Telegram Web
"#ስለትሕትና"

ከአባቶች አንዱ እንዲህ በማለት ተጠየቀ :- #ትሕትና ምንድን ነው ?እርሱም ሲመልስ እንዲህ አለ :- ትሕትና #ታላቅ_ስራ ነው ፡፡ የእግዚአብሔር ስራ ነው ፡፡ የትሕትና መንገዱ ስጋዊ ስራን መስራትንና ኃጢአተኛ መሆንን ማመን ነው፡፡ ራስህን ለሌሎች መግለጥ ነው ፡፡ ይህንን ከሰማ በኀላ ከአኃው አንዱ እንዲህ አለ:- #ራስን_ለሁሉ መግለጥ ማለት ምን ማለት ነው ? ሽማግሌው መለሰ ራስን ኃጢአተኛ አድርጎ መመለከት የሌሎችን በደል እንድትመለከት አያደርግህም፡፡ ሁልገዜም ትኩረትህ የምትሰጠው #ለራስህ_ኃጢአት ነው ፡፡ ያለማቋረጥ ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለህ ፡፡

ከአባቶች አንዱ እንዲህ አለ :- በማናቸውም ጊዜ የበላይነት ስሜት የሚሰማህ ከሆነ #ያጠፋሀል ፡፡ ትእዛዙን መጠበቅ አለመጠበቅህን ታውቅ ዘንድ አእምሮህንና ልቡናህን ቢታዘዙህ ፤ ትእዛዙን ሁሉ መጠበቅ ቢቻልህ ፤ ጠላትህን መውደድ ቢቻልህ ራስህን የማይጠቅም አገልጋይ እድርገህ ብትቆጥር ፤ #የኃጢያተኞችም ዋና አድርገህ ራስህን ብትቆጥር ትጠቀማለህ ፡፡ #ትሑትም ትሆናለህ ፡፡ ይህ አሳብህ በውስጥህ ያለውን ክፋት ያሰወግድልሃል ፡፡

#መልካም_ቀን🙏

የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
15
🕊                    💖                     🕊

[       ምን ልታዩ ወጣችሁ ?       ]

                        🕊                       


❝ ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ ? ነቢይን ? አዎን እላችኋለሁ ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን።

እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። እውነት እላችኋለሁ ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም ፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።

ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች ፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። ❞

[ ማቴ . ፲፩ ፥ ፱ ]

🕊                        💖                     🕊

❝ የአዋጅ ነጋሪ ቃል። የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ። ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል ፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል ፤ ጠማማውም ይቃናል ፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል ፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል ፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። ❞ [ ኢሳ . ፵ ፥ ፫ ]


[      🕊   እንኳን አደረሳችሁ   🕊      ]


🕊                        💖                       🕊
5
4
#ሰኔ_30 #ልደቱ_ለዮሐንስ መጥምቅ
ወብዙኃን ይትፌሥሑ በልደቱ ( በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል) ሉቃ 1 ፥14

የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ ወንድ ልጅም ወለደች። ወንድ ልጅም ወለደች ። ጎረቤቶቿም ዘመዶቿም ጌታ ምህረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርሷ ጋር ደስ አላቸው

በስምንተኛውም ቀን ሕጻኑን ሊገርዙት መጡ ፤ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ወደዱ ፤ እናቱ ግን መልሳ አይሆንም #ዮሐንስ ይባል እንጂ አለች ።  እነርሱም ከወገንሽ ማንም በዚህ ስም የተጠራ የለም አሏት ፤ አባቱንም ማን ሊባል እንደሚወድ ጠቀሱት ፤ ብራናም ለምኖ ስሙ #ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ ፤ ያን ጊዜም አፉ ተከፈተ አንደበቱም ተፈታ

#ዮሐንስ_ማለት ፦ ጸጋ እግዚአብሔር ማለት ነው። ከእግዚአብሔር የተሰጠ ምሕረት ፣ ጸጋ ፣ ደግነት ፣ ባለሟልነት ፣ ውበት እንደ ማለት ነው።

" እስመ መካን ወለደት ሰብዐ ( መካኒቱ ሰባት ወለደች )

1ኛ ሳሙ. 2 ፥ 5 / በማለት የነቢዩ ሳሙኤል እናት  መዘመሯ ለጊዜው ስለ ልጇ የተናገረቸው ሲሆን ፍጻሜው ግን መካኒቱ ኤልሳቤጥ ባለ ሰባት ፍሬ መልካም ዛፍ ቅዱስ ዮሐንስን አበቀለች ስትል ነው። አንድ ሰው አጣሁ ብላ ያዘነችውን ኤሌሳቤጥን የሰባት ክብር ባለቤት ፣ ሰባት ልጅ የመውለድ ያህል ደስታ ያለው ዮሐንስን ሰጣት ጥቂት ሲለምኑት ብዙ መስጠት ለእግዚአብሔር  ልማዱ  ነው ማለት ይህ ነው

#ሰባቱ_ክብር የተባሉትም 
ነቢይ ፣ ሐዋርያ ፣ ባሕታዊ ፣ ሰማዕት ፣ ጻድቅ ፣ መምሕር ፣መልአክ

በጣፋጭ አንደበቱ ወንጌልን የሚሰብክ ፣ ቀኙ የሚያቃጥል መለኮትን የዳሰሰች ፣ ጀርባው በግመል ጠጉር የተሸፈነ ፣ የዮሐንስን ደግነት ፈጽመን እንናገራለን
/ ድጓ ዘዮሐንስ /

ለመቀላቀል👇👇👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
7
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊

▷  " የአረጋዊው የዮሐንስ ምክር ! "


[   " አረጋዊው ዮሐንስ ዘዳልያታ "  ]

[                        🕊                        ]
-----------------------------------------------

❝ በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው ፤ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው። ❞

[  መዝ . ፹፱ ፥ ፯  ]


🕊                        💖                     🕊
                             👇
3
🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                         †                         


❝ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ❞

[ ፩ ዮሐ . ፩ ፥ ፱ ]



         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
1
🕊

[ †  እንኳን ለተባረከ ወር ሐምሌ እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

† እግዚአብሔርን ቸር የምንለው በባሕርዩ ፍጹም ቸር በመሆኑ ነው:: ይሕንን ደግሞ ለማረጋገጥ መቅመስ ይቻላል:: ይገባልም:: [መዝ.፴፫፥፯] ይሔው ደግሞ ያን ሁሉ ኃጢአታችንን ታግሶ ከወርኀ ሐምሌ አደረሰን:: ለዚሕ ቸርነቱ አምልኮ : ውዳሴና ስግደት ይገባዋል::
ለወርኀ ነሐሴ ደግሞ እንዲያደርሰን ልንማጸነው ይገባል::

🕊 † ቅዱስ አግናጥዮስ ሐዋርያዊ ሊቅ †  🕊

† ሐዋርያዊ ጳጳስና ሰማዕት ቅዱስ አግናጥዮስ ገና በልጅነቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያየ : ራሱ ጌታችን ትንቢት የተናገረለት [ማቴ.፲፰፥፩] እና ከጌታ ዕርገት በኋላ ሐዋርያትን የተከተለ አባት ነው:: ጌታ ሲያርግ የአምስት ዓመት ሕፃን ሲሆን ከሰላሳ ስድስት ዓመታት በላይ ሐዋርያትንና ቤተ ክርስቲያንን አገልግሏል::

ዕድሜው ወደ አርባዎቹ ሲደርስ [ኢየሩሳሌም በጠፋችበት ዓመት - በ፸ ዓ/ም] እርሱ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ሆኖ ተሹሟል:: አስቀድሞ ከወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ እግር ምሥጢርና ፍቅርን ጠጥቷልና የተለየ ሰው ነበር:: ቅዱስ አግናጥዮስ ከአንጾኪያ እየተነሳ ምድረ እስያንም በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሷል::

በአካል ያልደረሰባቸውን በጦማር [በክታብ] አስተምሯል:: በአካሉ እንኳ ምንም በጾም በጸሎትና በብዙ ድካም የተቀጠቀጠ ቢሆን ግርማው የሚያስፈራ ነበር:: ከነገር ሁሉ በኋላ የወቅቱ ቄሣር ጠራብሎስ ይዞ አሰቃይቶ ለአንበሳ አስበልቶታል:: በዚህ ምክንያት "ምጥው ለአንበሳ-ለአንበሳ የተሰጠ" እየተባለ ይጠራል::


🕊  † አባ ብዮክ እና አባ ብንያሚን †  🕊

† እነዚህ ቅዱሳን የሥጋ ወንድማማቾች ናቸው:: ካህን አባታቸው በሚገባ ቢያሳድጋቸው እነሱም ገና በወጣትነት የሚደነቅ የክህነት አገልግሎትን ሰጥተዋል:: ሙሉ ሌሊት ለጸሎት : ሲነጋ ለኪዳን : በሠርክ ደግሞ ለቅዳሴ ይፋጠኑ ነበር:: ሁሌም በየቤቱ እየዞሩ የደከመውን ሲያበረቱ : የታመመውን ሲፈውሱ : ያዘነውን ሲያጽናኑ ውለው ትንሽ ቂጣ ለራት ይመገባሉ::

ሰውነታቸው በፍቅር ሽቱ የታሸ ነበርና ብዙዎችን መለወጥ ቻሉ:: አንዴ ቅዳሴ ሊገቡ ሲሉ "አባታችሁ ሊሞት ነው" ቢሏቸው "ሰማያዊው አባት ይቀድማል" ብለው ቀድሰዋል:: አባታቸውንም ቀብረውታል:: በመጨረሻ ግን አንድ ቀን ለመስዋዕት ብለው ያዘጋጁትን የበረከት ሕብስት እባብ በልቶባቸው አገኙ:: እንደ ምንም ፈልገው እባቡን ገደሉት::

ነገር ግን ያ የተባረከ ሕብስት በሆዱ ውስጥ ነበርና ምን ያድርጉት? ጌታን ስለ ማክበር ሊበሉት ፈልገው ጌታን ቢጠይቁት መልአኩ መጥቶ "ሰማዕትነት ሆኖ ይቆጠርላቹሃል" አላቸው:: ሁለቱ ወንድማማቾች ብዮክና ብንያሚን ፈጣሪያቸውን አመስግነው በሉት:: ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ ሁለቱንም እንደተቃቀፉ ዐርፈው አገኟቸው:: መልካም እረኞቻቸው ናቸውና ከታላቅ ለቅሶ ጋር ቀብረዋቸዋል::

🕊 † ቅድስት ቅፍሮንያ ሰማዕት ወጻድቅት † 🕊

† ይህቺ ቅድስት እናታችን ደግሞ ገና በአሥራ ሁለት ዓመቷ ታላቅ እህቷን ተከትላ ገዳም ትገባለች:: በሚገርም ተጋድሎ በጥቂት ጊዜ አጋንንትን አሳፍራ መነኮሳይያትንም አስገርማቸዋለች:: ትጋቷ ግሩም ነበርና ስትታዘዝ : ስትጸልይና ስትሰግድ ያለ እንቅልፍና ምግብ ቀናት ያልፉ ነበር:: በዚህ የተቆጣ ሰይጣን አረማዊ መኮንንን ይዞባት መጣ::

ሌሎች ደናግል ሲያመልጡ እርሷ ለመከራ ተዘጋጅታ ጠበቀችው:: አዕምሮ የጎደለው መኮንኑም ክርስቶስን ካልካድሽ ብሎ ጽኑዕ ጽኑዕ መከራን አመጣባት:: በተጋድሎ ባለቀ አካሏ ሁሉንም ቻለች:: በዚህች ቀን ግን አንገቷን በሰይፍ አስቆርጧታል::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የወዳጆቹን ትዕግስትና ጽናት ለእኛም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊   † ቅዱስ ቶማስ    †    🕊

ዳግመኛ በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ይታሰባል::
ይኸውም ከሕንድ አውራጃዎች በአንዱ ወንጌልን ሰብኮ እኩሎቹ ሲያምኑ እኩሎቹ እንቢ አሉ:: ቅዱስ ቶማስም ያመኑትን "ከጣዖት አምልኮና ከዝሙት ሽሹ" ብሎ መከራቸው::

ምክሩን ከሰሙት አንዱ በዚያው ምሽት ሊጠጣ ወደ መሸታ ቤት ይገባል:: ሰው ሁሉ ከወጣ በኋላ ባለ መሸተኛዋ ሴት እንደለመደችው አብረው እንዲተኙ ስትጠይቀው "እንዴት ሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ እያለ እንዲህ ትይኛለሽ?" በሚል ሰይፍ አውጥቶ አንገቷን ቆረጣት::

እርሱ መልካም ያደረገ መስሎታል:: የሠራው ሥራ [መግደሉ] ግን አሕዛባዊ ግብር ነው:: በማግስቱ ቅዱስ ቶማስ ነገሩን ሰምቶ ሰዎችን ሰበሰበና "ይህንን የአውሬ ድርጊት የፈጸመ ማነው?" ሲል ጠየቀ:: ፈጻሚው ግን አልታወቅም በሚል ዝም አለ:: ወዲያው ቅዱሱ ሐዋርያ ዳቦ አንስቶ ቆረሰና "ለበረከት እያነሳችሁ ውሰዱ" አለ:: ሰውየው ተራውን ጠብቆ ሊያነሳ ሲል እጁ ሰለለች::

ሐዋርያው "ምነው ልጄ! ምን ሆንክ?" አለው:: እሱም እንዳላመለጠ ሲያውቅ እውነቱን ተናዘዘ:: ቅዱስ ቶማስ ግን ሕዝቡ ሁሉ እንደተሰበሰበ ያን ወጣት ገስጾ "አስከሬኑን አምጡልኝ" አለ::

የወጣቱን እጅ ፈውሶ "በል የገደልኩሽ እኔ:: የሚያስነሳሽ ግን ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:: ብለህ አንገቷን ቀጥለው" አለው:: እንዳለው ቢያደርግ የሞተችው አፈፍ ብላ ተነሳች:: ይህንን ተአምር ያዩ አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል::

††† ከሐዋርያው በረከት ይክፈለን::

🕊

[ † ሐምሌ ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አግናጥዮስ ሐዋርያዊ ሰማዕት
፪. አበው ቅዱሳን ብዮክና ብንያሚን
፫. ቅድስት ቅፍሮንያ [ ሰማዕት ወጻድቅት ]
፬. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፭. አቡነ ገብረ መድኅን ጻድቅ
፮. አባ ክልዮስ ዘሮሜ

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
፬. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፭. ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

" በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ወደ ጌታ ኢየሱስ ቀርበው "በመንግስተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን?" አሉት:: ሕፃንም ጠርቶ በመካከላቸው አቆመ:: እንዲህም አለ :- "እውነት እላቹሃለሁ:: ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ ወደ መንግስተ ሰማያት ከቶ አትገቡም:: እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ በመንግስተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው::" † [ማቴ. ፲፰፥፩]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🙏2
#ወላዲተ__አምላክ

#ድንግል_ማርያም ወላዲተ አምላክ እነደሆነች ማመን #የኦርቶዶክሳዊነት መሠረት መለኪያ መስፈሪያ ጣምም ነው። ማንም ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን #ድንግል_ማርያም ወላዲተ አምላክ እንደሆነች የማያምን ቢኖር #ከልዑል_እግዚአብሔር እቅፍ የወጣ ነው ሃይማኖትም የለውም"

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ነባቤ_መለኮት

              
#_ሰናይ__ቀን🙏

ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam
8🙏3
🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን።  ✞

[ ✞ እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]

🕊  †  ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ  †   🕊

ቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በተከተሉበት ሰዓት እድሜአቸው በ፫ ደረጃ የተከፈለ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ያሳያል::

¤ እንደ ዮሐንስ ወንጌላዊ ያሉት በ፳ ዎቹ ውስጥ:
¤ ቅዱስ ታዴዎስን የመሰሉት ደግሞ በ፴ ዎቹናና በ፵ ዎቹ ውስጥ የነበሩ ሲሆን
¤ እነ ቅዱስ ዼጥሮስ ደግሞ በ፶ ዎቹ ውስጥ የሚገኙ ነበሩ:: ደቀ መዛሙርቱ ከወጣቶችም: ከጐልማሶችም ከአረጋውያንም የተዋቀሩ ነበሩ ማለት ነው::

ቅዱስ ታዴዎስ በቀደመ ስሙ ልብድዮስ ይባል የነበረ ሲሆን በአንዳንድ መጻሕፍት ውስጥ [በተለይ በምሥራቅ ኦርቶዶክሶች] ስምዖን እና ይሁዳ እየተባለም ተጠርቷል::

ቅዱሱ ጌታችን ተከትሎ : -

¤ ከ፲፪ቱ አንዱ ሆኖ በፈጣሪው ተመርጦ:
¤ 3 ዓመት ከ፫ ወር ከጌታ እግር ተምሮ:
¤ በዕርገቱ ተባርኮ:
¤ በበዓለ ሃምሳም ፸፪ ልሳናትን ተቀብሎ:
¤ ሐዋርያት ዕጣ ሲጣጣሉ የበኩሉን አሕጉረ ስብከት ተካፍሎ ዓለምን ዙሯል::

ቅዱስ ታዴዎስ አንድ ቀን ከሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ጋር ወደ አንዲት ሃገር ይገባሉ:: ታዲያ ለቀናት ያለ ምግብ ወንጌልን ሲሰብኩ ቆይተው ነበርና ደጐቹ ሐዋርያት ራባቸው:: ወደ ከተማዋ ሳይገቡ አንድ ሽማግሌ ሲያርስ አይተው ሰላምታን ሰጡትና "እባክህ እርቦናልና አብላን" አሉት:: እርሱም ምንም ወገኑ ከአሕዛብ ቢሆነ አሳዝነውት በሬዎቹን ሳይፈታ እየሮጠ ሄደ::

ያን ጊዜ ቅዱስ ታዴዎስ ሊቀ ሐዋርያትን "እርሱ እስኪመጣ ለምን አናርስም" አለው:: ፪ቱ ተነስተው ታዴዎስ ሞፈር: ዼጥሮስ ደግሞ ስንዴውን ያዘ:: ቅዱሳኑ እየዘሩ ያረሱት ሰውየው ምግብ ይዞ እስኪመጣ አድጐ: አፍርቶ: እሸት ሆኖ ቆየው::

ገበሬው የተደረገውን ተአምራት ባየ ጊዜ ደነገጠ:: ሊያመልካቸውም ወደደ:: እነርሱ ግን "እኛ የልዑል ባሮች ነን" ብለው በክርስቶስ ማመንን አስተማሩት:: "ልከተላችሁ" ቢላቸው "የለም! ከእሸቱ ይዘህ ወደ ከተማ ግባና ራት አዘጋጅልን:: እኛ እንመጣለን" አሉት::

እርሱ ወደ ቤቱ ሲመለስ አሕዛብ ነገሩን ተረዱ:: ተሠብሥበውም "እነዚህ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እሳትም ሰይፍም አይበግራቸውም" ብለው ወደ ከተማ እንዳይገቡ ከበሩ ላይ ራቁቷን የሆነች ዘማ አቆሙ::

ቅዱስ ታዴዎስ ገና ከርቀት ስላያት ቀና ብሎ ቅዱስ ሚካኤልን "እርዳን" አለው:: ሊቀ መላእክትም ድንገት ወርዶ ዘማዋን ሴት በጸጉሯ በዓየር ላይ ሰቀላት:: በከተማዋ ያሉ አሕዛብም ይህንና ሌሎች ተአምራትን አይተው ሁሉም በጌታችን አምነው ተጠመቁ:: ለሐዋርያቱም ሰገዱላቸው::

አንድ ቀን ግን አንድ ጐረምሳ ባለ ጠጋ ቅዱስ ታዴዎስ "ሀብት ንብረታችሁን መጽውቱ" ሲል ሰምቶት ዘሎ የሐዋርያውን ጉሮሮ አንቆ ከሞት አድርሶት ነበር:: ያን ጊዜ "ጌታየ! ለካ ሀብታም ከሚጸድቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል ያልክ ለዚህ ነው!" ብሏል:: ባለ ጠጋው "እንዴት ይሆናል?" ቢለው መርፌ አሠርቶ ግመሉን ከነ ባለቤቱ በሰው ሁሉ ፊት ፫ ጊዜ አሳልፎታል::

ያም ማለት ጌታችን እንዳለው "በሰው ዘንድ የማይቻለው በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል::" [ማር.፲፥፳፫]  በዚህ ምክንያትም ያ ክፉ ባለ ጸጋ ወደ ልቡናው ተመልሶ ከቅዱስ ታዴዎስ እግር ሥር ወደቀ:: ሐዋርያውም አለው "ሀብትህን ለነዳያን ስጥ:: ይህንንም በትር እንካና እየዞርክ ወንጌለ መንግስትን ስበክ::" ባለ ጸጋውም የተባለውን ሁሉ ፈጽሞ በክብር ዐርፏል::

ቅዱሳኑ ታዴዎስና ዼጥሮስ ግን በሃገሪቱ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸው: ካህናትን ሹመው: ያቺን በዓየር ላይ የሰቀሏትን ዘማም የተባረከች መበለት አድርገው: በሌሎች አሕጉራት ወንጌልን ለማዳረስ ወጥተዋል::

ቅዱስ ታዴዎስም እስከ እርጅናው ድረስ ለወንጌል ሲተጋ ኑሯል:: ጌታችንም በየጊዜው በአካል እየተገለጸ አጽናንቶታል:: ከብዙ የድካምና የመከራ ዘመናት በሁዋላም በዚህች ቀን ዐርፏል::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሱ ሐዋርያ በረከት ይክፈለን::

[ † ሐምሌ ፪ [ 2 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ [ከ፲፪ቱ ሐዋርያት]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
፫. ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፬. ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ [ታላቁ]
፭. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፮. አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

" ጌታ ኢየሱስም ዘወር ብሎ አይቶ ደቀ መዛሙርቱን "ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል!" አላቸው:: ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ:: ጌታ ኢየሱስም ደግሞ መልሶ "ልጆች ሆይ! በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው! ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል" አላቸው:: " [ማር.፲፥፳፫-፳፰]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
1
2025/07/09 01:30:30
Back to Top
HTML Embed Code: