Telegram Web
ወደ ቀብር ስፍራ ሲገቡ ወይም ለዝየራ ሲሄዱ የሚባል ዱዓእ!

ከቡረይዳ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: እንዲህ ይላል፦ ነቢዩ (ﷺ) ወደ መቃብር ስፍራ ስንሄድ እንዲህ እንድንል ያስተምሩን ነበር፦

﴿السَّلامُ علَيْكُم أهْلَ الدِّيارِ مِنَ المُؤْمِنِينَ والمُسْلِمِينَ، وإنّا، إنْ شاءَ اللهُ لَلاحِقُونَ، أسْأَلُ اللهَ لَنا ولَكُمُ العافِيَةَ﴾

“በዚህ መቃብር ውስጥ የምትገኙ ሙእሚኖችና ሙስሊሞች ሆይ! ሰላም ይስፈንባችሁ። እኛም በአላህ ፍቃድ እንከተላችኋለን። ለኛም ለናንተም ከአላህ ዘንድ ደህንነትን እጠይቅላችኋለው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 975



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
👍1
ሀሙስ ጥር 29/2017 ከመግሪብ እስከ ኢሻ በሀሰን እና ሁሰይን መስጂድ ሸጎሌ ባስ እስቴሽን አካባቢ #ተናፋቂው መጣ በሚል ርዕስ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃቹሀል። በአካባቢው እና በዙሪያው የምትገኙ ውድ እህቶቼ እና ውድ ወንድሞቼ ተጋብዛቹሀል።
አላህ በሰጠን ጤና እና ጊዜ በመልካም ቦታ እናሳልፍ።
👍52
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 0⃣6⃣ #ሻዕባን 1⃣4⃣4⃣6⃣
ከተውበት (ከንስሃ) አትቦዝን!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ لو أخطأْتُمْ حتى تَبْلُغَ خطاياكم السماءَ، ثُمَّ تُبْتُم لَتابَ اللهُ عليكم﴾

“ወንጀላችሁ ሰማይ የደረሰ ቢሆን እንኳ፣ ከዛም ተውበት (ንስሃ) ካደረጋችሁ አላህ ከናንተ ተውበታችሁን (ንስሃችሁን) ይቀበላችኋል።”

📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 5235




https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
በዚህ መልኩ መደረጉ ለአንተ ባይገባክም አማራጭ ግን የለንም ኡስታዙና
ለዱዓቶች ለተፅእኖ ፈጣሪዎች ለቅርብ ወዳጆቹ የቀረበ ጥሪ
በበርካታ መድረኮች ያለውን ውድ ጊዜ፣ ገንዘብና እውቀት ለኡማው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል እያገለገለ ያለው ወንድማችን ኡስታዝ ካሚል ጣሃ የሁላችንንም እገዛ ይፈልጋል።
ሙሉ ጊዜውን ከሰጠው የዳዕዋ ስራው ጎን ለጎን በግል ስራውም ሆነ ተቀጥሮ ለመስራት ቢሞክርም ጥሪቱን አሟጦ ተጠቅሞ በራሱ ገንዘብ ሳይቆም በዙሪያው ካሉ ወንድሞቹ ጭምር ከባድ እዳ ውስጥ ገብቷል።
በእዳ የደከመ ልቡን በዳእዋና በቂርዓት እያስታመመ አመታትን ታግሷል። አበዳሪዎችና በዙሪያው ያሉ ጥቂት ወንድሞች እንጅ ህመሙን የሚያውቅለት አንድም ሰው የለም። በመልካም ፈገግታው የደበቀው የውስጥ ሲቃ አለው።
የቤት ኪራይ መክፈል ተስኖት ከአዲስ አበባ ርካሽ ቤት ፍለጋ ወደ ሸገሯ ከታ ተሰዷል። ይህንንም በአንዳንድ ወንድሞች ጥረትና እገዛ የሚከፈል ነው። ምክንያቱም የእርሱ የዘወትር ጭንቀት ያ እዳ ነውና። በአንድ ጎን እዳውን ለመክፈል፤ በሌላ ወገን ልጆቹን ለማሳደግ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል።
ይህንን የሰሙ ወንድሞች እንቅልፍ ቢነሳቸው ሹራ አደረጉና ወደ ሚወደው ህዝብ ጉዳዩን እንውሰደው የሚል ድምዳሜ ላይ ተደረሰ። ይህንን ጉዳይ ሲያማክሩት ፍቃደኛ ሊሆን አልቻለም። የእርሱ ምክንያት «ዳእዋው ይጎዳል» የሚል ነው። የእኛ መልስ ደግሞ አንተና ቤተሰብህም ስትጎዱ ዳእዋውም ይጎዳል የሚል ነው። እናም ደፍረን መጥተናል።
ከእዳው ልናላቅቀው፤ ከተሰካም የቤቱን ችግር መላ እንለው ዘንድ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ 50 ሎሚ ለሀምሳ ሰው ጌጥ ነው በሚለው የኡስታዝን ችግርና ህመም ልንጋራው ፊታችሁ ቁመናል።
ኡስታዛችን ደስታህ በቅርቡ ይመለሳል ኢንሻ አላህ.
1000340185308
ንግድ ባንክ
👍9
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 0⃣7⃣  #ሻዕባን 1⃣4⃣4⃣6⃣
የአማኝ ምሳሌው 🌾

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مثلُ المؤمنِ مثلُ السنبلةِ، تميلُ أحيانًا، وتقومُ أحيانًا﴾

“የአማኝ ምሳሌው እንደ ስንዴ ዘለላ ነው። አንዳንዴ ዘንበል ይላል አንዳንዴ ደግሞ ይነሳል።”

📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 2284



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 0⃣8⃣ #ሻዕባን 1⃣4⃣4⃣6⃣
በጁምዓ ቀን ወደ መስጂድ ስትገባ ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ቢሆንም ሁለት ረከዓ መስገድ ይኖርብሃል!

ከጃቢር ቢን አብደላህ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: እንዲህ ይላል፦

﴿جَاءَ رَجُلٌ وَالنَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَخْطُبُ النَّاسَ يَوْمَ الْجُمُعَةِ، فَقَالَ : " أَصَلَّيْتَ يَا فُلَانُ ؟ " قَالَ : لَا، قَالَ : قُمْ فَارْكَعْ رَكْعَتَيْنِ﴾

“አንድ ሰው ነቢዩ (ﷺ) ለሰዎች ኹጥባ እያደረጉ ሳለ ወደ መስጂድ ገብቶ ተቀመጠ። እከሌ ሆይ ሰግደሃልን? አሉት። አልሰገድኩም አለ። ተነስ ሁለት ረከዓ ስገድ አሉት።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 930




https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 0⃣9⃣ #ቫዕባን 1⃣4⃣4⃣6⃣
🚩"ፍልስጤማውያን ተበድለዋል፣
ህዝባችን ሽንፈትን አያውቅም፣
ጭንቅላቱን ዝቅ አድርጎ አያውቅም።
🚩 እነሱን ለመርዳት የሚጥሩት ሐቀኛ ናቸው ።
🚩ጽዮናውያን በደለኞች ናቸው፣ እነሱን ዝም የሚል፣
ግፍቸውን የሚደግፍ፣ ከነሱ ጋር የሚተባበር፣ ግንኙነት የሚፈጥር፣ ከዚህ በደል እና ሐሰት ውስጥ ተካፋይ ነው።"
* #አዋድ_አል_ቀርኒ


Amir Mohammed



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
👍2
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 1⃣0⃣ #ሻዕባን 1⃣4⃣4⃣6⃣
አፈር እንጂ…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لَوْ كانَ لاِبْنِ آدَمَ وادٍ مِن ذَهَبٍ، أحَبَّ أنَّ له وادِيًا آخَرَ، ولَنْ يَمْلأَ فاهُ إلَّا التُّرابُ، واللَّهُ يَتُوبُ على مَن تابَ.﴾

“የአደም ልጅ አንድ ሸለቆ ወርቅ ቢኖረው ሁለተኛ እንዲኖረው መመኘቱ አይቀርም፡፡ አፉን ከአፈር ውጭ የሚሞላው ነገር የለም፡፡ አላህ ደግሞ የተውበተኞችን ተውበት ይቀበላል፡፡”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1048




https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 1⃣1⃣ #ሻዕባን 1⃣4⃣4⃣6⃣
ጥንቃቄ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تدْعوا على أنفُسِكم ولا تدعوا على أولادِكم، ولا تدْعوا على أموالكم، لا توافِقوا من اللهِ ساعةً يُسأَلُ فيها عطاءٌ، فيَستجيبُ لكم﴾

“በነፍሶቻችሁ ላይ በመጥፎ ነገር ዱአ አታድርጉ። በልጆቻችሁም ላይ ዱአ አታድርጉ። በገንዘባችሁም ላይ ዱአ አታድርጉ። አላህ የጠየቃችሁትን መቼ እሺ እንደሚልላችሁም ሆነ እንደሚቀበላችሁ አይታወቅምና።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 3009



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
2
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 1⃣2⃣ #ሻዕባን 1⃣4⃣4⃣6⃣
ልብህን ጠይቅ!

ከነውዋስ ኢብኑ ሰምዓን (رضي ﷲ عنه) ተይዞ፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿الْبِرُّ حُسْنُ الْخُلُقِ، وَالْإِثْمُ مَا حَاكَ فِي صَدْرِكَ، وَكَرِهْتَ أَنْ يَطَّلِعَ عَلَيْهِ النَّاسُ﴾

“በጎ ነገር ማለት መልካም ስነ-ምግባር ነው። ወንጀል ማለት በደረትህ ውስጥ የተመላለሰ እና ሰዎች በሱ ላይ ሆነህ ቢያዩህ የምትጠላው ነው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2553



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
👍1
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 1⃣3⃣ #ሻዕባን 1⃣4⃣4⃣6⃣
👍2
2025/07/13 18:47:29
Back to Top
HTML Embed Code: