Telegram Web
​​​​​​​​. 🌂 Eyoba

💟
Eyoba..
👇 🌫 ርእሱ🌫👇
🧗‍♀አንቺ የጦሩ መሪ 🧗‍♀
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
♥️ ❤️
አንቺ የጦሩ መሪ አንቺ የነሱ አለቃ
ልቤን እንደወሰድሽ አመልሺም በቃ
ተይ ዉዴ መልሺ ምንም አይጠቅምሽም
የሰው ልብ ተወስዶ ሰላም አይመሽም
ልናገር ፈለኩኝ ልከስሽም ሄጄ
በስንት ድካም ዉስጥ ወጥቼ ወርጄ
ገባዉ ካዳራሹ ፍርድ ከሚሰጥበት
ሰዉ ልቡን ተሰርቆ ሰላም አይቀመጥ
ገና ከመግባቴ ሰው በአግራሞት ይመለከተኛል
የጦሯን መሪ ነዉ እያሉ ጎን ለጎን ያሙኛል
በቃ መሆኔ ነው ዘላለም ታሳሪ
የማትነካዉን አፍቅሬ የ ጦር መሪ።

ማለት የምትፈልጉት ነገር ካለ
@eyabu
@eyabu 👈👈 👈 enbox me
@eyabu
👆👆
ላይ ይፃፉልኝ፡፡

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@EnfoA1
@EnfoA1
@EnfoA1 // ,,
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​​​​​. 🌂 Eyoba

💟
Eyoba..
👇 🌫 🌫👇
🧗‍♀ 🧗‍♀
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
♥️ ❤️
.......------------ በቃ ------------......
መቼም ሟች ነኝና
ስገባ ካፈሩ
ትንሽዬም ብትሆን
ሐውልት ብትስሩ
"የርሱ ነገር ቀረ
በቃ ተከተተ"
ብላችሁ ፃፉልኝ
"ሳይመቸው ኖሮ
ሳይመቸው ሞተ". . .

---------->)(<--------

ማለት የምትፈልጉት ነገር ካለ
@eyabu
@eyabu 👈👈 👈 enbox me
@eyabu
👆👆
ላይ ይፃፉልኝ፡፡

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@EnfoA1
@EnfoA1
@EnfoA1 // ,,
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​​​​​. 🌂 Eyoba

💟
Eyoba..
👇 🌫 ርእሱ🌫👇
🧗‍♀ 🧗‍♀
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
♥️ ❤️
...........ጠይም ፎቶግራፍ...........
#አጭር_ልብወለድ

የተዘቀዘቀ ሕይወት በፎቶ ካልተነሳ ትዝታው ባዶ መሆኑ አይቀርም:: እኔ ከነፍስ በነፍስ ለነፍስ ስለ ነፍስ ወደ ምድር ስለመጣሁ ለፎቶ የሚሆን ሥጋ አልያዝኩም፤ መንፈስ ነኝ መሰለኝ፤ የቆሰለ አንጀቴ ተራራ ሲያጥረው፣ ለፈውስ ሳንካ ሲያደናቅፈው፣ ድቅድቅ ሌሊት፣ ቀን፣ ዐመት እርስ በርስ ይናከሳሉ። ማን በማን ተበላ? ማን አለቀ? ማን በርባሮስ ጠለቀ? ማን? በዘላለማዊ የኅልውና መስኮት አሾለቀ ነው። ጥያቄው ይህ እስቲፈታ ትኩስ አረንጓዴ ቅጠሎች ልባችን ቅርንጫፍ ላይ፣ በቅንፍ ዐይናችን ቅርንጫፍ ላይ ቅጠሎቹ ይለበለባሉ፤ ቅንፉ ይዘጋል። በሰሜንና በምስራቅ ማዕዘን ቅስሟ ቆሟል። ቅስሟም በንፋስ ሲበተን...

“አንገት ደፊ መከራ አቃፊ” ተሰበረ ቅስሙ ወዘናው ተንጠባጠበ፣ ይወዳታል፣ ፍቅር ልቡ ላይ ቂጥ አለበት፤ የምወድሽ ከሕልም ወዲያ ከተፈጠርንበት ወዲያ ሄጄ እዛ ባለው በልብሽ መቅደስ ውስጥ ዝማሬ አሰምቼ መለስ ቀለስ አልሁ ይላል፤ በልቡ አታውቅም! ጠይም ምስሏ አለቅ አለው፤ አርምሞ ጎደለበት፤ በስስት ላይ ፍቅር ይሁን ውሕደት? አታውቅም! በቁሙ ታመመ፤ ልቡ እንደ ጉልበቱ አላውቅህም ቻው! አለው። ይህ አፍታ ለእርሱ ውስብስብ ነበር፤ ነገው ከዝምታ ይንቀረፈፍበታል፣ በእንጥሏ ጫፍ ስትስመው፤ ሲሰማው፣ የድመት ጅራት ሲዳስሰው ይነቃል፣ ይቃትታል፤ ከልቡ ቅዠቱ ይሰፋል፣ ራቁት ቅዠቱን በቀጭን ልብስ የሚሸፍንለት ያጣል። ጥልቅ ባህር መሰረቱ አይገኝም የሚንጠለጠል እሳት ምናምን እያለ ያንጎላጃል። ጨለማው ነገን ለማስታወክ የሰሜንን ጉሮሮ በብርሃን ጣት ይጓጉጣል፤ ጩኸት የዝምታን ጡት ይለዘልዛል።

ትንሽ ቤት
ትንሽ በር (ሰው ባዶ) ዝም
ተብሎ የተተወ
...በልቦናው ቅርንጫፎች ላይ ሲረጭ ተሰማው፣ አሰበ፤ በልቡ ተሰቃይ ያለው ገላ እንዲያው ደርሶ ይሰቃያል። ሃጫ ነፍሱ ላይ ጥቁር ቁስል ይንጎራደዳል። ዝናብ ቆሞ ከሩቅ ሠማይ አንድ የዜማ ብርሃን ጭል-ጭል ጭልጭልታን ሲያይ፤
“ቀኑንም ትደግመው” የሚል ድምጽ ጆሮውን ጠቅ አደረገው፡፡
“ዝም፤”
“አንተ? አንተን አይደለምዴ ?”
ልዝዝ ያለ ሕልም በደመናና በብርሃን ሲለቃለቅ፣ በንፋስ አውታር ሽቅብ ተሰቅዬ፣ ከተሰነቀርኩበት ሽቅበት ቁልቁል ስመዘዝ፣ ወንድ አዝማሪ መሰንቆውን እየመታ፣ ሴቲቷ በአንገቷ እስክስታ እየመታች ትወርዳለች። እንባዬ በአንገቴ ትንኳለላለች፤ ጸጥታ ጸንቷል። ሽፍንፍን ለጥ፤ ማንንም አልሰማ፡፡

ከሁሉም በፊት
“እንዲህ ነው ሕይወት”
“እንዴት?”
ከእናትህ ማሕጸን በቅጽበታት ሂደትጂ የጀመርከው መንገድ፣ ከሕይወት አልፎ የሞት ድልድይን ተሻግሮ እስከ ማያውቀው ይጓዛል።
“ምን ? ምን ይጓዛል?”
“ሞትም ሕይወትም! የማይቆም ጉዞ ከ-እስከ እግርን በመንገድ እያለፉ፣ መሬት ለቆ መንፏቀቅ። እንዲህ ነው።”
“ምኑ?”
“ፍልስፍናው ሀሁ”
“ምነው ባልተኛሁ፤ ምነው ሕልምን በፈራሁ”
አሁን ወይ ....

እንደ ሀምሌ ውኃ አድፌያለሁ፣ አንገቴ ተሳክሯል፤ የጠገገው አንጀቴ ቆስሏል፤ ሀዘን ያንጠራራኛል ሰይጣን ይጠራኛል፡፡ ምንም እንኳ ቢጎነቸር ታሪኩ እወዳት ነበረ፤ ይህ በደም የተጻፈ ቁንጽል የገጽ ግንጣይ ነው። ላባ ጠብ ሳይልብኝ ዐይኗ ሳይዳስሰኝ፣ ክንዶቿ ላይ ሳልቀልጥ፤ ጭኖቿ ሳይሞቀኝ፣ ከንፈሯን ሳልቀነጥበው፣ ሲቃዋን ሳልደቃው፣ ጭቃ ሜዳዋን ሳይረግጠው፣ ወይንነቷ ይቅር ግድ የለም፤ ቅራሬነቷን ፉት ሳልለው በመንፈስ አውርተን ሞተች፤ ሙትትትት ሙትትትት!
እሷ ቀስተ ደመና ሥር ሆና የሞት ምጥ ቅሪቷ እኔ ነበርኩ፤ ስታጣጥር የእኔን ፎቶ አሰቀለች፤ ጠይም ፊቴን ቅዝዝዝ ብላ እያየች፣ እያየች በሞት አፍ ተላመጠች፡፡
ማን ነኝ? ማን ነበርኩ? ምንድነኝ? ወዴት ነኝ? ወዴት ነው የምሄደው?
ምናልባት ጥልቅ እንቅልፍ ግማሽ ሞት ይሆናል።

እርጥብ ላብ ግንባሬ ላይ ተንሳፏል። የማልወጣው፣ የማልወርደው ሸለቆ ወደ እኔ ይንደረደራል። ዘላለም የምጻትን ሥጋ መንጥቃ ስትወራጭ፤ ወገግ ብሎ ይታየኛል።
ሰው ባዶው ቤት ውስጥ ንፋስ ተጠቅጥቆ፤ ሽውሽውታን እየሰማ የክብ ይደንሳል። የቫንጎን “Stary Night” በግራ ዐይኔ ያየሁ ይወስል፣ ሥጋዬ ላላ፣ ነፍሴ ተመሰቃቅላ፣ ጭውውው ብሎብኝ ቆምኩ፡፡ ይህ ቤት፤
ሀ) የለዘበው ምሰሶ መረሬው ንቃቃት ውጦ አንቅዞታል።
ለ). ተወለጋግዷል።
ሐ) ትዝታ እንዳይሆን ሌጣ ቀለሙ ለቋል።
መ) መ እና ሀ
ሰ) ሰ ነው መልሱ!
“ከማንጯለቅ መስኮት መክፈት” ቀስ ብዬ ገባሁ፤ ፈዘዝ ያሉ ቀያይ መብራቶች ዐይኖቼ ላይ ቃተቱ፤ በቀጭን ገመድ የተሰቀሉ ነፍስ ያላቸው መልኮች ተንጠልጥለዋል። አሃ ፎቶ ማጠቢያ ቤት ነው። ግማሾቹ ቆስለዋል፣ ግማሾቹ ተጎሳቁለዋል። (መልካቸውን አጥተዋል።) ግን ታጥበዋል። ሥጋ ይዘዋል። ነፍስ እንጃ እንጂ!

አንዴ ይህንን የመሳሰሉና ሌሎችም ፊልሞችን ዐይቻለሁ፤ እንደ Till death ዐይነት ወይን ጠጡ፤ በስካር ናውዘው ሲነሱ፣ ራስ ምታቷ ላይ ደሞ የሌላው ድንጋጤ ተደፋባት፤ እሱ ራሱን ይገድላል፤ በሞቱና በሞቱ አምሳያ ጥግ ያንን ልዩነት ነበረው። የሚል ጥያቄ ይነሳል፤ እርግጥ ነፍሷ ባፏ ሊወጣ ምንም አልቀረው፤ ቀለም ዐልቦ፣ የጥፍር ቀለም (ጥፍረ መጥምጥ የራቀው) የሰማይ ማማ ሲጫናት አድባር ሲርቃት ግን ሁለቱም ጭጋግ ይፈራሉ፣ ጉሙን ይሸሻሉ፤ ጅሟሯቸውን ግን ጭጋግ ነው፣ ማብቂያቸውም ጭጋግ በጭጋግ ጀምሮ በጭጋግ ያበቃል።

“*ሸለቆውን ተሻግሮ ያለው እጅጉን የተለየ ነው። ክብደትም ሚዛንም የለም፤ ከአፍቃሪሽ ጋር ትሆኛለሽ የኔ ፍቅር! በሕዋው ውስጥ የናኘሽ የፍቅር ጠረን፣ ለኔ የተዘረጋቹ ክንፎች እስኪ ንገሪኝ በልቤ ጸጥታ አንሾካሽኪሊኝ፤ አንቺም እንደ እኔ ትፈልጊኛለሽ፤ ከእኔስ መለያየት ሕመም ነው። ለአንቺ እኔስ እራሴ በሕዋው የተስፋፋው መአዛና ክንፎች እሆን! የወንድሙ ቢጤ በሌላ አለም፣ ከሕይወት ወደ ሞት ጠርቶሽ ግን ተዐምር የሚሉት እህት፣ ጓደኞችሽ አሉ እንዴ፤ እጥፍ ጭካኔ በሃሴት ውስጥ የሚፈፀም” እስኪ ንገሪኝ?” ይህ ዘላለም የሚከተላት ፍቅራዊ ቃላት ተውሶ የጻፈላት፣ በወይን ያወራረደችው ደብዳቤ ነው።
ይህንን በሰመመን እያሰብኩ፣ ዐፎች ሲነቃነቁ ለጆሮ እረፍት የሚያስናፍቅ ቀጭን የማያቋርጥ ድምጽ የሚያወጣ ባዶነት ሲሰማኝ።
ነጭ ሱሪ ልልበስ...? በጎዳናው ላይ እንደ ቀበጥ ሕጻን ዝናብ... ያረስርሰኝ? ከአጠገቧ ቆሜ ጠያይም ፎቶዎችን ልነሳ እንጃ!
አሁን ንገሪኝ፣ ይኖር ይሆን የክፋት መንትያ!

#ተፈፀመ

ማለት የምትፈልጉት ነገር ካለ
@eyabu
@eyabu 👈👈 👈 enbox me
@eyabu
👆👆
ላይ ይፃፉልኝ፡፡

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@EnfoA1
@EnfoA1
@EnfoA1 // ,,
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​​​​​. 🌂 Eyoba

💟
Eyoba..
👇 🌫 ርእሱ🌫👇
🧗‍♀ 🧗‍♀
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
♥️ ❤️

#የፍቅር_ምትሃት

#አጭር_ልብወለድ

ያው እድለኛም አይደለሁ...
ታዋራኛለች!
ደፍሬ ስልኳን የጠየኩበት ቀን ትዝ ይለኛል።
ልዩ መሆኗ ግልፅ ነው... ድፍረቴ ቀርቶ!
“ይሄን ነገሬን ባትወደውስ?” ብዬ መስጋቴ ሌላ ታሪክ ነው!
ሰው እንዴት “ድምፄን ባትወደውስ?” ብሎ ይሳቀቃል?

እንደው ስንት አይነት ድምፅ ቢኖር ነው?
ብቻ እንዳልኩት እድለኛ ነገር ነኝ!
የመጀመርያ ቀን ደውዬላት፣ ቆንጆ ድምፅ እየሰማሁ ስቁነጠነጥ...
“ወይኔ መስዬ... ድምፅህ እንደዚህ የምስኪን ነው? እዛ ‘ቴሌግራም’ ላይ ስትፅፍ እኮ የሆነ አስፈሪ ኮስታራ ድምፅ ያለህ ነው የምትመስለው! “ አለቺኝ...

ኮስታራ ድምፅ እንዴት ያለው ነው?
Is ምስኪን ድምፅ a compliment?
ብቻ ከእነ ውዝግቤ የተጨመረልኝም የድምጿን በረከት እየባረክሁ ጥቂት ጊዜ አለፈ...
“አግኚኝ” ለማለት እስክደፍር...
በዚህ ጥቂት ጊዜ በስሟ እልፍ ግጥም ፃፍኩ...
ከእልፍ ቆነጃጂት ተኳረፍኩ...
እልፍ የፍቅር ዘፈን ተረጎምኩ...
ፍቅር፤ ፀሀፊ የሚያደርገው ነገር ሳይኖር አይቀርም!

‘ከፖስቶቼ’ ስር አስቀምጣ በምታልፈው ቀይ የልብ ቅርፅ፣ የልብ ልብ ተሰምቶኝ፣ እንድታገኘኝ መወትወት የጀመርኩበት ደፋር ሰሞን...
“የምትወደኝ መስሎኝ እኮ ነው...” ብላ አስደነገጠችኝ!
ለምን አልወዳትም?
አጭር እንደሆነች የማላውቅ መስሏት ይሆን?
ስንት ሰው ጠይቄ ስታወራ nervous እንደሆነችና እጆቿ እንደማያርፉ ያልሰማሁ መስሏት ይሆን?

“እንዴ... እወድሻለሁ እንጂ! ለምንድነው እማልወድሽ?” አልኳት ኮስተር ብዬ...
“ባክህ የመሰልኩህን ሴት ነው የምትወዳት፤ እኔን አይደለም! አታውቀኝም! ብታውቀኝ Lewis Capaldiን... Joel Corryን... አትጋብዘኝም... እየተረጎምክ በስሜ አትለጥፍልኝም ነበር! አብነት አጎናፍር ምን አለህ...?” አለቺኝ እንደማምረር እያደረጋት...

ጀንጃኝ ጎኔ አፍሮ ሲሽኮረመም egoዬ ምላሴን ተረክቦ... “እንዴ... እንዴ... ይኸው ልደታን! እሁድ እንደውም... Palmy የሚባል ቤት አብነትን ካላየን... ብዬ ልነዘንዝሽ ስል...” አላት!
“ውይ ደስ ይለኛል ጌታን!” አለቺኝ፤ ደስ በሚል ድምፅ!
ያው አርብና ቅዳሜ ሾፌሬን ይዤ፣ እሁድ የምለብሰውን ልብስ ፍለጋ ባከንኩ...
እድለኛም አይደለሁ... እሁድ ደረሰና አጭሯን ሱሴን አትላስ አገኘኋት...

እና ምን ለማለት ነው...
አብነት አጎናፍር ጥሩ ሰው አይደለም!
መጀመርያ ወደ መድረኩ ሲወጣ he is not intimidating at all... ጅንስ ሱሪው ውስጥ ሸሚዙን የሰገሰገ... የሚያብለጨልጭ ጫማ የለበሰ ጎልማሳ ምኑ intimidate ያደርጋል?
ደግሞ ከፈረንሳይኛ እስከ እንግሊዝኛ የፍቅር ዘፈኖች ተርጉሞና አስተርጉሞ ለጀነጀነ ሰው...
አብነትዬ መዝፈን ጀመረ...

“አንቺን ብሎ... ልቤ አልረጋ አለ...
ባሳብ ካንቺ ጋር... ሄዶ እየዋለ...
አስቻለሽ ወይ... ካለኔ ኑሮ...
ከበደኝ እኔን... እንጃ ዘንድሮ...

ለኔ ካለሽ... መቼም አይቀርም...
ውደጂኝ ብዬ... ሙጢኝ አልልም...
ለኔ ካለሽ... መቼም አይቀርም...
ውደጂኝ ብዬ... ሙጢኝ አልልም!”

እሷ በሳቀ ፊት ጮክ ብላ አብራው ትዘፍናለች...
ቁመቷን ናቅ አድርገው እንዳሻቸው ደረቷ ላይ የነገሱ ጡቶቿን 6-8 ምናምን እየጠበቀች nude ጥፍር ቀለም በቀባቻቸው ቆንጆ ትንንሽ ጣቶቿ ነካ ታደርጋቸዋለች...
አብነት ግን ምን ኾኖ ነው?
“ዞራ ዞራ የኔው ናት ዞራ ዞራ...” ምናምን በሚዘፈንበት ሀገር፣ እንዲህ መፈላሰፍ ምን የሚሉት ነገር ነው?

“... አለሁ... ይግባኝ አልጠየኩም...
ክፉም ነሽ አላልኩም...
ደግም ነሽ ሳልልም...
ብቻ ግን አለሁ...
እራሴን ባልጥልም...
አለሁ እንዳለሁ...”
ቱ...
እኔን ብሎ ገጣሚ!
እኔን ብሎ ተርጓሚ...
በጌታ ስም...
እሸማቀቃለሁ...
“... ዘንድሮስ ቸገረኝ... እምባዬ አልደርቅ አለኝ...
ሆዴም አልቆርጥ አለኝ... ድካሜ አሳዘነኝ...
ፍቅር አልቆይም አለኝ...
እየወሰወሰኝ... ከማጥ ወስጥ ዘፈቀኝ...”

እሷ እርክት እያለች ከአፍ ከአፉ ትቀበላለች...
እኔ እስከዛሬ “እንደዚህ ነው የምወድሽ...” ባልኩት እየተሳቀቅሁ አፈጣለሁ...
አብነት ሆዬ ይቀጥላል...
“...በርግጥ አታምኚም... አንቺን ማሰቤን...
ርቀሺኝ ስትሄጅ... ገፍተሺኝ እኔን...
አልጠላሽም... ስላልወደድሺኝ...
ካሳብ እንድድን... ብቻ ጠይቂኝ...”
እንዳልኩትም እድለኛ ነኝ...
ቆንጆ ብቻ ሳትሆን ልክም የሆነች ምትሀት ነው የወደድኩት!
ልክማ ነች...
የምወዳትን ያክል አልወደድኳትም...
እኔ ይሙት! 😂😂😂

____ ____
ማለት የምትፈልጉት ነገር ካለ
@eyabu
@eyabu 👈👈 👈 enbox me
@eyabu
👆👆
ላይ ይፃፉልኝ፡፡

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@EnfoA1
@EnfoA1
@EnfoA1 // ,,
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
ደብቄሽ ነው እንጂ ልብሽ ከሚሰበር
አንጀሊና ጆሊ ደውላልኝ ነበር 😜😂
ኧረ ወገን የመጨረሻው ዘመን ደርሷል ሴት ልጅ ካርድ ላከችልኝ🤔🤔
ባሌን ፈትኚልኝ ብላ ጓደኛዋን ልካት ልጁ ተመችቷት፣ ከዛ ቀማቻት...
#ፅናቱን_ይስጥሽ_ማማዬ 😢😢
ያሳለፍኩት ግዜ በጣም ይገርመኛል
ባስታወስኩሽ ቁጥር ወገቤን ያመኛል
#አላለም
ጠዋት ከእንቅልፍ ስትነሱ ስልክ አልጋ ላይ ከመዳሰስ ወደ ሚስት መዳሰስ ያሻግራቹ ! አሜን በሉ
ቀጥረሃት ከመጣች ምሳ ቤቷ በልታ
አግባት እንጂ ቶሎ ያውም በፈገግታ
😂😭😂😭😂😭😂
እወዳት ነበር እኮ ግን ምግብ አዝዘን እየበላን ከቦርሳዋ ሸገር ዳቦ ስታወጣ ዘጋችኝ ዘጋችኝ😡😡
ቴሌግራም ፕሮፋይልሽ ላይ ያለውን 80 ፎቶ አጥፊ pls ቤትሽ ስመጣ ምን ላይ ነው ?😂😭😭😭😂
​​​​​​​​. 🌂 Eyoba

💟
Eyoba..
👇 🌫 ርእሱ🌫👇
🧗‍♀ 🧗‍♀
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
♥️ ❤️
#ሚወቀስ_ትዝታ
.
.
ደንዳና ነው ልብሽ፤
ጀጋኝ ነሽ የኔ አለም!
የወንዙ መደፍረስ፤
መገምሸር መደርመስ፣
ሙላት መች አግዶሽ ዘልቀሽ ተሻግረሻል፣
"የኔ ነህ" 'ምትዪው፤
"የኔ ነሽ " የሚልሽ ሌላ አዳም ለምደሻል።
.
.
መልመዱንስ ልመጅ፤
ይቅናሽ አዲስ ጎጆ ፤
ይስመርለት ግብሩ ፍቅር ይሁን ዋልታው፣
የታመንሺው አምላክ፤
ምርቃት ያርግልሽ ጩኸትና ዋይታው።
.
.
ግና ለአንድ አፍታ ትዝ ባልኩሽ ሰሞን፣
ቀልቤን እንድገዛው አዘቦት እንዲሆን።
ፆሜን እንኳን ባልሽር፤
እንደው ላመል ያህል ትንሽ እንድል ዘና፣
ንግስናውን ካጣው፤
ገርጥቶ ከነጣው ከዘመመው ጎጆ ከቤቴ ነይና፣
አንሶላውን ውሰጅ፤
አልጋዬንም ውሰጅ፤
ትራሱንም ውሰጅ፤
"እፎይ" ልበል እስቲ ትላንቴን ልርሳበት፣
ትርፉ ማባከን ነው፤
አንቺን የሚያስታውስ መዓዛሽ ያለበት።


ማለት የምትፈልጉት ነገር ካለ
@eyabu
@eyabu 👈👈 👈 enbox me
@eyabu
👆👆
ላይ ይፃፉልኝ፡፡

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@EnfoA1
@EnfoA1
@EnfoA1 // ,,
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​​​​​. 🌂 Eyoba

💟
Eyoba..
👇 🌫 ርእሱ🌫👇
🧗‍♀ 🧗‍♀
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
♥️ ❤️
ፊደል :ለከንፈርሽ

ምስል :ላይ:ያየሁት:ረቂቅ:ቅንድብሽ
መች:ሆነብኝና:ድብቅ:እንቆቅልሽ
:
:
ቃላትን :ከርክሜ: እጅግ :ተጠብቤ
አወድሼዋለው :በስንኝ:አስውቤ::
ማመስጠር:ሳይከብደኝ:በቅኔ:ውዳሴ
አፍስሼለታለው:አራት:ቤት:ሥላሴ!
። ።።።።። ።።።።።።።።።።።።
ግና:በሃቂቃ :ከልቤ:ስነግርሽ !!!
ፈልጌ:አጥቻለው: ፊደል:ለከንፈርሽ !
:://///:::::

በጥርሶችሽ:መሐል:አድርገሽው:ሰብሰብ
ባማረ:ፈገግታ:በተዋበ:ገደብ ...
መግለፅ:አቅቶኛል:ከቋንቋ :ማኅደር
በጥርሶችሽ:ደምቆ:ያየሁትን:ከንፈር...




ሜክሲኮ :ሻይ ቡና: ብቻዬን:ቁጭ:ብዬ
ጣፋጩን:ቆይታ:ትዝታ:ታዝዬ

የብዕር:ቀለሜን:
ጨርሼ:እንደዋዛ

ስንኝ:ባሰናዳም
:ላንቺ:ውበት:ለዛ.......
....
ከፀጉርሽ:ጀምሮ:እስከ:እግርሽ:ጣቱ
ከስልምልም:አይንሽ:እይታሽ:ምትሐቱ🔆
:
:
ለሁሉም:አካልሽ:አጃኢብ:ቅንድብሽ
በሚመጥን:ሐረግ:ውዴ:ገጥሜልሽ!


ድክመቴን:ሳልፈራ:ከልቤ:ስነግርሽ
ፈልጌ:አጥቻለው:ፊደል:ለከንፈርሽ!?!

ማለት የምትፈልጉት ነገር ካለ
@eyabu
@eyabu 👈👈 👈 enbox me
@eyabu
👆👆
ላይ ይፃፉልኝ፡፡

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@EnfoA1
@EnfoA1
@EnfoA1 // ,,
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
"ቤት ማንም የለም" ብላኝ ሂጄ እንደደረስኩ ስደዉልላት..

"እንድጠብቅልን እኮ ነው" አለቺኝ ”
😂😭😂😭😭
"ለምንድንነው ስልኳን VLC ብለህ Save ያደረከው " ሲሉት

#ሁሉንም_ታጫውታለች 🤣😝
​​​​​​​​. 🌂 Eyoba

💟
Eyoba..
👇 🌫 ርእሱ🌫👇
🧗‍♀ እኔነቴን ልስጥክ🤰
ክፍል 2
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
♥️ ❤️
የመጀመሪያ አመት ተማሪ እንደመሆናችን እርስ በ እርስ ለመተዋወቅ ብዙ ጊዜ እንደሚፈጀብን አይምሮዬ ቀድሞ ነገረኝ,ነገር ግን ከመኪናዉ ስወርድ የያዝኩት ሻንጣ በጣም ከባድ ስለነበረ የሚያግዘኝ ሰዉ በጣም በምፈልግበት ሰአት ዳኒ የኔን እርዳታ ፈላጓት ገና ሳልጠይቀዉ ፈላጎቴን ተርድቶ ወደ እኔ መጣ, ሀይ ባልሳሳት የሚያግዝሽ ሰዉ ያስፈልግሻል አለኝ በሚያምር ድምጽ, እኔም ሳላንገራግር አዎ አልኩት, ዳኒ የኔንስሜት ሳልናገር እርዳታ መፈለጌን አዉቆ ወደ እኔ በመምጣቱ ስለሱ እንዳስብ አረገኝ, ከዛም ሻንጣዬን እየጎተተልኝ ወደ ተመደብኩበት ዶርም አብረን መሄድ ጀመርን, እኔ ለማዉራት በጣም ፈርቼዉ ነበር እሱ ግን ጥያቄዎችን ይጠይቀኝ ጀመረ, የመጀመሪያው ጥያቄ ከየት አገር ነው የመጣሽው የሚል ነበረ እኔም ለመመለስ ሰከንድ እንካን ሳይፈጅብኝ ከ ሀዋሳ ነው የመጣሁት በማለት መለስኩለት, ዋው የሀዋሳ ልጆች እኮ በጣም አሪፍ ናቸው ይባላል እንቺም ከእነሱ ዉስጥ አንዳ እንደሆንሽ ተስፋ አለኝ እያለ በሚያምር ፈገግታው ልቤን እያንበረከካት የተመደብኩበት ዶርም ደርስን,እኔም አንተስ ከየት አገር ነው ተመድበክ የመጣከዉ በማለት ጠየኩት የሰጠኝ መልስ ግን አስደሰተኝ, እንዲ ነበር ያለኝ እኔ እዚዉ የ አዳማ ልጅ ነኝ እና እዚዉ ተመድቤ የሚል መልስ ነበር, የ አዳማ ልጅ መሆኑ ያስደሰተኝ ምክንያት አዳማን ሙሉ በ ሙሉ እንደሚያስጎበኘኝ እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው። የርሳዉት ነገር ግን እኮ አልተዋወቅንም ስምሽን ማን ልበል በማለት ጠየቀኝ እኔም ሳሮን በማለት መለስኩለት እኔም በተራዬ ያንተስ በማለት ጠየኩት ዳኒ በማለት መልሶልኝ ስልኬን ተቀብሎኝ ሌላ ጊዜ እንገኛለን በማለት ቸዉ ብሎኝ ሄደ።

ክፍል 3 ይቀጥላል 😘❤️❤️❤️


ማለት የምትፈልጉት ነገር ካለ
@eyabu
@eyabu 👈👈 👈 enbox me
@eyabu
👆👆
ላይ ይፃፉልኝ፡፡

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@EnfoA1
@EnfoA1
@EnfoA1 // ,,
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
​​​​​​​​. 🌂 Eyoba

💟
Eyoba..

🧗‍♀ 🧗‍♀

♥️ ❤️
መተሽብኝ ነበር :
ለሊት ላይ በህልሜ፣
አቤት ብዬም ነበር :
ስምሽ መስሎኝ ስሜ፣
ግና ሳልጨርሰው :
ፍቅርን አጣጥሜ፣
ፍጥን እንደ ንፋስ :
እጥር እንደ #ጳጉሜ
..............አልሽብኝ አለሜ ።
ማለት የምትፈልጉት ነገር ካለ
@eyabu
@eyabu 👈👈 👈 enbox me
@eyabu
👆👆
ላይ ይፃፉልኝ፡፡

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@EnfoA1
@EnfoA1
@EnfoA1 // ,,
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
ወንድሜ ያገቡ ሴቶችን ብቻ እየመረጥክ ጀንጅን! #Single ሴት ስጀነጅን ፋክክርህ ከ 20 በላይ ወንዶች ጋ ነው #ያገባች ሴት ስጀነጅን ግን አንድ ተፎካካሪ ብቻ ነው ሚኖርብህ
:
#ብሎ_መከረኝ 🤣🤣
​​​​​​​​. 🌂 Eyoba

💟
Eyoba..
👇 🌫 ርእሱ🌫👇
🧗‍♀ እኔነቴን ልስጥክ 🧗‍♀
,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,

ክፍል 3

ሻንጣዬን ይዤ ወደ ተመደብኩበት ዶርም ስገባ 5 ስቱም ተማራዎች ገብተዋል ማለትም 6 ተኛዋ እኔ ነኝ ግን ከሁሉም ውሰጥ ሰላም የምትባለዋ ሚስጥርኛ ጉአደኛዬ እንደምትሆን እርግጠኛ ሆንኩ እርግጠኛ እንድሆን ያርገኝ ምክንያት ዶርም ውስጥ ከመግባቴ ሀይ ባልሳሳት እዚ ከ እኛ ጋር ተመድበሽ ነው በማለት ጠየቀችኝ አዎ የሚለዉ መልስ ስመልስላት ሻንጣዬን አግዛኝ ሎከር ውስጥ አስገብተነዉ እርስ በእርስ ብዙ ጥያቄዎችን ተጠያይቀን ሰላም የ ሀርር ልጅ ናት በጣም ግልጽ ናት የሳ ግልጽነት እና የኔ ቀበጥነት በጣም እንደሚያቀራርበን እርግጠኛ ነበርኩ ,ከ ሰላም ጋር እየተጨዋወትን እያለ በመሀል ስልኬ ጠራ የማላውቀው ስልክ ነበር አና ለማንሳት ብዙም አልዘገየዉም ሄሎ በማለት ስልኩን አንስቼ ማዉራት ጀመርኩ,ባነሳሁት የስልክ ጥሪ ዉስጥ ደስ የሚል ድምፅ ነበር የሰማሁት,ይሄን ያህል ናፈቄሽ ነበር በማለት ጠየቀኝ ማለት አልገባኝም በማለት መለስኩለት,ማለትማ ስልኩ ድጋሜ እንኳን እንዲጠራ እድሉን አልሰጠሽዉም በማለት መለሰልኝ,ኦ sorry ማንሳት አልነበርብኝም ማለት ነው ብዬ ልዘጋው ስል,አርቆይ እንደዚህ እማ ስሜታዊ ትሆኛለሽ ብዬ አልጠበኩም ነበር ዳኒ ነኝ ሲለኝ እራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ መርበትበት ጀመርኩ,ኦ ዳኒ ስልክህን አልጠበኩም ነበር በድንጋጤ,እሱም ማለት ስልክሽን የተቀበልኩሽ ልደዉልልሽ አይደል እንዴ ሲለኝ መርበትበቴ ገብቶት ይሆን እንዴ ብዬ በማሰብ ደንግጬ ኦ ዳኒ ይቅርታ በኋላ ልደዉልልክ አሁን ልብሶቼን በማስተካከል ቢዚ ሆኛለሁ አልኩት,እኔ ግን ካስተካከልኩኝ እኮ ቆይቻለዉ ምክንያቱ አልገባኝም ግን ፈርቼዋለዉ።እሱም አልተቃወመኝም ነበር እና እሺ ስልክሽን እጠብቃለሁ በማለት ስልኩን ዘጋው,ሰላም ግን የስሜቴ መቀያየር መርበትበቴ ገብታት ሳሮንዬ ከዚ ስልክ ጥሪ በሁላ ልክ አይደለሽም ማን ነበር የደወለው ብላ ጠየቀቺኝ እኔም ሰላም ልክ እንደ እህት ጉአደኛዬ እንድትሆን ስለምፈልግ ልደብቃት አልፈለኩም, ዳኒ ይባላል ዛሬ ነው የተዋወቅነው እና ለምን እንደሆነ እላቅም ሲደዉልልኝ በጣም ተደናገጥኩ እና በዉሀላ እደውላለሁ ብዬ ዘጋሁበት አልኩእት, ማለት ተማሪ ነው በማለት ጠየቀቺኝ? አዎ እንደኛው የመጀመሪያ አመት ተመሪ ነው ግን ለየት የሚያርገዉ ነገር የዚዉ የ አዳማ ነው ብዬ መለስኩላት, ሰላም በጣም ፈታ ያለች የሀረር ልጅ ስለሆነች እና እራፊ ነዋ እንዲያውም አዳማ በማታ ምን እንደምትመስል ያስጎበኘናል ደዉይለት እና ለማታ ቅጠሪዉ አለቺኝ, እኔ ግን እጆቼ ቁጥሮቹን ለመንካት እንኩአን ፈራዉ ይሄ ነገር ፍቅር ነው እንዴ በማለት እራሴን ጠየኩት ገና በመጀመሪያ ቀን እንደዚህ አይነት ስሜት ከተሰማኝ ቀናቶች በሄዱ ቁጥር ምን ልሆን ነው በማለት ከራሴ ጋር ሙግት ያዝኩ ሆኖም ሰላምን ላለማስቀየም ስል ደወልኩለት ስልኩም ጠራ,

ይቀጥላል ........

ማለት የምትፈልጉት ነገር ካለ
@eyabu
@eyabu 👈👈 👈 enbox me
@eyabu
👆👆
ላይ ይፃፉልኝ፡፡

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@EnfoA1
@EnfoA1
@EnfoA1 // ,,
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
❤️ህልም አይቼ ማታ🥰
💖ከማዶ መስኩ ላይ❤️
ቁጭ ብለን ዋርካው ስር 👸
💝ፍቅርን ስንወያይ 😉
🌼የሚወድሽ ልቤ ❤️
💐ገና አይቶሽ ሳይበቃው🙈
🥀በጆችሽ ደባብሰሽ ❤️
💏ልታቅፊኝ ስትይ ነቃሁ😔
🤷‍♂ምን አለ🤦‍♂
🙆‍♂ባልነቃስ ከንቅልፌ🥱
🤦‍♂እንዳልም በክንድሽ ታቅፌ☺️
💔ብተኛ ተመልሼ እንዳልም🙌
😞ለካ አንዴ ነው ህልም አይደገምም!
2025/01/10 08:39:47
Back to Top
HTML Embed Code: