EOTCLIBILERY Telegram 16007
የእመቤታችን ድንግልና በተመለከተ ለጠየቀችን

ለሁለቱም መልስ በአጭሩ በአጭሩ ማስቀመጥ ይቻላል። ይህን ቪዲዮ ስመለከተው የተናገርሁት ጥቅስ ስሐተት መሆኑ ተረዳሁና ጥቅሱን ብቻ ከማስተካክል ለምን ሀሳቡንስ ትንሽ ጨመር አላደርግበትም ብዬ ነው ይህችን ጽሑፍ የሞነጫጨርኩት።

ጥቂት የማይባሉ በተለይ በእኛ ሀገር ያሉ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና ላለመቀበል የሚያነሷቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች ውስጥ አንደኛው ይህች ልጅ የጠየቀችው ነው። በዚሁ አጋጣሚ በጽሑፍም ትንሽ እናብራራው። ሌሎች ምክንያቶቻቸውን ደግሞ አስፈላጊ ከሆነ ሌላ ጊዜ ማየት ይቻላል።

ዮሴፍ እጮኛዋ ለምን ተባለ?
ጠባቂዋ እንዲሆን።

የሚጠብቃትም ከሦስት መሠረታዊ ጉዳዮች ነው። የመጀመሪያው እንዲሁ በድንግልና ጸንሳ ብተገኝ ኖሮ በድንግልና መጽነሷን የሚያረጋግጡበት መንገድ ስለማይኖራቸው በሕጋቸው በምንዝር የተያዘች ሴት ላይ የሚፈረደውን ፍርድ ፈርደው በድንጋይ ወግረው እንዳይገድሏት ነው። ታዲያ ይህንን ለማድረግ እጮኛዋ ሳይሆን መጠበቅ አይችልም ወይ የሚል ቢኖር ያኛውማ የበለጠ ያስቀጠዋል። እንዲያውም እርሱንም ጭምር አመነዘረ ብለው አብረው ተቀጭ ያደርጉት ወይም ይወግሩት ነበር እንጂ እርሷን ለመጠበቅ ወይም ከሚያመጡት ጉዳት ለማዳን አያስችለውም ነበር። እንዲህ ያለ ነገር እንዴት ሊሆን ይችላል ካልን ይህን የሚያውቅ ጌታ አስቀድሞ እንዲህ ያለ ሕግ በኦሪቱ ሰጥቶ ነበር።

“ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል፥ ወይም ራሱን በመሐላ ቢያስር፥ ቃሉን አይስበር፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ። ሴትም ደግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል፥ እርስዋም በአባትዋ ቤት ሳለች በብላቴንነትዋ ጊዜ ራስዋን በመሐላ ብታስር፥ አባትዋም ራስዋን ያሰረችበትን መሐላ ስእለትዋንም ቢሰማ፥ አባትዋም ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ሁሉ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል። አባትዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለትዋ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላዋ አይጸኑም፤ አባትዋ ከልክሎአታልና እግዚአብሔር ይቅር ይላታል። በተሳለችም ጊዜ ራስዋንም በመሐላ ያሰረችበት ነገር ከአፍዋ በወጣ ጊዜ ባል ያገባች ብትሆን፥ ባልዋም ቢሰማ፥ በሰማበትም ቀን ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ይጸናል። ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ በእርስዋ ላይ ያለውን ስእለትዋን ራስዋንም በመሐላ ያሰረችበትን የአፍዋን ነገር ከንቱ ያደርገዋል፤ እግዚአብሔርም ይቅር ይላታል።”/ዘኁ 30 ፡ 2 -8/

በዚሁ አጋጣሚ ቪዲዮው ላይ ምዕራፍ 28 ለማለቴም ይቅርታ እጠይቃለሁ። በርግጥ ይህችን ለመጻፍም ምክንያቴ ይኼው ስሕተት ነው።

በዚህ ጥቅስ ውስጥ ያለው መሠረታዊ መልእክት አንድ ነገር ነው። ይሔውም አንዲት ሴት በድንግልና ለመኖር ብጽዓት ቢኖራት ያን መጠበቅ ስለምትችልበት እና ስለማትችልበት ሁኔታ ማብራራት ነው። ከዚህ ውስጥ ብጽዓት ስትገባ አባቷ አይሆንም ካላት ታገባለች፤ እግዚአብሔርም ብጽዓቷን እንደሻረች አይቆጥርባትም። አባቷ ዝም ካለ ግን የድንግልና ብጽዓቷን ጠብቃ ትኖራለች ማለት ነው። ሁለተኛው ደግሞ ከታጨች በኋላ ለእጮኛዋ ብጽዓቷን ነግራው ከተቀበለ ከእጮኛዋ ጋር ሆና ብጽዓቷን ለመጠበቅ መብት ይሰጣታል። እርሱ እንደሰማ ከተቃወመ ግን እጮኛዋ ባሏ ይሆናል ብጽዓቷም ይሻራል፤ በእግዚአብሔርም እንደበደለኛ አትቆጠርም ማለት ነው።

ይህን መነሻ ይዘን ዮሴፍ ባሏ ሆኖ የሚኖርማ ቢሆን ኖሮ “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል” ብላ መልአኩን ለምን ትጠይቀው ነበር? ስለዚህ ወዳጄ ሆይ አስተውል፤ ከላይ በኦሪቱ የተቀመጠው ቃል መጀመሪያም የተሠራው ይህን የእመቤታችን እና የዮሴፍ እጮኝነት እድፈት የሌለበት መሆኑን ለማመልከት እና በኦሪት ሕግ መሠረት የተፈጸመ መሆኑን ለማመልከት ነው ማለት ነው።
ሌላው እመቤታችን ካለምንም ወንድ በድንግልና ላለመጽነሷ ምን ማረጋገጫ አለ ከሚል ጥርጣሬም ነጻ እንድትወጣ የሆነችውም እመቤታችን ከዮሴፍ ጋር በመኖሯ ነው። ስለዚህ በድንግልና መጽነሷን ከመልአክክ ብሥራትም ጭምር በመረዳት በኋላ ለሚነሣው ትውልድ ሁሉ መሰናከያ እንዳይሆን ጠባቂዋ ዮሴፍ ነበረ። ለዚህ ነው መልአኩም “እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ” ያለው። እንዲህ ብሎ መልአኩ ለምን አሳሰበው ብለን ብንጠይቅ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው እውነታ ነው።

ሌሎች እንደሚሉት ሚስቱ ብትሆን ሊፈራ አይችልም። ሚስቱ ሳትሆንስ ለምን ይፈራል ብንል ደግሞ ሊያስፈራው የሚችለው ሁለት ነገር ነው። አንደኛው ብጽዓቷን አስፈረስክ ወይ? ተሳሳትክ ወይ የሚለው የሚያስፈራው ነው። ከእርሱ ጋር ካልሆነ ደግሞ ከአንተ ጋር በሚስትነት ካልኖረች ከማን ጸነሰች የሚለውንም ይፈራዋል። ምክንያቱም ይህን ሊመልሰው የሚችል አይደለምና። እንደተጻፈውም የሆነውን ሙሉ በሙሉ የሚያውቀው ጌታ ከተወለደ በኋላ ነውና። ስለዚህ ዮሴፍ የፈራው እመቤታችን በድንግልና ለመኖር በብጽዓት የምትኖር ስለሆነና እና በዚህም ጸንታ እንድትኖር ዮሴፍ ጠባቂዋ ሆኖ ስለተሰጠ ነው።
ጌታ እመቤታችንን ልክ ዮሐንስ መጠምቅን በበረሃ እንደጠበቀው በአምላካዊ ከሃሊነቶ እርሷን ሰውሮ እና ጠብቆ መወለድ ይችል ነበር። ያን ቢያደርገው ኖሮ ግን አምላክነቱን ቀርቶ አምላክ ሰው መሆኑንም ለማመን ያስቸግር ነበር። ለምን ምትሐት አለመሆኑን፤ እርሷም ኃይል አርያማዊት አለመሆኗን በምን ይታውቅ ነበር? ምትሐት ነው ቢሉስ? ከርሷ አልተወለደም ቢሉስ? እነዚህ ሁሉ በታወቀ ለታሪክ በመመዘገብ እና በሰዎች መካከል መደረግ ነበረበት ። ስለዚህ ዮሴፍ ሦስተኛው የጠበቃት ደግሞ በምትሐት እና መሰል ነገር ጸነሰች ወለደች ተብሎ የጌታ አምላክነት ከሌላ መንፈስ እና ከመሳሰሉት ጉዳቶችም እንዳይያያዝ የጠበቃት ዮሴፍ እጮኛዋ በመሆኑ ነው። ስለዚህ ዮሴፍ በትክክል የእመቤታችን እጮኛ ጠባቂዋ ነው። ለጌታችን በድንግልና መጸነስ እና መወለድ የመጀመሪያው ምስክር እርሱ ሆነ፤ ለዚህም የተመረጠ ሆነ ማለት ነው፤ በእውነት የዚህ ጻድቅ ሰው በረከቱ ይድረሰን።

@EotcLibilery

tgoop.com/EotcLibilery/16007
Create:
Last Update:

BY EOTC ቤተ መጻሕፍት

Share with your friend now:
tgoop.com/EotcLibilery/16007

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Clear A few years ago, you had to use a special bot to run a poll on Telegram. Now you can easily do that yourself in two clicks. Hit the Menu icon and select “Create Poll.” Write your question and add up to 10 options. Running polls is a powerful strategy for getting feedback from your audience. If you’re considering the possibility of modifying your channel in any way, be sure to ask your subscribers’ opinions first. Healing through screaming therapy “[The defendant] could not shift his criminal liability,” Hui said. Some Telegram Channels content management tips
from us

Telegram EOTC ቤተ መጻሕፍት
FROM American