Telegram Web
🕊              

[  † እንኳን ለታላቁ ሊቅና ጻድቅ ቅዱስ አንስጣስዮስ እና አቡነ ዓምደ ሥላሴ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †  ቅዱስ አንስጣስዮስ ሊቅ  †  🕊

† ቅዱስ አንስጣስዮስ በ ፬ [4] ኛው ክ/ዘመን የተነሳ ሶርያዊ የነገረ መለኮት ሊቅ: ገዳማዊ ጻድቅና የመንበረ አንጾኪያ ሊቀ ዻዻሳት ነበር:: ቅዱሱ ርጉም አርዮስን ካወገዙ ፫፻፲፰ [318]ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት አንዱ ነው:: በወቅቱ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ሱባኤውንና ጉባኤውን የመሩ ሲሆን አንዱ ይህ ቅዱስ ነው::

ከ ፭ [5] ዓመታት በሁዋላም ብዙ ድርሳናትን ጽፎ: ሐዋርያዊ አገልግሎቱን ፈጽሞ በ፫፻፴ [330] ዓ/ም አርፏል:: ያረፈው ግን አርዮሳውያን ባቀረቡት ክስ በሃሰት ተመስክሮበት በግፍ ተሰዶ ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ስለ ውለታው የውዳሴ ድርሳን ጽፎለታል::


🕊   †  አቡነ ዓምደ ሥላሴ  †  🕊

† እኒህ ታላቅ ጻድቅ ሐዋርያዊ አባት አቡነ ዓምደ ሥላሴ የትውልድ ሃገራቸው ጎጃም ሲሆን የተወለዱት በዚሁ ዕለት [የካቲት ፳፯ (27) ነው:: ጻድቁ በአጼ ሱስንዮስ [በ፲፯ [17]ኛው መቶ ክ/ዘ)] የነበሩ ድንቅ ሠሪ : ተአምረኛና ገዳማዊ አባት ናቸው::

የካቲት ፲፮ [16] ቀን መንኩሰው ወደ ተጋድሎ ገብተዋል:: በዋልድባ በነበራቸው ቆይታም እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት የካቲት ፲፮ [16] ቀን እንድትከበር ማድረጋቸውም ይነገራል:: ጻድቁ በሌሎች ገዳማትም የነበሩ ሲሆን ዛሬም ድረስ ረድኤታቸው የሚደረግበት : ስማቸው የሚጠራበት ገዳም ግን ማኅበረ ሥላሴ ይባላል::

ገዳሙ የሚገኘው በሃገራችን ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ : በመተማ በርሃ ውስጥ ነው:: ይህንን ቅዱስ ገዳም የመሠረቱትም ራሳቸው አባ ዓምደ ሥላሴ ናቸው:: ገዳሙ ዛሬም ብዙ ምሑራንና መናንያን ያሉበት : በደህና ሁኔታም የሚገኝ ነው:: ግን በርሃውን የኔ ብጤ ደካማ ሰው የሚችለው አይደለም::

ስለ ጻድቁ ዓምደ ሥላሴ ከሚነገሩ ታሪኮች ቅድሚያውን የሚይዘው የተዋሕዶ ጠበቃነታቸው ነው:: በ፲፮፻፫ [1603] ዓ/ም ዼጥሮስ [ፔድሮ] ፓኤዝ የሚባል ካቶሊካዊ እሾህ ወደ ሃገራችን ገብቶ ነበርና ንጉሡን ሱስንዮስን አባብሎ ተዋሕዶን አስካዳቸው:: ነገሩ ውስጥ ለውስጥ ሲበስል ቆይቶ በ፲፮፻፱ [1609] ዓ/ም በመገለጡ እነ ራስ ዮልዮስ ለሃይማኖታቸው ጠዳ ላይ ተዋግተው ግንቦት ፮ [6] ቀን ተሰው::

ይህ ነገር ሲሰማ ወንድ ሴት : ትልቅ ትንሽ ሳይመረጥ በገጠሩም : በከተማውም : በገዳሙም ያሉት ሁሉ የተዋሕዶ ልጆች መንቀሳቀስ ጀመሩ:: ፯ [7] ዓመታት እንዲህ አልፈው በ፲፮፻፲፮ [1616] ዓ/ም ግጭቱ በይፋ ተጀመረ::

"ተዋሕዶን ካልካዳችሁ" በሚል በቀን እስከ ፰ሺህ [8,000] ሰው በሰይፍ ታረደ:: ይህን ያደረጉት ደግሞ አልፎንሱ ሜንዴዝ : ንጉሡ ሱስንዮስና ጀሌዎቻቸው ነበሩ::

በጊዜውም ከቤተ መንግሥት እነ ንግሥት ወልድ ሰዓላ [የሱስንዮስ ሚስት] : ከጻድቃን አበው ዘርዓ ቡሩክ ዘግሺ : ሐራ ድንግል ዘደራ : ምዕመነ ድንግል ዘጩጊ : ዓምደ ሥላሴ ዘማኅበረ ሥላሴ . . . ከቅዱሳት እነ ፍቅርተ ክርስቶስ : ወለተ ዼጥሮስ : ወለተ ዻውሎስ : እኅተ ዼጥሮስ . . . ለሃይማኖታቸው ተዋሕዶ ጥብቅና ቆመው ሕዝቡን አስተማሩ:: መከራም ተቀበሉ::

ብዙ ኢትዮዽያውያን የመከራ ጽዋን ተጐንጭተው ለክብር ከበቁ በሁዋላ የእግዚአብሔር ፍርድ ተገለጠ:: በጻድቃኑ እነ አባ ዓምደ ሥላሴ ሐዘን ንጉሡ ታመመ:: ምላሱ ተጐልጉሎ ወጣ::

በዚህ ጊዜ አቤቶ ፋሲለደስ ለአባ ዓምደ ሥላሴና ለሌሎቹ ቅዱሳን "አባቴን አድኑልኝ! ተዋሕዶም ትመለስ" አላቸው:: ጻድቁም ከባልንጀሮቻቸው ጋር ጸልየው ንጉሡን አዳኑት:: በፈንታውም ይህንን አሳወጁ::

† ፋሲል ይንገሥ!
ሃይማኖት (ተዋሕዶ) ይመለስ!
የሮም ሃይማኖት ይፍለስ! †

ከዚህ በሁዋላ በ፲፮፻፳፬ [1624] ዓ/ም ፋሲል ሲነግሥ አባ ዓምደ ሥላሴ ለገዳማቸው ብዙ ቦታ አስከልለው : በተጋድሎ ኑረው በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

† አምላከ ቅዱሳን በቀናችው እምነት ተዋሕዶ ሁላችንም እስከ ፍጻሜ ዘመናችን ያጽናን:: ከበረከተ ቅዱሳንም ይክፈለን::

🕊

[  † የካቲት ፳፯ [ 27 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. አባ አንስጣስዮስ ርቱዓ ሃይማኖት [ዘአንጾኪያ]
፪. አቡነ ዓምደ ሥላሴ

[    † ወርኀዊ በዓላት    ]

፪. የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
፪. አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
፫. ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት ሁሉ አለቃ]
፬. ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
፭. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፮. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፯. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት

" የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::"
[፩ጴጥ.፪፥፳፩-፳፭] [1ዼጥ. 2:21-25]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖
1👍1
3
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †

💖 

    [   ዓ ለ ም ን   ስ ለ መ ተ ው !   ]

           [     ክፍል ስድስት     ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ አንዳንዶች ጡቦችን በዓለቶች ላይ ገነቡ፡፡ ሌሎች በገላጣ መሬት ላይ ዐምዶችን አቆሙ፡፡ ሌሎችም አጭር ርቀት ተጉዘው ጡንቻዎቻቸውና ጅማቶቻቸው ፈጥኖ የሚግልባቸው አሉ፡፡ ማስተዋል የሚችል ሁሉ ይህን ምሳሌአዊ ቃል ያስተውል፡፡

ምክንያቱም ጊዜአችን አጭር ነውና በጊዜ ሞታችን ያለ ፍሬና በሚያጠፋ ረሀብ ሆነን እንዳንገኝ በአምላካችንና በንጉሣችን እንደ ተጠሩ ሰዎች ሆነን መንገዳችንን በጉጉት እንሩጥ፡፡ ከዘመቻው በኋላ ተገቢውን የአገልግሎታችን ዋጋ የምንሻ ነንና ወታደሮች ንጉሣቸውን ደስ እንደሚያሰኙት ጌታን ደስ እናሰኘው፡፡ አራዊትን ከምንፈራበት ባላነሰ ጌታን እንፍራው፡፡ እግዚአብሔርን ሳይፈሩ ለመስረቅ ይሄዱ የነበሩ ሰዎችን ተመለከትሁ ፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን መፈራታቸው እንስሳትን እንደ መፍራታቸው መጠን ሊደርስ አልቻለም ነበርና የውሾችን ጩኸት ሲሰሙ በአንዴ ወደ ኋላ ተመለሱ፡፡

ቢያንስ ባልንጀሮቻችንን የምናከብረውን ያህል እግዚአብሔርን እንውደደው፡፡ ዘወትር እግዚአብሔርን የሚያሳዝኑና ይህም በመሆኑ ጥቂት እንኳ የማያስጨንቃቸው ሰዎችን ተመለከትሁ፡፡

እነዚያኑ ራሳቸው ሰዎች ወዳጆቻቸውን በማይረባ ጉዳይ ሲያስቆጡና ቀጥሎም ሁሉንም ዓይነት ማስመሰያ በማድረግ ፣ በማንኛውም ዘዴ ፣ በማንኛውም መሥዋዕት ፣ በማንኛውም ይቅርታ ፣ በሁለቱም በራሳቸውም ሆነ በወዳጆቻቸውና በዘመዶቻቸው በኩል የቀደመ ወዳጅነታቸውን መልሰው ለማግኘት ብለው ያልተቆጠቡ ስጦታዎችን መሥዋዕት ሲያደርጉ ተመለከትሁ፡፡ ❞

[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                       💖                     🕊
3
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     [  ም ክ ረ ቅ ዱ ሳ ን   ]   🕊


▷  " የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር "


[  " በቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ... ! "  ] 

[                         🕊                         ]
----------------------------------------------------

❝ ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።❞  [ ፊልጵ.፬፥፮ ]


🕊                       💖                   🕊
1
Audio
1
🥰12
🕊                    

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

[  † እንኩዋን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †   ]


🕊  † ቅዱስ ቴዎድሮስ ዘሮም †  🕊

ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: [ማቴ.፭፥፵፬] [5:44] ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

ቅዱስ ቴዎድሮስ በዘመነ ሰማዕታት [በ፫ (3) ኛው መቶ ክ/ዘመን] በቀድሞው የሮም ግዛት ውስጥ ከተነሱ ታላላቅ ሰማዕታት አንዱ ነው:: በወቅቱ መሪ የነበረው ክሀዲው መክስምያኖስ "ክርስቶስን ክደህ ለጣኦት ስገድና በከተማዋ ላይ እሾምሃለሁ" ቢለው "ለእኔ ሃብቴም ሹመቴም የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" በማለቱ ንጉሡ ተቆጥቶ በብረት ዘንግ አስደበደበው::

በመንኮራኩር አበራየው:: ለአናብስት ጣለው:: አካላቱን ቆራረጠው:: በእሳትም አቃጠለው:: ቅዱስ ቴዎድሮስ ስቃዮችን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በትዕግስት ተቀበለ:: በፍፃሜውም አንገቱን በሰይፍ ተመትቶ ፫ [3] አክሊላት ወርደውለታል::

ከፈጣሪው ዘንድም ነጭ መንፈሳዊ ፈረስና ቃል ኪዳን ተቀብሏል:: ስሙን የጠራ: መታሠቢያውን ያደረገ ዋጋው አይጠፋበትም:: [ማቴ.፲፥፵፩] [10:41]

አምላከ ቅዱሳን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከት ይክፈለን:: አይተወን:: አይጣለን:: ጾሞ ለማበርከትም ያብቃን::

🕊

[   † የካቲት ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]
፪. ፮ ሺህ ፫ መቶ ፬ [6,304] ሰማዕታት [በቅ/ቴዎድሮስ አምላክ አምነው ሰማዕትነት የተቀበሉ]

[    † ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ]
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ

" እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን:: " [ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. ፸፫] [73]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖
1
10
#አባ-ጳኲሚስ ዘወትር፣ #አማኑኤል ክርስቶስ፣ የሰው ልጆችን ለማዳን ሲል በዕለተ ዓርብ የተቀበለውን መከራ በማሰብ አብዝቶ ይሰግድ ነበር፤

አንድ ቀን እንዲህ እየሰገደ ከሰውነቱ በሚወጣው ላብ መሬቱን አረጠበው፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ተገለጠለት፤

#አባ_ጳኲሚስም "ጌታዬ እንዲህ የምኾነው አንተን #አገኛለኊ ብዬ ነው" አለው፤

#ጌታችንም በዕለተ ዓርብ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ታየውና "እኔም አንተን #ለማዳን ብዬ ነው፣ እንደዘህ የተሰቀልኩት" አለው።


[ ታላቁ ቅዱስ ጳኲሚስ - የተጋድሎ ሕይወቱ እና ሥርዐተ ገዳሙ ፤ በወ/ሮ ዘውዴ ገ/እግዚአብሔር ፤ ገጽ፦ ፸፬/74 ፤፳፻፫/


#ሰናይ___ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
14
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †

💖 

    [   ዓ ለ ም ን   ስ ለ መ ተ ው !   ]

           [     ክፍል ስምንት     ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ከዓለም በመለየታችን መጀመሪያ ላይ በጻማና በኀዘን ሆነን ትሩፋትን መፈጸማችን ርግጥ ነው፡፡ በእነርሱ እያደግን ስንሄድ ግን ጨርሶ አልያም ጥቂት እንኳ ኀዘን አይሰማንም፡፡ ነገር ግን ወዲያውኑ ሙት የሆነ አሳባችን ሲጠፋና በቅንዓታችን ሲገዛ ፣ በሙሉ ደስታና መጓጓት ፣ በፍቅርና በመንፈሳዊ እሳት እንፈጽማቸዋለን፡፡

ገና ከውጥኑ በአንዴ ትሩፋትን የሚከተሉና ትእዛዛትን በደስታና በፍጥነት ሆነው የሚፈጽሙ በርግጥም ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በምናኔ ሕይወት ረዥም ጊዜ ያሳለፉ ገና ለሕግጋቱ ለመታዘዝ ሲደክሙ ለሚገኙ በርግጥ ኀዘኔታ ይገባቸዋል፡፡

ከውጫዊ ሁኔታዎች ተነሥተን ብቻ ዓለምን መተውን አንንቀፍ ወይም አንቃወም፡፡ ወደ ስደት ይኮበልሉ የነበሩ ሰዎች ንጉሥን በጉዞ ላይ ሳለ ድንገት አግኝተው ፣ ከባለሟሎቹም ጋር ተደባልቀው ወደ ቤተ መንግሥቱ ሲገቡና ከእርሱም ጋር ማዕድ ሲቀርቡ ተመለከትሁ፡፡ ዘር ድንገት በመሬት ላይ ወድቆና የበዙ ያበቡ ፍሬዎችን አፍርቶ ተመለከትሁ፡፡ ተቃራኒውን ደግሞ አይቻለሁ፡፡ በሌሎች ምክንያቶች የተነሣ ወደ ሐኪም ቤት የመጣን ሰው ተመለከትሁ ፣ ነገር ግን በሐኪሙ ደግነትና ትሕትና ተሸንፎ ፣ ከሥቃዩም በመታከም ፣ በዓይኑ ላይ ከጋረደው ጨለማ ነጻ መሆንን አገኘ፡፡ ስለሆነም ለአንዳንዶቹ ያልታሰበ የነበረው በሌሎች ታስቦ ከነበረው ይልቅ ጠንካራና የበለጠ አስተማማኝ ሆኖ ነበር፡፡

በኃጢአቱ ክብደትና ብዛት የተነሣ ማንም ራሱን ለገዳማዊ ቃል ኪዳን የማይበቃ እንደ ሆነ አድርጎ አይናገር ፣ ተድላን በመውደዱም የተነሣ ራሱን በማሳነስ ስለ በዛ ኃጢአቱ ለራሱ ይቅርታን አያድርግ [መዝ.፻፵፥፬]፡፡ የበዛ ጥፋት ያለ እንደ ሆነ ጉድፎችን ሁሉ ለማስወገድ ተገቢውን ሕክምና ማድረግ ተፈላጊ ነው፡፡ ጤነኛ ሰው ወደ ሐኪም ቤት አይሄድም፡፡ ❞

[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                       💖                     🕊
1
👍3
                       †                           

†    🕊  ተግባራዊ  ክርስትና  🕊    †

                     💖 

      [   ጥቅም አልባ እውቀት !   ]

            [     ክፍል ሁለት     ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

የዚህን ዓለም ጥበብ የሚያፈቅሩ ሁሉ .... !


❝ ሁለተኛው የማይጠቅም እውቀት ምሳሌ ደግሞ ከንቱ የማወቅ ፍላጎት ነው፡፡ አዋቂ ለመሆን ብቻ ሲባል ስለ ብዙ ነገሮች የማወቅ ጥማት፡፡ ይህ እንዴት ሊጎዳኝ ይችላል? መልካም! አበው እንዳሉት፦ ይህ በጠቅላላ እውቀት መሞላት [ መጠቅጠቅ ] ከሌሎች የተሻለ አዋቂ እንደሆንኩ ወደማሰብና ወደ ኩራትና ትዕቢት ይመራኛል፡፡ እውቀቴንም በሌሎች ፊት ማሳየት ስለምፈልግ ወሬኛ እሆናለሁ፡፡ ባሕታዊው ቴዎፋን እንዳለው ከሆነ በመጨረሻ አእምሮአችን ራሱ የምናመልከው ጣዖት ይሆንብናልና፡፡ ሃሳበ ግትር እንሆናለን ፤ ሁሉን እስካወቅን ድረስም ሌሎችን ለማማከርም ሆነ ምክርን ለመቀበል ፈቃደኞች አንሆንም፡፡ ይህም በመንፈሳዊ ጉዳዮችም ጭምር በራስ ወደ መደገፍ የሚመራን የሕሊና ትዕቢት ሲሆን እጅግ አደገኛ ነው፡፡

ክርስቲያናዊውን ፍጹምነት መከተል ከፈለጋችሁ ሕሊናችሁን ከዚህ አይነቱ የእውቀት ሱስ ማላቀቅ አለባችሁ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በ፩ቆሮ.፫፥፲፰ ላይ፦
"ማንም በዚህች ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን፡፡ የዚህች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና፡፡"

መንፈሳዊ ጥበብና ዓለማዊ ጥበብ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሊሄዱ አይችሉም፡፡ የዚህን ዓለም ጥበብ የሚያፈቅሩ ሁሉ እጅግ የሚዋሹ ሰዎች ብዙ ጊዜ በእግዚአብሔር የማያምኑ ይሆናሉ፡፡ በትዕቢተኛ አእምሮአቸው ተወጥረው እግዚአብሔርን ይክዳሉ፡፡ በዚህ የተነሣም ቅዱስ ጳውሎስ ፦ "ጢሞቴዎስ ሆይ በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤ ይህ እውቀት አለን ብለው አንዳንዶች ከእምነት ስተዋልና ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን አሜን!" [ ፩ጢሞ.፮፥፳ ] ❞

[ አቡነ አትናስዮስ እስክንድር ]


🕊                       💖                     🕊
2
2025/07/14 17:52:30
Back to Top
HTML Embed Code: