወዮ ! እንደ ጠዋት ጤዛ ለሚጠፋ ያውም እጅግ ከባድ ጉዳትን የሚያመጣ እርካታን ለማግኘት ብለው የዘለዓለምን መንግሥትን የሚያጡት እነዚህ ሰዎች ከሚያገኛቸው መከራ በላይ ምን መከራ አለ ? ❞
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❤2
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 [ የጽድቅ በር ] 🕊
▷ " ት ክ ክ ለ ኛ ጾ ም "
[ " በቅዱሳን አባቶቻችን አንደበት ... ! " ]
[ 🕊 ]
----------------------------------------------------
❝ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ ፥ ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ ፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን። ❞ [ ቆላ.፩፥፲ ]

❤3
🕊
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
[ ✞ እንኩዋን ለጻድቁ "አቡነ ክፍለ ማርያም" እና ለሰማዕቱ ቅዱስ "ፊልሞን መዓንዝር" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]
🕊 ✞ አቡነ ክፍለ-ማርያም ✞ 🕊
ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ክፍለ-ማርያም በሐዋርያዊ አገልግሎቱ የተመሠከረለት: ለበርካታ ዓመታት በጾምና በጸሎት በአቱን አጽንቶ የኖረ: ከቅድስናው የተነሳ መላዕክት ሰማያዊ ኅብስት ይመግቡት: ውሃም ከአለት ላይ ይፈልቅለት የነበረ አባት ነው::
በዘመኑም ረሃብ ነበርና እርሷ ሳታውቀው እናቱን በረሃብ ጠውልጋ ቢያያት በጣም በማዘኑ እንዲባርከው ከቀረበለት የሰንበት ቁርስ ለእናቱ አድልቶ ብዙ ሰጣት:: በዚሕ ምክንያት መልዐኩም ሰማያዊ ኅብስቱን አስቀረበት: ምንጩም ደረቀች::
ጥፋቱ የገባው አባ ክፍለ-ማርያም ለ፲፩ [11] ዓመታት ንስሃ ገብቶ እግዚአብሔር መልሶለታል:: ከብዙ የገድል ዓመታት በሁዋላም በዚህች ቀን ተሠውሯል::
🕊 ✞ ቅዱስ ፊልሞን ሰማዕት ✞ 🕊
ይህን ቅዱስ "ፊልሞን መዓንዝር" ብሎ መጥራቱ የተለመደ ነው:: እርሱ በቀደመ ሕይወቱ አዝማሪ [ዘፋኝ] ነበርና:: ዘፋኝነት [አዝማሪነት] ደግሞ በክርስትና ከተከለከሉ ተግባራት አንዱና ዋነኛው በመሆኑ ዘፈን [ሙዚቃ] መስማትም ሆነ ማድመጡ ኃጢአት ነው::
ነገር ግን ሁሉ እንዲድን የሚፈቅድ ጌታችን ጥሪውን ወደ ሁሉም ሰው በየጊዜው ይልካል:: ቅዱስ ፊልሞንም የክርስቶስ ጥሪ የደረሰው በከንቱ የዘፋኝነት [የአዝማሪነት] ኑሮ ውስጥ ሳለ ነው:: ነገሩ እንዲህ ነው :-
በ፫ [3] ኛው ክ/ዘ መጨረሻ [በ፪፻፺ [290] ዎቹ] አርያኖስ የሚባል ሹም በግብጽ [እንዴናው] ክርስቲያኖችን ጨፈጨፈ:: ባለማወቅም ክርስቶስን የሚያመልኩ ሚሊየኖችን በሰይፍ በላቸው:: ከዚህ ድርጊቱ መልስ ደግሞ በጣዖቱ [አዽሎን] ፊት እያስዘፈነ ከንቱነትን ይሰዋ : ይዝናናም ነበር::
ከዘፋኞቹ መካከል ደግሞ ይህ ፊልሞን አንዱ ሆኖ ለዘመናት በፊቱ ተጫወተለት:: አንድ ቀን ግን እንዲህ ሆነ:: አስቃሎን የሚባል ቅዱስ ክርስቲያን ለጣዖት እንዲሰዋ ታዘዘ::
ይህ አስቃሎን [አብላንዮስም ይባላል] ወንድሙን ፊልሞንን ያድነው ዘንድ ተጠበበ:: ወደ ፊልሞን ሒዶ "እኔ ገንዘብ እሰጥሃለሁ:: የእኔን ልብስ ለብሰህ : እኔን መስለህ ለጣዖት ሰዋልኝ" አለው:: አስቃሎን ይህንን ያለው ለጥበቡ ሲሆን ፊልሞን ግን "ገንዘብ ካገኘሁ" ብሎ የባልንጀራውን ልብስ ተሸፋፍኖ ወደ ጣዖቱ ፊት ቀረበ::
ያን ጊዜ ተሸፍኖ መስዋዕት ማቅረብ ክልክል ነውና ሹሙ አርያኖስ ግለጡት ሲል አዘዘ:: ቢገልጡት ፊልሞን ሁኖ ተገኘ:: መኮንኑ ገርሞት "ምን እያደረክ ነው?" ቢለው "እኔ ክርስቲያን ነኝ" ሲል አሰምቶ ተናገረ::
ለጊዜው ሁሉም እየቀለደ መስሏቸው ነበር:: ፊልሞን ግን ይህንን ያለው ከልቡ ነው:: ምክንያት በቅዱስ አስቃሎን ልብስ ተመስሎ መንፈስ ቅዱስ ልቡን ለውጦለት ነበር:: ተገልጦ ቀና ሲልም ቅዱሳን መላእክት ከበውት አይቶ ልቡ ጸንቶለታል::
ሹሙ አርያኖስም የቀልዱን እንዳልሆነ ሲያውቅ "ታብዳለህ?" ቢለው ፊልሞን "ምን አብዳለሁ! ዛሬ ገና ከእብደቴ ሁሉ ዳንሁ እንጂ" ሲል መልሶለታል:: አሕዛብ ሁሉ እያዩም በዚያች ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ በደመና አምሳል ወርዶ አጥምቆታል::
በሆነው ሁሉ የተበሳጨው ሹሙም ቅዱስ ፊልሞንን ከክርስቶስ ፍቅር ይለየው ዘንድ ደበደበው : ገረፈው : ጥርሱን አረገፈው : ደሙንም መሬት ላይ አፈሰሰው:: በዚህ ሁሉ ግን ጸና:: ቅዱስ አስቃሎንም ፈጥኖ መጥቶ በመከራው መሰለው::
በመጨረሻም ፪ [2] ቱም ቅዱሳን በቀስት ተነድፈው ይገደሉ ዘንድ ተፈረደባቸው:: ነገር ግን ለእነሱ የተወረወረ ቀስት መንገዱን ስቶ የሹሙን [የአርያኖስን] ዐይን በማጥፋቱ ወታደሮቹ በንዴት ፪ [2] ቱንም ሰይፈው ገድለዋቸዋል::
ዐይኑ የጠፋበት አርያኖስም ስቃዩ ሲበዛበትና ከሚያመልካቸው የረከሱ ጣዖታት መፍትሔ ሲያጣ ከቅዱሳኑ ደም ተቀባ:: ዐይኑም ፈጥኖ በራለት:: በዚህም ምክንያት ምድራዊ ሹመቱን : ሃብት ንብረቱን : ትዳርና ቤቱን : ጣዖት አምልኮውን ትቶ በክርስቶስ አምኖ ለሰማዕትነት በቅቷል::
አምላከ ቅዱሳን በወዳጆቹ አማላጅነት የምናስተውልበትን አዕምሮ አይንሳን:: በረከታቸውንም ያድለን::
🕊
[ † የካቲት ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አቡነ ክፍለ-ማርያም ዘዲባጋ [የተሰወረበት]
፪. አቡነ ገብረ-መርዐዊ ዘአግዶ [ኢትዮዽያዊ]
፫. ቅዱስ ፊልሞን መዐንዝር [ከአዝማሪነት በክርስቶስ አምኖ ለሰማዕትነት የበቃ ቅዱስ ሰው]
፬. ቅዱስ አስቃሎን አናጉንስጢስ [ሰማዕት]
፭. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት [የታላቁ ሐዋርያዊ አትናቴዎስ ደቀ መዝሙር]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፫. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፬. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ
፭. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፮. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
" ስትጦሙም እንደ ግብዞች አትጠውልጉ . . . አንተ ግን ስትጦም በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ: ፊትህንም ታጠብ:: በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ያስረክብሃል:: " [ማቴ.፮፥፲፮]