Telegram Web
8
#ወዳጆቼ

#ይህ_ብርድ አንድ ታላቅ ውለታ አያስታውስህም
ብርድ ሲበርድህ የብርድ መከላከያ ነገር ትፈልጋለህ (ብርድ ልብስ)
#ለስጋህ እንዲህ አደረክ
#ነፍስህ ስትበረድስ ምን ታለብሳት?
አዳምና ሔዋን
#በኀጢአት ብርድ በወደቁ ጊዜ ክርስቶስ ስጋን ለብሶ #የኀጢአት_ብርድን አስወገደላቸው።
ታዲያ ወዳጄ በነፍስ ተበርደህ ከሆነ መፍትሄው
#ክርስቶስን መልበስ ነው

"፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን
#ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም #ለሥጋ አታስቡ።

(ወደ ሮሜ ሰዎች 13: 14)

#መልካም__ቀን 🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
12🙏5
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷     "  የጥንካሬ ዓይነቶች  " 

💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖  ]

[           🕊                  🕊              ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬


❝ ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ ፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን። ❞

[  ቆላ . ፩ ፥ ፲፪   ]



🕊                       💖                   🕊
1🙏1
🥰2
                        †                           

🕊   💖  ዼጥሮስ ወዻውሎስ  💖   🕊

                         🕊                         

[  እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ዼጥሮስ ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ   ]


❝ ስማቸው ጴጥሮስና እንድርያስ ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ፣ ፊልጶስና በርተሎሜዎስ ፣ ቶማስና ማቴዎስ ፣ ታዴዎስና ናትናኤል ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ማትያን በመባል ለሚጠሩ ለ ፲፪ ቱ የመድኅን ሐዋርያት ሰላምታ ይገባል። ❞

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ አቤቱ በስምኽ የሰበኩ ፤ በታላቅ መከራ በረኀብና በጥም ፤ በብርድና በመራቆት ፤ በመውዛትና በመድከም ፤ ከነገሥታትና ከመኳንንት ዘንድ ተፈርዶባቸው መከራን በመቀበል በምድር ኹሉ ውስጥ የቃልኽን መዝገብ ስለዘሩ ስለነዚኽ ደቀ መዛሙርትኽ ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ ፤ በእሳት በመከራ የተቀበለ አለ ፤ በጦርም የተወጋ አለ ፤ በሰይፍም የተቆረጠ አለ ፤ በመንኰራኲርም የተፈጨ አለ ፤ በደንጊያም የተወገረ ፤ በበትርም የተቀጠቀጠ አለ ፤ ስለነርሱ ብለኽ ማረኝ አስበኝም ፤ ስለሥቃያቸው ስለመቸገራቸውና ስለደማቸው ብለኽ የእኔን የአገልጋይኽን የዕዳ መጽሐፌን ቅደድ ፤ አሜን። ❞

[   ተአምኆ ቅዱሳን   ]

ሕዝብ ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡራን አዕማደ ቤተክርስቲያን ፣
ሰመየ ስሞሙ ደቂቀ ብርሃን ጴጥሮስ ወጳውሎስ።


†     🕊   እንኳን  አደረሰን    🕊    †


🕊                        💖                       🕊
                                   
🙏2
🥰3
🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

❖   ሐምሌ ፭    ❖

[ 🕊 ✞ እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ዼጥሮስ ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ 🕊 ]

ፍጡር ቢከብር ከእመ ብርሃን ቀጥሎ የእነዚህን ቅዱሳን ያህል የሚከብር አይኖርም:: ለቤተ ክርስቲያን ያልሆኑላት ምንም ነገር የለምና እርሷም "ብርሃኖቼ: ዐይኖቼ: ዕንቁዎቼ" ብላ ትጠራቸዋለች::


🕊  † ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት †  🕊

የዮና ልጅ ስምዖን ዼጥሮስ [ኬፋ] የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው:: ይሔውም ዓለት [መሰረት] እንደ ማለት ነው::

¤ በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ አድጐ

¤ ሚስት አግብቶ ዕድሜው ፶፮ [56] ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው:: በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ: በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል:: ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል:: [ማቴ.፲፮፥፲፯] (16:17) , [ዮሐ.፳፩፥፲፭] (21:15)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሰራው ስሕተት ንስሃ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል:: ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በሁዋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከት አካፍሏል:: ምንም የርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል::

በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል:: አሕዛብ ግብራቸው እንደ እንስሳ ነውና በአባታችን ላይ ቀልደዋል:: እርሱ ግን ሁሉንም ታግሷል:: የቅዱሱን ታሪክ ለመናገር ከመብዛቱ የተነሳ ይከብዳልና ልቡና ያለው ሰው ሊቃውንትን ሊጠይቅ እንደሚገባ እመክራለሁ::

ቅዱስ ዼጥሮስ መልካሙን ገድል ተጋድሎ በ፷፮ [66] ዓ/ም የኔሮን ቄሳር ወታደሮች ሲሰቅሉት ለመናቸው:: "እባካችሁን? እኔ እንደ ጌታየ ሆኜ መሰቀል አይገባኝም" አላቸው:: እነሱም ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል:: በበጐ እረኝነቱም የማታልፈውን ርስት ከነመክፈቻዋ ተቀብሏል:: በሰማዕትነት ሲያርፍም ዕድሜው ወደ ፹፰ [88] አካባብ ደርሶ ነበር::

†  የቅዱስ ዼጥሮስ መጠሪያዎች :-

፩. ሊቀ ሐዋርያት
፪. ሊቀ ኖሎት [የእረኞች / ሐዋርያት አለቃ]
፫. መሠረተ ቤተ ክርስቲያን
፬. ኰኩሐ ሃይማኖት [የሃይማኖት ዐለት]
፭. አርሳይሮስ [የዓለም ሁሉ ፓትርያርክ]

🕊 † ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ † 🕊

የቤተ ክርስቲያን መብራቷ ቅዱስ ዻውሎስን እንደ ምን ባለ አማርኛ እንገልጠዋለን?

¤ ስለ እርሱ መናገርና መጻፍ የሚችልስ እንደ ምን ያለ ሰው ነው?
¤ የዓለምን ነገር ሲጽፍ በኖረ እጄስ እንደ ምን እጽፈዋለሁ?
¤ ይልቁኑስ የርሱን ፲፬ [14] ቱን መልዕክታትና ግብረ ሐዋርያትን መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም::

ቅዱስ ዻውሎስ ከነገደ ብንያም ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት: ቀናተኛና ፈሪሳዊ ነበር:: ጌታ በደማስቆ ጐዳና ጠርቶ በ፫ [3] ቀናት ልዩነት ምርጥ ዕቃ አደረገው:: ይህ የሆነው በ፵፪ [42] ዓ/ም: ጌታ ባረገ በ፰ [8] ኛው ዓመት ነበር:: ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ:: ጨው ሆኖ አጣፈጠ::

ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም: ከእንግሊዝ እስከ እልዋሪቆን [የዓለም መጨረሻ] ወንጌልን ሰበከ:: ስለ ወንጌል ተደበደበ: ታሠረ: በእሳት ተቃጠለ:: በድንጋይ ተወገረ: በጦር ተወጋ:: ባፍም በመጣፍም ብሎ አገለገለ:: በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ:: ለ፳፭ [25] ዓመታት ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ::

እርሱን የመሰሉ: እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ: በ፷፯ [67] ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል:: ከ፲፬ [14] ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ አግዞታል:: ልክ ቅዱስ ዼጥሮስ ማርቆስን እንዳገዘው ማለት ነው::

🕊 † የቅዱስ ዻውሎስ መጠሪያዎች ፦

፩. ሳውል [ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ]
፪. ልሳነ ዕፍረት [አንደበቱ እንደ ሽቱ የሚጣፍጥ]
፫. ልሳነ ክርስቶስ [የክርስቶስ አንደበቱ]
፬. ብርሃነ ዓለም
፭. ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን [የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ]
፮. የአሕዛብ መምሕር
፯. መራሒ [ወደ መንግስተ ሰማያት የሚመራ]
፰. አእኩዋቲ [በምስጋና የተሞላ]
፱. ንዋይ ኅሩይ [ምርጥ ዕቃ]
፲. መዶሻ [ለአጋንንትና መናፍቃን]
፲፩. መርስ [ወደብ]
፲፪. ዛኅን [ጸጥታ]
፲፫. ነቅዐ ሕይወት [የሕይወት ትምሕርትን ከአንደበቱ
ያፈለቀ]
፲፬. ዐዘቅተ ጥበብ [የጥበብ ምንጭ / ባሕር]
፲፭. ፈዋሴ ዱያን [ድውያንን የፈወሰ] . . .

ጌታችን እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ብርሃን ያብራልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

🕊

[ †  ሐምሌ ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
፫. ቅዱሳን ፸፪ [72] ቱ አርድእት [ዛሬ ሁሉም ይታሠባሉ]
፬. ቅዱስ ሳቁኤል ሊቀ መላእክት
፭. ቅድስት መስቀል ክብራ [የቅዱስ ላሊበላ ሚስት]
፮. ቅዱሳን ዘደብረ ዓሣ
፯. ቅዱሳት አንስት [ዴውርስ: ቃርያ: አቅባማ: አቅረባንያና አክስቲያና-የቅዱስ ዼጥሮስ ተከታዮች]

[ †  ወርሐዊ በዓላት ]

፩. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
፪. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
፫. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
፬. ቅድስት አውጋንያ [ሰማዕትና ጻድቅ]

"ጌታ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው:: "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይሕንን አልገለጠልህምና ብጹዕ ነህ:: እኔም እልሃለሁ:: አንተ ዼጥሮስ ነህ:: በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ:: የገሃነም ደጆችም አይችሏትም:: የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ:: በምድር የምታሥረው ሁሉ በሰማያት የታሠረ ይሆናል:: በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል::"  [ማቴ.፲፮፥፲፯] (16:17)

" በመሥዋዕት እንደሚደረግ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና:: የምሔድበትም ጊዜ ደርሷል:: መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ:: ሩጫውን ጨርሻለሁ:: ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ:: ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል:: ይሕንም ጻድቅ: ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል:: " [፪ጢሞ.፬፥፮] (4:6)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
2🙏1
1
2025/07/12 23:39:29
Back to Top
HTML Embed Code: