Telegram Web
2
🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡

🕊  †   እንኳን አደረሳችሁ  †  🕊

[ †  ሰኔ ፩  [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  † ]


†  🕊   ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ   🕊

ቤተ-ክርስቲያን በዚህ ስም ብዙ ቅዱሳን አሏት:: በተለይ ደግሞ እስራኤል የተባለ የቅዱስ ያዕቆብ ልጅ ቅዱስ ዮሴፍ ከሁሉም ቅድሚያውን ይይዛል:: ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ላይ በስፋት ታሪካቸው ከተጻፈላቸው ቅዱሳን አንዱ ነው::

ስለዚህ ቅዱስ ዝርዝር መረጃን ለማግኘት ኦሪት ዘፍጥረትን ከምዕራፍ ፴፱ [39] እስከ ፶ [50] ድረስ ማንበብ ይኖርብናል:: ከዚህ በተረፈም በዜና ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሱ ብዙ ተብሏል::

መጽሐፍ ቅዱስ ሲጀምር ስለ ቅዱስ ሰው አዳም ይነግረናል:: ቀጥሎም ስለ ቅዱሳኑ  ፦
- ሴት
- ሔኖክ
- ኖኅ
- ሴም
- አብርሃም
- ይስሐቅና
- ያዕቆብ
ነግሮን ቅዱስ ዮሴፍ ላይ ይደርሳል::

ቅዱስ ዮሴፍ ያዕቆብ [እስራኤል] ከሚወዳት ሚስቱ ራሔል ከወለዳቸው ፪ [2] የስስት ልጆቹ አንዱ ነው:: ቅዱሱ ምንም እናቱ ብትሞተበትም በአባቱና በፈጣሪው ፊት ሞገስ ነበረው:: ምክንያቱም ቅን: ታዛዥና የፍቅር ሰው ነበርና::

እንዲያ አምርረው ለሚጠሉት ወንድሞቹ እንኳን ክፋትን አያስብም ነበር:: ይልቁኑ ለእነሱ ምሳ [ስንቅ] ይዞ ሊፈልጋቸው በበርሃ ይንከራተት ነበር እንጂ::
መንገድ ላይ ቢርበው አለቀሰ እንጂ ስንቃቸውን አልበላባቸውም:: የአባቶቹ አምላክ ግን ድንጋዩን ዳቦ አድርጐ መግቦታል:: ፲ [10] ሩ ወንድሞቹ ግን ስለ በጐነቱ ፈንታ ሊገድሉት ተማከሩ:: ከፈጣሪው አግኝቶ በነገራቸው ሕልም "ሊነግሥብን ነው" ብለው ቀንተውበታልና::
በፍጻሜው ግን በይሁዳ መካሪነት ለዐረብ ነጋድያን ሸጠውታል:: በዚህም ለምስጢረ ሥጋዌ [ለጌታ መሸጥና ሕማማት] ምሳሌ ለመሆን በቅቷል:: ወንድሞቹ ለክፋት ቢሸጡትም ቅሉ ውስጡ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበትና በባርነት በተሸጠበት በዺጥፋራ ቤት ፈጣሪው ሞገስ ሆነው::
ወጣትነቱን በፍቅረ እግዚአብሔር ሸብ አድርጐ አስሮ ነበርና የዺጥፋራ ሚስት የዝሙት ጥያቄ አላንበረከከውም:: "ማንም አያየንም" ስትለውም "እፎ እገብር ኃጢአተ በቅድመ እግዚአብሔር" [ማንም ባያይስ እንዴት በፈጣሪየ ፊት ኃጢአትን አሠራለሁ?] በማለት ከበደል አምልጧል:: ስለዚህ ፈንታም የእሥር ቅጣት አግኝቶታል::
ጌታ ከእርሱ ጋር ቢሆን በእሥር ቤትም ሞገስን አገኘና አለቅነትን ተሾመ:: "ኢኀደረ ዮሴፍ ዘእንበለ ሲመት" እንዲል መጽሐፍ:: ከዚያም የንጉሡን [የፈርዖንን] ባለሟሎች ሕልም ተረጐመ:: ቀጥሎም ንጉሡን በሕልም ትርጓሜ አስደመመ::
ፈርዖንም ቅዱሱን በግዛቱ [ግብጽ] ላይ ሾመው:: ቅዱስ ዮሴፍ በምድረ ግብጽ ነግሦ ሕዝቡን ከረሃብ ታደገ:: ለቅዱስ አባቱ ለእሥራኤልና ክፉ ለዋሉበት ወንድሞቹም መጋቢ ሆናቸው:: አስኔት [አሰኔት] የምትባል ሴት አግብቶም ኤፍሬምና ምናሴ የተባሉ ልጆችን አፍርቷል::
በመንገዱ ሁሉ እግዚአብሔርን አስደስቶ: ከአባቱ ዘንድም ምርቃትና በረከትን ተቀብሎ በ፻፲፩ [110] ዓመቱ በዚህች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፏል:: ወገኖቹም በክብርና በእንባ ቀብረውታል:: "አጽሜን አፍልሱ" ብሎ በተናገረው ትንቢት መሠረትም ልጆቹ [እነ ቅዱስ ሙሴ] ከግብጽ ባርነት ሲወጡ አጽሙን ወደ ከነዓን አፍልሠዋል::

†  🕊 ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት  🕊

ቅዱሱ የተወለደው በ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት ነገሥታቱን ያገለግል ነበር:: ድንግል: ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው::

እርሱ ግን ምን ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ ይጸልየው: ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የታሸ ነውና ብዙ ጉዋደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት: ከክፋት ወደ ደግነት መልሷል::

የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ ጊዜም አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት: ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር::

በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገቱን ተሰይፏል:: ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና በእምነት እንጥራው:: ቤተ ክርስቲያንም ዛሬ የቅዱሱን ተአምራት ታስባለች:: ቅዳሴ ቤቱም የተከበረው በዚሁ ዕለት ነው::

አምላከ ቅዱሳን ወርኀ ሰኔን የፍሬ: የበረከት: የንስሃና የጽድቅ አድርጐ ይስጠን:: ከሰማዕቱ ጽናትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

[ †  ሰኔ ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ [የያዕቆብ ልጅ]
፪. እናታችን አስኔት [የቅ/ ዮሴፍ ሚስት]
፫. ቅዱስ ለውንትዮስ ክቡር ሰማዕት
፬. ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት
፭. ቅዱስ ቆዝሞስ ሰማዕት

[ †  ወርኃዊ በዓላት ]

፩፡ ልደታ ለማርያም
፪፡ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፫፡ ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
፬፡ ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
፭፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

" እንዲህም አላቸው:- "ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ:: አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ አትዘኑ:: አትቆርቆሩም:: እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከእናንተ በፊት ሰዶኛልና . . . እግዚአብሔርም በምድር ላይ ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ: በታላቅ መድኃኒትም አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ:: "  [ዘፍ.፵፭፥፬-፰] (45:4-8)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
1👍1
🕊

† እንኩዋን ለበዓለ ዸራቅሊጦስ [ መንፈስ ቅዱስ ] በሰላም አደረሳችሁ †

[ † በዓለ ጰራቅሊጦስ [ መንፈሰ ጽቅድ ] † ]

ከዚሕ በፊት እንደተመለከትነው የጌታችን ዓበይት በዓላቱ ፪ ጊዜ [ ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው ] ይከበራሉ:: ዛሬም ከ➊➒➐➏ ዓመታት በፊት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን እናስባለን::

† ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

† ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል

- ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ:
- በማሕጸነ ድንግል ተጸንሶ:
- በኅቱም ድንግልና ተወልዶ:
- ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕጻናት አድጐ:
- በ፴ [ 30 ] ዘመኑ ተጠምቆ:
- ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ:
- በፈቃዱ ሙቶ:
- በባሕርይ ስልጣኑ ተነስቶ:
- በአርባኛው ቀን ያርጋል::

ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው ነበርና በተነሳ በ፶ [50] ኛው ቀን: በዐረገ በ፲ [10] ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው::

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች:: ፻፳ [120] ው ቤተሰብ ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ በአምሳለ እሳት አደረባቸው::

ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች: አሮጌ ሕሊና የነበራቸው ሐዲሶች ሆኑ:: በአዕምሮ ጐለመሱ: ቁዋንቁዋ ተናገሩ: ምሥጢርም ተረጐሙ:: በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ::

ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሰዋል:: አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል:: ሳይሳሱም አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል::

" ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ :
ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ:
ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ:: " እንዳለ ደራሲ::

† በዚህ ቀን ፪ [ 2 ] ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ :-

፩. " የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት :- "

† እርሱ ከአብ የሠረጸ: ቅድመ ዓለም የነበረ: በባሕርይ ስልጣኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል የሆነ: የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን ነውና::

፪. " ቅድስት ቤተ ክርስቲያን :- "

† አብ ያሰባት: ወልድ በደሙ የቀደሳት: መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት: አንድም ቤት ናትና:: ዛሬ በጉባዔ ተመስርታለች::

† የመንፈስ ቅዱስ ቸርነቱ ፤ ምሕረቱ ፤ ጸጋው ይደርብን፡፡

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
#ዕርገተ__እግዚእ

+የክብር ባለቤት መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ (በሕማሙ: በሞቱ) ዓለምን አድኖ: ፵ ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል::

+በ፵ኛው ቀን ፻፳ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው: ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ #ዐርጓል::

ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን ዕርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሳኤውን አማናዊ እንደኾነ ለማስረዳት በ፵ኛው ቀን ዐረገ::

አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል::

"ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ::
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን::
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ"
(መዝ. ፵፮:፮)

"እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ #ሰማይም_ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ::"
(ሉቃ. ፳፬:፶-፶፫)

         #መልካም_ዕለተ_ሰንበት🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
9
                       †                        

  [    🕊    ክብርት ሰንበት     🕊   ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ወዮ ይህች ዕለት ያረጀችዋ ያለፈችባት አዲሲቱ የጸናችባት ናት ፤ ወዮ ይህች ዕለት እስረኞች [ ነፍሳት ] የተፈቱባት ባሮች [ ደቂቀ አዳም ] ነጻ የወጡባት ናት። ወዮ ይህች ዕለት የፈረሰ የታነጸባት ሰይጣንም የጠፋባት ናት።

ዳግመኛም ይህች ዕለት በምትሠለጥንበት ጊዜ [ አመ ትሰፍን ወይም ለዘለዓለም ጸንታ በምትኖርበት ጊዜ ] አዲስ ሥራ አዲስ ነገርም ይሆናል ፤ ያን ጊዜ የፀሐይና የጨረቃ የከዋክብትም ብርሃን ፣ ወይም ፀዳል [ ማንም ዓይነት ብርሃን ] ፣ ክረምት ወይም በጋ የለም።

ክብርት የምትሆን ይህች ሰንበተ ክርስቲያን ምን ትደንቅ ! እንደ አብ የሠለጠነች እንደ ወልድ የምትገዛ እንደ መንፈስ ቅዱስ [ ለዘለዓለም ] የምትኖር ናት ፤ ይህች ቅድስት ሰንበተ ክርስቲያን ምን ትደንቅ ! ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ለምኝልን ፣ ስለኛም አማልጂ ለዘለዓለሙ ! ❞

[ ቅዱስ ያሬድ ]

                           †                          


❝ አንተ ግን ከሆድ አውጥተኸኛልና ፥ በእናቴ ጡት ሳለሁም በአንተ ታመንሁ። ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ላይ ተጣልሁ ፤ ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ። ❞

[ መዝ.፳፪፥፱ ]

    [   🕊  ክብርት ሰንበት !  🕊   ]


†                       †                       †
💖                    🕊                    💖
3
3
                       †                           

🕊     [   በዓለ ዸራቅሊጦስ  ]      🕊


🕊  የቤተክርስቲያን የልደት ቀን  🕊

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ጰራቅሊጦስ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል። ❞ [ ዮሐ.፲፬፥፳፮ ፤ ፲፭፥፲፮ ]

ቅዱሳን ሐዋርያት

❝ ከአብ የሠረፀ የሁላችንም መጽናኛ የሚሆን ዓለሙንም ሁሉ ያዳነ ከአብና ከወልድ ጋር ህልው የሚሆን መንፈስ ቅዱስን ላከልን፡፡ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስም አንድ ነው። ...

በዚህች ቀን በሦስት ሰዓት ኢየሱስ  ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና በላያችን ኃይልን ሞላ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን እንዳለው በአዲስ ቋንቋ ተናገርን ፤ ❞ [ ዲድስቅልያ ]

🕊                                              🕊

❝ ጰራቅሊጦስ የሚያነጻና የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም በጉባኤያቸው ነበረ፡፡ ❞ [ መጽሐፈ ምሥጢር ]

❝ ሃሌ ሉያ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ንጹሕ ክቡር ልዩ ነው። ❞ [ ቅዱስ ባስልዮስ ]

[ 🕊 እንኩዋን አደረሳችሁ 🕊 ]


🕊                        💖                    🕊
1
#ሰላም ፡ ለዕርገትከ ፡ ዘኢይትረከብ ፡ መጠኑ ፡
ወለንብረትከ ፡ ሰላም ፡ ለአቡከ ፡ ውስተ ፡ የማኑ ፡
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ፡ እለ ፡ ኪያከ ፡ ተአመኑ ፡
ቅዱሳነ ፡ ዘአምኀቤከ ፡ ወንጹሐነ ፡ ይኩኑ ፡
ጰራቅሊጦስሃ ፡ መንፈሰከ ፡ ፈኑ።

#ትርጉም ፦ጌታየ ኢየሱስ ሆይ ምጥቀቱ ለማይመረመር ዕርገትህ ሰላምታ ይገባል።በአባትህ ቀኝ ለመቀመጥህ #ክብር_ይገባል ።ፈጣሪየ ክርስቶስ ሆይ በአንተ ለሚያምኑና ለሚተማመኑ ሁሉ የተቀደሱ ንጹሐን ይሆኑ ዘንድ አንደ በረዶ የሚያነፃ አንደውሃ የሚያጠራ ካንተ ዘንድ የሚገኝ #መንፈስህን_ላክላቸው

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ
#የእርገት_በዓል በሰላም አደረሳችሁ🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
9
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     ጾ መ ሐ ዋ ር ያ ት     🕊

▷  ❝  በዚያ ጊዜም ይጦማሉ ❞

[   " በመ/ር አምኃ በላይ ... ! "   ]

[                       🕊                       ]
-----------------------------------------------

❝ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።

በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም ፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና ፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።

በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም ፤ ቢደረግ ግን ፥ አቁማዳው ይፈነዳል ፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል ፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል ፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ። ❞

[ ማቴ . ፱ ፥ ፲፭ ]


🕊                        💖                     🕊
                             👇
1
👍2
2025/07/13 10:49:19
Back to Top
HTML Embed Code: