Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
ውድ ኦርቶዶክሳዊ አንባብያን እነሆ
አርሴማን ጥሩልኝ
ተፈፀመ



በጣም ከወደዳችሁት= 1
ከወደዳችሁት = 2
ካልወደዳችሁት= 3
#ታኅሣሥ 19 በዓሉ ለቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት 🎉🌹

#ገብርኤል ማለት እግዚእ ወገብር ማለት ነው ። በዕለተ እሑድ መላእክት መኑ ፈጠረነ ሲሉ ዲያቢሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሉ ፈጥሮ ለማሳየት እጁን ከእሳት ከትቶ አቃጥሎት መላእክት በተረበሹ ጊዜ በያለንበት እንቁም ብሎ ያረጋጋቸው መላእክ ነው ። በዚህም ምክንያት ጌታ " ወበእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል ። ከዚህም በኃላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል ።

"በዚህች ዕለት አግብርተ እግዚአብሔር አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ከእቶን እሳት አድኗቸዋል ። አሜን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሆ ገብርኤል እኛንም ከጭንቅ ከመከራ ከዚህ ዓለም ስቃይ በክንፈ ረድኤቱ ከልሎ በምህረት ቸርነት ያስጎብኘን ። እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ገብርኤል በዓል አምላካችን በሰላም በጤና አደረሰን መልካም በዓል።
እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ::ሉቃ 1:19

ገብርኤል ሆይ፣ከጭንቅና ከመከራ ለማውጣት የተላክ መልአክ ነህና ሠለስቱ ደቂቅ በእሳት ጉድጓድ በተጣሉ ጊዜ ሁለቱ ክንፎችህን ጋርደህ ከመቃጠል እንዳዳንካቸው እኔንም አገልጋይህን በረድኤትህ ሀይል አድነኝ።
(መልክዓ ገብርኤል)
እንኳን አደረሳችሁ 🙏🙏
"መንገርስ ለአንቺ ነው መማፀን ወደ አንቺ ፤
ተስፍን ለምትቀጥይ ህልምን ለምትፈቺ።"

እመብርሃን እናቴ ጥላቻ ያቆሸሸውን ስግብግብነት የደፈነውን ኃጥአት ያጨለመውን ልባችንን አብሪልን።


🌹መልካምና ብሩህ ቀን❤️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከሚከተሉት ውስጥ የማይደገመዉ የቤተ ክርስቲያን ምሥጢር የቱ ነው?
Anonymous Quiz
15%
ጥምቀት
7%
ሜሮን
33%
ተክሊል
46%
ሁሉም
"ለዓለም ጨው ለራሴ አልጫ ሆንኩ ለዓለም ብርሃን ለራሴ ጨለማ ሆንኩ ከእውነተኛው ዳኛ ከጌታዬ ፊት ስቆም ምን እመልሳለሁ?"
''አቡነ ተክለሃይማኖት''

እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት አይነት ሐዋርያ ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ጊዜ ላይ እንገኛለን እባክህ አባታችን ደግመህ ተወለድልን።
እለተ አርብ የፍቅር ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ ስለ ሰው ልጆች ብሎ መስቀል ላይ የዋለበት ልክ ቀን እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን መስቀል ዓለም የተቀደሰበት ሰይጣን ያፈረበት ኋያላችን ክብራችንና ሕይወታችን ስለሆነ እንኮራበታለን፡፡
«የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኋይል ነዉና፡፡» 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡18


አቤቱ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበን🤲
ኃጢአት ጸሎት የማቋረጥ ውጤት ነው። እውነተኛ ጸሎት ኃጢአትን የማቆም ምልክት ነው። ሰው ኃጢአትን ልምዱ ካላደረገ በቀር እየጸለየ የሚበድል፣ ከአምላኩ ጋር እየተነጋገረ የሚያምጽ የለም። አዳም እጸ በለስን የቆረጠው ከአምላኩ ጋር የነበረውን ንግግር (ጸሎቱን) በማቋረጡ ነው። ይኸውም አዳምን ጠርቶ "ወዴት ነህ?" ባለው በፈላጊው ድምጽ ተረጋግጧል።

🌹መልካም ቀን ይሁንልን❤️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
'' መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤  ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።'' - ሉቃስ 2÷10

እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ🙏
ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ።

ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረው እርሱ ሕፃን ኾኗልና፡፡ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ። ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚኾን፣ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ፡፡ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ። ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት። ይህን ወዷልና፤ (ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ 66፥17)።

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኔታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ።
2025/01/08 11:59:11
Back to Top
HTML Embed Code: