Telegram Web
እንኳን አደረሳቹሁ
#ጥር21_አስተርእዮ_ማርያም_ ( #በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_(ለሶልያና )
#እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡
#ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ
#ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት
#ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት፡፡
፠ ጌታችን ለእናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና  አባቷ  ወደተቀበሩበት  ወደ ጌቴ  ሴማኒ  ሲወስዷት  አይሁድ  አይተው፤  ልጇ ተነሳ፥ አረገ  እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው  አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ  በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ ….. ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ በነሐሴ 14 ነው  ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››ረፍታ ለሶልያና(ለማርያም)
ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡
#ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡
*የእመቤታችንን ዕረፍት ሊቁ ቅዱስ  ያሬድም  ‹‹ሞትሰ  ለመዊት ይደሉ፥  ሞታ  ለማርያም የአጽብ ለኵሉ፡፡ /ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁለን ያስደንቃል፡፡›› በማለት አደንቆ ጽፏል፡፡
*እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ የላይ ቤት (የግምጃ ቤት ማርያም) አብነትና የታች ቤት(የበዓታ) አብነትን ሁለቱንም አዘጋጅተንላችኋል፡፡ መልካም ክብረ በዓል፡፡
**ክብረ በዓሉ በሃገራችንና በዓለማችን ክፍሎች ባሉ የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት የሚከብሩ ቢሆንም ግን፤ በልዩ ሁኔታ እንደ ጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደ ጥምቀት በዓል፤ ከዋይዜማው ጀምሮ ወደ ጥምቀተ ተወርዶ በማደር ክብረ በዓሉ በልዩ ሁኔታ መከበሩን ልብ ይሏል::
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
🛑 || የቸርነት በር || እጅግ ድን...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
የቸርነት በር
             
Size:-93.4MB
Length:-1:40:54

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
🛑 || የሰማዕታት ውበት || እጅግ ...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
የሰማዕታት ውበት
             
Size:-59.9MB
Length:- 1:04:40

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
የደቡቧ ኮከብ ብርብር ማርያም= የኦሪትና የሀዲስ ኪዳን ማህተም
~~~~~~~

የደቡቧ የአጥቢያ ኮከብ በመባል የምትታወቀው ብርብር ደብረ ማርያም ገዳም የምትገኘው በጋሞ ዞን በምዕራብ ዓባያ ወረዳ ቦላ ሔራ ቀበሌ ልዩ ስሙ ደጋ ብርብር እየተባለ በሚጠራው ከፍተኛ ቦታ ላይ ነው፡፡

ደብረ ማርያም ብርብር ገዳም ቀደም ሲል በኦሪት ቤተ መቅደስ የተተከለችው ከጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ ልደት 400 ዓመት አካባቢ ነበር።

በሀገራችን ኢትዮጵያ መሥዋዕተ ኦሪት ከሚሰዋባቸው ትምህርተ ብሉይ ከሚሰጥባቸው አክሱም ጽዮን፣ ተድባብ ማርያም፣ መርጡለ ማርያምና ጣና ቂርቆስ አብያተ መቃድስ ጋር በኦሪቱ ሥርዓትና በምኩራብ በአይሁድ ደንብ ትተዳደር ነበር።

በዘመነ ሐዲስ በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ደግሞ የቤተ መቅደስዋን የጥንት ታሪክና ዝና የሚያውቁት አጼ ገብረ መስቀል ብርብር በተባለችው ቤተ መቅደስ ሥርዓት ሐዲስ ዘመንን የሚመለከት ታቦት ገብቶ ሊወደስባትና ሊቀደስባት እንደሚገባ አስበው በታቦተ ማርያም ስም ቅዱስ ያሬድ እና ጻድቁ አቡነ አረጋዊን ታቦተ ማርያምን አስይዘው በአያሌ ሠራዊት ታጅበው ከአክሱም ጽዮን በብዙ ጉዞና ድካም ወደ ቦታው ደረሱ።

ግንቦት 21 ቀን ጻድቁ አቡነ አረጋዊ ቤተ መቅደሱን በሜሮን አክብረው ታቦተ ማርያምን አስገብተው ቅዳሴ ቤቷን አከበሩ።

በዚህ መሠረት አገልግሎቷን ከኦሪት እስከ ሐዲስ ኪዳን ስትቀጥል የደቡብ ኢትዮጵያ የሃይማኖት ማዕከል
በመባል የምትገለጸው ጥንታዊቷ ደብረ ማርያም ብርብር ገዳም በየዘመኑ የቤተክርስቲያናችን ላይ የሚነሱ አጽራረ አብያተ _ ክርስቲያናት ታሪኳን ለማጥፋት ቢጥሩም በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ድንቅ ተዓምራትን በማድረግ ለዚህ ትውልድ ደርሳለች።

አናኒያንና አዛሪያን የሚባሉ ሊቃነ ካህናት ታቦተ ጽላቱን ከኢየሩሳሌም ቀይ ባህርን አሻግረው ከአክሱም ታቦተ ፅዮን ጋር እንዳመጧት ይነገራል፡፡
ብርብር ማርያም በምትባለው የታሪክ የእውነት የመመረጥ እና የበረከት ዶሴ ውስጥ በምኩራብ ስርዓት በዘመነ ኦሪት ከነበሩት ከሊቃ ካህኑ ሳዶቅ ልጅ ካህኑ አዛርያስ እስከ ጉባኤ ኒቂያ አዘጋጅ ከሆነው የንግስት እሌኒ ልጅ ንጉስ ቆስጢንጢኖስ ድረስ በድምቀት ጎልተው ይነበባሉ።

በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ታሪክ የመጀመርያው ሊቀጻጳስ ከሆኑት ከአቡነ ከሳቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ ) እስከ ከሳቱ ቅዱሳን አካል ከሆኑት አቡነ አረጋዊ ድረስ በእዚህች ገዳም በረከት አፈስው ሱባኤ ይዘው ፀሎትና ቡራኪያቸውን አስቀምጠው ለትውልድ አልፈዋል።

የዜማው ሊቅ ስውሩ አባታችን ቅዱስ ያሬድ በመላእክት ጣዑመ ዜማ በሰማያውያን ለዛ በእዚህች ገዳም የምስጋና መሰዋት ዘርግቶ አልፎባታል።
በእዚህች ገዳምን ፃዲቁ አባታችን አቡነተክለሐይማኖት መንበረ አድርገዋት የወንጌል ዘርን በደቡብ ኢትዮጽያ ውስጥ ዘርተዋል።

ከኢዛና ሳይዛና እስከ አፄ ልብነድንግል፤ከአፄ ገብረመስቀል እስከ አፄ ዘርያዕቆብ ፤ ከአፄ ምኒልክ እስከ ጃንሆዬ ድረስ እጅ መንሻ እና መባ ለደቡቧ ኮከብ ለሆነችው ለብርብር ማርያም ሰጥተዋታል በረከት አፍሰውባታል።
በሀገር ላይ መከራ እና ወረራ ተከስቶ ጠላቶች በተነሱበት ጊዜ ከታቦተ ጽዮን እስከ ግማደ መስቀል በእዚህች ገዳም ሰንብተው ህዝቡን ባርከው ምድሯን ቀድሰው አልፈዋል።

እንግዲህ የእዚህች ገዳም ስም የደቡቧ ኮከብ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ሰማያዊት ጽዮን ብርብር ማርያም ትባላለች።

በህገ ኦሪት ከክርስቶስ ልደት 800 ዓመት በፊት በደብተረ ደንኳን በሊቀ ካህኑ ሳዶቅ ልጅ ካህኑ አዛርያስ ህገ እግዚአብሔር ተዘርግቶባታል።
በ1440 ዓ.ም አፄ ዘርዓ-ያዕቆብ ከትግራይ፣በ530 ዓ.ም አፄ ልብነ-ድንግል እንዲሁም በ1961 ዓ.ም ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ወደ ቤተ-ክርስቲያኗ በመምጣት መሳለማቸውና ድጋፍ እንዲሆን የሰጧቸው የተለያዩ ንዋዬ ቅድሳትን በገዳሟ ይገኛሉ።

የብርብር _ ማርያም ገዳም ከጋሞ ዞን ርዕሰ ከተማ አርባምንጭ 67 ኪ.ሜ ርቀት እንዲሁም ከምዕራብ አባያ ወረዳ ከተማ ብርብር 82 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡
ከተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የሚጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ምዕመናን አዘውትረው ፀሎት የሚያደርሱበት ስፍራ ነው፡፡

ጥንታዊና ታሪካዊ የሆኑ በርካታ ንዋየ ቅድሳትና መንፈሳዊ ቅርሶች ያቀፈች ገዳም ናት።
በዚህች ገዳም በርካታ ሀገርንና ህዝብን ሊጠቅሙ የሚችሉ የባህልና የቅርስ ማስረጃዎች ይገኛሉ።
ይህንንም ከግምት በማስገባት የኢፌድሪ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን በሀገር ቅርስነት መዝግቦ በተለያዩ ጊዜያቶች እየተንከባከባትም ይገኛል።

የገዳሟ የቅርስ ይዘትን ስንመለከት ፦ በርካታ የብራና መፃህፍት፣ ከነገሥታት የተበረከቱ ጥንታዊ መፅሐፍት ፣ የቅዳሴ መስቀሎችና ሌሎች ቅርሶች ይገኛሉ።
የዚህችን ገዳም ታሪካዊነት ከሚያሳዩ የቁም ማስረጃዎች ዋና ዋናዎቹ ገዳሟ በአካባቢው የጋሞ ቤት አሰራር መሠረት የተሰራ ሲሆን የህንጻው ባህላዊ የቤት አሰራርም ጥበብ አሁን ላይ ይዘቱን እንደጠበቀ ይገኛል፡፡

የብርብር ማርያም ገዳም በአሁኑ ወቅት በጥሩ ሁኔታ ላይ ብትሆንም ቅርሶቹ የሚገኙበት ሁኔታ ካላት ውድ ዘመን ተሻጋሪ ሀብት አንጻር ለአደጋ የተጋለጠ በመሆኑ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ዘመናዊ ቤተ-መዘክር ሊገነባለት ይገባል።
አክሱም ጽዮንን ተሳልመው ይሆናል፤ጣና ቂርቆስን ረግጠው ሊሆን ይችላል፤ከተድባባ እና መርጦለማርያምንም በረከት ቢያፍሱም መልካም ነው።

ነገር ግን ብርብር ማርያም የምትባል አንድ ደቡቧዊር የህገ ኦሪትና ህገ ወንጌል ግምጃ ቤት በጋሞዎች መንደር አለች።

እሷ ትቀራችዋለች። ይሳለሟት፤ይርገጧት። በረከትና ቃልኪዷኗ ነፍስን አንጽቶ ስጋን የሚያከብር ነው።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የማርያም አዳራሽ - መርጡለ ማርያም !

ባሕር ዳር: ጥር 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጎጃም ከሚገኙት አያሌ ቅዱሳት ገደማት መካከል አንዷ የታላቋ እና የጥንታዊቷ ርዕሰ ርዑሳን መርጡለ-ማርያም ገዳም ናት።

ርዕሰ ርዑሳን መርጡለ ማርያም ገዳም የምትገኘው በጎጃም በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ዋና ከተማ መርጡለ-ማርያም ነው።

መርጡለ-ማርያም ትርጉሙ የማርያም አዳራሽ ማለት ነው። ርዕሰ ርዑሳን መርጡለ ማርያም ገዳም አሁን የያዘችውን የስም መጠሪያ ከመያዟ በፊት በተለያዩ ዘመናት አራት ጊዜ የስም መለዋወጦች አጋጥሟታል።

መጀመሪያ ሀገረ ሰላም ቀጥሎ ሀገረ እግዚአብሔር ተብላለች። ከዚያም ጽርሐ አርያም ተብላ ተጠርታለች በመጨረሻም አሁን የምትጠራበትን መርጡለ ማርያም የሚለውን ስያሜ አግኝታለች።

ይች ታላቅ እና ጥንታዊት ገዳም የተመሠረተችው ከእስራኤሉ ንጉሥ ሰሎሞን እና ከኢትዮጵያዊት ንግሥት ሳባ (ማክዳ) የተወለደው ቀዳማዊ ምኒሊክ ይዟቸው በመጣ ፫፻፲፰ (318) የኦሪት ካህናት በ4500 ዓመተ ዓለም ነው።

ወደ ዚች ቦታ የመጡት የኦሪት ካህናት መሥዋዕተ ኦሪትን በመሰዋት የኦሪትን አምልዕኮት ሲፈጽሙ ኖረዋል። መርጡለ ማርያም በኢትዮጵያ መስዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባቸው ከነበሩት አራቱ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም አክሱም ጽዮን፣ ተድባበ ማርያም እና ጣና ቂርቆስ መካከል አንዷ ነበረች፡፡

ገድለ አብርሃ ወ አጽብሃ እና ገድለ አባ ሰላማ ከሳቴብርሃን እንደሚያስረዱት ሕሩያን ነገሥታት አብርሃ ወ አጽብሃ ከጳጳሱ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ጋር በመኾን በ፫፻፴፫ (333) ዓ.ም ዓባይን ተሻግረው ጎጃም ምድር መርጡለ ማርያም ደረሱ።

በዚህ ቦታ ሕዝበ ክርስቲያኑን ወንጌል አስተምረው መክረው ከኦሪት ወደ ሐዲስ ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መልሰው ካጠመቁ በኋላ ሕዝበ ክርስቲያኑ አምልኮቱን የሚፈጽምበት ቤተ ክርስቲያንን ለመሥራት አሰቡ።

ቦታው ላይ የሚያምር ቤተ ምኩራብ ስለ ነበር ይህንን ለታሪክ ትተን ሌላ ቦታ ላይ እንሥራ በማለት በስተምሥራቅ አሻጋሪ ካለው ተራራ አሁን ግንብ ወሬ እየተባለ ከሚጠራው ኮረብታ ላይ ቁፋሮ ጀመሩ።

ነገር ግን መሬቱ የእሳት ትንታግ እየተፋ አልቆፈር አለ። በመኾኑም በዚህ ቦታ ቤተ ክርስቲያን እንሠራ ዘንድ እግዚአብሔር አልፈቀደም። ፈቃደ እግዚአብሔርን እናውቅ ዘንድ ለ፫ (3) ተከታታይ ቀናት ሱባኤ እንግባ በማለት በ፭ (5) በአካባቢው ባሉ የተለያዩ ኮረብታዎች ሱባኤ ገቡ።

ሱባኤ የገቡባቸው ከረብታዎችም፡-
👉የኦሪቱ ሊቀ ካህን አብኒ ኮረብታ
የሐዲሱ ሹም ሐዲስጌ ኮረብታ
👉የጳጳሱ አቡነ ሰላማ ሰላምጌ ኮረብታ
👉በንጉሥ አብርሃ አብርሂ ኮረብታ
👉በንጉሥ አጽብሃ ዜነዎ ኮረብታ ላይ እንደነበሩ ይነገራል

ንጉሥ አጽብሃም ከሁሉም አስቀድሞ ወደ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን በመሄድ ያየውን ራዕይ ተናገረ። ሌሎችም መጥተው ያዩትን ሁሉ ተናገሩ አባ ሰላማም ይህንን ራዕይ ያዩ መኾናቸውን ነገሯቸው። ሁሉም በአንዲት ሌሊት አንድ ዓይነት ራዕይ አዩ።

ያዩት ራዕይም « ዐሥራ ሁለት በሮች ያላት አንድ አምደ ብርሃን የቤተ መቅደሱ መሠረት ከተጀመረበት ኮረብታ ተነስታ እያበራች የጥንቱ ቤተ ምኲራብ ከሚገኝበት ጽርሐ አርያም አምባላይ ስታርፍ » ነበር፡፡

ጧት ወደ ቦታው ሲሄዱ የጥንቱ አስደናቂው ቤተ ምኩራብ መሬት ውስጥ ተቀብሮ ለጥያለ አረንጓዴ ሜዳ ኾኖ አገኙት፡፡

ነገሥታቱ አብርሃ ወ አጽብሃ በቦታው ቤተ መቅደስን ይሠሩ ዘንድ ወደዱ። በወርቅ እና በእንቁ አምዶችን እና አረፍቶችን ልዩ አድርገው በማስጌጥ የማርያምን ቤተመቅደስ ሠሩ።

ሥርዓትንም በመደንገግ ካህናትን ዲያቆናትን እንዲሁም ሁሉንም ሊያሥተዳድር የሚችል ሊቀ ካህናት ርዕሰ ርዑሳን ብለው ሾሙ። መቅደሷንም መርጡለ ማርያም ብለው ሰየሟት።

ንጉሥ አብርሃ ወ አጽብሃም እግዚአብሔር በመራቸው መሠረት በጳጳሱ በአባ ሰላማ አስባርከው በጽርሐ አርያም አምባላይ አስደናቂውን ባለ ፲፪ (12) ቤተመቅደስ ባለ ፩ (1) ፎቅ ቤተ መቅደስ ሠርተው በወርቅ በእንቁ በከበሩ ማዕድናት አስጊጠው ጥር ፳፩ (21) ቀን የእመቤታችንን ጽላት በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስገብተዋል።

ይህ ቤተ ክርስቲያን እጅግ የተለየ በልዩ ልዩ ቅርፅ ያጌጠ በወርቅ እና በእንቁ የተለበጠ አስደናቂ የጥበብ አሻራ ያረፈበት ነበር። ይህ ቤተ መቅደስ በዮዲት ጉዲት ዘመን በ፰፻፵፪ (842) ዓ.ም ተቃጥሏል።

በ፰፻፹፪ (882) ዓ.ም የነገሠው አንበሳ ውድም በዮዲት የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንደገና አሠርቶታል። ይህንን ቤተ ክርስቲያን ዐፄ በእደ ማርያም በ፲፬፻፷ (1460) ዓ.ም አሳድሶታል። ባለቤቱ ንግሥት እሌኒ ደግሞ የአንባውን ዙሪያ አሠርታለች። አሁንም የገዳሟ ዙሪያ የእሌኒ ውድሞ ይባላል።

ገድለ አብርሃ ወ አጽብሃ፣ ገድለ አባ ሰላማ ከሳቴብርሃን እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተሠራ ዘጋቢ ፕሮግራም እንደሚያስረዳው መርጡለ ማርያም በዋጋ የማይተመን ከፍተኛ የቅርስ ክምችት ያላት ገዳም ናት፡፡

እነዚህ ውድ ቅርሶች በመርጡለ ማርያም ሙዚየም ውስጥ የሚገኙ የአብርሃ ወአጽብሃ የወርቅ መስቀል፣ በ445 ዓ.ም የተጻፈ ግዕዙን በግዕዝ የሚተረጉም አርባዕቱ ወንጌል፣ የአጼ በእደ ማርያም ራስ ቁር እና የወርቅ ለምድ፣ የንግሥት እሌኒ የክብር ካባ እና የብር ዋንጫ፣ የብር እና የወርቅ መስቀሎች፣ የወርቅ አክሊሎች፣ የወርቅ ከበሮ፣ የአጼ ገላውዲዮስ ዳዊት እና ካባ፣ የብራና መጻሕፍት እና የመሳሰሉትን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

ጥር 21 የሚከበረው በዓለ አስተርእዮ ማርያም የመርጡለ ማርያም ልዩ የክብረ በዓል ቀን ነው፡፡ አስተርእዮ ማርያም በመርጡለ ማርያም በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች የሚከበር ደማቅ በዓል ነው፡፡

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
🔴 ተዓምረ ማርያም || አዲስ እጅግ ...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
ተአምረ ማርያም
             
Size:-120.6MB
Length:-2:10:16

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
🔴 ትዳር ክቡር ነው || አትፋቱ || ...
Enqo silassie
ትዳር ክቡር ነው አትፋቱ
             
Size:-64.2MB
Length:-1:09:17

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@Mezigebehayimanot
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ጾመ ነነዌን አስመልክተው አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል !

ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ሰኞ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም የሚጀመረውን የፈጾመ ነነዌን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት  የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሙሉ መልእክቱ እንደሚከተለው ቀርቧል

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈ የምህላ ሱባኤ፡-

‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ አስተጋብኡ ሕዝበ ሊቃውንተ ሕዝብ፤ ጾምን ቀድሱ፣ጉባኤውንም አውጁ፤ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ኣምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ (ኢዩ ፩÷፲፬)።

ሁላችንም እንደምናውቀው ያለንበት ዓለም የመከራ ዓለም ነው፣ መከራው በኛ ስሕተትና ክፋት የመጣና እየሆነ ያለ መሆኑም ይታወቃል፤ እኛ የምንፈጽመው ጥቃቅንና ትላልቅ ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን እንደሚያስቈጣ በቅዱስ መጽሐፍ ተረጋግጦ ያደረ ነው፤ ለዚህም ከነነዌ ነዋሪ ሕዝብ የበለጠ ማስረጃ የለንም፤ የነነዌ ከተማ ነዋሪዎች በፈጸሙት ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን አስቈጥተዋል፤ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ ቢሆንም እሱ ምሕረቱን ማስቀደም ስለፈለገ በዮናስ በኩል አስጠንቅቆአቸዋል፤ የነነዌ ነዋሪዎችም በዮናስ በኩል የደረሳቸውን የንስሓ ጥሪ ወዲያውኑ ተቀብለው በምህላ፣ በጾም፣ በጸሎት ንስሓ ስለገቡ እግዚአብሔር ፍጹም ይቅርታ አድርጎላቸዋል፤

•  የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን !

እኛ ሰዎች ዛሬም በየሰዓቱ ብቻ ሳይሆን በየደቂቃው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ አበሳ እንደምንፈጽም ማወቅ ኣለብን፣ አበሳውና ኃጢኣቱ ሲበዛ እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነውና ወደ ዳኝነት ተግባሩ ይገባል፤ይህ ደግሞ በሰብአ ትካት በሰዶምና በጎሞራ ያስተላለፈውን ዳኝነት ያስታውሰናል፤ አሁን ያለንበት ዘመን ዓመተ ምሕረት በመሆኑ እግዚአብሔር ለጊዜው ቢታገሠንም በኃጢኣታችን የምንጠየቅበት ጊዜ አዘጋጅቶአል፤ ዛሬም ቢሆን የማናስተውለው ሆነን ካልሆነ በስተቀር እግዚአብሔር ተግሣጹን ማስተላለፍ አላቆምም፤ በምድራችን ላይ በምናደርሰው የተዛባ ተግባር በጐርፍ፣ በድርቅ፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በአየር መዛባት እየገሠጸን እንደሆነ ማስተዋል አለብን።

እግዚአብሔር ከጥንቱ ከጠዋቱ ጀምሮ ምድርን እንድንከባከባት፤ እንድናበጃት፣ እንድናጠብቃትና እንድናለማት አዞናል፤ ሆኖም ይህን ትእዛዙን ገሸሽ አድርገን በኬሜካልና በመርዛም ጋዝ ምድርን በመበከል፣ደንዋን በመመጠርና ራቁቷን በማስቀረት በምናደርገው ድርጊት አበሳ እየፈጸምን እንደሆነ ያወቅነው አይመስልም፤ በዚህም ምክንያት በጐርፍ፣ በድርቅ ለሰው ልጆች በማይመች የኣየር ፀባይ ወዘተ . . . ስጋት ውስጥ እየወደቅን ነው።

በሌላም በኩል በምናወሳስበው የአስተዳደር ርእዮትና መሳሳብ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና ያላስፈላጊ አደጋ ላይ እንድወድቅ እያደረግን ነው፤ በዚህም ጠንቅ ሰላም እየደፈረሰ፣ ፍቅርና አንድነት እየላላ የሃይማኖት ክብርና ልዕልና እየተነካ ራሳችንንም እየጐዳን ነው፤በዚህ ሁሉ ተግባራችን  እግዚአብሔርን እያሳዘንን ነው፤ ይህ ሊገባንና ሊቈረቁረን ይገባል፤

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት

ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፤በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል፤ ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአየር መዛባት፣የድርቅ መከሠት፣የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣ የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ. . . . ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን፤ ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ  ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፤ እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላካችን ምሕረቱን ይቅርታውንና ሰላሙን ለሀገራችንና ለዓለማችን ይስጠን፤ ምህላችንንም ይቀበልልን።

   “እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ”

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት

ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ...
ማኅበረ ጽዮን
የጸናውን አስቡ
             
Size:-63.4MB
Length:-1:08:26

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
"ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ ፡-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው" ስምዖን አረጋዊ

#የካቲት_8  ፤ የጌታችን  ከከበርች ልደት በኋላ  ወደ ቤተመቅደስ የገባበት ዕለት ኾነ ፡፡ በዓሉ ከጌታችን ንዑስ በዓሎች መኻከል አንዱ ነው ፡፡
++++
የካቲት 8 ፤ ልደተ ስምዖን አረጋዊው  ፣ ካህን ፣ ጻድቅ ፣ ነቢይ ፡፡

+ በዓሉ የመድኀኔዓለም ቢሆንም ስምዖን አረጋዊ አማናዊ ድኅነት አግኝቶበታልና ፣  በእርጅና ምክንያት ከአልጋ ላይ ተጣብቆ ሲኖር ታድሶበታልና እንደ 30 ዓመት ጎልማሳም ዘሏልና  በዓሉ ይከብራል ። ስምዖን ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ሁሉ የድኅነት ባለቤት ኾኖበታልና በዓሉ ይከብራል ።

++++

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በተወለደ በ40 ቀኑ የኦሪትን ሕግ ለመፈጸም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ ። ይህም ሕግን ሊፈጽም እንጂ ሊያፈርስ አለመምጣቱን በቃልም ፣ በግብርም የገለጠበት በዓል መኾኑን ያስረዳናል። ሥርዓቱን ለመፈጸም እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምና አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ጌታቸውን ይዘው፣ የርግብ ግልገሎችና ዋኖስ ጨምረው ወደ ቤተ መቅደስ ሔዱ ።

++++

የስምዖን አረጋዊ ነገርም እንዲኽ ነው ..
ዓለም በተፈጠረ በ5,200 ዓመታት በጥሊሞስ የተባለ ንጉሥ በግሪክ ነግሦ ነበር። ዓለሙን እንደ ሰም አቅልጦ፣ እንደ ገል ቀጥቅጦ የገዛው መሆኑን ገልጦ፣ የቀረው ነገር አለመኖሩን ሲናገር ባለሟሎቹ በእሥራኤል ጥበብ የመላባቸው 46 መጻሕፍት ስላሉ እነርሱን አላስተረጎምክም አሉት። እስራኤልን አስገብሮ ስለነበር 46ቱን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከ72 የአይሁድ ሊቃውንት ጋር አስመጣ። አይሁድ ተንኮለኛ መኾናቸውን ስለሚያውቅ 36 ድንኳን እንዲዘጋጅ አድርጎ ኹለት ኹለቱን መድቦ፣ የየድንኳኑን ሊቃውንት የሚቆጣጠሯቸው አንዳንድ ጠባቂዎች ጨምሮ  እንዲተረጕሙ አዘዛቸው።

በዚህ ምክንያት በ284 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት 46ቱ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከዕብራይስጥ ወደ ልሳነ ጽርዕ (ግሪክ) በ70ው ሊቃናት ተተረጐሙ። ከ70 ሊቃናት በመኻከል አንዱ የነበረው #ስምዖን ምሁረ ኦሪት ነበር። ይተረጕም ዘንድ መጽሐፈ ኢሳይያስ ደረሰው። ታዲያ ይህ ሊቅ የትንቢቱን መጽሐፍ እየተረጎመ ሳለ ምዕራፍ ፯ ላይ ሲደርስ የሕይወቱን አቅጣጫ ወደ ዘላለማዊ በረከት የሚያሳድግ ልዩ ገጸ ንባብ ገጠመው ።  እርሱም
“ ስለዚኽ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነኾ ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” ኢሳ 7፥14 የሚል ነበር።
ስምዖንም "እንዴት ድንግል ትፀንሳለች?" ብሎ "ድንግል" የሚለውን "ሴት" ብሎ ቀይሮ " ሴት ትፀንሳለች " ብሎ ለማረም ይሞክርና አመሻሽ ላይ ስለነበር እንቅልፍ ሸለብ አድርጎት ሲነቃ የቀየረው ተቀይሮበት " ድንግል ትጸንሳለች" የሚል ሁኖ ያገኘዋል።  ተሳስቼ ነው ብሎ አሁንም ሊያበላሽ ሲሞክር መልአኩ ሦስት ጊዜ አርሞበት  በሦስተኛው መልአኩ ራሱ ተገልጦለት "ይህችን ድንግል ሳታይና ልጇንም ታቅፈህ ሳትባረክ አትሞትም"
( የተጠራጠርከውን ሳታይ አትሞትም ብሎ ብሎ ነግሮት )  ተሰወረ። አረጋዊ ስምዖንም ከዚያች ዕለት ጀምሮ መድኅን ክርስቶስ እስከሚወለድ ለ284 ዓመታት ከአልጋ ጋር ተጣብቆ ኖረ።
አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በተወለደ በ40 ቀኑ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ወደ ቤተ መቅደስ ይዘውት ወጡ ። በዕለቱም መልአከ እግዚአብሔር አረጋዊ ስምዖንን ቀስቅሶ ተስፋ የሚያደርገው አዳኝ ክርስቶስ መምጣቱን ነገረው። በዚህ ጊዜ አረጋዊ ስምዖን አካሉ ታድሶ፣ እንደ 30 ዓመት ወጣት እምር ብሎ ከአልጋው ተነሣ። በፍጥነትም ወደ መቅደስ ገባ። መድኀኔዓለምን ከድንግል ማርያም ተቀብሎ በመታቀፍ "ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ፡-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው"

(" ጌታ ሆይ፥ አን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ ፤ ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና፤
ይኽም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ፳ኤል ክብር ነው።" (ሉቃ 2÷29-32)  )
በማለት ጸለየ። 

አምላኩም ጸሎቱን ሰምቶት በዛሬው ዕለት ዐረፈ። ከበዓሉ በረከት ይክፈለን። አሜን!!

የሊቁ ስምዖን  አረጋዊ በረከት እና ምልጃ አይለየን !
በዓለ ስምዖን በዐይቢይነት  ሜላት ደብረ ገነተ ኢየሱስ  ይከብራል  ፡፡
ጐንደር   -- › አንዳቤቴ ወረደ   -- › ገነተ ኢየሱስ  
በ13ኛ መቶ ክፍለ  ዘመን በአጼ ሰይፈ አርዕድ ዘመነ መንግስት
ልዕልት ሜላተ ወርቅ ያሰተከለችው ደብር ነው ፡፡
+++
በዓሉ በኢየሱስ ስም የተሰየሙ አድባራትና ገዳማት ላይ ይከበራል !

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2025/03/13 14:33:38
Back to Top
HTML Embed Code: