Telegram Web
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊

▷     "  የሚያበራ ንጽሕና !  "

[   💖   አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ   💖   ]

[                        🕊                        ]
-------------------------------------------------

❝ ወዳጆች ሆይ ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን ፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።

በእርሱም ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል። ❞

[   ፩ዮሐ.፫፥፪  ]


🕊                       💖                     🕊
4
Audio
🥰2
5
🕊

[  † እንኳን ለቅዱሳን ጻድቃነ ዴጌ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †   ጻድቃነ ዴጌ   †  🕊

† እነዚህ ጻድቃን ኢትዮዽያውያን ባይሆኑም ያበሩት በሃገራችን ነው:: ቅዱሳኑ በቁጥር ፫ ሺህ [3,000] : በዜግነት ሮማውያን ናቸው:: ከሺህ አዝማናት በፊት ከሮም ግዛት ተሰባስበው እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮዽያ [አክሱም] መጥተዋል::

ቀጥለውም እዛው አካባቢ ወደሚገኝ ገዳም ገብተዋል:: ይህ ቦታ ለአክሱም ቅርብ ሲሆን በዘመነ ሐዋርያት የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ በዓት ነበር:: የሐዋርያው በትረ መስቀልም እስካሁን አለች::

ጻድቃነ ዴጌ ሕጋቸው አንዲት : እርሷም ፍቅር ናት:: ለዘመናት በፍቅረ ክርስቶስ ታሥረው : ፍቅርን ለብሰው : በፍቅር ኑረዋል:: ሁሌም በ፳፱ [29] የጌታችንን ስም እየጠሩ ጽዋ ጠጥተዋል:: ስለ ፍቅራቸውም ጌታችን ፫ ሺህ ፩ኛ [3,001] ኛ ሆኖ : ነዳይ መስሎ አብሯቸው ጠጥቷል::

በመጨረሻም ፫ ሺው በአንድነት ተሠውረዋል::

† ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን:: እኛንም በወዳጆቹ ጸሎት ይማረን:: . . .አሜን !

🕊

[   † ጥር ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ጻድቃን ቅዱሳን ማሕበረ ዶጌ [ዴጌ ጻድቃን]
[አክሱም አካባቢ በቁጥር ወደ ፫ ሺህ [3,000] ሲሆኑ ከመድኃኔ ዓለም ጋር ማሕበር ይጠጡ የነበሩና በአንድ ላይ የተሠወሩ ቅዱሳን ናቸው]
፪. አባ ገብረ ናዝራዊ ዘቃውንት [ኢትዮዽያዊ]
፫. ቅድስት አክሳኒ ፈላሲት
፬. ቅዱስ ሰርያኮስ ሰማዕት
፭. አባ እስጢፋኖስ ገዳማዊ
፮. ከድሮዋ ሮም የተነሱ ቅዱሳት አንስት

[    † ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. ቅድስት አርሴማ ሰማዕት
፪. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ እናታችን
፫. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍፃሜተ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፭. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ

" ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘለዓለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም:: " † [መዝ.፴፮፥፳፱]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🙏1
9❤‍🔥1
#_______ፀሎት

#ፀሎት ልማድህ ሲሆን ተአምራቶች የህይወትህ ዘይቤ ይሆናሉ።
#ፀሎት የሰው ልጅ ካለምንም የአለማዊ ኔትዎርክ ዝርጋታ በቀጥታ #ከእግዚአብሔር ጋር የምንነጋገርበት የመገናኛ መስመር ነው።
#ፀሎት ዘር ነውና መኸር አለው፣
#ፀሎት እንባ ነውና ሳቅ አለው፣
#ፀሎት ትግል ነውና ድል አለው፣
#ፀሎት ጩኸት ነውና መልስ አለው፣
#ፀሎት መንበርከክ ነውና ማሸነፍ አለው
በእግዚአብሔር ፊት #የሚንብረከክ ሰው በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ መቆም ይችላል።
#በፀሎት የማይቻለው ይቻላል🙏🙏🙏

#መልካም__ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
11🙏4
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[ የመርሐ-ግብር ማሳወቂያ ! ]

🕊

[ 💖 መንፈሳዊው መሰላል 💖 ]

እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በቀኑ መርሐ-ግብር የቅዱስ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ] ድርሳን ላይ "መንፈሳዊው መሰላል" በሚል ርዕስ የቀረበው ትምህርትና ድንቅ ምክር ለንባብ እንዲመች እየተመጠነ የሚቀርብ ይሆናል።

በመርሐ-ግብሩ ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ ልንወጣ ስለሚገባን የቅድስና መሰላልና የንጽሕና ሕይወት ጉዞ አስደናቂ ትምህርቶችን የምናገኝበት ነው፡፡

[   🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊  ]

- ተከታታይ መርሐ-ግብር
- ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ
- ከቀኑ ፱ ሰዓት [ 09:00 ] ላይ


🕊                       💖                     🕊
6👍1
7
                         †                        

 [       🕊    ፍኖተ ቅዱሳን    🕊      ]

[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

             [        ትሕትና !         ]

------------------------------------------

❝ አባ ኤስድሮስ እንዲህ አለ ፦ ሁል ጊዜ የምትጾም ከሆነ በትዕቢት ራስህን ወደ ላይ አታውጣ ፤ ከዚህ የተነሣ ራስህን ከፍ አድርገህ የምትመለከት ከሆነ ግን ሥጋ ብትበላ ይሻልሃል፡፡ ለአንድ ሰው ራሱን በትዕቢት ከመንፋትና ራሱን ከማክበር ሥጋ ቢበላ ይሻለዋልና፡፡ ❞
-------------------------------------------

❝ ቅድስት ሰንቀሌጢቃ እንዲህ አለች ፦ "መርከብ ያለ ምስማር ሊሠራ እንደማይችል ሁሉ ድኅነትም [ መዳንም ] ያለ ትሕትና ሊገኝ አይችልም፡፡ " ❞
--------------------------------------------

ለአባ ዮሐንስ ፦ " ሰውች መላእክትን አየናቸው ይላሉ። " አሉት። እርሱም ፦ " ብፁዕስ ሁል ጊዜ ኃጢአቱን የሚያይ ሰው ነው።" አላቸው
-------------------------------------------

🕊

የደጋግ አባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡


†                         †                         †
💖                      🕊                      💖
1🥰1
6
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊

▷   "  ደስተኛ መሆን ትፈልጋለህ ? "

[   💖  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  💖  ]

[                        🕊                        ]
-------------------------------------------------

❝ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር ፥ ደስታ ፥ ሰላም ፥ ትዕግሥት ፥ ቸርነት ፥ በጎነት ፥ እምነት ፥ የውሃት ፥ ራስን መግዛት ነው። ❞

[   ገላ.፭፥፳፪  ]


🕊                       💖                     🕊
🥰32
Audio
🥰21
🥰6
🕊

[  † እንኳን ለቅዱሳት አንስት ሶፍያ ወአዋልዲሃ: ኦርኒ ወማኅበራኒሃ እና ለሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  † ቅድስት ሶፍያና ልጆቿ  †  🕊

† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ታዋቂ ከሆኑ የእናቶቻችን ስሞች "ሶፍያ" ቀዳሚው ነው:: ቃሉ በጥሬው ሲተረጐም "ጥበብ [ጥበበ ክርስቶስ] Wisdom of God" ማለት ነው:: ከጻድቃንና ከሰማዕታት ወገን በዚህ ስም የተጠሩ እናቶች አሉ::

ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆነችው በዕለቱ የምናስባት እናት ቁጥሯ ከሰማዕታት ነው:: ዋናው ዘመነ ሰማዕታት ከመጀመሩ በፊት የነበረችው ቅድስት ሶፍያ ከሕግ ትዳር ፫ ሴቶች ልጆችን አፍርታለች::

ስማቸውንም:- ጲስጢስ [ሃይማኖት] : አላጲስ [ተስፋ] : አጋጲስ [ፍቅር] ስትል ሰይማቸዋለች:: እንደሚገባም በሥርዓቱ አሳድጋ እድሜአቸው 9 : ፲ እና ፲፪ ሲደርስ ለሰማያዊ ሙሽርነት አጭታቸዋለች::

በዘመኑ "ክርስቶስን ካዱ" የሚል መሪ ተነስቶ ነበርና ቅዱሳቱ በመድኃኒታችን አምነው : ጣዖትን ዘልፈው አንገታቸውን ሰጥተዋል:: ክብረ ሰማዕትን : ሃገረ ክርስቶስንም ወርሰዋል::


🕊  †  ቅድስት ኦርኒ ሰማዕት  †  🕊

† "ኦርኒ" ማለት በምሥራቃውያን ልሳን "ሰላም" ማለት ነው:: ቅድስቲቱ አርበኛ የዘመነ ሐዋርያት የቤተ ክርስቲያን ፍሬ ስትሆን ተወልዳ ያደገችውም በቀድሞው የሮም ግዛት ውስጥ ነው::

ምንም ዛሬ ያለ ትውልድ ቢዘነጋት ቅድስት ኦርኒ ተወዳዳሪ የሌላት ሰማዕት : ሐዋርያዊት : ድንግል ናት:: እርሷ ውበቷን : ንግሥናዋን : ክብሯን : ሃብቷን : ወጣትነቷንና ያላትን ሁሉ ስለ ፍቅረ ክርስቶስ ሰውታለችና ክብርት ናት::

በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ቤተ መንግስት የተወለደችው ቅድስት ኦርኒ እስከ ወጣትነቷ ድረስ ክርስቶስን ልታውቀው አልተቻላትም ነበር:: ምክንያቱ ደግሞ ንጉሡ አባቷ ጣዖትን ማምለኩ ነበር::

ንግሥት እናቷ ምንም ክርስቲያን ብትሆንም ስለ ክርስትና ልትነግራት አልደፈረችም:: ይህን ብታደርግ የሚደርስባትን መከራ ታውቃለችና:: ግን ደግሞ ውስጥ ውስጡን ትጸልይላት ነበርና ፈጣሪ መንገዱን ሊከፍት ጀመረ::

መምለኬ ጣዖት አባቷ ሰው እንዳያያት ቤተ መንግስት ሠርቶ : ፲፪ ሞግዚቶችን መድቦ ጣዖት ከፊቷ አቁሞ ለዘመናት ዘጋት:: የሚገርመው ግን መልኳን እንዳያይ በበር ሆኖ የሚያስተምራት ፈላስፋ ተቀጥሮ ነበርና የዚህ ሰው ማንነቱ ነው::

መምለኬ ክርስቶስ ደግ ሰው ነበርና ፈሊጥን ይሻላት ገባ:: በዚህ መካከል ቅድስት ኦርኒ ራዕይን ታያለች:: የቤቷ መስኮቶች ተከፍተው ሳሉ በስተምሥራቅ ነጭ ርግብ : የዘይት [የወይራ] ዝንጣፊ ይዛ ገብታ : ከማዕዷ ላይ ጥላው ወጣች::

እርሷን ተከትሎ ቁራ በምዕራብ ገባ:: እባቡን ማዕዷ ላይ ጣለው:: በ3ኛው ደግሞ ንስር ገብቶ አክሊል ትቶላት ወጣ:: ቅድስቲቱም እየገረማት አረጋዊ መምህሯን "ተርጉምልኝ" አለችው::

† እርሱም :-

• ርግብ = ጥበብ [ መንፈስ ቅዱስ ]
• ዘይት = ጥምቀት
• ቁራ = ክፉ ንጉሥ
• እባብ = መከራ
• ንስር = ድል ነሺነት [ ልዑላዊነት ]
• አክሊልም = ክብረ ሰማዕታት ነው" ብሎ ተርጉሞ : ክርስቲያን ሆና ይህ ሁሉ እንደሚደረግ ነግሮ ተሰናበታት::

እርሷም ስትጸልይ ቅዱስ መልአክ ተገልጦ አጽናናት:: ያጠምቃትና ያስተምራት ዘንድም ሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስን ልኮላታል:: ሐዋርያውም የቤተ መንግስቱን ግድግዳ ሰንጥቆ ገብቶ : ለሰማያዊ ሙሽርነት የሚያበቃ ትምህርትና ጥምቀትን ሰጥቷት ሔዷል::

ቅድስት ኦርኒም የአባቷን ጣዖታት ቀጥቅጣ ሰብራ ከአባቷ ጋር ተጣላች:: እርሱም "እገድላታለሁ" ብሎ በእንስሳት ጅራት ላይ ጸጉሯን ሲያስር እንስሶቹ ደንብረው : እጁን ገንጥለው መሬት ላይ ጥለው ገደሉት:: ቅድስት ኦርኒ ግን ጸሎት አድርሳ አባቷን ከሞት አስነሳችው:: እጁንም ቀጠለችለት::

በዚህ ምክንያት በዚያች ዕለት ብቻ አባቷና ፴ ሺህ [ 30,000 ] የከተማው አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል:: ቅድስት ኦርኒ ግን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ ታጥቃ ክርስትናን ሰበከች:: ብዙም ተሰቃየች:: ንጉሡ ዳኬዎስ : ልጁና ሌሎች ፪ ያህል ነገሥታት በእሳት : በአራዊት : በግርፋትና በጦር ፈትነዋታል::

እርሷ ግን ሁሉን በኃይለ ክርስቶስ ድል ነስታለች:: ሙታም የተነሳችበት ጊዜ አለ:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ወደ ሰማያዊ ርስት [ ገነት ] ተመስጣለች:: በዘመነ ስብከቷ ካሳመነቻቸው ባሻገር ፻፴ ሺህ [ 130,000 ] የሚያህሉ ሰዎች ለሰማዕትነት እንዲበቁም ምክንያት ሆናለች::


🕊  † ቅዱስ ጐርጐርዮስ ታኦሎጐስ  †  🕊

† ቅዱሱ :-

• የዘመነ ሊቃውንት ፍሬ:
• የእንዚናዙ ኤጲስ ቆጶስ:
• የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ:
• የጉባዔ ቁስጥንጥንያ [ በ381 ዓ/ም] ፫ኛ ሊቀ መንበር:
• ባለ ብዙ ድርሳን:
• የቂሣርያ [ ቀጰዶቅያ ] ኮከብ:
• ብሩህ ገዳማዊ:
• መልካም እረኛ የነበረ አባት ነው::
መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በጻፋቸው ብዙ መጻሕፍትና በስብከቱ ከሊቃውንት ወገን "ታኦ(ዎ)ሎጐስ" ተብሎ የተጠራ እርሱ ብቻ ነው:: ትርጉሙም በግዕዙ "ነባቤ መለኮት" ማለት ነው:: በአማርኛም "አንድነትን : ሦስትነትን የተናገረ [ያመሠጠረ] እንደ ማለት ነው:: ቅዱሱ ዛሬ ዕረፍቱ ነው::

† አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው ይክፈለን፡፡
በመጽናታቸውም ያጽናን፡፡

† እንዲህ ኃጢአታችን ጽዋዑን ሞልቶ በተረፈበት በዚህ ዘመን አንዲት ሰዓትም ውድ የሆነች የንስሃ ዕድሜ ናት:: እግዚአብሔር ግን ደግ ነውና ይሔው ጥርን አስፈጸመን:: ባይገባን ነው እንጂ በዚሕች ወር ውስጥ ሚሊየኖች በደዌ የአልጋ ቁራኛ ሁነዋል::

ሚሊየኖችም ለንስሃ ሳይበቁ እንዲሁ አንቀላፍተዋል [ሙተዋል]:: እስኪ እርሱ አምላካችን ቀሪውን ዘመን ደግሞ ለንስሃና ለመልካም ሥራ ባርኮ ይስጠን::

† ወርኀ ጥርን በቸር ያስፈፀመ አምላከ ቅዱሳን ወርኀ የካቲትን እንዲባርክልን እንለምነው::

🕊

[  † ጥር ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅድስት ሶፍያና ሦስቱ ሰማዕታት ልጆቿ [ጲስጢስ አላጲስና አጋጲስ]
፪. ቅድስት ኦርኒ ሰማዕት [በ፭ ነገሥታት እጅ የተሰቃየች : የሐዋርያው ጢሞቴዎስ ተከታይና ወደ ብሔረ ሕያዋን የተነጠቀች እናት]
፫. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፬. አባ አክርስጥሮስ
፭. አምስቱ ደናግል ሰማዕታት [ጤቅላ: ማርያ: ማርታ: አበያ: ዓመታ]
፮. ጻድቃነ ዴጌ [የተሠወሩበት]
፯. አባ ሚናስ ሊቀ ጳጳሳት
፰. ፻፴ ሺህ "130,000" ሰማዕታት [የቅድስት ኦርኒ ማኅበር]

[   † ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ
፪. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፫. አባ ሣሉሲ ክቡር

" ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: " † [ ፩ጴጥ. ፫፥፫ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
3👍1
2025/07/09 17:19:05
Back to Top
HTML Embed Code: