Telegram Web
#___ወዳጆቼ

የንጉሥ ሥልጣን #በሥጋ ላይ ነው፤ የካህን ሥልጣን ግን #በነፍስ ላይ ነው፡፡

ንጉሥ ይቅር ቢል #የገንዘብን ዕዳ ነው፤ ካህን ይቅር ሲል ግን #የበደል_የኃጢአት ዕዳን ነው፡፡

ንጉሥ #ያዝዛል፤ ካህን ግን #ያስተምራል ይዘክራል፡፡

ንጉሥ #ያስገድዳል፤ ካህን ግን #ነጻ ፈቃድን ያያል፡፡

ንጉሥ ቁሳዊ #የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፤ ካህን ግን ረቂቅ (#መንፈሳዊ) የጦር ዕቃ መሣሪያ አለው፡፡

ንጉሥ የጦር ዕቃ መሣሪያውን ቢሰብቅ አንገዛም ብለው ባመፁት (እንዲሁም #ከወራሪዎች ሥጋውያን ደማውያን) ላይ ነው፤ ካህን ግን ውጊያው ከጨለማ አበጋዞች #ከአጋንንት ጋር ነው፡፡

ስለዚህ ሥልጣነ ክህነት ከሥልጣነ #መንግሥት ይበልጣል፡፡ እንዲህም በመኾኑ ንጉሥ #አንገቱን ለካህናት እጅ ያጎነብሳል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ትንቢተ ኢሳይያስ፣ ድርሳን ፬ በተረጎመበት ድርሳኑ)

      #ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
11
🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  እኛ በማሕፀን መፀነስን ወደደ ! ]

🕊                    💖                       🕊

❝ በሥጋ ከመጀመሪያው ሰው ከአዳም : ከአብርሃም ከዳዊት ከተገኘ ባሕርይዋም ኃጢአት የሌለበት ፤ በነፍስ በሥጋ ፍጹም የሚሆን አካልን ሊዋሐደው ፈጠረ ፤ ከማርያም የነሣውን ሥጋ ከኃጢአት ፤ ከዘር የራቀ አደረገው ከማሕፀን ጀምሮ በማይመረመር ግብር በአንድ ባሕርየ መለኮት ከእርሱ ጋር አንድ አደረገው። [ዕብ.፪፥፲፮ ]

በማይመረመር ምሥጢር እንደ እኛ በማሕፀን መፀነስን ወደደ። እርሱ ሰው እንደ መሆኑ በማሕፀን ሳለ በባሕርየ መለኮቱ በሰማይ በምድር ከምድርም በታች ምሉእ ነው። በማይመረመር ፥ በማይነገር ጌትነቱም በአብ ዕሪና ይኖር ነበር።

የሕይወት እስትንፋስ ያላቸው ሁሉ በላይ በታች ያሉ ፍጡራንም ሁሉ በመሀል እጁ ናቸው። አቸናፊ ፤ ፈጣሪ እርሱ እንደ ከሀሊነቱ ሁሉን ያዝዛቸዋል። [ ሉቃ.፩፥፵፪ ና ፶፩ ። ዕብ.፩፥፪፬ ]

ወልድ በድንግል ማሕፀን ሳለ ፤ በሰማይም በምድርም ከአባቱ ጋር በአንድ ባሕርየ መለኮት ህልው ነውና ከኃጢአት በቀር በድንግል ማሕፀን ሥጋ ሆኖ ከተፈጠረ ከፍጹም ትስብእት ጋርም በማይመረመር ባንድ ባሕርየ መለኮት መቸም መች አንድ ነውና። [ ዮሐ.፲፬፥፲ ]

እርሷም በሥጋ ወለደችው ዳግመኛም በሥጋ ጨርቅ ያለበሱት እርሱን ነው። ከሰው የተወለደ ትንሽ ልጅ እንደ መሆኑ በበረት ጣሉት። ዳግመኛ ከልዕልናው ከጌትነቱ የማይለወጥ አምላክ ሲሆን ከድንግል ጡት ወተትን የጠባ እርሱ ነው። [ ሚል.፫፥፮ ] ❞

[    🕊   ቅዱስ ቄርሎስ   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                         †                         †
💖                     🕊                      💖
5
3
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †


            [   ክፍል  ሠላሳ አምስት  ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ አንድ ሰው ኑዛዜ ለማድረግ ከወሰነ ፣ በዚህ ምክንያት ነፍስ ኃጢአትን ከመፈጸም በልጓም እንደ ተያዘ ትያዛለች፡፡ በድፍረት እያደረግነው ሳንናዘዝ የምንተወው ከሆነ በጨለማ እንዳለ እንሆናለንና፡፡

የበላዩ በማይኖርበት ጊዜ ፊቱን በዓይነ ሕሊና መሳልና ዘወትር በፊታችን እንደ ቆመ በማሰብ ፣ መሰባሰብንም ሁሉ ፣ ወይም ንግግር ወይም ምግብ ፣ ወይም መኝታ ፣ ወይም እርሱ ይጠላዋል ብለን የምናስበውን ማንኛውንም ሌላ ነገር ሁሉ ካስወገድን ፣ እንኪያስ በእውነት እውነተኛ መታዘዝን ተምረናል፡፡ ዲቃላ ልጆች የመምህራቸውን መቅረት [ አለመኖር ] እንደ ደስታ ይቆጥሩታል ፣ በሕግ የተወለዱት ግን እንደ ጉዳት ይቆጥሩታል፡፡

አንድ ጊዜ እጅግ ልምዱ ካላቸው አባቶች አንዱን ትሕትና እንዴት በመታዘዝ እንደሚገኝ ይነግረኝ ዘንድ አጥብቄ ጠየቅሁት፡፡ እርሱም ፦ ለይቶ ለይቶ የማወቅ ጸጋ ያለው ታዛዥ ሰው ፣ ሙት የሚያስነሣና የአንብዕ ጸጋ የተሰጠው ፣ እንዲሁም ከፀብእ [ ከፀብአ አጋንንት ] ነጻ ቢሆን እንኳ ፣ ያን ያደረገው የመንፈሳዊ አባቱ ጸሎት እንደ ሆነ አድርጎ የሚያስብ ነው ፣ ከከንቱና ባዕድ አሳብም የተለየ ሆኖ ይኖራል፡፡ እርሱም ራሱ እንዳመነው ስለ ተደረገው ነገር በአባቱ እርዳታ እንጂ በራሱ ጥረት እንደ ሆነ አድርጎ እንዴት ራሱን ሊያስታብይ ይችላል? አለኝ፡፡ ❞

[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                      💖                     🕊
4
1
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷  " ብ  ር  ቱ     ት  ግ  ል  [  ፪   ] "

[  💖     የሶሎሞን መዝሙር     💖  ] 

[                        🕊                        ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ በጠበበው ደጅ ግቡ ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና ፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ፤

ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና ፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው። ❞

[ ማቴ . ፯ ፥ ፲፫ ]


🕊                       💖                   🕊
1
3
🕊

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡   †

†    እንኳን አደረሳችሁ   †

[ † ግንቦት ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  † ]

🕊   †  አርዋ ቅድስት  †   🕊

እናታችን ቅድስት አርዋ በስነ ገድላቸው ከደመቁ የቀደመው ዘመን ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት:: በሕጻንነቷ የሚገባውን የክርስትና ትምሕርት ተምራለችና ምርጫዋ ሰማያዊው ሙሽርነት ሆነ::

ለሰዎች ሕይወት እንቅፋት እየሆኑ ከሚያስቸግሩ ነገሮች አንዱ መልክ ነው:: እግዚአብሔር የፈጠረውን ደም ግባት [ቁንጅና] በማይገባ ተጠቅመው የአጋንንት ራት የሆኑ: ሌሎችንም አብረው ያጠፉ ሰዎች ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው:: አርዋ ግን ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ብትሆንም እርሷ ለዚሕ ቦታ አልነበራትም:: በለጋ እድሜዋ በክርስቶስና በድንግል እናቱ ፍቅር ተጠመደች እንጂ::

ቅድስት አርዋ ሁሉ ያላት ስትሆን ስለ መንግስተ ሰማያት ሁሉን ንቃለች:: በተለይ ደግሞ ሥጋዊ ፍትወትን ትገድል ዘንድ ያሳየችው ተጋድሎ በዜና ቤተ ክርስቲያን የተደነቀ በመሆኑ "መዋኢተ ፍትወት" [የሥጋን ፍላጎት ድል የነሳች] አስብሏታል::

የሚገርመው የቅድስቷ እናታችን ሕይወት በጾምና በጸሎት ብቻ የተወሰነ አልነበረም:: በሰው ሁሉ ፊት ብርሃን መሆን የቻለ የደግነት: ርሕራሔ: የፍቅርና የምጽዋት ሕይወትም ነበራት እንጂ::

አንድ ቀን በተንኮለኞች የሐሰት ምስክር ያለ ጥፋቷ ለፍርድ ቀረበች:: ፍርደ ገምድል ዳኛ ሞት ፈረደባት:: በአደባባይ በጭካኔ ቅድስት እናታችንን ገደሏት:: እግዚአብሔር ግን ድንቅ ነውና ከሞት አስነስቷት ገዳዮቿ እንዲጸጸቱ አድርጓል:: ከዚሕ በኋላም በንጹሕ አኗኗሯ ቀጠለች::

አንድ ቀን ግን ከባድ ፈተና መጣባት:: አንድ በደም ግባቷ ተማርኮ ሲፈልጋት የኖረ ጐልማሳ አሳቻ ሰዓትና ቦታ ላይ አገኛት:: የሥጋ ፈቃዱን ይፈጽም ዘንድ አስገደዳት::

እርሱን መታገሉ ከአቅሟ በላይ ስለሆነባት እርሱ ልብሱን እያወለቀ እርሷ ከወደቀችበት ሆና ወደ ፈጣሪዋ ለመነች :- "ጌታየ ሆይ! የእኔንም ድንግልና ጠብቅ: እርሱንም ኃጢአት ይሠራ ዘንድ አትተወው:: ስለዚሕም ነፍሴን ተቀበላት" ብላ አለቀሰች::

እመቤታችን እንደ ዐይን ጥቅሻ ወርዳ ነፍሷን አሳረገች:: ጐልማሳው ወደ ጣላት ቅድስት ዘወር ቢል ሙታ አገኛት:: እርሱም ተጸጸተ:: ወገኖቿ በዝማሬ እናታችን ቅድስት አርዋን ቀብረዋታል::

🕊  †  ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ  †   🕊

ዳግመኛ በዚህች ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቆሮስ አርፏል::

ቅዱስ ቆሮስ ከ72ቱ [ ፸፪ቱ ] አርድእት አንዱ ሲሆን ከጌታችን እግር የተማረ: ለስብከተ ወንጌል ብዙ ሃገራትን የዞረ ታላቅ ሐዋርያ ነው:: ባስተማረባቸው ቦታዎች ብዙ ሕማማትን ተቀብሏል::

ብዙ አሕዛብንም ወደ አሚነ ክርስቶስ መልሷል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለዓመታት አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስ ሲታሠር መልዕክቶችንም ይወስድለት ነበር::

† ወርኀ ግንቦትን በሰላም ላስፈጸመን እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን:: አምላካችን ከወዳጆቹ በረከትን ይክፈለን::   †

🕊

[ † ግንቦት ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅድስት አርዋ እናታችን
፪. ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ዲማዲስ ሰማዕት
፬. አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት

[ †  ወርኃዊ በዓላት ]

፩፡ ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
፪፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
፫፡ አባ ሣሉሲ ክቡር
፬፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት
፭፡ ቅድስት ሶፍያና ሰማዕታት ልጆቿ

" መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ:: አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ:: ውበት ሐሰት ነው:: ደም ግባትም ከንቱ ነው:: እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች:: ከእጇ ፍሬ ስጧት:: ሥረዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት:: " [ምሳሌ.፴፩፥፳፱] (31:29)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
3
1
#ወዳጄ!!

#ጠላቶች_ስንሆን፣በደለኛ ስንሆን በልጁ ይቅርታ ያደረገልን ማን እንደ #እግዚአብሔር አለ።
ሰው ሲበድል ተበዳዩን ካሳ ሰጥቶ ይቅርታ ይጠይቃል፣ እግዚአብሔር ግን በደለኞች ስንሆን ፣እርሱ እራሱ ካሳውን ከፍሎ
#ይቅርታ_አደረገልን🙏 እንዴት ያለ #ፍቅር ነው
"፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ
#እግዚአብሔር_አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። "
(የዮሐንስ ወንጌል 3: 16)

            
#_ሰናይ__ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
9
                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት  "    ]
             
             [     ክፍል አምስት    ]

❝ ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። ❞ [ ፪ጴጥ.፩፥፳ ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                         👇
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     [   በዓለ ዸራቅሊጦስ  ]      🕊

† እንኩዋን ለበዓለ ዸራቅሊጦስ [ መንፈስ ቅዱስ ] በሰላም አደረሳችሁ †

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው ፦ " ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ፣ ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር የሚኖር የእውነት መንፈስ እሰጣችኋለሁ። [ ሐዋርያትም ] ' አንተ ካረግህ እንዳንተ ያለ ከዴት እናገኛለን!? ፣ ስለ ትንሣኤህስ [ ብንሰብክ ] ማን ያምነናል !? ' አሉት። ኢየሱስም " እናንተ በእኔ ናችሁ እኔም በአባቴ ነኝ ፣ መንፈሴን ተቀበሉ እና ትንሣኤየን ስበኩ " አላቸው። ❞ [  ድጓ ዘፋሲካ  ]

🕊

❝ ሃይማኖት ከአብ ዘንድ የተገኘች ናት ፣ ወደ ወልድ የምታደርስ ናት ፣ በመንፈስ ቅዱስም የምትፈጸም [ ፍጽምት የምትሆን ] ናት። ❞ [ ድጓ ዘፋሲካ ]


🕊  የቤተክርስቲያን የልደት ቀን  🕊


🕊                       💖                   🕊
2025/07/13 18:36:53
Back to Top
HTML Embed Code: