Telegram Web
የሊጉን ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳካው ኢትዮጵያ መድን

#Ethiopia: የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2017 ዓ.ም. ውድድር ዘመን በኢትዮጵያ መድን አሸናፈነት ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ቡድኑ በ2018 ዓ.ም. የውድድር ዘመን በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ ይወዳደራል፡፡ ኢትዮጵያ መድን በ1987 ዓ.ም. ቀድሞ በነበረው የአፍሪካ ክለቦች ‹‹ካፍ ካፕ›› ውድድር እስከ ግማሽ ፍፃሜ ደርሶ በአይቮሪኮስቱ ስቴላ አቪጃ በደርሶ መልስ ውጤት ተሸንፎ ከውድድር ውጪ መሆኑ ይታወሳል፡፡
በ1970ዎቹ አጋማሽ እንደተመሠረተ የሚነገርለት ኢትዮጵያ መድን፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሁን በያዘው ስያሜ የሊጉን ዋንጫ በ2017 ዓ.ም. ከፍ ሲያደርግ የመጀመሪያው ነው፡፡ ቀደም ሲል በጅማ አባ ጅፋርና በመቀለ 70 እንደርታ በ2017 ዓ.ም. የውድድር ዘመን ደግሞ ኢትዮጵያ መድን ይዘው የኮከብ አሠልጣኝነትን ክብር ለሦስተኛ ጊዜ ያሳኩት አሠልጣኝ ገብረ መድኅን ኃይሌ፣ ለዓመታት ከአኅጉራዊ መድረክና ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ የራቀውን ኢት...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/142702/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
10👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ‹‹ስምረት ትግራይ›› ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ ጠዓመ ዓረዶም ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ከተናገሯቸው በጥቂቱ፡
“ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መሆን ይፈልግ ነበር”
“የኦሮ-ማራ ጥምረት ህወሓትን ለማባረር ጠቅሟል”
“ሻዕቢያ ከመከላከያ ላይም ዘመናዊ ታንኮችን ይወስድ ነበር”
ሙሉ ቃለ-ምልልሱን ዛሬ ከቀኑ 8 ሰአት በዩትዩብ ቻናላችን ላይ ይጠብቁ፡፡
13👎4
የሕወሓት የጦርነት ድግስ የተወገዘበትና የትግራይ ፖለቲከኞችን ያሰባሰበው መድረክ

#Ethiopia: የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናቶች ኢንስቲትዩት ሕንፃን ተጎራብቶ በሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ድጋፍ በተሠራው መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ፣ ዓርብ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. የትግራይ ፖለቲካ ልሂቃን ተሰባስበው ነበር፡፡ ከአንጋፋው የሕወሓት መሥራች አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) እስከ ወጣቱ የባይቶና ፓርቲ ሊቀመንበር ክብሮም በርሄ፣ በዕድሜና በልምድ ብቻ ሳይሆን፣ በፖለቲካ አቋምም የተለያዩ የትግራይ ፖለቲከኞች የተሳተፉበት ነበር፡፡ በማኅበራዊ የትስስር ገጾች የሚታወቁ፣ በመደበኛ ሚዲያዎችም የቆዩና ከተለያዩ የትምህርት ማዕከላት የመጡ ተሳታፊዎችም ታድመዋል፡፡ ከቀድሞ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ጀምሮ በአሁኑ ጊዜ በሥልጣን ላይ ያሉ የሥራ ኃላፊዎች ድረስ ተገኝተዋል፡፡ ከትግራይ የመጡ ወጣቶችና የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮችም ታድመው ነበር፡፡ ከትግራይ ልሂቃን በተጨማሪ የውይይት መድረኩ ሚዲያዎችን በሰፊው ያሳተፈ ሲሆን፣ ከሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎችም የተጋበ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/142738/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
17👍10👎5🤪3😢1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ማስታወቂያ

ስልክዎ ላይ ቅርንጫፍ ከፍተናል!
****
ወዲህ ወዲያ ሳይሉ ባሉበት ፍላጎትዎን ልናሟላ
ስልክዎ ላይ ቅርንጫፍ ከፍተናል!

በሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ
ህይወትዎን ቀላል ያድርጉ!

#cbe #digitalbanking #mobilebanking #banking #ethiopia
****
የሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያን ለማግኘት፡

• Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.mobilebanking
• IOS: https://apps.apple.com/us/app/cbe-mobile-banking-new/id1534203410#?platform=iphone
6👎1
#ማስታወቂያ

Tajaajila Intarneet Baankiingii Baankii Siinqee mijataa fi amansiisaa ta'e yoomeessi osoo isin hindaangessiin salphumatti itti fayyadamaa!

ጊዜና ቦታ ሳይገድብዎ ምቹ እና አስተማማኝ የሆነዉን የሲንቄ ባንክ ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎትን በቀላሉ ይጠቀሙ!

Use Siinqee Bank's  user-friendly  and secured Internet Banking, accessible anytime and anywhere!

#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ  #Siinqee_Digital #Siinqee_Ihsan
#EMPOWERED_TOGETHER
5😁2👎1
ከፍተኛ የዕድገት ምጣኔ እያስመዘገበ ያለው ከወለድ ነጻ የፋይናንስ አገልግሎት

#Ethiopia: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የመጀመሪያው ይሆናል የተባለውንና ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት ስትራቴጂ በአማካሪ ድርጅት ሊያሠራ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ ከወለድ ነፃ የሚሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ የዕድገት ምጣኔ ከመደበኛው የባንክ አገልግሎት ከሚሰበሰበው ብልጫ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ራሱን የቻለ መንገድ እንዲመራ ያስችላል የተባለውን ከወለድ ነፃ የፋይናንስ ስትራቴጂ፣ ከባንኩ ውጭ ባሉ አማካሪ ድርጅቶች እንዲሠራ በመወሰን፣ አማካሪዎች ለመቅጠር ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱ ታውቋል፡፡
ኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ ከተባለ ተቋም ጋር በመተባበር ሊዘጋጅ የታሰበው ከወለድ ነፃ የፋይናንስ ስትራቴጂ፣ ተጫራቾች የሚወዳደሩት ለተጠቀሙት አገልግሎቶች የሚሆን ፕሮፖዛል በማቅረብ ሲሆን፣ የሚመረጠው ስትራቴጂ ሲተገበርም ለአሸናፊው ድርጅት ስድስት ወር የማማከር ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡
ስትራቴጂው አጠቃላይ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ፋይናንስ ሥር ያሉትን...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/142730/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
7👍2👎1🤔1
ዘወትር ዕረቡ የሚጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
የ ጨረታ ማስታወቂያዎች ↠ ReporterTenders.com
👍63
የውጭ አገር ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን የሚችሉበት አዋጅ ፀደቀ

#Ethiopia
መሬት የመሸጥና የመለወጥ መብት የላቸውም

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ አገር ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን የሚችሉበትን አዋጅ፣ ትናንት ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. አፀደቀ፡፡
ረቂቅ አዋጁን መርምሮ የውሳኔ ሐሳብ ያቀረበው የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሰጠው ማብራሪያ፣ አዋጁ የኢትዮጵያውያንን መብት በማይነካ መልኩ፣ የውጭ አገር ዜጎች የመኖርያ ቤት ባለቤት በመሆን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሠማሩና ሥራዎችን እንደሚሠሩ ገልጿል።
የውጭ አገር ዜጎች ወደ ኢትዮዽያ ገብተው በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺሕ ዶላር ነው።
የቀረበው የገንዘብ መጠን አነስተኛ መሆኑ በምክር ቤቱ የተነሳ ሲሆን፣ የተቀመጠው የገንዘብ መጠን አሁን በኢትዮጵያ ካለው የቤት ገበያ ጋር በማነፃፀር የወጣ ስለመሆኑም ተብራርቷል።
የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺሕ ዶላር ሲሆን፣ በጊ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/142816/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
12👍4👎4
በጂቡቲ ወደብ ለ2.1 ሚሊዮን ተረጂዎች የሚውል ሰብዓዊ ዕርዳታ የመበላሸት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

#Ethiopia: ለ2.1 ሚሊዮን ተረጂዎች የሚውል ሰብዓዊ ዕርዳታ በጂቡቲ ወደብ የመበላሸት አደጋ እንደተጋረጠበት፣ የአፍሪካ ዴቨሎፕመንት ባንክ ግሩፕ ሪፖርት አመላከተ፡፡
በአፍሪካ ዴቨሎፕመንት ባንክ ግሩፕ (AfDB) "Country Focus Report 2025 Ethiopia" በሚል ርዕስ ከቀናት በፊት ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) የሚደረጉ የውጭ ዕርዳታ ፕሮግራሞች በሰፊው እንዲቋረጥ መወሰኑን አስታውሷል።
በዚህ ውሳኔ መሠረት 2.1 ሚሊዮን ሰዎችን ለአንድ ወር መመገብ የሚያስችልና ወደ ኢትዮጵያ መግባት የነበረበት ሰብዓዊ ዕርዳታ፣ ጥቅም ላይ የመዋል ዕድል ላይኖረው ይችላል ተብሏል።
ሰብዓዊ ዕርዳታው 34,880 ሜትሪክ ቶን ማሽላ፣ ጥራጥሬና ዘይት መሆኑንና ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ የሚከፈል ገንዘብ ባለመኖሩ ምክንያት፣ በጂቡቲ ወደብ ተይዞ እንደሚገኝ ተጠቅሷል። በዚህም ለተቸገሩ ሳይደርስ የመበላሸት አደጋ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/142824/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
14😢14👍2😱2
የወልቃይት ውጥረት ማገርሸትና የጦርነት ሥጋት

#Ethiopia: በወልቃይት አካባቢ ውጥረቱ በድጋሚ አገርሽቷል፡፡ የተመድ የሰብዓዊ ረድዔት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት (UNOCHA) በቅርቡ ባዘጋጀው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎችን በካርታ አስደግፎ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ተጠቀመ የተባለው ካርታ፣ የትግራይና የአማራ ክልሎች ፖለቲከኞችን ሲያወዛግብ መሰንበቱ ይታወሳል፡፡ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አጨቃጫቂ ከሚላቸው መሬቶች አንዱ የሆነውንና የትግራይና የአማራ ክልሎችን ሲያጋጭ የቆየውን አካባቢ፣ በካርታው ላይ የአማራ ክልል ሆኖ ነው የቀረበው ያሉ የትግራይ ፖለቲከኞች ጠንካራ ተቃውሞ ማቅረባቸው አይዘነጋም፡፡
የካርታው ጉዳይ ያስነሳው ውዝግብ ጥቂት በረድ ካለ በኋላ ደግሞ ተፈናቃዮች ሊመለሱ ይገባል የሚለው ሙግት አዲስ ትኩሳት ከሰሞኑ ፈጥሯል፡፡ የአሁኑ የተፈናቃዮች መመለስን መነሻ አድርጎ የተቀሰቀሰው ውጥረት ማየል ደግሞ፣ ጉዳዩ የጦርነት መነሻ እንዳይሆን እያሠጋ ነው፡፡ ከወልቃይትና ከሌሎች አጨቃጫቂ መሬቶች የተፈናቀሉ በትግራይ ክል...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/142887/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
19👍2🤔2👎1
ክልሎች ሕገወጥ ኬላን የሥራ ዕድል ምንጭ ማድረጋቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

#Ethiopia
በ11 ወራት 19 ቢሊዮን ብር ግምት የሚያወጣ ኮንትሮባንድ መያዙ ተገልጿል

ክልሎች የሕገወጥ ኬላ ግብረ ኃይል በማቋቋም ለሥራ ዕድል ፈጠራ አማራጭ አድርገው እየሠሩበት ነው ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር  ወቀሳ አቀረበ፡፡
የገቢዎች ሚኒስትሯ ወ/ሮ አይናለም ንጉሤ የተቋማቸውን የ11 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርቡ ነው ይህ የተነገረው፡፡
ሚኒስትሯ በማብራሪያቸው የሚመሩት ተቋም በ14,220 የሰው ኃይል ወይም መዋቅሩ ከሚጠይቀው በ52 በመቶ ብቻ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የጉምሩክ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ ሕገወጥ ኬላን ማቋቋም ለጉምሩክ ኮሚሽን የተሰጠ ሥልጣን ቢሆንም፣ ክልሎች ሕገወጥ ኬላዎችን ዘርግተው ግብር የሚሰበስቡ የመንግሥት ተቋማት ሆነዋል ብለዋል፡፡ በክልል ፖሊስ በሚሊሻ መዋቅሮች እንደሚታገዝና በአንዳንድ ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/142839/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
10👍7😁1
It is lauded as 'a symbol of the financial sector’s liberation' and simultaneously decried as a source of profound disappointment. Some see it as having doubled exports, while others point to its role in halving the working capital of import-dependent businesses. It is cheered for boosting the country’s forex supply, yet derided as the reason behind the mounting pile of rejected loan applications across banks. One side considers it the least painful remedy for Ethiopia’s economic ailments, and at the same time it is a likened to ‘chemotherapy'—emphasizing its indiscriminate harm….
The July issue of Reporter Magazine has arrived! Pick up yours at your nearest supermarket.

Website: https://thereportermagazines.com/
16👍2
የትግራይ ክልል ወርቅ በዋናነት ወደ ኤርትራ በሕገወጥ መንገድ እንደሚወጣ በሪፖርት ተመላከተ

#Ethiopia: በትግራይ ክልል ከሚመረተው ወርቅ በየዓመቱ እስከ 80 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣው፣ በዋናነት ወደ ኤርትራ በሕገወጥ መንገድ እንደሚወጣ ሰሞኑን በወጣ በአዲስ ሪፖርት ተመላከተ።
‹‹ሥልጣንና ዘረፋ፣ የኤርትራ ጦር ጣልቃ ገብነት በትግራይ›› በሚል ርዕስ ያሰናዳውን ሪፖርት ይፋ ያደረገው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጦርነት ወቅት የተፈጸሙ ወንጀሎችን የሚመረምረውና የፖሊሲ ተቋም የሆነው ‹‹ዘ ሴንትሪ›› (The Sentry) የሚባለው ድርጅት ዘገባ እንደሚያስረዳው፣ በማዕድን ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም. እና በ2016 ዓ.ም. ለኩባንያዎች የማዕድን አሰሳና ምርት ሥራ ፈቃድ የተሰጠባቸውና አሁንም በኤርትራ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር በሚገኙ የትግራይ ግዛቶች ጭምር ውስጥ የሚደረገው ወርቅ ማምረት በከፍተኛ ደረጃ ውድድር የሌለበት፣ ውስብስብና ኃይል የተቀላቀለበት ነው።
እንደ ሪፖርቱ ማብራሪያ፣ ከትግራይ ክልል መሬትና ማዕድን ቢሮ የተገኘ መረጃ በየዓመቱ በክልሉ ከሚመረተው ወርቅ ከ75 እ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/142836/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
10👍4😁1
#ማስታወቂያ

እንዲህም  መክፈል ተችሏል!
ጠጋ ማድረግ ብቻ...
*
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፖሶች (POS) ካርድዎን በማስጠጋት ብቻ ክፍያዎን ይፈፅሙ!

የያዙት ካርድ  ያለንክኪ እንደሚሠራ የሚያሳየውን የሞገድ ምልክት (የዋይፋይ ምልክት)  ልብ ይበሉ፡፡

#CBE #POS #contactlesscards
#DigitalBanking #Ethiopia
6👍1
#ማስታወቂያ

Bara dargaggummaa keetti dalagaa seera Shari'aan hayyamame irratti bobba'uun  dhamaatee kan argatte irraa herreega qusannaa Dargaggootaa Waadihaa tajaajila baankii dhalarra bilisaa  Siinqee  IHSAN  kan ta’e ’ Lel-shabaab’ har’uma banattee  itti qusachuun abajuu kee dhugoomsi!

በወጣትነት እድሜህ  በሸሪዓ በተፈቀደ ስራዎች ላይ ተሰማርተህ ያገኘኸውን የልፋትህን ዋጋ  ሸሪዓ መርህ በተከተለው በሲንቄ ኢህሳን  ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት  “ሊል-ሸባብ” የወጣቶች የዋዲያህ ቁጠባ ሒሳብ በመክፈት ሕልምህን ለማሳካት ዛሬውኑ እኛጋር ቆጥብ!

#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ  #Siinqee_Digital #Siinqee_Ihsan
9👍1👎1
አዋሽ ባንክ ከታክስ በፊት 22.7 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ገለጸ

#Ethiopia
በሒሳብ ዓመቱ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቱን አስታውቋል

አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት የትርፍ ምጣኔውን በእጥፍ በማሳደግ፣ ከታክስ በፊት 22.7 ቢሊዮን ብር ማትረፉንና በአንድ ዓመት ከ106 ቢሊዮን ብር በላይ አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
ባንኩ የ2017 የሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ ትናንት ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ በሁሉም የሥራ አፈጻጸሞ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን፣ በተለይ ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን በእጥፍ ማሳደግ አንዱ ስኬት እንደነበር ገልጿል፡፡
የአዋሽ ባንክ  ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው፣ ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ ውጤታማ አፈጻጸም ካሳየባቸው ክንውኖች መካከል የትርፍ መጠኑን ከእጥፍ በላይ ማሳደግ መቻሉ ነው ብለዋል፡፡ በሒሳብ ዓመቱ ከታክስ በፊት ያስመዘገበው 22.7 ቢሊዮን ብር ባለፈው ዓመት አስመዝግቦት ከነበረው 10.8 ቢሊዮን ብር ትርፍ ጋር ሲነፃፀር የ12 ቢሊዮን ብር...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/142833/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
24👍5
ክቡር ሚኒስትሩ ከማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪያቸው ጋር የዋጋ ግሽበትን በተመለከተ እየተወያዩ ነው


• የዋጋ ግሽበትን መቀነስና ማኅበረሰባችን የገጠመውን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ ብዙ ብንሠራም በቂ ውጤት ማምጣት አልተቻለም።
• ክቡር ሚኒስትር ግሽበቱ በተወሰነ ደረጃ ዕድገቱ ቢቀንስም እርስዎ በትክክል እንደገለጹት ውጤቱ በፈለግነው ደረጃ አልሆነም።
• ለምን አልሆነም? ችግሩ ምንድነው? 
• ክቡር ሚኒስትር ችግሩ ሥር የሰደደ በመሆኑ በአጭር ጊዜ መፍትሔ ማምጣት አይቻልም። 
• አይቻልም የሚል ምላሽ መስማት አልፈልግም፣ ለምን አይቻልም?
• ክቡር ሚኒስትር የዋጋ ግሽበትን ለመፍታት ያሉት አማራጮች ሁለት ናቸው። 
• ምንና ምን?
• አንደኛውና መሠረታዊ የሚባለው መፍትሔ የምርት አቅርቦትን መጨመር ነው። 
• ታዲያ ስንዴ እያመረትን አይደለም እንዴ? 
• ልክ ነው፣ ግን የስንዴ ምርት ጨምሯል ማለት ፍላጎት ተመልሷል ማለት አይደለም፣ በተጨማሪም...
• በተጨማሪ ምን?
• የገጠመን የምርት አቅርቦት እጥረት የስንዴ ምርት በመጨመሩ ብቻ አይፈታም።
• ምን ማለትህ ነው?
• ልክ እንደ ስንዴው በሁሉም ምርቶች ላይ ርብርብ በማድረግ ምርታማነትን ማሳደግ ይኖርብናል፣ ይህ ደግሞ ጊዜ ይጠይቃል።
• ጊዜ ይጠይቃል ማለት?
• የዋጋ ግሽበትን ለመፍታት መሠረታዊና ዘላቂው መፍትሔ ምርታማነትን ማሳደግ ነው፣ ነገር ግን ሒደት የሚጠይቅ በመሆኑ ፈጣን መፍትሔ አያመጣም። 
• እሺ...
• ፈጣን መፍትሔ ለማግኘት የሚረዳው ሁለተኛው አማራጭ ነው።
• ሁለተኛው አማራጭ ምንድነው?
• ሁለተኛው አማራጭ በኢኮኖሚው ውስጥ የተሠራጨውንና የሚዘዋወረውን ገንዘብ መሰብሰብ ነው።
• ታዲያ ይህን የመፍትሔ አማራጭ መተግበር ያስፈልጋል ብላችሁ ወስነንበት የለም እንዴ?
• ትክልል ነው ክቡር ሚኒስትር። 
• ታዲያ?
• በውሳኔው መሠረትም የባንኮች የብድር ሥርጭት ላይ ገደብ መጣልና ሌሎች መሰል የገንዘብ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ አድርገናል።
• እና ለምን ለውጥ አልመጣም?
• በቂ አይደለም እንጂ ለውጥማ መጥቷል ክቡር ሚኒስትር።
• ለምንድነው በቂ ያልሆነው?
• ተግባራዊ የተደረጉት የገንዘብ ፖሊሲ መሣሪያዎች መሰብሰብ የሚችሉት በባንክ ሥርዓት ውስጥ ያለውን ገንዘብ ነው። 
• ማለት?
• ከባንክ ሥርዓት ውጪ የሚሠራጨውን ገንዘብ መሰብሰብ የሚቻለው የፊስካል ፖሊሲያችንን ጥብቅ በማድረግ ነው።
• ጥብቅ ማድረግ ስትል?
• የገንዘብ ሥርጭቱን ሊያሳድጉ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን ለጊዜው ማጠፍ ወይም ማዘግየት ማለት ነው።
• ታዲያ ትርጉም ያላቸው የካፒታል ፕሮጀክቶች እንዲታጠፉ አልተወሰነም እንዴ?
• ተወስኗል።
• ታዲያ ምንድነው የምትለው?
• ከበጀት ፖሊሲው ውጪ ያሉ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ነው፣ በዚህም ምክንያት...
• ቀጥል...
• እነዚህን ፕሮጀክቶች ለጊዜው ማቆም ካልተቻለ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚዘዋወረውን ገንዘብ መቆጣጠርና የዋጋ ግሽበቱን በሚፈለገው ልክ ማውረድ አዳጋች ነው።
• ታዲያ ለምን የውሳኔ ሐሳብ አታቀርቡም?
• እ...?
• ቆይ ከበጀት ፖሊሲው ውጪ እየተከናወኑ ያሉት የትኞቹ ፕሮጀክቶች ናቸው?
• ክቡር ሚኒስትር እነዚህም ፕሮጀክቶች አይጠቅሙም ማለቴ አይደለም።
• ገባኝ... ዋናውን ችግር ለመፍታት ቢዘገዩ ነው ያልከው፣ አይደለም?
• ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር።
• እኮ የትኞቹ ፕሮጀክቶች ናቸው።
• ክቡር ሚኒስትር ተናገር ካሉኝ እናገራለሁ።
• ተናገር እኮ ነው እያልኩህ ያለሁት፡፡
• እሺ አንደኛው ኮሪደር ልማቱ ነው።
• ምን? 
• ክቡር ሚኒስትር አይጠቅምም አላልኩም፣ ነገር ግን ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ እየተደረገበት ያለ በመላ አገሪቱ የሚካሄድ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።
• እሺ ከኮሪደር ሌላ ከበጀት ፖሊሲ ውጪ እየተካሄደ የሚገኝ ፕሮጀክት አለ?
• ሌላው ያው እርስዎ የሚከታተሉት ፕሮጀክት ነው። 
• የትኛው ፕሮጀክት ማለትህ ነው?
• ያ የምናውቀው ነዋ።
• ምን?
• አይጠቅምም ማለቴ አይደለም ክቡር ሚኒስትር።
• እና?
• የዋጋ ግሽበቱን መፍትሔ ይቅደም ከተባለ ብዬ ያነሳሁት ሐሳብ ነው። 
• ለዋጋ ግሽበት መፍትሔ ሳይሆን በእኔ ላይ ነው የመጣኸው?
• እ...?
• በዓይኔ ነው የመጣኸው፣ እናም…
• አቤት ክቡር ሚኒስትር?
• መፍትሔህን ይዘህ ውጣ!
65😁33👍16😢1
2025/07/13 23:31:38
Back to Top
HTML Embed Code: