🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
የካቲት ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
[ † 🕊 ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ 🕊 † ]
እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም የተወለደው ንጽቢን በምትባል የሶርያ ግዛት ውስጥ በ፪፻፺፰ [298] / ፫፻፮ [306] ዓ/ም ነው:: ወላጆቹ በክርስቶስ የማያምኑ አላውያን ነበሩ:: [ምንም አንዳንድ ምንጮች ክርስቲያኖች ነበሩ
ቢሉም]
ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ንጽቢን ዽዽስናን የተሾመ ቅዱስ ያዕቆብ የሚባል ታላቅ ሰው ነበር:: የሰማዕትነት: የሐዋርያነት: የጻድቅነትና የሊቅነት ግብር ያለው አባት ነው:: ታዲያ ቅዱስ ኤፍሬም ይሔ አባት ሁሌ ሲያስተምር ይሰማው ነበርና በስብከቱ ተማርኮ ደቀ መዝሙሩ ለመሆን በቃ::
ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱስ ያዕቆብ እጅ ከተጠመቀ በሁዋላ ሙሉ የጣትነት ጊዜውን ያሳለፈው በትምሕርት ነው:: የሚገርመው መምሕሩ ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡ የሚወድና ጠርቷት የማይጠግብ አባት ነውና ለልጁ ለቅዱስ ኤፍሬም ይሕንኑ አጥብቆ አስተምሮታል::
ቅዱስ ኤፍሬም ክርስትናን ሲመረምር የእመቤታችን ፍቅር ይበዛለት ጀመር:: ምክንያቱም እመ ብርሃንን ሳይወዱ ክርስትና የለምና:: እንደ እርሱ የሚወዳት የለም እስኪባል ድረስ ያገለግላት: ይገዛላትም ገባ::
እንዲህ እንደ ዛሬ የድንግል ማርያም ምስጋና በአንደበት እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበር:: እርሱ ግን ከወንጌለ ሉቃስ በስድስተኛው ወርን [ይዌድስዋን] እና ጸሎተ ማርያምን [ታዐብዮን] አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ ፷፬ ፷፬ [ 64 64 ]ጊዜ ያመሰግናት ነበር::
በእንዲህ ያለ ግብር እያለ አርዮስ በመካዱ እርሱን ለማውገዝና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ለማጽናት በ ፫፻፲፯/፫፻፳፭ [ 317 / 325 ] ዓ/ም ፫፻፲፰ [318] ቱ ሊቃውንት በኒቅያ ሲሰበሰቡ አንዱ መምሕረ ኤፍሬም ቅዱስ ያዕቆብ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ኤፍሬም ከሊቃውንቱ ትምሕርትና በረከትን አግኝቷል::
ከጉባዔ መልስ መንገድ ላይ በራዕይ የብርሃን ምሰሶ አይቶ "ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ "ይህማ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ነው" አለው:: እርሱም መምሕሩን ቅዱስ ያዕቆብን ተሰናብቶ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ [ቂሣርያ] ወረደ:: ተገናኝተውም በአንድ ሌሊት ቁዋንቁዋ ተገልጦላቸው ሲጨዋወቱ አድረዋል::
በቦታው ብዙ ተአምራት ተደርጉዋል:: ቅዱስ ኤፍሬም ከታላቁ ባስልዮስ ከተማረ በሁዋላ ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ያስተምር ጀመር:: ሁል ጊዜ ታዲያ ጸሎቱ ይሔው ነበር:: "እመቤቴ ሆይ! ምስጋናሽ እንደ ሰማይ ከዋክብት: እንደ ባሕር አሽዋ በዝቶልኝ: እንደ እንጀራ ተመግቤው: እንደ ውሃ ጠጥቼው: እንደ ልብስም ተጐናጽፌው" እያለ ይመኝ ነበር::
አፍጣኒተ ረድኤት: ፈጻሚተ ፈቃድ እመ ብርሃንም በገሃድ ተገልጻ የልቡን ፈቃድ ፈጸመችለት:: ዛሬ ጸጋ በረከት የምናገኝበትን ውዳሴ ማርያምን ደረሰላት:: ሲደርስላትም እርሷ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላ ወርዳ: በፊቱም ተቀምጣ ሲሆን እርሱ ደግሞ ባጭር ታጥቆ: በፊቷ ቆሞ: በመንፈስ ቅዱስም ተቃኝቶ ነው::
ውዳሴዋን በ፯ [7] ቀናት ከደረሰላት በሁዋላ በብርሃን መስቀል ባርካው: ሊቀ ሊቃውንትም እንዲሆን ምስጢር ገልጣለት ዐረገች:: ከዚህ በኋላ በምስጢር ባሕር ውስጥ ዋኝቶ ፲፬ [14] ሺህ ድርሰቶችንም ደርሷል:: ዛሬ ሶርያ ውስጥ የምንሰማውን ዜማም የደረሰው ይህ ቅዱስ ነው::
እንዲያውም አንድ ቀን የምሥጢር ማዕበል ቢያማታው "አሃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" ብሎ ጸልዩዋል:: [የጸጋህን ማዕበል ያዝልኝ] እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በመጨረሻ ሕይወቱ ተክሪት በምትባል ሃገር ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል::
በጣፋጭ ስብከቱ ብዙዎችን ካለማመን መልሷል: የምዕመናንንም ሕይወት አጣፍጧል:: ለመናፍቃንና ለአርዮሳውያን ግን የማይጋፉት ግድግዳ ሆኖባቸው ኑሯል:: በዘመኑም ብዙ ተጋድሎ አፍርቷል: ተአምራትንም ሠርቷል:: በተወለደ በ፷፯ [67] ዓመቱ በ፫፻፷፭/፫፻፸፫ [365 / 373 ዓ/ም ዐርፎ ተቀብሯል::
ቅዱሱ ለሶርያ ብቻ ሳይሆን እመቤታችንን ለምንወድ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ሞገሳችን ሆኗል:: ስለዚህም እንዲህ እያልን እንጠራዋለን :-
፩. ቅዱስ ኤፍሬም
፪. ማሪ ኤፍሬም
፫. አፈ በረከት ኤፍሬም
፬. ሊቀ ሊቃውንት ኤፍሬም
፭. ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም
፮. አበ ምዕመናን ኤፍሬም
፯. ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም . . . አባታችን አንተ ነህ::
❖ የካቲት ፫ ቀን ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዓመታዊ የፍልሠት በዓሉ ነው፡፡
ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን::
[ † 🕊 አባ ያዕቆብ ገዳማዊ 🕊† ]
ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት "ለስሒት መኑ ይሌብዋ- ስሕተትን ማን ያስተውላታል" [መዝ] ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ታላቅ ቅዱስ ሰው በኃጢአት ብዙ ተፈተነ:: ወደ በርሃ ወጥቶ: በምናኔ ጸንቶ: በጾምና በጸሎት ተግቶ ዘመናትን ስላሳለፈ ሰይጣንን አሳፈረው::
ግን ደግሞ ክፉ ጠላት ባልጠረጠረው መንገድ መጥቶ መከራ ውስጥ ከተተው:: የአገረ ገዢው ልጅ ታማ "ፈውሳት" አሉት: ፈወሳት:: ወደ ቤቷ ስትመለስ ግን አመማት:: "ከአንተ ጋር ትቆይ" ብለው ትተዋት ቢሔዱ ከመለማመድ የተነሳ በዝሙት ወደቀ::
እንዳይገለጥበት ስለ ፈራም ገደላት:: በሆነው ነገር ተስፋ ቆርጦ ወደ ዓለም ሲመለስ: ቸር ፈጣሪ የሚናዝዝ አባትን ልኮ ንስሃ ሰጠው:: ጉድጓድ ምሶ: ድንጋይ ተንተርሶ ለ፴ [30] ዓመታት አለቀሰ:: እግዚአብሔርም ምሮት: የቀደመ ጸጋውን ቢመልስለት: ዝናምን አዝንሞ ሕዝቡን ከእልቂት ታድጓል:: በዚህች ዕለት ዐርፎም ለርስቱ በቅቷል::
[ † 🕊 ታላቁ አባ ዕብሎይ 🕊 † ]
ይህ ቅዱስ የአቡነ አቢብ ደቀ መዝሙር ሲሆን በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳንም ቀዳሚው ነው:: ብዙ መጻሕፍት 'ርዕሰ ገዳማውያን' ይሉታል:: የቅዱሱ ተጋድሎ እጅግ ሰፊ ነው::
[ † የካቲት [ ፫ ] 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት † ]
፩. ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ [ አፈ በረከት-በዓለ ፍልሠቱ ]
፪. ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ [ ሕይወቱ መላዕክትን የመሰለ ግብፃዊ አባት ]
፫. አባ ያዕቆብ መስተጋድል
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ ዘካርያስና ስምዖን ]
፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭. አቡነ ዜና ማርቆስ
፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
፯. ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ [ ዓምደ ሃይማኖት ]
+ "ለምኑ ይሰጣችሁማል:: ፈልጉ ታገኙማላችሁ:: መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል:: የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና:: የሚፈልገውም ያገኛል:: መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል::" + [ማቴ.፯፥፯]
+ " የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" [መዝ.፴፯፥፴]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

#ጾም_መድኃኒት_ናት፡፡ አወሳሰድዋን በትክክል ላላወቁ ግን ጥቅም የላትም፡፡ ይህችን መድኃኒት የሚወስድ ሰው በየስንት ሰዓቱና በምን ያህል መጠን እንደምትወሰድ፣ ለምን ዓይነት በሽታ እንደምትጠቅም፣ በየትኛው አከባቢና የአየር ኹናቴ እንደምትወሰድ፣ ከእርሷ ጋር የሚኼዱና የማይኼዱ ምግቦችን እንዲሁም ከእርሷ ጋር የማይስማሙ ሌሎች ነገሮችን ለይቶ ማወቅ አለበት፡፡ እነዚህን ግምት ውስጥ አስገብቶ የማይወስዳት ሰው ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ታመዝንበታለች፡፡ አንድ በሐኪም የታዘዘልንን የደዌ ዘሥጋ መድኃኒት እንዲያሽለን ስንፈልግ በጥንቃቄ ልንወስደው ያስፈልጋል፤ የነፍሳችንን ደዌና በአእምሮአችን ውስጥ ያሉ ቁስሎችን ለመፈወስ ብለን በምንወስደው መድኃኒት ደግሞ ከዚህ የበለጠ መጠንቀቅ ይገባናል፡፡
#እንኳን_ለፆመ_ነነዌ_በሰላም_አደረሳችሁ 🙏
#መልካም__ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
#እንኳን_ለፆመ_ነነዌ_በሰላም_አደረሳችሁ 🙏
#መልካም__ቀን🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
🕊
🕊 † ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ † 🕊
† ታላቁ ሊቅና አፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዛሬ የፍልሰቱ መታሰቢያ ነው። †
🕊 💖 🕊
† [ ከስብከቱ ] †
+ ❝ መለኮት ሥጋን ካልለበሰ በቀር ሞትን ሊሞት ሲኦልም ልትሸከመው ስለማትችል በሥጋ ከድንግል ማርያም መወለድ አስፈለገው። በዚህ ምክንያት ጌታችን የኢየሩሳሌምን ውድቀትና የልጆቿን ጥፋት ለማወጅ በአህያይቱ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም እንደገባ እንዲሁ ሲኦል እርሱን ትገናኘውና በሆዷ ትሸከመው ዘንድ ልትቀበለው ከድንግል ተወለደ። ከድንግል በነሣውም ሥጋ ወደ ሲኦል በመውረድም በዘበዛት ሀብቶቿን ሁሉ በማራቆት ባዶ አደረጋት። ❞
† [ ከተግሣጽ ] †
+ ❝ ፌዘኝነትን የምታፈቅራት ከሆነ ፣ ሁለመናህ እንደ ሰይጣን ነው። በባልንጀራህ ላይ የምታፌዝ ከሆነ ፣ ራስህን የዲያብሎስ አንደበት አድርገሃል። በባልንጀራህ ጉድለት ድክመት ላይ ስም እየሰጠህ የምትሳለቅ ፣ በዚህም ደስ መሰኘትን የምትወድ ከሆነ ፣ ይህን ትፈጽም ዘንድ ያተጋህ ሰይጣን አይደለም ፣ ነገር ግን አንተ የእርሱን ቦታ በጉልበት ነጥቀህ ይዘህበት ነው እንጂ። ❞
🕊
† ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን::

[ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ አጋቦስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
† 🕊 ቅዱስ አጋቦስ ሐዋርያ 🕊 †
† ከ፸፪ [ 72 ] ቱ አርድዕት አንዱ የሆነው ቅዱሱ ሐዋርያ ሃብተ-ትንቢት የተሠጠውና በዘመነ ሐዋርያት [በቀላውዴዎስ ቄሳር ጊዜ] በዓለም ላይ ከባድ ረሃብ እንደሚሆን ትንቢት የተናገረና በርካታ ክርስቲያኖችን ከረሃብና ከሞት የታደገ ትልቅ ሐዋርያ ነው:: [ሐዋ.፲፩፥፳፯ ] (11:27)
በቅዱስ ጳውሎስ ላይ የሚደርሰውን መከራ በመናገሩም "ሐዋርያ ትንቢት" ተብሏል:: በአገልግሎቱ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎችን ወደ ክርስትና በመሳቡ የተበሳጩ አይሁድም በዚህች ቀን ገድለውታል:: በተቀደሰ ሥጋው [መቃብሩ] ላይ ብርሃን ሲወርድ ያየች አይሁዳዊት ሴትም በክርስቶስ አምና ተሰውታለች::
††† የአባታችን በረከት ይደርብን::
[ † ካቲት ፬ [ 4 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አጋቦስ ነቢይ: ሐዋርያና ሰማዕት
፪. አባ ዘካርያስ ትሩፈ ምግባር
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ ወልደ ነጎድጓድ
፪. ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
፫. ቅድስት ሶፊያ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ
† " በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ:: ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነስቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ:: ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ::
ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው: እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ:: እንዲህም ደግሞ አደረጉ:: በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት::" † [ሐዋ. ፲፩፥፳፯]
† " ስለ እኛ ትጸልዩ ዘንድ ይገባቹሃል: ለሁሉ መልካም ነገርን እንደምትወዱና እንደምትሹ እናምናለን:: " † [ዕብ. ፲፫፥፲፰]