tgoop.com/EnfoA1/863
Create:
Last Update:
Last Update:
"እኔ አንተን ቢያረገኝ"
እኔ አንተን ቢያረገኝ.......
የቁም ሞቴን አሜን ብየ
ክፉነቴን በበደል ስም አጣጥየ
ከሰራኸኝ እጥፉኑ እሰራለሁ
የእኔ ሲታይ ባንተ ስራ እጸድቃለሁ
እኔ አንተን ቢያረገኝ......
ጸጸት ጓዙን አራግፌ
በእንባቸዉ ተንሳፍፌ
እርጥበቱ ሳይሆነኝ ብርድ
በሲቃቸዉ ዉስጤ ሲርድ
አቤት ሳልል ሰዉነቴ
እንዳያሰንፈኝ ከእኔነቴ
እኔ አንተን ቢያረገኝ......
ይቅርታ ፍቺዉ ሳይገባኝ
በአራቱ ሆሄ ሳልቃኝ
የአመታት የእምነት ድር
በአንዲት ቃል በጣጥሼ ሳደናብር
አደርገዋለሁ እዉን ነዉ
ከአንተ ብሼ ነዉ ምገኘዉ
ግን!ግን ይሄንን ማደርገዉ
እኔ አንተን ሲያደርገኝ
አንተ አኔን ብትሆን ነው።
✍️✍️ትእይንት
BY ✍️€yoba ግጥምን በ Voise 🎤እና በ Video 🎞& መሳጭ ታሪክ ❤🥰
Share with your friend now:
tgoop.com/EnfoA1/863