ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
መዝሙር 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ² ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። ³ እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። ⁴ ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፥ ነገር ግን…
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“አምባዬና መጠጊያዬ አንተ ነህና ስለ ስምህ መንገዴን አቅና ምራኝም።”
— መዝሙር 31፥3
ለሰዎች አጋሩ🙏🙏
For Your #Profile
#profile #wallpaper #በዓል #Telegram #user
#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story
ለኦርቶዶክሳዊ Wallpaper ይቀላቀሉ👇🙏
https://www.tgoop.com/aserorthodoxwallpaper
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ 😊
https://www.tgoop.com/Ethiopian_Ortodoks

❤️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፫ 🙏
#አባ_ለትጹን
ሰኔ 17 ዳግመኛም ታላቁ አባት አባ ለትጹን አረፈ። ይህም አባት ከብህንሳ አገር ነበር ጐልማሳ በነበረ ጊዜም “ነፍሱን ሊያድናት የሚሻ ይጣላት ነፍሱን ስለ እኔ የጣላትም ያገኛታል ለዘላለም ሕይወትም ይጠብቃታል” የሚለውን በ #ቅዱስ_ወንጌል ውስጥ የተጻፈውን የሕያው ንጉሥን ቃል ሰማ ወዲያውኑ ልቡ ስለ #እግዚአብሔር ፍቅርና ስለ ዘላለማዊ ተድላ እንደ እሳት ነደደ።
#ቅዱስ_ቁርባንንም ተቀብሎ እስዋሕት ወደሚባል ገዳም ሔደ በጾም በጸሎትና በስግደት ታላቅ ተጋድሎን ያለ ማቋረጥ ይጋደል ጀመር ሰባት ሰባት ቀንም ይጾም ነበረ። የ #እግዚአብሔርም መልአክ ተገለጸለትና የምንኵስና ልብስን ያለብሰው ዘንድ ወደ አባ ኤስድሮስ እንዲሔድ አዘዘው እርሱም መልአኩ እንዳዘዘው ሔደ አባ ኤስድሮስም በልብሱና በአስኬማው ላይ አርባ ቀኖች ጸለየ ከዚያም በኋላ ልብሱንና አስኬማውን አለበሰው በገድል መጠመድን ጨመረ።
ከዚህም በኋላ በመምህሩ ፈቃድ ወጥቶ እየተጋ እየጾመና እየተጋደለ ብቻውን ኖረ። ከእርሱም አቅራቢያ የሆነ አንድ ገዳም ነበረ የገዳሙን መነኰሳትም ይጐበኛቸው ነበር። በአንዲት ዕለትም ወደዚያ ገዳም ሔደ አበ ምኔቱንም ታሞ ለሞት ደርሶ አገኘው መነኰሳቱም በዙሪያው ሆነው ያለቅሱ ነበር። አባ ለትጹንም የሰይጣን ሠራዊትን ከበውት ደስ ሲላቸው አያቸው።
አባ ለትጹንም አባት ሆይ በአንተ ላይ የሆነው ምንድን ነው ብሎ አበ ምኔቱን ጠየቀው እርሱም መነኰሳቱን ከአጠገቡ እንዲርቁ አዘዛቸው።
ከዚህም በኋላ ያደረገውን በደሉን ሊነግረው ጀመረ እንዲህም አለው ከእኔ አስቀድሞ እንደርሱ ያለ ማንም ያልሠራው ኃጢአትን ሠርቻለሁና አባቴ ሆይ በጸሎትህ አትርሳኝ እኔ ቅስና ልሾም ፈልጌ ባልሾሙኝ ጊዜ ወደ ሌላ አገር ሔድሁ ኤጲስቆጶሱም ቅስና ሹሞኛል ብዬ በድፍረት በቁርባኑ ላይ የምቀድስ ሆንኩ። ለጠላሁትም በቍርባኑ መሥዋዕት ውስጥ መርዝ አድርጌ አሰጠዋለሁ እርሱም ይሞታል ከእናቴም ጋራ ዐሥር ጊዜ ተኝቼ አለሁ ከእኔም ፀንሳ ለመውለድ በደረሰች ጊዜ ሥራይ አጠጥቼ ሕፃኑን በሆድዋ ውስጥ ገደልሁት ኃጢአቴ ብዙ ነው ተነግሮ አያልቅም። ከበጎ ሥራም ምንም ምን የሠራሁት የለም ነገር ግን በጸሎትህ አትርሳኝ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መውጫዬ ደርሷልና ወዲያውም በክፉ አሟሟት ሞተ ነፍሱንም አጋንንት ሲቀበሏትና በየራሱ በሆነ ሥቃይ ሲአሠቃይዋት አባ ለትጹን አያት። አባ ለትጹንም ልቅሶን አለቀሰ።
አባ ለትጹን “ስለ ወዳጆቹ ነፍሱን አሳልፎ የሚሰጥ ያለ ከሆነ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም” የሚለውን የ #ቅዱስ_ወንጌልን ቃል አሰበ። አባ ለትጹንም ስለዚህ ኃጥእ ሰው ነፍስ ክብር ይግባውና #ጌታችንን እየለመነ አምስት ጊዜ እስከሚሞት ሰውነቱን ሊአሠቃያት ጀመረ።
የመላእክት አለቃ #ቅዱስ_ሚካኤልም መጥቶ አስነሣውና እንዲህ አለው ስለዚያ ኃጢአተኛ ነፍስ ንፍስህን አትግደል ምሕረት አይገባውምና #እግዚአብሔር ዕውነት ፈራጅ ስለሆነ በደሉ አይሠረይለትም አባ ለትጹን ግን መሐሪ ይቅር ባይ ወደ ሆነ #እግዚአብሔር ስለዚያ ኃጢአተኛ እየለመነ ራሱን ማሠቃየት አልተወም።
ከዚህም በኋላ ራሱን በባሕር አስጥሞ ሞተ ያን ጊዜም ታላቅ ነጐድጓድ ሆነ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወርዶ በባሕሩ ዳር ተቀመጠ ከባሕርም አውጥቶ ከሞት ያድነው ዘንድ #ሚካኤልን አዘዘው እርሱም አድኖ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን ፊት አቆመው።
#ጌታችንም የመረጥሁህ ለትጹን ሆይ ኃጢአቱ እጅግ ብዙ ስለ ሆነ ከኃጢአተኞች ሁሉ በደል ስለሚከፋ ምሕረት ስለማይገባው ስለዚያ ኃጢአተኛ ብዙ ጊዜ ነፍስህን ለምን ትገድላለህ አለው። አባ ለትጹንም እንዲህ ብሎ መለሰ መሐሪና ይቅር ባይ #ጌታዬ_ፈጣሪዬ_ሆይ ያን ኃጢአተኛ ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ ያለዚያ ነፍሴን ከእርሱ ጋራ ወደ ሥቃይ ውሰዳት።
ከዚህም በኋላ #ጌታችን የዚያን ኃጥእ ነፍስ ያመጣት ዘንድ #ሚካኤልን አዘዘውና አመጣት በከበሩ እጆቹም ዳሠሣት እንዳልተፈጠረችም አደረጋት። ይቺ ነፍስ አፈር ትሁን እንጂ ለሥቃይ ወይም ለሕይወት አትሁን አለ። አባ ለትጹንም ስለ ይቅርታውና ቸርነቱ ገናናነት #መድኃኒታችንን ፈጽሞ አመሰገነው።
ከዚህም በኋላ #ጌታችን አባ ለትጹንን የመረጥሁህ ለትጹን ሆይ በዕውነት እነግርሃለሁ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ በስምህ መባ ለሚአስገባ ወይም የተራበ ለሚያበላ የተጠማ ለሚያጠጣ የተራቆተ ለሚያለብስ ወይም ገድልህን ለሚጽፍ እኔ የሁሉንም ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ ስማቸውንም በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ በጎ ዋጋቸውንም እሰጣቸዋለሁ #ጌታችንም ይህንን ብሎ ወደ ሰማያት ዐረገ።
ቅዱስ አባ ለትጹንም እጅግ ደስ አለው ወደ በዓቱም ተመልሶ እየተጋደለ ብዙ ዘመን ኖረ። #እግዚአብሔርንም አገለገለው። መልካም ገድሉንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በተጋዳይ በአባ ለትጹን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

የኅሊና ዳኛ
እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ኅሊና ውስጥ፣ ኹል ጊዜ ንቁና ትጉ የኾነ ዳኛ ያስቀመጠው ስለ ምንድን ነው ብለኅ ብትጠይቀኝ፣ ከሰው ወገን ይኽን የ'ኅሊና ዳኛ'ን የመሰለ፣ እንቅልፍ የለሽ ዳኛ ስለሌለ ነው ብዬ እመልስልሃለኹ፤ ዳግመኛም፣ የውጪ ዳኞች በገንዘብ፣ በውሸት በመደለል፣ የሐሰት ፍርድ እንዲሰጡ በማስፈራራት፣ እንዲኹም በሌሎች መጠነ ብዙ ምክንያቶች፣ ርቱዕ የኾነ (ያልተዛባ) ውሳኔአቸውን ሊያጣምሙ ይችላሉ፤ የ'ኅሊና ዳኛ'ን ግን በእነዚኽ በገለጽናቸው ምክንያቶች በምንም መንገድ የሚደለል አይደለም፤ ጉቦ ብንሰጠው፣ ልንዋሸው ብንሞክር፣ ብናስፈራራው፣ ሌላ ሌላም ብናደርግ እንኳ፣ ይኽ የ'ኅሊና ዳኛ' ለምናስበውና ለምንሠራው ኀጢአት ምንም ሳይጠመዝዝ እውነተኛ ፍርድን ይሰጣል፤ ኀጢአት የሠራ ሰው፣ ሌላ ሰው ባይወቅሰውም እንኳ፣ ርሱ ራሱ ራሱን ይወቅሳል፤ አንዴ ወይም ኹለቴ ብቻ አይደለም፣ መላ ዘመኑን እየደጋገመ ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ኅጢአት የሠራነው ከረዥም ዘመናት በፊት ሊኾን ይችላል፤ የኅሊናችን ዳኛ ግን ያን የሠራነው ጥፋት ፈጽሞ አይረሳውም።
የኅሊና ዳኛ ኀጢአት ከመሥራታችን በፊትም ይኹን በኋላ ምንም ሳይሸፋፍን በግልጽ ይወቅሰናል፡፡ በተለይ ደግሞ ከሠራነው በኋላ፡፡ ኀጢአት በምንሠራበት ሰዓት ግን ይኸን ዳኛ አጥርተን አንሰማውም፡፡ ይኸውም በምንሠራው ክፉ ሥራ ስለምንሰክር ነው፡፡ ኀጢአት መሥራታችንን ባቆምን ጊዜ ግን ወድያው የጸጸት ሽመሉን ይመዠልጣል፡፡ ይኽም በቀጥታ ምጥ ከያዛት ሴት ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ እርጉዝ ሴት ምጥ የያዛት ጊዜ እጅግ አስጨናቂ የኾነ ሕመም ይሰማታል፡፡ ከወለደች በኋላ ግን በቃላት ሊገለጽ የማይችል ዕረፍት ይሰማታል፡፡ በወለደችው ልጅ ታላቅ ሐሴት ይሰማታል፡፡ ኀጢአት ስንሠራ ግን ከዚኹ ተቃራኒ ነው፡፡ በሐሳብ የፀነስነውን ኀጢአት በግብር እስክንወልደው ድረስ “ደስታ" ይሰማናል፡፡ ከፉው ልጃችንን (ኀጢአታችንን) በግብር ከወለድነው በኋላ ግን በልጃችን ፊት ከፍተኛ ሐፍረት ይሰማናል፡፡ ምጥ ከያዛት ሴት በላይም ያሰቃየናል፡፡
ስለዚኽ ልጆቼ! ይኽን ከፉ መሻት ከመዠመርያ አንሥተን ከመቀበል እንከልከል፡፡ ከተቀበልነው እንኳ ገና ፍሬ ሳያፈራ ሳለ ከውስጣችን (በገቢር ሳንገልጥ) እንግደለው፡፡ ይኽን ማድረግ ሳንችል ቀርተን ልጃችንን በገቢር ከወለድነው ግን በንስሐና በዕንባ እንዲኹም ራሳችንን በመውቀስ እንግደለው፡፡
(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 49-50)
@Ethiopian_Ortodoks