Telegram Web
6
#ጌታችን ስምኦን ቤት ተቀምጦ ሳለ፣ መላ #ህይወቷን_ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቶዋ ማርያም)፤‹‹ከእንግዲህ ወዲህ #በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን #ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል #አምላክ_መጣ›› ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦሰት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በጠጉሩ(በራሱ)ላይ በማርከፍከፍ ጌታችንን ቀብታዋለች በረከቷ ይደርብን

     
#መልካም__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
11🙏5
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[ 💖 መንፈሳዊው መሰላል 💖 ]


[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ] "መንፈሳዊው መሰላል" ድርሳን ]

🕊

❝ የሕይወት ምንጭ እግዚአብሔር እንደ መሆኑ ፣ ከእርሱ ውጭ በራሱ ሕይወት ያለው ነገር የለም፡፡

ስለሆነም መንፈሳዊ ሕይወት ስንል ሰዎችና መላእክት ከእግዚአብሔር ሕይወትነት ያላቸው ሱታፌ ሲሆን ይህ ሱታፌም አንድ ቦታ ላይ የሚያቆምና የተገደበ ሳይሆን እያደገ የሚሄድ ነው፡፡

እግዚአብሔር ፍጻሜ የሌለውና “እስከዚህ ድረስ” ተብሎ የማይወሰን አምላክ እንደመሆኑ ፣ ከእርሱ ጋር ኅብረትና አንድነት ይኖራቸው ዘንድ በእርሱ ሕይወት የሚሳተፉ ሁሉ ጉዟቸው መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ የለውም፡፡ የመንፈሳዊ ጉዞ አስደሳችነቱም ይህ ነው ፤ ወደማይደረስበት ፣ ግን ደግሞ ከመጀመሪያው ጀምሮ አብሮ ወዳለ አምላክ የሚደረግ የማያቋርጥ ጉዞ !

ይህ ጉዞ ፣ ያዕቆብ ከምድር እስከ ሰማይ ተዘርግቶ ባየው መሰላል አንጻር ሥዕላዊ በሆነ ሁኔታ ተገልጦልናል፡፡ በመሰላሉ ላይ [ ከመሰላሉ ጫፍ ላይ ሳይሆን ከመሰላሉ በላይ ] እግዚአብሔር “ተቀምጦ” ነበር፡፡ መሰላሉ በመሬት ላይ የተዘረጋ መሆኑ እግዚአብሔር ወደ እርሱ የምንወጣበትን የቅድስና መሰላል ልንደርስበት በምንችለው በመሬት ላይ የዘረጋልን መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ፣ እግዚአብሔር ከመሰላሉ በላይ ቆሞ መታየቱ ደግሞ ከላይ ሆኖ “አይዟችሁ ፣ ወደ እኔ ኑ" እያለ በፍቅሩ የሚጠራንና የሚስበን እርሱው ራሱ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ስለዚህ ከታች ከመሬቱ ጀምሮ የሚጠራንና የሚስበን ፣ በመሰላሉ ላይ የትኛውም ደረጃ ላይ ብንደርስም አሁንም ከዚያ በላይ ወዳለው እንድንቀጥል የሚያደርገን ከመሰላሉ በላይ ያለው እርሱ ነው፡፡

እንደዚያ ሆኖም ግን እርሱ ከመሰላሉ በላይ [ ማለትም በባሕርዩ ሊደረስበት የማይችል ] ነው፡፡ እግዚአብሔር ማለት ይህ ነውና ፤ ከራሳችን በላይ ለራሳችን የቀረበ የውስጥና የቅርብ መጋቢና ተንከባካቢ አባት ፣ ሆኖም ግን በባሕርዩ የማይታወቅና የማይደረስበት ረቂቅ አምላክ ! ❞

[   ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]  "መንፈሳዊው መሰላል" ድርሳን ትርጓሜ ላይ የሰጡት አስተያየት  ]


🕊                       💖                     🕊
🥰3
👍54
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊

▷     "  አ  ስ  ተ  ካ  ክ  ለ  ኝ  "

[   💖  አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ  💖  ]

[                        🕊                        ]
-------------------------------------------------

❝ ትእዛዝህን እንደ ወደድሁ ተመልከት ፤ አቤቱ ፥ በምሕረትህ ሕያው አድርገኝ። የቃልህ መጀመሪያ እውነት ነው ፥ የጽድቅህንም ፍርድ ሁሉ ለዘላለም ነው። ❞

[   [ መዝ. ፻፲፱፥፻፶፱ ]  ]


🕊                       💖                     🕊
2
Audio
😢2
😢3
🕊

[  † እንኳን ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ዼጥሮስ እና ለ፻፶ [150] ው ቅዱሳን ሊቃውንት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †  ቅዱስ ዼጥሮስ ሰማዕት †  🕊

† የቅዱሳን ሰማዕታት መነሻቸው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን ፍጻሜአቸው ደግሞ ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት ነው::

ይህ ቅዱስ የሚታወቀው "ተፍጻሜተ ሰማዕት [የሰማዕታት መጨረሻ]" በሚለው ስሙ ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
የቅዱሱ ሃገረ ሙላዱ ግብጽ ናት:: ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ወላጆቹ ካህን ቴዎድሮስና ቡርክት ሶፍያ ልጅ አጥተው ሐምሌ ፭ ቀን ወደ ፈጣሪ ቢማጸኑ በራዕይ ዼጥሮስ ወዻውሎስ ተገልጠው ብሥራትን ለሶፍያ ነገሯት:: በወለደችው ጊዜም በራዕዩ መሠረት "ዼጥሮስ" አለችው::

ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜም ለቤተ እግዚአብሔር ሰጥተው በሊቀ ዻዻሳቱ ቅዱስ ቴዎናስ እጅ አደገና በወጣትነቱ ሊቅ: ጥዑመ ቃልና በጐ ሰው ሆነ:: ዲቁናና ቅስናን ተሹሞ ሲያገለግል ቅዱስ ቴዎናስ በማረፉ ቅዱስ ዼጥሮስን የግብጽ ፲፯ [17] ኛ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት::

ዘመኑ ደግሞ እጅግ ጭንቅ ነበር:: ክርስቲያኖች በተገኙበት ስለሚገደሉ: አብያተ ክርስቲያናትም ስለ ተቃጠሉ የቅዱሱ መከራ የበዛ ነበር:: ለ፲፬ [14] ዓመታት በፍጹም ትጋት ከመንጋው ጋር ተጨነቀ::

አርዮስን [ተማሪው ነበር] አውግዞ ለየው:: ከጌታ ጋርም ብዙ ጊዜ ተነጋገረ:: ብዙ ተአምራትንም ሠራ:: በዚህ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን በመንበረ ዽዽስናው ላይ አልተቀመጠም:: በሁዋላ ግን ጨካኙ ንጉሥ እንዲገደል አዘዘ::

ሕዝቡ "ከእሱ በፊት እኛን ግደሉን" በማለታቸው ሁከት እንዳይነሳ ቅዱስ ዼጥሮስ ተደብቆ ሔደና በፈቃዱ ለወታደሮች ተሰጠ:: በዚያች ሌሊትም የእርሱ ደም የግፍ ማብቂያ እንዲሆን እያለቀሰ ጮኸ:: ከሰማይም "አሜን! ይሁን!" የሚል ቃል መጣ:: ያን ጊዜ የእርሱ አንገት ተሰየፈ:: ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ::

† የቅዱሳንን ዝክር ከማንበብ ባለፈ በስማቸው መጸለይ [ዘፀ. ፴፪፥፲፫ ] : በምጽዋትም ማሰብ [ ማቴ.፲፥፵፩ ] ይገባል::

† ወርኀ የካቲትን ይባርክልን !

🕊

[  † የካቲት ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ፻፶ [ 150 ] ቅዱሳን ሊቃውንት ዻዻሳት [በቁስጥንጥንያ ተሠብሥበው መናፍቃንን ያወገዙበት: ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን ያፀኑበት /ጉባዔ ቁስጥንጥንያ/ በ፫፻፲፰ [381] ዓ/ም::
ከወቅቱ ቅዱሳን ሊቃውንት እነዚህ ይጠቀሳሉ:-
- ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
- ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ
- ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት
- ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም
፪. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት [ቅዳሴ ቤቱ]
፫. ታላቁ ቴዎዶስዮስ ጻድቅ [ንጉሠ ቁስጥንጥንያ]

[   † ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. ልደታ ለቅድስት ድንግል ማርያም እግዝእትነ
፪. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
፬. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
፭. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

" ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ዻዻሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በሁዋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ 3 ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቁዋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ:: " † [ ሐዋ. ፳፥፳፰ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
👍1
2👍2
#ቅዳሴ__ማርያም

✥ ድንግል ሆይ ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ።

✥ ድንግል ሆይ በቤተ ልሔም ካንቺ የተወለደውን መወለድ በጨርቅ የተጠቀለለውንም አድግና ላህም በብርድ ወራት እስትንፋስን ያሟሟቁትንም አሳስቢ።

✥ ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ከርሱ ጋር ካገር ወደ አገር ስትሸሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ።

✥ ድንግል ሆይ ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የፈሰሰውን መሪር ዕንባ አሳስቢ።

✥ ድንግል ሆይ ረኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ኃዘኑን ከርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ።

✥ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ መዓትን አይደለ ምሕረትን አሳስቢ።

✥ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥአን አሳስቢ ለንጹሓን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ።


#መልካም_ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
8🥰3❤‍🔥2
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊          ጾ መ ነ ነ ዌ             🕊

  [  እንኳን ለነነዌ ጾም አደረሰን   ]

🕊                        💖                      🕊

- ሰኞ = የካቲት ፫ [ 3 ]
- መላው ኦርቶዶክሳዊ
- በንስሐ በምሕላ ጸሎት

🕊

❝ የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ፥ ለጾም አዋጅ ነገሩ ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ ። ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናጸፊያውና አወለቀ ማቅም ለበለ ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ ። አዋጅም አስነገረ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንቱን ትእዛዝ አሳወጀ ፥ እንዲህም አለ ፦ ሰዎችን እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን እንዳይቀምሱ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ ፥እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ ፥ ከጽኑ ቁጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል ?

እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ በሥራቸውን አየ ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም። ❞

[ ት.ዮናስ ፫፥፭ -፲ ]

🕊                        💖                      🕊

❝ ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ ፥ ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፉ። እኔም። ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ አልሁ። ❞ [ዮና.፪፥፬]


🕊                        💖                      🕊
4👍2
Audio
3😢1
5🥰1
                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ]

🕊             
             
❝ ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል ? ቃልህን በመጠበቅ ነው። ❞  [ መዝ . ፻፲፱ ፥ ፱  ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ሕይወተ ወራዙት [ የወጣቶች ሕይወት ! ]

          [   ክፍል -  አሥራ ሁለት  -    ]

            💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

      [    ድንግልናን መጠበቅ    ]


የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]


🕊                        💖                      🕊
                             👇
👏2
2025/07/09 13:28:32
Back to Top
HTML Embed Code: