Telegram Web
🕊

[ † እንኳን ለቅዱሳን ነቢያት ዮሐንስና ኤልሳዕ ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊† መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ † 🕊

† የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ :-

- በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ
- በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
- በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
- እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
- የጌታችንን መንገድ የጠረገ
- ጌታውን ያጠመቀና
- ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን :-

ነቢይ :
ሐዋርያ :
ሰማዕት :
ጻድቅ :
ገዳማዊ :
መጥምቀ መለኮት :
ጸያሔ ፍኖት :
ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች::

🕊  †  ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ  †  🕊

† ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ ኤልሳዕ :-

- ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ
- መናኔ ጥሪት የተባለ
- በድንግልና ሕይወት የኖረ
- የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት
- እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ
- አንዴ በሕይወቱ : አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው:: ቅዱሳት መጻሕፍት ሁለቱን ቅዱሳን በመልካቸውም ይገልጿቸዋል::

ቅዱስ ዮሐንስ ፦

- ቁመቱ ልከኛ
- አካሉ በጸጉር የተሸፈነ
- የራሱ ጸጉር በወገቡ
- ጽሕሙ እስከ መታጠቃያው የወረደ
- ግርማው የሚያስፈራ የ31 ዓመት ጎልማሳ ነበር::

ቅዱስ ኤልሳዕ ፦

- በጣም ረዥም
- ራሱ ገባ ያለ [ ራሰ በራ ]
- ቀጠን ያለ
- ፊቱ ቅጭም ያለ [የማይስቅ] ሽማግሌ ነበር::

በዚሕች ቀን በ፫፻፶ [350] ዓ/ም አካባቢ የሁለቱም ቅዱሳን አጽም ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ ፈልሷል:: በወቅቱ ክፋተኛ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር:: ለዚሕ እንዲረዳው በ፸ [70] ዓ/ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም ፫ [3] ጊዜ ፈረሰበት::

ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ እሱን አውጥተህ አቃጥል" አሉት:: ሲቆፈር በመጀመሪያ የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው : ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል:: እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል::

በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል:: በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል::

† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅር ያድለን::

🕊

[ † ሰኔ ፪ [ 2 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት [ፍልሠቱ]
፪. ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ [ፍልሠቱ]
፫. አባ ቀውስጦስ ኢትዮዽያዊ

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
፫. ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፬. ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ [ታላቁ]
፭. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፮. አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

" ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ :: " † [ማቴ.፲፩፥፯-፲፭] (11:7-15)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2
#እንኳን_ለጾመ_ሐዋርያት በሰላም አደረሳችኹ!

ከዐቢይ ጾም ቀጥሎ የሚመጣው ጾም "ጾመ ሐዋርያት" ወይም በተለምዶ "የሰኔ ጾም" ይባላል።

ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው። በዚኽም የወንጌል ሥራቸው ሰምሮላቸዋል።

ስለዚኽም አልጫ የነበረውን ዓለም በወንጌል ለማፋጠን ቅዱሳን ሐዋርያት #ከጾም እና #ከጸሎት ጋር የቱን ያኽል እንደተጋደሉና መንፈስ ቅዱስም በሐዋርያት አድሮ የሠራውን ድንቅ ሥራ ለማሰብ ለእኛም በረከቱን ይሰጠንንና ለመልካም ተግባራቶቻችን መሳካት ያድለን ዘንድ #በትሕትና እና #በፍቅር የምንጾመው ጾም ነው።

ለመንፈሳዊነት ቅድሚያ እንስጥና የእግዚአብሔርን ብድራት እንጠብቅ። 🙏 እግዚአብሔር ጾማችንን ሰይጣንን ድል መንሻ - የኃጢኣት መደምሰሻ - መንግሥተ ሰማያትን መውረሻ ያድርግልን!

#ለቅድስት_ቤተክርስቲያናችን እና ለሀገራችን ኢትዮጵያም ሰላሙን ያውርድልን!

         #_ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
7👍1
🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[    የባሕርይ አምላክ ሲሆን ... !   ]

🕊                    💖                       🕊

❝ አምላክ እንደ መሆኑ ሰብአ ሰገል ሰገዱለት ፤ መላእክትም አመሰገኑት ፤ አምላክ እንደመሆኑ ጥበበኞች እጅ መንሻ አቀረቡለት ፤ ሰውም እንደ መሆኑ ለሥጋ እንደሚገባ ተገዘረ ፤ ሰውም እንደ መሆኑ ስለእርሱ መሥዋዕት አቀረቡ። [ ማቴ.፪፥፩-፲፪ ። ሉቃ.፪፥፮-፳፬ ]

ለዘመዶቹም ታዘዘ ፤ ያችውም ያለ ዘርዐ ብእሲ የወለደችው እናቱ ናት። በሥጋ ከእርሷ መወለዱም እንደ ሴቶች መፅነስ ሥርዓት ልማድ አይደለም። ከሴቶች መፅነስ ሥርዓት ልማድ የተለየ ነው እንጂ። ድንግል ቃልን በሥጋ ያለ ዘርዐ ብእሲ ወለደችው። [ ሉቃ.፩፥፳፮-፴፯ ። ፪፥፶፩ ]

በጊዜው በዘመኑ ሁሉ ከአብ ጋር ትክክል የባሕርይ አምላክ ሲሆን ሰው እንደ መሆኑ በሥጋ አካል በየጥቂቱ አደገ ፤ በመለኮቱ ፍጥረትን ሁሉ የሚያከብር ሲሆን ለሰው እንደሚገባ በዮርዳኖስ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ። [ ሉቃ.፪፥፶፪ ። ማቴ.፫፥፲፫—፲፯ ]

ተራበ ፤ ተጠማ ለሰው እንደሚገባ አንቀላፋ ፤ ነቃ መንገድ በመሔድ ደከመ ፤ በላ ጠጣ አለቀሰ ተከዘ ፡ አዘነ። ይህ ጽዋዕ [ሞት] ከርሱ ያልፍ ዘንድ ለሰው እንደሚገባ መላልሶ [ በተገብቶ ] ማለደ።

[ ማቴ.፩፥፫ ። ፷፥፳፭ ፡ ፳፮፥፴፰—፭ ። ዮሐ.፬፥፮ ። ፲፩፥፴፫-፴፱ ። ፲፱፥፳፰ ] ❞

[    🕊   ቅዱስ ቄርሎስ   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                         †                         †
💖                     🕊                      💖
1
                       †                        

   🕊      እንኳን አደረሳችሁ !    🕊

         [    ጾመ ሐዋርያት !    ]

†   🕊   †    🕊   †

[  ክፍል አንድ  ]

በስመ አብ ፥ ወወልድ ፥ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።

በየአመቱ በዕለተ ሰኑይ ብቻ [ ሰኞ ቀን ብቻ ] የሚጀምሩ ሦስት አጽዋማት አሉ፡፡ እነርሱም ዓቢይ ጾም፣ ጾመ ነነዌ እና ጾመ ሐዋርያት ናቸው፡፡ እነዚህአጽዋማት ምን ጊዜም ቅበላቸው እሁድ ሲሆንየሚገቡት ደግሞ ሰኞ ቀን ነው፡፡ በየትኛውም ዓመት ይህን ዕለት አይለቁም፡፡

ስለዚህ የ፳፻፲፭ [2015] ዓ.ም ጾመ ሐዋርያት ዛሬ ሰኞ ግንቦት ፳፰ [28] ገብቷል፡፡ ቤተ  ክርስቲያናችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ በየግላችንም ያጋጠሙንን መንፈሳዊና ሥጋዊ ውጊያዎች በማሰብ ድል የምናደርግበትን ኃይል ፈጣሪያችን ይሰጠን ጾሙን ከወትሮው በበለጠ ጥንቃቄ ልንጾመው ይገባናል፡፡

የጾሙን ታላቅነት ተረድተን እንድንጾመው የትመጣውን ፣ ትንቢቱን ፣ ምሳሌውንና ምሥጢሩን መረዳት አጋዥ ስለሚሆነን አስቀድመን ስለጾሙ እንማር ዘንድ በአጭሩ ቀርቧል !

ጾመ ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ዕድሜያቸው ለጾም የደረሱ ምእመናን በሙሉ እንዲጾሙአቸው ካወጀቻቸው ሰባት የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጌታችንና በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ አንደበት ቀን የተቀጠረለት ፣ ትንቢት የተነገረለትና ምሳሌ የተመሰለለት ጾምመሆኑ ከአጽዋማት ሁሉ ለየት ያደርገዋል፡፡

ጌታችን ስለዚህ ጾም ትንቢት በመናገር ፣ ምሳሌ በመመሰል ሰፊ ትምህርት የሰጠው ፈሪሳውያን ወደ እርሱ ቀርበው " ደቀ መዛሙርትህ የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው ? " ብለው በጠየቁት ጊዜ ነው፡፡ እርሱም ሲመልስ እንዲህ አላቸው ፦ " ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገርግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ፤ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ፡፡ በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም ፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና ፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል፡፡ በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም ፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል ፤ የወይን ጠጁም ይፈሳል፡፡ አቁማዳውም ይጠፋል፡፡ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል ሁለቱም ይጠባበቃሉ፡፡" [ ማቴ.፱፥፲፬ ]

በዚህ የጌታችን መልስ ውስጥ "ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል በዚያ ጊዜም ይጦማሉ፡፡" የሚል ስለ ጾመ ሐዋርያት የተነገረ የትንቢት ቃል እናገኛለን፡፡ ይህ አምላካዊ ቃል ጾሙ ስለሚጀመርበት ወራት ቀጠሮ ይሰጣል፡፡ ያም ጊዜ ሙሽራው ከእነርሱ ከተወሰደ በኋላ ያለው ጊዜ ነው፡፡ "ሙሽራው ከተወሰደ" በኋላ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ማለት ሲሆን በቤተ ክርስቲያን ጾመ ሐዋርያት ከዕርገት በኋላ የሚጀምረው በዚህ ቃል ምክንያት ነው፡፡ ይህም ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና መጽሐፍቅዱሳዊ መሆኗን ይመሠክራል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡ ወለወላዲቱ ድንግል ፡ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

[ ቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

ይቀጥላል ......

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
3
1
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   [ የጽድቅ በር   ]  🕊


▷   "  ት ክ ክ ለ ኛ ጾ ም   "


[  " በቅዱሳን አባቶቻችን አንደበት ... ! "  ] 

[                         🕊                         ]
----------------------------------------------------


❝ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ ፥ ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ ፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን። ❞ [ ቆላ.፩፥፲ ]


🕊                       💖                   🕊
7
7
🕊

[ † እንኳን ለኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን እና ለእናታችን ቅድስት ማርታ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊 †  አቡነ ተጠምቀ መድኅን  †  🕊

† ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ፲፮፻፲ [1610] ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው ወልደ-ክርስቶስና ወለተ-ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ ፪ [2] ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር ፲፩ [11] ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ጸጋ-እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ::

ሕጻን እያሉ ቃለ-እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም::

ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን: ነብሩን: ተኩላውን ሰብስበው:- "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ: ከፍየሉ: ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን: ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ::

ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: ፳፫ [23] ዓመት ሲሞላቸው ወደ መርጡለ_ማርያም ሔደው መንኩሰዋል:: ከዚሕ ጊዜ በሁዋላ ለ፴፯ [37] ዓመታት:-

፩. በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል
፪. ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል
፫. ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል [ካህን ናቸውና]
፬. ፯ "7" ገዳማትንና ፲፪ "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::

† ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ፷ [60] ዓመታቸው በ፲፮፻፸ [1670] ዓ/ም [በአፄ ዮሐንስ_ጻድቁ ዘመን] ዐርፈዋል:: እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ በጋሾላ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል::

🕊   †  ቅድስት ማርታ  †   🕊

† እናታችን ቅድስት ማርታ በቀደመ ሕይወቷ እጅግ ኃጢአቷ የበዛ ሴት ነበረች:: እጅግ ቆንጆ መሆኗን ሰይጣን ለኃጢአት እንድትጠቀምበት አባበላት:: እርሷም ተቀበለችው:: በወጣትነት ዘመኗ በመልኩዋና በገላዋ በርካቶችን ወደ ኃጢአት ሳበች::

መጽሐፍ እንደሚል ለሁሉም ሰው የመዳን ቀን ጥሪ አለውና አንድ ቀን [በበዓለ ልደት] ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች:: ዘበኛው ግን ሲያያት ተጸይፏልና አትገቢም አላት:: ተከራከረችው: ለመነችው:: ግን አልተሳካላትም:: ሰዓቱ የቅዳሴ ቢሆንም እርሷ እሪ አለች:: ለቅዳሴ የቆሙ ሁሉ በመታወካቸው ዻዻሱ ወጥቶ ገሰጻት::

ያን ጊዜ ነበር ወደ ልቧ የተመለሰችው:: በጉልበቷ ተንበርክካ መራራ ለቅሶን አለቀሰች:: ዻዻሱንም ተማጸነችው:- "እጠፋ ዘንድ አትተወኝ:: ወደ ጌታየ አድርሰኝ" አለችው:: ወዲያውም ወደ ቤቷ ሔዳ የዝሙት እቃዋን አቃጠለች:: ጸጉሯን ተላጨች:: ንብረቷን ሁሉ ለነዳያን አካፈለች:: ዻዻሱም ንስሃ ሰጥቶ ወደ ገዳም አሰናበታት::

ወደ ገዳም ገብታ: በዓት ተቀብላ: ጾምና ጸሎትን ከእንባ ጋር አዘወተረች:: ለ፳፭ [25] ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ከበዓቷ ሳትወጣ: አንድም ሰው ሳታይ ኖረች:: ከማረፏ በፊትም ብዙ ተአምራትን አድርጋለች::

† የቅዱሳን አምላክ ለእኛም እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሐ አይንሳን:: ከበረከታቸውም ያድለን:: †

🕊

[ †  ሰኔ ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅድስት ማርታ ተሐራሚት
፪. አቡነ ተጠምቀ መድኅን ጻድቅ [ኢትዮዽያዊ]
፫. ቅዱስ ኢላርዮን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ኮርዮን ሰማዕት

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ዘካርያስና ስምዖን]
፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭. አቡነ ዜና ማርቆስ
፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል

" አልሞትም : በሕይወት እኖራለሁ እንጂ:: የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ:: መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ:: ለሞት ግን አልሠጠኝም:: የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ:: ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ:: ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት:: ጻድቃን ወደ እርስዋ ይገባሉ:: ሰምተኸኛልና: መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ:: " †  [መዝ.፻፲፯፥፲፯-፳፪] (117:17-22)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2
1
#ሳታቋርጡ__ጸልዩ

"ሥራ የሚሠራ ሰው ቀኑን ሙሉ በጸሎት ተጠምዶ መዋል አይችልም" አትበለኝ፤ ይችላል። በጸሎት የሚያስፈልገው ድምፅ ሳይሆን ሀሳብ ነው ፤ እጅ ሳይሆን እደ ልቦናን ማንሣት ነው፤ አፍአዊ ሳይሆን ውስጣዊ አኳኋን ነው ።ይህን ለማድረግ ደግሞ ቦታም ጊዜም አይገድብህም። በጉልበትህ ባትንበረከክ፤ ደረትህንም ባትደቃ እንኳን መንፈስህ ትጉ ከሆነ
#ጸሎትህ ሥልጡን ነው ።

#ቅዱስዮሐንስአፈወርቅ

          
#መልካም_ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
14👍3
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊  [ ም ክ ረ ቅ ዱ ሳ ን  ]  🕊


▷  ❝ የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው ! ❞


💖  በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ  💖

[                        🕊                        ]
---------------------------------------------------

❝ ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው ፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና። የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው ፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና። ❞

[ ማቴ . ፭ ፥ ፰  ]


🕊                       💖                      🕊
2👍2
9
2025/07/13 18:18:20
Back to Top
HTML Embed Code: