Telegram Web
- በታላቅ ወንድሙ ቅዱስ ባስልዮስ መሪነት ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል::
- በመንኖ ጥሪት ተመስግኗል::
- ተገብቶትም በኑሲስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኗል::
- እርሱ ሲሔድ በከተማው የነበሩ ክርስቲያኖች ፲፩ [11] ብቻ የነበሩ ሲሆን እርሱ ሲያርፍ ክርስቶስን የማያመልኩ ሰዎች ቁጥር ፲፩ [11] ብቻ ነበር::
- ቅዱስ ጐርጐርዮስ ፍጹም ሊቅ ነበርና ከቁጥር የበዙ ድርሳናትን ደርሷል::
- ታላቁን ጉባኤ ቁስጥንጥንያን [በ፫፻፹፩ [381] ዓ/ም] መርቷል:: ብዙ መናፍቃንንም አሳፍሯል::

ከንጽሕናው የተነሳ መላእክት ያቅፉት: እመ ብርሃንም ትገለጥለት ነበር:: ለ፴፫ [33] ዓመታት እንደ ሐዋርያት ኑሮ በዚህ ቀን ድንግል ጠራችው:: ቀድሶ አቁርቦ: ሕዝቡን አሰናብቶ: የቤተ መቅደሱን ምሰሶ እንደ ተደገፈ ዐርፎ ተገኝቷል:: በዝማሬና በፍቅር ቀብረውታል::


🕊 †  ቅድስት ኢላርያ   †  🕊

† "ኢላርያ" ማለት "ፍሥሕት [ደስ የተሰኘች]" እንደ ማለት ነው:: ከተባረኩ ቅዱሳት አንስት ትልቁን ሥፍራ ትይዛለች:: ማን እንደ እርሷ !

ቅድስት ኢላርያ ማለት :-

- የታላቁ ንጉሠ ነገሠት: የደጉ ዘይኑን [Emperor Zenon] የበክር ልጅ
- በ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደች
- ትምሕርተ ሃይማኖትን: ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የተማረች
- ምድራዊ ንግሥናን ንቃ ፍቅረ ክርስቶስን የመረጠች
- የአባቷን ቤተ መንግስት ትታ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ [ገዳመ አስቄጥስ] የወረደች:
- ስሟን ከኢላርያ ወደ ኢላርዮን ቀይራ በወንዶች ገዳም የመነኮሰች
- ራሷን በፍጹም ገድል ቀጥቅጣ ከወንዶቹ በላይ በሞገስ ከፍ ከፍ ያለች
- ትንሽ እህቷን ጨምሮ በርካቶችን የፈወሰች
- በእርሷ ምክንያት ለግብጽና በመላው ዓለም ለሚገኙ ገዳማት ብዙ ቸርነት በዘይኑን የተደረገላት ታላቅ እናት ናት::

ቅድስት ኢላርያ ማንም ሴት መሆኗን ሳያውቅባት: አባ ኢላርዮን እንደ ተባለች በዚህች ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስቲያንም እነሆ ላለፉት ፩ ሺህ ፬ መቶ [1,400] ዓመታት: ቅድስቲቱንና የተባረከ አባቷን ዘይኑንን: ስለ በጐነታቸውና ውለታቸው ታስባቸዋለች::

† የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን:: †

[  † ጥር ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት  ]

፩. በዓለ አስተርዕዮ ማርያም [እመቤታችን ከእረፍቱዋ በሁዋላ ለደቀ መዛሙርት በዚሁ ቀን ተገልጣ ነበር]
፪. ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ [ታላቅ ሊቅና ጻድቅ]
፫. ቅድስት ኢላርያ እናታችን [የዘይኑን ንጉሥ ልጅ]
፬. ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ
፭. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
፮. ቅዱስ ኒቆላዎስ ሰማዕት
፯. አባ ፊቅጦር

[    † ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. አባ ምዕመነ ድንግል
፪. አባ አምደ ሥላሴ
፫. አባ አሮን ሶርያዊ
፬. አባ መርትያኖስ
፭. አበው ጎርጎርዮሳት

" ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን:: እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን:: አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ:: አንተና የመቅደስህ ታቦት:: ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ:: ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው:: ስለ ባሪያህ ስለ ዳዊት. . ." [መዝ.፻፴፩፥፯]

" ወዳጄ ሆይ ! ተነሺ:: ውበቴ ሆይ ! ነዪ:: በዓለት: በንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ ቃልሽ መልካም: ውበትሽም ያማረ ነውና: መልክሽን አሳዪኝ:: ድምጽሽንም አሰሚኝ:: " [መኃ.፪፥፲፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🙏2👍1
❤‍🔥42
"#የህይወት_እናት_ድንግል_ማርያም__ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤
እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል።

#የኃጢአቴ__ቁስል ያላንቺ ጸሎት እንዳይድን ልዑል እግዚአብሔር ያውቃልና፣ ኃጢአቴ ከዓለም ሉሉ ኃጢአት እንዲበልጥ ተረዳ፣ ንጽሕናሽ ደግሞ ከቅዱሳን ሁሉ ንጽሕና እንዲበልጥ እንዲበዛ ዐወቀ። ለዚህም #ፍቅርሽን_በልቡናዬ ጨመረ። ጽኑ ቁስል ያለ ጽኑ ዕፁብ ድንቅ መድኃኒት እንዳይጠግ ያውቃልና።

#የእግዚአብሔር የጥበቡ ርቀት ምን ይረቅ ምን ይጠልቅ? ...ደግነቱና ይቅርታውንስ ማን ይናገራል። በኃጢአት ቁስለኞች ፊት #መድኃኒት አዘጋጀ። ተቀብተው በእርሱ እንዲድኑ ነው።

#ድንግል_ሆይ፤ የእኔን አመንዝራነቴን እናገራለሁ ያንቺን ንጽሕና የልጅሽኝ ቸርነት አወራለሁ። #ድንግል_ሆይ የኔን ስሕተት ያንቺን ማማለድ የልጅሽንም መታገስ እናገራለሁ። #ድንግል_ሆይ የኔን ስንፍና ያንቺን ምክር የልጅሽንም ይቅርታ እናገራለሁ።"

እንኳን ለአስተርዮ ማርያም በዓለ እረፍት በሰላም አደረሳችሁ ልመናዋ ፍቅሯ አማላጅነቷ አይለየን አሜን🙏🙏

       #_መልካም_በዓል🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
11❤‍🔥1
                        †                             

 †   🕊  ንግሥታችን ፣ እናታችን  🕊  †

💖

❝ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ! ተዝቆ ከማያልቀው ጸጋሽ እንባረክ ዘንድ እነዚኽ ጥቃቅኖች ቃሎቻችንን እንደ ቁም ነገር ቈጥረሽ ተቀበዪልን  ከመትከፈ ልቡናችን እንደወጡና ክብርሽን ለማመስገን የበቁ እንደኾኑ አድርገሽ ተቀበዪልን።

ጸጋን የተመላሽ ፣ እመቤታችን ፣ ንግሥታችን ፣ እናታችን ፣ ወላዲተ አምላክና ዓለም በመላ የሚቀደስበትን መዝገብ የተሸከመች አማናዪቱ ታቦት ሆይ ከንግግሮቻችን አንዳች መልካም ነገር ብታገኚባቸው እያልን እኛና ፍጥረታት ኹላችን አምኃ ዝማሬያችንን እናቀርብልሻለን ...

ድንግል ሆይ ! በእውነቱ አንቺ ከታላላቆች ይልቅ ታላቅ ነሽ ማኅደረ ቃለ አብ ሆይ ! አንቺን ሊተካከል የሚችል ታላቅ ማን ነው ? ድንግል ሆይ ! ከየትኛው ፍጥረት ጋር አወዳድርሻለኊ ?

አንቺ ቀድሞ በወርቅ ካጌጠችው የሕጉ ታቦት ይልቅ በንጽሕና ያጌጥሽ ታላቅ ነሽ ! እውነተኛውን መና የተሸከምሽ የወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ መና የተባለውም መለኮት የተዋሐደው ሥጋው ነው። ❞

[    ቅዱስ አትናቴዎስ    ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
❤‍🔥7🥰2👍1
6❤‍🔥4
                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]

            [     ክፍል  ሰባ ሰባት     ]

                         🕊  

[  አባ ወቅሪስን ስለ ክፉ ሃሳቦች አስተማረው ! ]

🕊

❝ አባ ወቅሪስ ከሌሎች አኃው ጋር አብሮ ከአባ መቃርዮስ ጋር ተቀምጦ ሳለ አባ መቃርዮስን ፦ “ ሰይጣን በወንድሞች ላይ ይወረውራቸውና ይፈትንባቸው ዘንድ እነዚህን ሁሉ ክፉ ሃሳቦች እንዴት ሊያገኝ ቻለ? ” ብሎ ጠየቀው፡፡

አባ መቃርዮስም እንዲህ አለው ፦ “በምድጃ እሳት የሚያነድ ሰው በእጁ ብዙ ማቀጣጠያ እንጨት ይይዛል ፣ ያንንም ወደ ምድጃው ከመጣል አያመነታም ፣ ወደ ኋላም አይልም፡፡ ዲያብሎስም እንደዚህ ነው፡፡ እሳቶችን ይለኩሳል ፣ ያቀጣጥላል ፣ ከዚያም ወደ እያንዳንዱ ሰው ልቡና ማንኛውንም ዓይነት የክፉ አቀጣጣይ የሆኑ ነገሮችን ማለትም ርኩሰቶችን ከመጣልና የተለኮሰውን እሳት አብዝቶ እንዲነድ ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም፡፡

ውኃ የእሳትን ኃይል እንደሚያጠፋውና አሸናፊው እንደ ሆነ እናያለን፡፡ እኛን የሚረዳንና የሚጠብቀን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይልና ድል የማይነሣው የመስቀሉ ኃይልም እንዲሁ ነው፡፡

ድካማችንን ከእርሱ እግር ሥር ብንጥል የዲያብሎስ ክፉ ሃሳቦች ከነ ቅርንጫፎቻቸው ከእኛ ውስጥ ይጠፋሉ ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ልባችን በሰማያዊ እሳት በመንፈስ እንዲቃጠልና በሐሤት እንዲሞላ ያደርገዋል፡፡ ❞

🕊

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


💖                      🕊                      💖
5👍1
8
                         †                        

 [       🕊    ፍኖተ ቅዱሳን    🕊      ]

[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

             [        መታዘዝ !         ]

🕊

❝  አንድ አረጋዊ " ለመንፈሳዊ አባቱ በመታዘዝ የሚኖር ወደ በረሃ ሄዶ ብቻውን ከሚኖር የበለጠ ይጠቀማል።" አለ፡፡
..................

አባ ሚናስ እንዲህ አለ ፦ " መታዘዝ መታዘዝን ይጠራዋል። አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ሲታዘዝ እግዚአብሔር ደግሞ ልመናውን ይሰማዋል። "
..................

አንድ አረጋዊ እንዲህ አለ ፦ " ዕድገት የማናሳይበት ምክንያት ዓቅማችንንና ልካችንን ስለማናውቅ ነው። እንዲሁም በጀመርነው ሥራ ስለማንጸናና የመልካም ምግባር ሕይወትን [ የቅድስና ሕይወትን ] እንዲሁ ያለ ድካም ማግኘት ስለምንፈልግ ነው። ❞

🕊

የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡


†                         †                         †
💖                      🕊                      💖
👍1
3
#ድንግል_ሆይ_ትወጅኛለሽ🙏🙏
የህይወት እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል፤ የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትወጂኛለሽን? ብየ አልጠይቅሽም ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለአለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና፤ አትናፍቂኝምን? ብየም አልጠይቅሽም ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና፤ ሆኖም እመቤቴ ሆይ፦ እንደ ቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም እንደ ዮሃንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ የዮሃንስ ፀጋ ግን የለኝም፤ እናቴ ሆይ፦ እንደ ኤልሳዕ የልቦናዬ አይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና አዝናለሁ ኤልሳዕ በፀሎት ሃይል የግያዝን አይን እንዳበራ አንቺም አይኔን ታበሪልኝ ዘንድ ሃይልሽን በእኔ ላይ አበርቺ፡፡ ድንግል ሆይ፦ ይህን የምል የእምነት ማረጋገጫ ፈልጌ አይደለም በልጅሽ መሰረትነት የታነፅኩኝ በልጅሽ ስምም የተጠመቅኩኝ ነኝና፤ ነገር ግን ስለምትናፍቂኝ ይህን አልኩኝ ስለዚህም ነይ ነይ እምየ ማርያም እያልኩኝ እንደ እናቶቼም እለምንሻለሁ፡፡ የብርሃን ልብስሽን ለብሰሽ ነይ የክብር አክሊልሽን ደፍተሽ ነይ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ነይ እናይሽ ዘንድ ነይ፡፡"
የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን

የአመት ሰው ትበለን 🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
5❤‍🔥1
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊

▷   "  ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው ! "

[    💖   አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ   💖    ] 

[                        🕊                        ]
-------------------------------------------------

ዘይትህ መልካም መዓዛ አለው ፤ ስምህ እንደሚፈስስ ዘይት ነው ፤ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ።

ሳበኝ ፥ ከአንተም በኋላ እንሮጣለን ፤ ንጉሡ ወደ ቤቱ አገባኝ በአንተ ደስ ይለናል ፥ ሐሤትም እናደርጋለን ፤ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እናስባለን፤ በቅንነት ይወድዱሃል። ❞

[ መኃ.፩፥፫ ]


🕊                       💖                     🕊
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊

▷   "  ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው ! "

[    💖   አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ   💖    ] 

[                        🕊                        ]
-------------------------------------------------

ዘይትህ መልካም መዓዛ አለው ፤ ስምህ እንደሚፈስስ ዘይት ነው ፤ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ።

ሳበኝ ፥ ከአንተም በኋላ እንሮጣለን ፤ ንጉሡ ወደ ቤቱ አገባኝ በአንተ ደስ ይለናል ፥ ሐሤትም እናደርጋለን ፤ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እናስባለን፤ በቅንነት ይወድዱሃል። ❞

[ መኃ.፩፥፫ ]


🕊                       💖                     🕊
1👍1
🔥5
🕊

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †

[  † ጥር ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

🕊   †   አባ እንጦንስ  †   🕊

በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ " ታላቁ / ዓቢይ / THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው:: አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው:: በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን::

ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::

ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም [በበርሃ] ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::

ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::

ከጌታ ዕርገት በኋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::

ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ፹ [80] ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ 'የባሕታውያን አባት'
ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::

ይህ ከሆነ ከ፳ [20] ዓመታት በኋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኳሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::

እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::

🕊  †  አባ እንጦንስ  †  🕊

አባ እንጦንስ የመነኮሳት ሁሉ አባታቸው: ለገዳማውያን ሁሉም ሞገሳቸው ናቸው:: እንዲያውም ብዙ ጊዜ "ኮከበ ገዳም: ማኅቶተ ገድል [የበርሃው ኮከብ: የተጋድሎ መብራት]" ተብለውም ይጠራሉ::

ቤተ ክርስቲያን ለጀማሪዎች ትልቅ ትኩረት ትሰጣለች:: ለምሳሌ:- አባ ዻውሊን [የካቲት ፪ የሚከበሩ] ለብሕትውና መሠረትን ስለ ጣሉ "አበ ባሕታውያን" ብላ ታከብራለች:: አባ እንጦንስን ደግሞ "አበ መነኮሳት [የመነኮሳት አባት] : ቀዳሚሆሙ ለመነኮሳት [ለመነኮሳት ቀዳሚና ጀማሪ] ስትል ትጠራቸዋለች::

አባ እንጦንስ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለሚነሱ ቅዱሳን መነኮሳት ሁሉ መንገድን ይጠርጉ ዘንድ ብዙ መከራን በትዕግስትና በአኮቴት ተቀብለዋል:: ላለፉት ፩ ሺህ ፯ መቶ [1,700] ዓመታት እንደ ሻማ እየቀለጡ ያበሩ አበው ቅዱሳን ሁሉ የአባ እንጦንስ ልጆች ናቸው::

ከምጥ የከፋ የዲያብሎስ ፈተናን ተቀብለው ከመንፈሳዊ አብራካቸው ቅዱሳኑን ወልደዋል:: የመነኮሳት አለቃ የሆኑትን ታላቁን መቃርዮስን ጨምሮ በርካቶችን አመንኩሰው ለቅድስና አብቅተዋል::

አባ እንጦንስ ግብጻዊ ሲሆኑ የተወለዱት አቅማን በምትባል ቦታ አካባቢ ነው:: ጊዜውም በ፪መቶ ፶፪ [252] ዓ/ም ነው:: የተባረኩ ወላጆች ለቅዱሱ እንጦንስና አስከትለው ለወለዷት ሴት ልጃቸው አስቀድመው ፍቅረ ክርስቶስን: አስከትለውም ሃብት ንብረታቸውን አውርሰው ዐርፈዋል::

በዚህ ጊዜ የአባ እንጦንስ እድሜ አፍላ ወጣትነት ላይ ነበር:: በልጅነት ጊዜአቸውም አባ እንጦንስን ሲስቁ: ሲጫወቱ: አልያም ሲቀልዱ አየሁ የሚል ሰው አልነበረም:: ፍጹም ቁም ነገረኛና ታዛዥ: በዚያ ላይም አስተዋይ ነበሩና ሙሉ ጊዜአቸውንም ከቅዱስ ቃሉ በመመገብ: በትምሕርትና በማስቀደስ ያሳልፉ ነበር::

ዘወትርም ዜና ሐዋርያትን እያነበቡ በመንፈሳዊ ቅናት ይቃጠሉ ነበር:: በጊዜው የምናኔ ሕይወት ጐልቶ ባለ መገለጡ አባ እንጦንስ የሚያደርጉት ይጨንቃቸው ነበር:: ሲጸልዩም "አበው ሐዋርያት ይሕንን ክፉ ዓለም ንቃችሁ ጌታችሁን የተከተላችሁበት ጥበብ እንደ ምን ያለ ነው!" እያሉ ይደነቁ ነበር:: መሻታቸውን ያወቀ ጌታም ምሥጢርን ገለጠላቸው::

አንድ ቀን በቅዳሴ ላይ ወንጌል ሲነበብ ካህኑ ስለ ምናኔ የሚጠቅሰውን ክፍል አነበበ:: ለአንድ ባለ ጠጋ ሕግጋትን ከነገረው በኋላ "ፍጹም ልትሆን ከወደድክስ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ተከተለኝ" [ማር.፲፥፲፯] የሚለውን ጥቅስ ሲሰሙ ተገርመው "ጌታ ሆይ! ይህንን የተናገርኸው ለእኔ ነው" ሲሉ አሰቡ:: በቀጥታም ሃብታቸውን ለአካባቢው ሰው አካፍለው: እህታቸውን ከደናግል ማኅበር ደምረው እርሳቸው ወደ ዱር ሔዱ::

ከዚህች ቀን ጀምረው አባ እንጦንስ ከ፹ [80] እስከ መቶ ለሚገመቱ ዓመታት ከአጋንንት ጋር በጦርነት ነበር የኖሩት:: በንጹሕ አምልኮታቸውና በቅድስናቸው የቀና ጠላት ሰይጣን በብዙ ጐዳና ፈተናቸው:: አቅም ቢያጥረው አራዊትን መስሎ ታገላቸው::

በዚህ አልሳካ ቢለው የእሳት ሰንሰለትን አምጥቶ ገረፋቸው:: በሞትና በሕይወት መካከል ጥሏቸው ሔደ:: ወድቀው ያገነኟቸው ሰዎች ለዘመዶቻቸው ሰጥተዋቸው አገገሙ:: ልክ ሲነቁ ግን ፈጥነው ወደ በርሃ ተመለሱ::

ሰይጣን በርሃው የቅዱሳን ማደሪያ እንዳይሆን ሰግቷልና ጨክኖ ታገላቸው:: ግን አልቻላቸውምና ተረታ:: አምላከ ኃያላን ክርስቶስ ከቅዱሱ ጋር ነበርና:: ከዚህ በኋላ ግን ጸጋው በዝቶላቸው ድውያንን የሚፈውሱና ሰይጣን የማይቀርባቸው ሰው ሆኑ::

በረዥም ዘመነ ቅድስናቸውም :-

፩. ብዙ አርድእትን ከመላው ዓለም ሰብስበው: አስተምረው: ምናኔ ከግብጽ ማዶ በመላው ዓለም አስፋፉ::
፪. በደመና እየተጫኑ ብዙ አሕጉራትንም እየዞሩ ሰበኩ:: በዚህም አሕዛብን ወደ እምነት: ኃጥአንን ወደ ንስሃ መለሱ::
፫. ጊዜው ዘመነ ሰማዕታት ነበርና ወደ አደባባይ ሒደው ከሃዲዎችን ገሠጹ:: ማንም ደፍሮ ግን አልገደላቸውም::

እነዚህንና ሌሎች ተግባራትን እየሠሩ በቅዱስ ሚካኤል እጅ መነኮሱ:: እርሳቸውም ብዙዎችን አመነኮሱ:: አርጅተው እንኳ ከተጋድሎ ያላረፉት አባታችን የጣመ ነገር ቀምሰው: ገላቸውን ታጥበው አያውቁም:: በ፫፻፸፪ [372] ዓ/ም በዚህች ቀን ሲያርፉም ዕድሜአቸው ፻፳ [120] ደርሶ ነበር::

የአባ እንጦንስን በዓል ለማክበር የምትሹ ቤተ ክርስቲያናቸው ጎንደር ከተማ ከቀሃ ኢየሱስ በላይ ይገኛል::

" ለአባታችን እንጦንዮስ / እንጦንስ / እንጦኒ ክብር ይገባል::"
3👍1
2025/07/09 10:55:15
Back to Top
HTML Embed Code: