#_አድዋ_
#ውብ_የኢትዮጵያ_እና_የተዋሕዶ_ታሪክን
እጅጉን በአጭሩ እናጫውታችሁ
አንድ የኢጣሊያ እስረኛ ንጉስ አጴ ምኒልክ የተማረኩ እስረኞችን በሚፈቱበት ዕለት #እንዲህ_አላቸዉ ?
ንጉስ ሆይ ያኔ ጦርነት ሲካሄድ በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ወታደረዎትን ይመራ የነበረው የኛን ትጥቅ የሚመስል የለበሰው #ጄኔራሎት አንዴ ያሳዩኝ አላቸው
#እርሳቸውም ማን እንደሆነ ገባቸውና "#እሱማ_የኢትዮጵያ_ንጉስ_ነው" ብለው ሲመልሱለት በመደንገጥ "እርስዎስ አላቸው "እርሳቸውም እኔማ #ባሪያው_ነኝ"
አሉት ።
በዚህ የተነሳ በየዓመቱ አራዳ #ጊዮርጊስ እዲነግስ አደረጉ።
#መልካም_ዕለተ_ሰንበት🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam

❤10👏1
†
[ የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ]
[ 🕊 ቅድስት 🕊 ]
💖
" ቅድስት " ማለት ‹ የተለየች ፣ የነጻች ፣ የከበረች › ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን ጾም የጀመረባት ፣ ልዩ ፤ የተቀደሰች ፤ የከበረች ፤ ልዩ ፣ ንጹሕ ፣ ክቡር በሚኾን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጾመች መኾኗን ያመላክታል፡፡
ይህች ጾም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አራት የተገለጠችው የጌታችን ጾም ስትኾን ፣ ስያሜዋና የዕለቷ የምስጋና ሥርዓትም የቅዱስ ያሬድ ነው፡፡አምላካችን በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት በጾመበት ጊዜያት እነዚህ ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል አድርጓል፡፡
ሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ የሚባሉትም ፦ ትዕቢት ፣ ስስትና ፍቅረ ንዋይ ናቸው፡፡ በእነዚህ ሦስት ኃጢአቶች ጌታችን በዲያሎስ በተፈተነ ጊዜ በትዕቢት ቢመጣበት በትሕትና ፤ በስስት ቢመጣበት በትዕግሥት ፤ በፍቅረ ንዋይ ቢመጣባት በጸሊዓ ንዋይ ጌታችን ዲያሎስን ድል አድርጎታል፡፡ ለእኛም እነዚህን ድል ለማድረግ የምንችልበትን ጥበብ – ጾምን ገልጦልናል፡፡
ትዕቢት ያልተሰጠንን መሻት ፣ ስስት አልጠግብ ባይነት ስግብግብ መኾን ፣ ፍቅረ ንዋይ ለገንዘብ ሲሉ ፈጣሪን መካድ ነው፡፡ አንደ ክርስቲያን ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል ካደረገ ሌሎችን ኃጣውእ በቀላሉ ድል ማድረግ ይቻለዋል፡፡
[ በመምህር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ ]
🕊 [ ክብርት ሰንበት ] 🕊
🕊 💖 🕊

🙏1
🕊 💖 🕊
[ የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ]
💖
[ 🕊 ቅድስት 🕊 ]
ቅድስት ማለት የከበረች የተለየችና የተመሰገነች ማለት ነው ፤ ይኸውም በባሕርዩ ቅዱስ የሆነው ጌታ ጾምን ቀድሶ የጀመረባት ዕለት በመሆኑ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይህ ሳምንት ቅድስት የሚል ሥያሜ ሰጥቶታል::
ይህ ሳምንት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ እግዚአብሔር የባሕርይ ቅድስና እንዲሁም ቅዱስ እግዚአብሔር ስለቀደሳቸው ቅዱሳን አካላት [ ጾም ቅድስት ፣ ሰንበት ቅድስት ፣ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ወዘተ እያለች ] የምታስተምርበት ሳምንት ነው።
ሰው ሁሉ በቅድስና መንገድ በመመላለስ የክብሩ ባለቤት የመንግሥቱ ወራሽ እንዲሆን እግዚአብሔር " እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ " በማለት ስለማስተማሩ ስፊ ትምህርት ይሰጥበታል።
እግዚአብሔርን ማየትና የእግዚአብሔር የሆነውን ሥርዓት መከተል ስለሚያስችል ዕለት ዕለት መልካም በማድረግ ቤተ መቅደስ ተብሎ የተነገረለትን ሰውነታችንን በንጽሕና በመጠበቅ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕቃ ሆነን መቅረብ እንደሚገባን ይዘከርበታል።
እግዚአብሔር አምላካችን ቅዱስ ነው እያልን በልባችን አምነን በአፋችን መስክረን በተግባር ግን ከቅድስና ርቀን እንዳንኖር እግዚአብሔር እንደቀደሰንና ልጅነትን እንደሰጠን በማመን በተቀደሰ ሁኔታ መኖር ይገባናል።

❤1
#እንኳን_ለአድዋ_ድል_በዓል_አደረሳችሁ
"ኦ ፍጡነ ረድኤት እምሩፀተ ነፋስ ወአውሎ ለዘይጼውአከ በተወክሎ #ጊዮርጊስ ቅረብ ለምሕረት ወለተሣህሎ ተወከፍ ወትረ ጸሎትየ ወቃለ ጽራህየ ኩሉ አስመ ልበ አምላክ ርህሩህ በኀቤከ ኀሎ"
ትርጉም:- ረድኤትህ ከነፋስ እና ከአውሎ የፈጠነ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሆይ ለሚማፀኑህ ሁሉ ለምሕረት ቅረብ የኔንም ፀሎቴን የመማፀኔን ቃላት ሁሉ ተቀበል የአምላክ ልብ በአንተ ለለመነው ሩህሩህ ነውና"
ለመቀላቀል👇👇👇👇

❤6👍2
🕊 💖 🕊
[ 🕊 ቅድስት 🕊 ]
💖
[ ቅድስና ምንድነው ? ]
ቅድስና ማለት ቀደስ ባረከ ፤ ለየ ፤ አከበረ ፤ አመሰገነ ፤ አነጻ ፤ ሰውነቱን ከርኩሰት ልቡን ከትዕቢት አራቀ ከሚለው ከግዕዝ ሥርወ ግሥ የተገኘ ኀይለ ቃል ሲሆን ቅድስና ማለት መለየት ፤ መክበር ፤ መመስገን ፣ መንጻትና መጽናት ማለት ነው፡፡
ሰውም ሆነ ሌላውም ነገር ቅዱስ የሚሆነው የእግዚአብሔር ስለሚሆን ብቻ ነው ፤ ሰው ሃይማኖት ይዞ በሥነ ምግባር እየተቀደሰ ሊሄድ ይችላል ፤ [ ዮሐ ፲፯ ፥ ፲፯ ] ዳግመኛ የሰው ልጅ ከመንፈስ ቅዱስ ሲወለድ የቅድስና ሥራ ይጀምራል ፤ በሕይወቱ ደግሞ ቅድስናውን እያሳደገ ይሄዳል ፤ በዕለተ ምጽአት ቅድስናው ፍጹም ይሆናል። [ ፩ኛ ቆሮ.፲፭ ፡ ፶፩ ፣ ፩ኛ ተሰ.፬ ፥ ፬ ]
ቅድስና በአማኝ ሕይወት ውስጥ የሚያድገው በእግዚአብሔር ኀይል ነው ፤ ነቢዩ ሕዝቅኤል " መቅደሴ ለዘለዓለም በመካከላቸው በሆነ ጊዜ እኔ እስራኤልን የምቀድሰው እግዚአብሔር እንደሆንኩ አሕዛብ ያውቃሉ::" በማለት ተናግሯል:: [ ሕዝ ፴፯ ፥ ፳፰ ]
የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ በመሆኑ በፍጹም ኀይሉ በፍጹም ነፍሱ በፍጹም ልቡ እግዚአብሔርን መውደድ አለበት:: ቅድስናውና ፍቅሩ ደግሞ ትእዛዙን በመጠበቅ ይገለጣል። [ማር.፲፪ : ፴፫ ፣ ዮሐ.፲፬፥፳፩ ፣ ፊል.፪፥፲፪ ፣ ፩ኛዮሐ.፭፥፳፫ ፣ ዘሌዋ.፲፱፥፪ ፣ ፩ኛ ጴጥ.፩፥፲፭ ]

🕊
[ † እንኳን ለአባታችን ቅዱስ አጋቢጦስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ቅዱስ አጋቢጦስ † 🕊
+ ይህንን ዓለም ንቆ ለበርካታ ዘመናት በፍፁም ምናኔ የኖረ::
+ ምድራዊ ሃብትና ሹመት ሞልቶለት ሳለ ከሁሉ የክርስቶስን ፍቅር የመረጠ::
+ ከደግነቱ ብዛት የተነሳ ምግብ ሲያዘጋጅ ሽምብራውን ከክቶ ለሌሎች ከሰጠ በሁዋላ ለራሱ የሚመገበው ገለባውን [ አሠሩን ] ነበር::
ሌሊቱን በጸሎት ለመትጋት ማታ ማታ አመድ ይመገብ ነበር:: በዚህም ቅዱስ ዳዊት "አመድን እንደ እህል በላሁ" ያለው በዚህ ቅዱስ ሕይወት ላይ ተገልጧል:: [መዝ.፻፩፥፱] (101:9)
ቅዱስ አጋቢጦስ በዘመኑ ከሠራቸው ይህኛው እጅግ ይገርመኛል:: እርሱ በበርሃ የነበረበት ዘመኑ የሰማዕታት በመሆኑ ብዙ ክርስቲያኖች በርጉማን መክስምያኖስና ዲዮቅልጢያኖስ ተገድለዋል:: ቅዱሱን ግን በአካባቢው የነበረ ሃገረ ገዢ ከበዓቱ አስወጥቶ ወደ ውትድርና ሥራ አስገብቶታል::
ሰይጣን በዚህ ከተጋድሎና ከቅድስና ሕይወት እንደሚያርቀው ተማምኖ ነበር:: ቅዱስ አጋቢጦስ ግን በወታደሮች መካከል ሆኖም ተጋድሎውን ቀጠለ:: የጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ቢሾሙትም እርሱ ከበጐ ማንነቱ ፈጽሞ አልተለወጠም::
ክርስቲያን ማለት እንዲህ ነውና:: ክርስትና ሲመቸን : ሲመቻችልን : በአጋጣሚ ወይም በምክንያት የምንኖረው ሕይወት አይደለም:: ፍጹም ፍቅር የጊዜ : የቦታ : የሁኔታ ገደብ የለውምና አባቶቻችን በጊዜውም : ያለ ጊዜውም ጸንተው ክርስቶስ መድኃኒታችንን አስደሰቱ::
ከቅዱስ ዻውሎስ ጋርም እንዲህ ሲሉ ዘመሩ:- "መኑ ያኀድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ" [ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል ! ]
ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና ቅዱስ አጋቢጦስ ለዘመናት ሰው ሳይገድል : ፈጣሪውን ሳይበድል : ከጾም ከጸሎት : ከምጽዋትና ትሕርምት ሳይጐድል ኖረ:: በዚህም ሰይጣንን አሳፈረ:: ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ::
በዚህ ጊዜም ወደ በዓቱ ለመመለስ መንገድን ይፈልግ : ይጸልይም ገባ:: እግዚአብሔርም ወደ በርሃ የሚመለስበትን መንገድ በቸርነቱ አቀናለት::
ነገሩ እንዲህ ነው:: ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ራትዕ [የቀና] ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ነገሠ:: ስደት ቆመ:: የታሠሩ ተፈቱ:: አብያተ ክርስቲያናት ታነጹ:: ለክርስቲያን ቀደምቶቻችንም ታላቅ ተድላ ሆነ::
ጊዜው ለሁሉ ክርስቲያን የተድላ ቢሆንም አንድ ወጣት በደዌ ሰይጣን ያሰቃየው ነበር:: ወጣቱ የንጉሡ የቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ባለሟል : ባለብዙ ሃብት : መልኩ ያማረ ነውና ሁሉ ያዝንለታል:: ይልቁኑ ቅዱሱ ንጉሥ ተጨነቀለት::
አንድ ቀን ግን ከወታደሮቹ አንዱ ያን ወጣት "አንተንኮ አጋቢጦስ ይፈውስህ ነበር" ይለዋል:: ወጣቱ ግን አላወቀምና "ከመቼ ወዲህ የጦር አለቃ እንዲህ አድርጐ ያውቃል?" ሲል በጥያቄ ይመልስለታል:: ወታደሩ ግን ቀስ አድርጐ ምሥጢሩን ይነግረዋል::
ይህ ነገር ሲያያዝ ከንጉሡ ደርሶ ቅዱስ አጋቢጦስን አስጠርቶ "እባክህ ፈውስልኝ?" ይለዋል:: "ካዳንክልኝም የፈለግኸውን አደርግልሃለሁ" ሲል ያክልለታል:: ቅዱስ አጋቢጦስም ወደ ፈጣሪው ለምኖ ሰይጣንን ይገስጸዋል:: በቅጽበትም በክርስቶስ ኃይል ወጣቱ ይድናል::
ቅዱስ ቆስጠንጢኖስም ከደስታው ብዛት "ምን ላድርግልህ?" ቢለው ቅዱሱ "ከሹመቴ ሻረኝ : ወደ በርሃ አሰናብተኝ" ብሎ መሻቱን ገለጸለት:: ቅዱሱ ንጉሥም በመገረም ቡራኬውን ተቀብሎ ወደ በርሃ ሸኝቶታል::
ወገኖቼ ! . . . በዓለማዊም ሆነ በመንፈሳዊው እርከን ስልጣንን የሚንቁ ሰዎችን ካላገኘን መፍትሔው ሩቅ ነው:: እኛም ከሥልጣን መሻት እንራቅ:: ማር ይስሐቅ እንደ ነገረን ሰይጣን ያደረበት ሰው ሹመትን [ሥልጣንን] በመሻቱ ይታወቃልና::
ቅዱሱ በፍፃሜ ዘመኑ እረኝነት [ዽዽስና] ተሹሞ ብዙ ኢ-አማንያንን ወደ ክርስትና መልሶ: ድውያንን ፈውሶ: እውራንን አብርቶ: በርካታ ተአምራትንም አድርጎ በዚህች ቀን አርፏል::
††† ልመናው በረከቱ ይደርብን::
🕊
[ † የካቲት ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አጋቢጦስ [ ጻድቅ ኤዺስቆዾስ ]
፪. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት [ዘጋዛ]
፫. ቅዱስ ሚናስ ዘቆዽሮስ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት [ መምሕረ ትሩፋት ]
፪. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፫. ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
፬. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
፭. ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
፮. ፳፬ቱ "24ቱ" ካኅናተ ሰማይ [ ሱራፌል ]
† " የሚያሳድዷችሁን መርቁ . . . ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ:: ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ:: እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ:: የትዕቢትን ነገር አታስቡ:: ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ ::" † [ሮሜ.፲፪፥፲፬] (12:14-16)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

#ቅድስት፤ #ሁለተኛው_የዐቢይ_ጾም_ሳምንት
‹‹ ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡
የዚህቸ የሰንበት ክብር እጅግ ልዩ ነው ከዳግም ምጽዓት በኃላ ጸንታ የሚትቆየው ብቻኛዋ ዕለት ይህች ሰንበት ነች
‹‹ እምኵሉ ዕለት ሰንበት አክበረ
ወእምኵሉን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ››
ከዕለታት ሁሉ ሰንበትን አከበረ ከሴቶች ሁሉ ደግሞ #ማርያምን_አፈቀረ መረጠ ‹‹ቅዱስ ያሬድ ››
#መልካም_ቀን🙏

❤10😢1