Telegram Web
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †

💖 

    [   ዓ ለ ም ን   ስ ለ መ ተ ው !   ]

           [     ክፍል አምስት     ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

አሳባችንን ወደ የውሃት .... !

❝ የሆነ አሳባችንን ወደ የውሃት ፣ ወደ ጥልቅ ቍጣ አልባነት፣ ወደ ንቍነትም በማምጣት ፣ የንጽሕናና የንቍነት ወዳጅ እስካላደረግነው ድረስ በተለይ በቸልታ ሕይወት በሚኖሩ ዘንድ ፣ በርካታ የሚሆኑ የማይታዩ መከራትን የሚያመጣ ነውና ይህ በእውነት ታላቅ ፣ በእውነት እጅግ ታላቅ መከራ ነው፡፡

ሆኖም ግን ደካማና በፈቃደ ሥጋ የምንመላለስ እኛ ጽናት የለሽነታችንንና ደካማ ጠባያችንን ጥርጥር በሌለበት እምነት ወደ ክርስቶስ እናቀርብ ፣ ይህንም ለእርሱ እንናዘዝ ዘንድ እንበርታ ፤ ሳናቋርጥ ጥልቅ ወደ ሆነ ትሕትና ራሳችንን የምንጥል ከሆነ ብቻ ፣ ለእኛ ከሚገባው በላይ የሆነውን የእርሱን ርዳታ እንኳ እንደምናገኝ ርግጠኛ እንሆናለን፡፡

ወደ እዚህ አስደናቂ ፣ ጽኑና አስቸጋሪ ቢሆንም ቅሉ ፣ ነገር ግን ደግሞ ቀላል ወደ ሆነው መልካም ተጋድሎ የገቡ ሁሉ ፣ በእውነት ሰማያዊ የሆነው እሳት በውስጣቸው ያድር ዘንድ የሚጠብቁ ከሆነ ወደ እሳቱ ዘለው መግባት እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው አገልግሎቱ ወደ ገዛ ፍርዱ ወደ ገዛ ፍርዱ እንዳይመራው ፣ ራሱን ይመርምር እንጀራውንም ከመራራ ቅጠል ጋር ይብላ ፣ ጽዋውንም ከእንባ ጋር ይጠጣ፡፡ ተጠምቆ የነበረ ሰው ሁሉ ድኅነት ያላገኘ ከነበረ ተከትሎ ስለሚሆነው ነገር ዝም እላለሁ፡፡

ወደዚህ ተጋድሎ የገቡ ጽኑ መሠረትን ማኖር ይችሉ ዘንድ ሁሉንም ነገር መተው ፣ ሁሉንም ነገሮች መናቅ ፣ በሁሉም ነገሮች ላይ መዘበትና ሁሉንም ነገሮች አራግፈው መጣል አለባቸው፡፡ ለሦስቱ ንጣፎችና ለሦስቱ ምሰሶዎች ግሩም መሠረት የውሃነት ፣ ጾም ፣ ራስንም መግዛት ነው፡፡ በተፈጥሮ ሕፃናት የሆኑትን አርአያነት በመንሣት ፣ በክርስቶስ ሕፃናት የሆኑ ሁሉ በእሊህ ምግባራት ይጀምሩ፡፡ በእነርሱ [በሕፃናት] ዘንድ ከቶም አንዳች ተንኮል ወይም ማታለል አታገኝምና፡፡ እነሱ የማይረካ ፍላጎት ፣ የማይጠግብ ሆድ ፣ የሚቃጠል ወይም እንደ አውሬ ቍጡ የሆነ ሰውነት የላቸውም ፤ ምናልባት ግን አድገው የበዛ ምግብ የሚመገቡ እንደ መሆናቸው መጠን ፣ ተፈጥሮአዊ ፈቃዶቻቸው [ምኞታቸው] ደግሞ ይጨምራሉ፡፡ ❞


[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                       💖                     🕊
3
👍2
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   ዐቢይ ጾም [  ጾመ እግዚእ  ]  🕊


▷   "    ስ ለ ፈ ቃ ድ      "


[ " በአቡነ አትናቴዎስ ዘእስክንድር ... ! " ] 

[                         🕊                         ]
----------------------------------------------------

" በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና ፥ ነገር ግን በብልቶቼ ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝን ሌላ ሕግ አያለሁ።

እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል ? " [ ሮሜ.፯፥፳፪ ]


🕊                         💖                         🕊
🙏1
8👍2
🕊

[  † እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ አቡፋና እና ቅዱስ እንጦኒ ሐዲስ ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊  †  አባ አቡፋና   †    🕊

† ታላቁ አባ አቡፋና ፦
በምድረ ግብጽ ተጋድሏቸውን የፈፀሙ፣
በመዐልት አምስት መቶ ጊዜ በሌሊትም አምስት ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ይጸልዩ የነበሩ፣
በአርባ ቀን አንድ ጊዜ ብቻ እህል ይቀምሱ የነበሩና ሙሉ ዘመናቸውን በበርሃ በታላቅ ጽሙና የፈፀሙ አባት ናቸው።

ጻድቁ በጣም የሚታወቁት ከማበጡ የተነሳ እጅግ ግዙፍ በነበረ እግራቸው ነው። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ስለ መድኃኔ ዓለም ፍቅር አልቀመጥም፤ አልተኛም ብለው ለአሥራ ስምንት ዓመታት በመቆማቸው ነው።

አሥራ ስምንት ዓመት የመቆማቸው ዜናስ እንደምን ነው ቢሉ ፦
አንድ ቀን "እኔ ግን ከዚህ ዓለም የምለየው መቼ ይሆን?" ሲሉ አሰቡ። በእርግጥ ይህንን ሐሳብ ብዙ ሰዎች ሊያስቡት ይችላል። ሐሳቡ ጠቃሚም ያልተፈቀደም ነው።
፩. "ጠቃሚ ነው።" ያልኩት አንድ ሰው ሞት እንዳለ ካወቀ ወይም 'መቼ ነው የምሞተው' ብሎ ካሰበ ንስሐ ይገባል ፤ ክፋትን ይተዋል ተብሎ ስለሚታመን ነው። ወገኔ ሁሉ እንደ አውሬ ሲባላ ፣ ደም ሲያፈስ ፣ ክፋትን ሲጐነጉን የሚውል "እሞት ባይ" ሳይሆን "እኖር ባይ" ሆኖ ነውና።
ግን ሞት በቅርቡ እንዳለ በኃያሉ አምላክ ፊት ራቁቱን ለፍርድ እንደሚቀርብ ለወገኔ ማን በነገረው !
፪. "ያልተፈቀደ ነው።" ያልኩት ደግሞ በሁለት ምክንያት ነው።
"ኢትበሉ ለጌሰም [ ለነገ አትበሉ። ]" የሚል አምላካዊ ቃል ስላለ። [ማቴ. ፮፥፴፬]
ሰው [በተለይ ዓለማዊው] የሚሞትበትን ቀን ቢያውቅ አጭር ጊዜ ከሆነ ሽብር ጭንቀት ይበላዋል። ወዲህ ደግሞ ጊዜው ረዥም ቢሆን እንደ ሰብአ ትካት [ማለትም በኖኅ ዘመን እንደ ነበሩ ሰዎች] 'ብዙውን ልዝናናበት [ኃጢአት ልሥራበት']ና ንስሐ እገባለሁ።' ይላልና ነው።

በዚያውም ላይ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ቅዱስ ሰውና የነቢያት አለቃ ቅዱስ ሙሴ የሞቱን ጊዜ ጠይቆ እጅግ መቸገሩን መጥቀሱ በራሱ በቂ ነው። ጌታ "ዓርብ ቀን ትሞታለህ።" ብሎት ለሁለት ዓመታት ዓርብ ዓርብ ሲገነዝ ሲፈታ ኑሯል።

በመጨረሻም ዓርብ ቀን ድንገት መልአከ ሞት መጥቶበታል። ስለዚህ "ወድልዋኒክሙ ንበሩ - ተዘጋጅታችሁ ኑሩ። መባላችንን አስበን ልንኖር ግድ ይለናል። [ማቴ. ፳፬፥፵፬]

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ አቡፋና ይህንን የዕረፍታቸውን ነገር ሲያስቡ ቅዱስ መልአክ ተገልጦ "ተርፈከ አሠርቱ ወሰመንቱ - አሥራ ስምንት ቀርቶሃል።" አላቸው። እርሳቸውም "ጌታዬ አሥራ ስምንት ምን?" ሲሉ ቢጠይቁትም ሳይመልስላቸው ተሠወረ።

ከደቂቃ እስከ ኢዮቤልዩ ብዙ አሥራ ስምንቶች አሉ። እርሳቸው ግን "አሥራ ስምንት ቀን ነው!" ብለው ለጌታ ተሳሉ። ስዕለታቸውም "ከዚህ በኋላ አልቀመጥም።" የሚል ነው። እየጾሙ እየጸለዩ ለአሥራ ስምንት ቀናት ቆሙ። ሞት አልመጣም።

"አሥራ ስምንት ሱባኤ ይሆን!" ብለው አሥራ ስምንት ሱባኤ [መቶ ሃያ ስድስት ቀናት] ቆመው ጸለዩ። አሁንም ሞት አልመጣም። "አይ! አሥራ ስምንት ወር ሊሆን ይችላል።" ብለው ለአሥራ ስምንት ወራት (ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር) ቆመው ተጉ። አሁንም ግን ሞት የውኃ ሽታ ሆኖ ቀረ።

ይህን ጊዜ ግን ወደ ፈጣሪ ለመኑ። "ጌታዬ! ያልከኝ ምን አሥራ ስምንት ነው?"
ቅዱስ መልአኩም መጥቶ "አቡፋና ሆይ! የቀረህ አሥራ ስምንት ዓመት ነውና ጽና።" ብሏቸው ተሰወረ። ልብ በሉልኝ "እስክሞት አልቀመጥም።" ብለው ተስለዋል።

ቅዱሱ ገዳማዊ በቃላቸው የሚገኙ እውነተኛ ክርስቲያን ነበሩና ለአሥራ ስምንት ዓመታት እንደተተከለ ምሰሶ ቆመው ጸለዩ፣ ጾሙ። እንዲህ ያሉትን ቅዱሳን ሊቃውንት፦
"ሰላም ለከ ጽኑዕ ከመ ዓምድ
ዘኢያንቀለቅሎ ሞገድ።"
[ማዕበለ ዓለም የማያናውጸው ብርቱ ምሰሶ ሆይ! ምስጋና ይገባሃል።] የሚሏቸው።

ስለ ቅዱሱ የተጻፈ አርኬም ፦
"ሰላም ለቁመተ አቡፋና ዘአልቦ ኑታጌ
እስከ ተመሰለ እግሩ ከመ እግረ ነጌ።" ይላል። ከመቆም ብዛት አካላቸው ደቆ እግራቸው የዝሆን እግር እስኪመስል ወፍሮ ነበርና።

† አባ አቡፋና በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተው በዚህች ቀን አርፈዋል።


🕊  † ቅዱስ እንጦኒ ሐዲስ ሰማዕት †  🕊

† ቅዱስ እንጦኒ [Anthony] በትውልዱ ከሶርያ ዐረቦች ሲሆን በቀደመ ሕይወቱ ክርስቲያኖችን ያሳድድ ፣ ካህናትን ይደበድብ ፣ አብያተ ክርስቲያናትንም ያቃጥል ነበር። እግዚአብሔር በንስሐ ሲጠራው ግን ደግ ፣ ጻድቅና ምርጥ ዕቃ ሆኖ ተገኘ። በመጨረሻም ከብዙ መከራ በኋላ ለሰማዕትነት በቅቷል።

† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ትጋት፣ ጽናት፣ ፍቅርና በረከት ያድለን። ከማስተዋልም አያጉድለን።

🕊

[  † የካቲት ፳፭ [ 25 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
፪. ቅዱስ እንጦኒ ሐዲስ ሰማዕት
፫. ቅዱሳን ሰማዕታት አውሳንዮስ፣ ፊልሞናና ሉቅያ ድንግል [የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ደቀ መዛሙርት]
፬. ቅዱስ ቶና ዲያቆንና ሰማዕት
፭. ቅዱስ ሚናስ ዘሃገረ ቁስ

[    † ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
፪. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፫. ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፭. አቡነ አቢብ [ አባ ቡላ ]

" ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ። አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን ይህን አደረገልኝ። ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምሕረትን አገኘሁ።" † [፩ጢሞ ፩፥፲፪-፲፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖
👍4
1
#ጾም_ከሆድ ብቻ አይደለም
#ዐይን ከዝሙት ይጾማል፡፡
#ምላስ ከሀሜትና ከስድብ ይጾማል፡፡
#እጅ ከዘፈን ጭብጨባ ይጾማል፡፡
#ስሜት ከሆታ ይጾማል፡፡
#ጆሮ ከመጥፎ ወሬ ይጾማል፡፡

ከመብል ብዛት ጨጓራ ያርፋል፡፡
ጾም ሁለንተናዊ ነው  የጠገበን ያበርዳል፡vየቆሸሸን ያጸዳል፡  ሰውን ከእንስሳት የሚለየው ጾም ነው
ጾም ሲመጣ ሳጥናኤል ይናደዳል፡ ስጋ ይጨነቃል፡፡
ነፍስ ግን ደስታውን አትችለውም፡፡
ጾምን አምላክ በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ ቀን ጹሞ በተግባር ያስተማረን ነው፡፡
መጾም አምላካዊ ባህሪን መላበስ ነው፡፡
ዛሬ መጾም አቅቶት ምግብ ሲውስ የነበረው ስጋ በስብሶ አፈር መሆኑ አይቀሬ ነው፡ ዐይን ቢያምር ፈራጭ ነው፡ ገላ ቢለሰልስ አፈር ነው፡፡
አንጎል በጥበብ ቢጠበብ ነገ ይበላሻል፡፡ ጥፍርም ይነቀላል፡፡ ዛሬ ይምንኮራበት ተክለ ቁመና ነገ አፈር ይሆናል ነፍስ ግን ህያው ናት የአምላክ እስትንፋስ ናትና ፆሙን በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስጨርሰን አሜን 🙏🙏🙏

         
#ሰናይ__ቀን 🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
9🙏5👍3
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †

💖 

    [   ዓ ለ ም ን   ስ ለ መ ተ ው !   ]

           [     ክፍል ስድስት     ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

የቀደመው ሙቀት ሊመለስ የሚችለው ... !

❝ ገና በጅምሩ ከውጊያ ተጋድሎ መዘግየትና በዚህም ምክንያት የመምጣታችንን ምልክት [ማስረጃ]  ለገዳዩ መስጠት በጣም የተጠላና አደገኛ ነገር ነው። ጽኑ የሆነ ጅማሮ በርግጥ ኋላ ላይ ደከም ስንል የሚጠቅመን ነው። መጀመሪያ ላይ ብርቱ ፣ በኋላ ግን ዛል የምትል ነፍስ በቀደመ ቅንዓቷ ትውስታ የምትገፋፋ ናት፡፡ በዚህም መንገድ ሁሌም አዳዲስ ክንፎች የሚገኙ ናቸውና፡፡

ነፍስ ራሷን ስትክድና በረከቷን እንዲሁም ትኵሳትን መናፈቅ ስታጣ ፣ ይህ የማጣቷ መንስኤ ምን እንደ ሆነ በጥንቃቄ ትመርምር፡፡ ለዚህ መንስኤው ምንም ሆነ ምን ራሷንም በናፍቆትና በቅንዓት ሁሉ ታስታጥቅ፡፡ የቀደመው ሙቀት ሊመለስ የሚችለው በወጣበት ተመሳሳዩ በር ብቻ ነው፡፡

ከፍርሃት የተነሣ ዓለምን የሚተው ሰው በመዐዛ እንደሚጀምር ዳሩ ግን በጢስ እንደሚጠናቀቅ የሚቀጣጠል ዕጣን ነው፡፡ የሚያገኘውን ዋጋ አስቦ ዓለምን የሚተው ሰው ሁሌም በተመሳሳይ አቅጣጭ እንደ ሚዞር የወፍጮ ድንጋይ ነው፡፡ ነገር ነገር ግን እግዚአብሔርን ከመውደዱ የተነሣ ከዓለም የሚለይ ሰው ገና ከጅምሩ እሳትን አገኘ ፤ ነዳጅ እንደ ተደረገበት እሳትም ፈጥኖ በዝቶ ይቀጣጠላል፡፡ ❞


[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                       💖                     🕊
2👍2
4
                       †                           

†    🕊  ተግባራዊ ክርስትና  🕊   †

💖 

     [   ጥቅም አልባ እውቀት !   ]

            [     ክፍል አንድ     ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

ዓለማዊ ወሬዎችን እያስወገድኩ ነው ....!


❝ ክርስቲያናዊ ፍጹምነትን ለማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ሕሊናህን ለነፍስህ ከማይጠቅም ወሬ መጠበቅ አለብህ፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ዘመኑ የመረጃና የመረጃ ጥበብ ዘመን ነው፡፡ ዓለም በቲቪ፣ በመጻሕፍት፣ በጋዜጦች ብቻ ሳይሆን በመረጃ መረብ ጭምር የሚያጥለቀልቅ መረጃን ከምንጊዜም በላይ እያቀረበችልን ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ጥቅም የለሽ መረጃ እኔ የአእምሮ ብክለት ብዬ ለምጠራው ችግር ይዳርጋል፡፡ በዚህ ዘመን ለሥራቸው ውጤታማነት ቢጠቅምም ባይጠቅምም መረጃን በመረጃነቱ ብቻ የሚፈልጉ የመረጃ ሱሰኞች አሉ፡፡

በዐቢይ ጾም ወቅት የማደርገውን ልንገራችሁ ፤ በሬድዮ ዜናን ከመስማት ፣ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ከማንበብ እከለከላለሁ፡፡ እመኑኝ ምንም ነገር አያመልጠኝም ፤ አይጎድልብኝም ፤ ይልቁንስ ሕሊናዬ ከመረጃ ብክለት ነፃ ይሆናል ፤ ስለዚህ በትክክል እንደሚሰራ አምናለሁ፡፡

የአንድ መነኩሴ ታሪክ ሰምተን ነበር ፤ ይህ መነኩሴ ከሌሎች መነኮሳት ጋር ሲነጋገር ቆይቶ ወደ በዓቱ ከሔደ በኋላ እጅግ በተደጋጋሚ በአቱን ሲዞር አንድ መነኩሴ ተመለከተውና ምን እያደረገ እንደሆነ ጠየቀው ፤ እርሱም መለሰ "ስናወራቸው የነበርናቸውን ዓለማዊ ወሬዎችን እያስወገድኩ ነው ፤ ወደ በዓቴ ይዤ መግባት አልፈልግም፡፡ ❞

[ አቡነ አትናስዮስ እስክንድር ]


🕊                       💖                     🕊
3👍1
5
🕊

[  † እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሆሴዕ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †  ቅዱስ ሆሴዕ ነቢይ  †  🕊

† ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን [አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር] : መጻዕያትን [ገና ለወደ ፊት የሚሆነውን] የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው ደግሞ በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::

ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: [ሐዋ.፲፩፥፳፯] ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ::

ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: [ቅዳሴ ማርያም]

የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::

ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: [ዮሐ.፬፥፴፮]

ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: [ማቴ.፲፫፥፲፮ , ፩ዼጥ.፩፥፲] ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::

ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት

¤ ፲፭ [15] ቱ አበው ነቢያት :
¤ ፬ [4] ቱ ዐበይት ነቢያት:
¤ ፲፪ [12] ቱ ደቂቀ ነቢያትና
¤ ካልአን ነቢያት ተብለው በ፬ [4] ይከፈላሉ::

"፲፭ [15] ቱ አበው ነቢያት" ማለት :-

- ቅዱስ አዳም አባታችን
- ሴት
- ሔኖስ
- ቃይናን
- መላልኤል
- ያሬድ
- ኄኖክ
- ማቱሳላ
- ላሜሕ
- ኖኅ
- አብርሃም
- ይስሐቅ
- ያዕቆብ
- ሙሴና
- ሳሙኤል ናቸው::

"፬ [4] ቱ ዐበይት ነቢያት"

- ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
- ቅዱስ ኤርምያስ
- ቅዱስ ሕዝቅኤልና
- ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::

"፲፪ [12] ቱ ደቂቀ ነቢያት"

- ቅዱስ ሆሴዕ
- አሞጽ
- ሚክያስ
- ዮናስ
- ናሆም
- አብድዩ
- ሶፎንያስ
- ሐጌ
- ኢዩኤል
- ዕንባቆም
- ዘካርያስና
- ሚልክያስ ናቸው::

"ካልአን ነቢያት" ደግሞ :-

- እነ ኢያሱ
- ሶምሶን
- ዮፍታሔ
- ጌዴዎን
- ዳዊት
- ሰሎሞን
- ኤልያስና
- ኤልሳዕ . . . ሌሎችም ናቸው::

ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::

- የይሁዳ [ኢየሩሳሌም]:
- የሰማርያ [እሥራኤል] ና
- የባቢሎን [በምርኮ ጊዜ] ተብለው ይጠራሉ::

በዘመን አከፋፈል ደግሞ :-

- ከአዳም እስከ ዮሴፍ [የዘመነ አበው ነቢያት] :
- ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል [የዘመነ መሳፍንት ነቢያት]
- ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት [የዘመነ ነገሥት ነቢያት]
- ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ [የዘመነ ካህናት ነቢያት] ይባላሉ::

ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::

ቅዱስ ሆሴዕ ቁጥሩ ከ፲፪ [12] ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ/ል/ክርስቶስ በ፰ መቶ [800] ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው:: አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ ፲፬ [14] ምዕራፍ: ሲያንስ አንድ ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል::

ነቢይና ጻድቅ ቅዱስ ሆሴዕ 'ዖዝያ' በመባልም ይታወቃል:: ቅዱሱ ነቢይ የቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ-ቃል ባልንጀራ የነበረ ሲሆን በ፬ [4] ነገሥታት ዘመን [ዖዝያን : ኢዮአታም : አካዝና ደጉ ሕዝቅያስ] ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናግሯል:: የትንቢት ዘመኑም ከ፸ [70] ዓመት በላይ ነው::

ከ፲፪ [ 12 ]ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሆሴዕ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራም በስፋት ተንብዩዋል:: ፲፬ [14] ምዕራፎች ያሉት የትንቢቱ ጥራዝ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል:: ሆሴዕ ማለት መድኃኒት ማለት ነው:: የመዳን ትምሕርትንና ትንቢትን ሊናገር ተመርጧልና::

† ቸር አምላከ ነቢያት የነቢያቱን መከራ አስቦ ከመከራ: በእንባቸውም ከእንባ ይሰውረን:: ከተረፈ በረከታቸውም አያጉድለን::

🕊

[   † የካቲት ፳፮ [26] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ሆሴዕ ነቢይ [ከ፲፪ [12]ቱ ደቂቀ ነቢያት]
፪. ቅዱስ ሳዶቅ ሰማዕት
፫. ፰፻፰ ["808"] ሰማዕታት [ከቅዱስ ሳዶቅ ጋር የተሰየፉ]

[    † ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፬. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፭. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

" ኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንመለስ:: እርሱ ሰብሮናልና: እርሱም ይፈውሰናል:: እርሱ መትቶናል: እርሱም ይጠግነናል:: ከሁለት ቀን በሁዋላ ያድነናል:: በሦስተኛውም ቀን ያስነሳናል:: በፊቱም በሕይወት እንኖራለን:: እንወቅ:: እናውቀውም ዘንድ እንከተል . . . "
[ሆሴዕ.፮፥፩-፫]  (6:1-3)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖
4👍2
Audio
👍1
4👍1
#አርጋኖን__ዘረቡዕ 

ምዕራፍ ፩ 

፩. ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሜ እግዚአብሔርን አመግናለሁ፡፡ ስላንቺም፡፡ (ሮሜ ፩- ፰)
፪. የውዳሴሽ ወሬ በዓለም ሁሉ ተሰምቷልና በመንፈስ ቅዱስ እንደተናገርሽ እንዲህ ስትይ እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል፡፡ (ሉቃ፣ ፩፣ ፵፰) 
፫. በውነት ምስጋና ይገባሻል፡፡ የእግዚአብሔር እናቱ ሁነሻልና በውነት መደነቅ ይገባሻል፡፡ ዓለምን ሁሉ በመሐል እጁ የያዘ እርሱን ወልደሻልና በዕውነት ብፅዓን ይገባሻል ለዕውነተኛ ፀሐይ መውጫ ሆነሻልና፡፡ 
፬. በዕውነት መመስገን ይገባሻል ለማለዳው ኮከብ ምሥራቅ ሆነሻልና በውነት መደነቅ ይገባሻል፡፡ ለጥምቀት ልጆች መመከያ ሆነሻልና፡፡ በውነት ብፅዕና ይገባሻል፡፡ ለሃይማኖት መሠረት ጽናተ ሆነሻልና፡፡ 
፭. ከኪሩቤል ክብር ገናንነት ላንቺ ይገባል፡፡ ከሱራፌልም ውዳሴ ከመላእክትም እልልታ ከመላእክት አለቆችም ዝማሬ ላንቺ ይገባል፡፡ 
፮. ከነቢያት ትንቢት ከሐዋርያት ስብከት ላንቺ ይገባል፡፡ ከቅዱሳን ሰማዕታት እናታችን መባል ከመሐይምናንም እመቤታችን መባል ከክርስቲያንም ሁሉ አፍ የመድኃኒታችን ቀንድ መባል ላንቺ ይገባል፡፡ 
፯. ከመሲሓውያን ነገስታት አፍ ንግሥታችን መባል ከልዑላንም መላእክት በላይ ከፍ ከፍ ማለት ከታችኞችም ፍጡራን ላንቺ መገዛት ይገባል፡፡ እንግዲህ አንቺ ከሰማይ ትበልጫለሽ ከተራሮችም ከፍ ትያለሽ፡፡ ስለ አንቺም እንዲህ እላለሁ ከፀሐይ ብርሃን ከጨረቃም ድምቀት አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ 
፰. ስለ አንቺ እንዲህ እላለሁ፡፡ ከአርዮብ መልክ ከመብረቅም ብርሃን አንቺ ታበሪያለሽ፡፡ ስላንቺ ደግሞ እንዲህ እላለሁ በሰማይ ካሉ ትጉሃን መላእክት ትከብሪያለሽ፡፡ ከመናብርትም ከሥልጣናትም ትቀደሻለሽ፡፡ 

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
11👍1🙏1
#መድኃኒዓለም_ዛሬም_የወደድከኝ_ተመስገን!

የነፍሴ ንጉስ የህይወቴ ቤዛ ጌታዬኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! አመሰግንሃለሁ ። እኔን መውደድህ
#ይገርመኛል እንደሞተ ውሻ የምቆጠረውን ማፍቀርህ #ይደንቀኛል ። ኣምላኬ ሆይ ! ምኔን አይተህ ነው #የወደድከኝ ? ራሴን በጽሞና ሳየው ራሴን እንኳ መውደድ አቃተኝ ። አንተ ግን ህይወት ንጹህ ሳለህ እንደ ወንጀለኛ #ተከሰስክልኝ ። የኔ አፍቃሪ ንጉስ የማይገባኝን ልትሰጠኝ የማይገባህን መከራ #ተቀበልክልኝ ።የምለው ባጣ እንዲሁ ተመስገን ! እልሃለው ።በማላውቀው ጉዳይ እፈርዳለሁ አንተ ግን ብምታውቀው ጉዳይ #ትምራለህ ። እባክህን እውቀትና ዕድሜ ያልለወጠኝን እባክህ አንተ የልቤ ጌታ #ለውጥልኝ ። እንደወደድከኝ መጠን ልወድህ #አልችልም ነገር እባክህን አቅም ስጠኝና እንደ አባቶቼ ቅዱሳን አብዝቼ #ልውደድህ! ዛሬም ተመስገን!

        
#መልካም__ቀን 🙏

ለመቀላቀል👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
8🙏3
2025/07/14 12:32:22
Back to Top
HTML Embed Code: