Telegram Web
በፈጣሪ ስም ይቅርታችሁ ትድረሰን 🙏
✍️ደብረታቦር
══════◄✣••✥••✣►══════
ደብረታቦር ማለት በወይራ የተከበበ ተራራ ማለት ። ደብረታቦር ከጌታ ከዘጠኙ በዓላት አንዱ ነው። ወእምድኅረ ስሱ መዋዕል ነሥኦሙ እግዚእ ኢየሱስ ለጴጥሮስ ወለ ያዕቆብ ወለዮሐንስ እኍሁ ወአዕረጎሙ ደብረ ነዋኃ እንተ ባሕቲቶሙ ማቴ 17:-1 ከስድስተኛው ቀን በኃላ ወደ ጴጥሮስ፣ዮሐንስ፣ያዕቆብን ወደ ተራራ አወጣቸው ማለት በፍልጵስዩስ ከተማ የሰውን ልጅ ሰው ማን ይልዋል ብሎ ጠይቋቸው ዮሐንስ ነው የሚሉህ አሉዉ ኤልያስ ነው የሚሉህ አሉዉ እናተስ ማን ነው ትሉኛላችሁ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ የእግዚአብሔር አብ የባህይሪ ልጅ ነህ ቢለው በአንተ ቃል መሰረትነት ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን አንፃታለው።የሲኦል ደጆችም አይበረታቱባትም። ══════◄✣••✥••✣►══════
ነሐሴ 13 ከነቢያት መሴና ኤልያስን። ከሐዋርያት ያዕቆብ፣ጴጥሮስና ዮሐንስን ይዞዎ ካወጣቸው በኋላ ባህርየ መለኮቱን ቢገልጥባቸው ያዕቆብና ጴጥሮስ ወደቁዉ ሙሴም መቃብሬ ይሻለኛል አለ። ኤልያስም በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ተነጠቀ። ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ሲሆን ቢወድቁም አትፍሩ እኔ ነኝ አላቸው። ለምን ምስጥሩን በከተማ አላደረገውም ቢሉ በከተማ አድርጎት ቢሆን ምስጢር አፈሳ በሆነ ነበርና። ለምን በታቦር አደረገው ቢሉ ሐዋርያት በሲኖዶስ ታቦር ብለው አንስተውታል። ══════◄✣••✥••✣►══════
ትንቢት ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ ተብሎ ተነግሯል። ምሳሌም ባርቅ ሲሳራን ድል ነሥቶበታል። ጌታም በልበ ሐዋርያት ያደረውን ሰይጣን ድል ነስቶበታል። ከደናግል ኤልያስን ከመአስባን ሙሴ ማምጣቱ መንግሥተ ሰማያትን ማአስባንም ደናግልም እዲወርሳት ሲያጠይቅ ነው ። መልካም በዓል። ══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @eotc27 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
መልካም ወጣት ማለት 🤷
══════◄✣••✥••✣►══════
💁‍♂️በሆሆታ እና በዳንኪራ ወጣት አይገነባም። ወጣቱን ገና ከዩንቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ዘርግቶ ለሀገር እና ለወገን ከብሄር እና ጎጠኝነት የፀዳ እንክርዳድ ያልገባበት መልካም ዘርን ለሚያመርተው ማህበረ ቅዱሳን ታላቅ ክብር አለኝ። አለም እንዲህ ያሉትን ማህበራት አትወድም አለም ወርቅ እና ብሯን ምትሰጥህ ማንነትህን ከጣልክ ነው። ለዚህ ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትር ደረጃ የተንቆለጳጰሰውን ሀገር የተባለችውን ሀይማኖቱን ወጣቱን በብር እየደለለ ሚገዛውን ዬናታንን ማየት ነው።
══════◄✣••✥••✣►══════
🚫መልካም ወጣት በሚል ሰበብ ማህተብህን ምትበጥስ አንተ ሰው አስተውል ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ይልሀል " ባለጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና አጥብቃችሁ ተቃወሙት ፩ ጴጥ ፭
══════◄✣••✥••✣►══════
⚠️ብር ልስጥህ እምነትህን ካድ ፣ቤተክርስትያን ይቅርብህ አዳራሽ ና፣ፓስተር እገሌ ጋር ልውሰድህ ፣ ስራ አስገባሀለው ትዳር ታገኛለህ ፣ሲልክ አጥብቀህ ተቃወም።እመነኝ ብሩ ያልቃል አንተ ግን ከገባህ መውጫም የለህ ።እንደ ጨው ሟሙተህ ትቀራለህ። ከቀደመችው አባቶችህ ለተሰውባትለተሰደዱባት ለታረዱባት ከተዋህዶ በረት ሚለይህን ሁሉ ለይ። ይች አለም ምድራዊ ነች ታልፋለች ትመክናለች ።የማታልፈው ዘልዐለማዊ ርስት መንግስተ ሰማያትን ለስባሪ ሳንቲም ብለህ በምስር ወጥ እምነትህን እንዳታጣ አስተውል‼️የመጨረሻው ዘመን እንደሰረሰ አትዘንጋ‼️
══════◄✣••✥••✣►══════
🧠ታስታውሳለህ አይደል ሀዋርያት ጌታችንን ንገረን የመምጣትህ ምልክት ምንድን ነው ብለው ሲጠይቁት የመለሰላቸውን ማቴ 24 የጥፋት እርኩሰት በተቀደሰው ቦታ ላይ ስታዩ አስተውሉ ‼️ወንድሜ (እህቴ) እናስተውል ዛሬ በተቀደሰው ስፍራ ለይ እርኩሰት አለ።የይሁዳ ልጆች ካህናት ጌታችንን ደሙን ያፈሰሰበትን መስቀል ይዘው ፣የቅዱስ አባ እንጦንስ ቆብ ደፍተው ስለመለየት እና መገንጠል ይሰብኩናል ።አስተውል አስቀድሞ ጌታ ባይነግረን አልቆልን ነበር ግን እንደሚመጡ ነግሮናል መጥተዋልም ። እመነኝ ሀሳባቸው ምድራዊ ነው ሆዳቸው አምላካቸው ነው ከእነዚህ ደግሞ ራቅ ሽሽ።አንተ ግን የቀደመችውን መንገድ ታውቃታለህ የቅዱስ ያሬድ ሀገር ኑር።የተክለሀይማኖት የሰማዕታት ሀገር አለችህ። የጠላትን ወሬ አትስማ በተማርክበት ፀንተህ ኑር።
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️🙏

✍️አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ።

💁ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው። ወንጌላዊ ዮሐንስም፣ እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ።የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤ ታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕዐ ሕይወት ሥር ተቀምጦአየው። የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እን ዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው። እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት። ያን ጊዜም ከዕዐ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ። የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመለሱ።የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግልማርያም አማላጅነት ያማረን ። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ ፡ ማትያስ ፡ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር፤ ለዘለዓለሙ አሜን።

💝በዚችም ዕለት ዳግመኛ የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ አገር ወደ አገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው።የሥጋውም ፍልሰት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋ ፍልሰት ጋር አንድ ሁኗልና ስለዚህም እርሷን መው ደዱን የሚያውቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ በስሙ ለሚማፀኑየድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በኃያሉ ተጋዳይ በጊዮርጊስም ጸሎት በእኛ ላይ ምሕረት ይቅርታ ቸርነት ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።

💁‍♂️በዚችም ቀን የሶርያ መስፍን ጊጋር በሰማዕትነት ሞተ።ሰማዕት የሆነበትም ምክንያት ጌታችን ከእመቤታችን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋራ በተሰደደ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ሳለ ኀሮድስ ሰምቶ ከበው ይዘው ይገድሏቸው ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ ጊጋርም ጭፍሮች እንዲያገኙአቸው አሸሻቸው።ስለዚህም ኄሮድስ ተቆጣ ጊጋርንም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ሕዋሳቱንም ሁሉ ቆራረጠ። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦለት መታሰቢይውን ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት በሦስት አክሊሎችም ተጋረደ ሦስት አክሊላትን ተቀዳጀ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
🍀🍀🍀🍀🙏🙏🙏🙏🍀🍀🍀🍀══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
🗣ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል‼️🗣
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም::ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ::ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂️ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂️ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ (ኢሳ 38:5)
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነውበደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን ይላል መሐሪው (ሕዝ 18፥23)
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል:: እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: በጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን🙏🙏 ══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
#መልክአ_ተክለ_ሃይማኖት❤️💒✝️🙏🙏✝️

#ለሰኮናከ

#ተክለ ሃይማኖት ሆይ፤ በቁመት ብዛት እግርህ በመሠበሩ በደም ለተነከረ ሰኮናህ ሰላም እላለሁ፡፡
ቅዱሱ አባት ሆይ፤ ትዕግስትህ ፍጹም እንደ ኢዮብ ትዕግስት ነው እኮን፡፡ አባት ሆይ፤ ኖኅ ልጆቹ ሴምንና ያፌትን እንደባረካቸው አንተም በዓለሙ ሁሉ ያሉ ልጆችህን ደቀ መዛሙርትህን ባርካቸው፡፡

#ሰላም_ለከ

#ተክለ ሃይማኖት ሆይ፤ ይህን ዓለም ንቀህ አጥቅተህ የወንጌልን ፍለጋ ተከትለህ በረኻ ለገባኸው ለአንተ ሰላም እላለሁ፡፡

#ቅዱሱ አባት ሆይ፤ መሥዋዕተ ቁርባንህ ከአቤል መሥዋዕት ይልቅ እጅግ የሠመረ ነው፡፡
አባት ሆይ አባ አባ እያልኩ ስጠራህ ፈጥነህ ስማኝ፤ በላይ በሰማይም አለሁልህ በለኝ፡፡

#አቤቱ የተክለ ሃይማኖት አምላክ ሆይ፤ እኔን አገልጋይህን ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቀኝ ቸርነትህ ለሁልጊዜ አይለየኝ፡፡ በመዓልትና በሌሊት ቸር ጠባቂ መልአክ እዘዝልኝ፡፡
የቅዱሱን አባት የተክለ ሃይማኖትን በረከት አሳትፈኝ፤ ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ሠውረኝ ለዘላለሙ አሜን።

#እንኳን ለጻዲቁ አቡነ ተክለሃይማኖት አመታዊ የልደታቸው በዓል አደረሳችሁ።
🙏🙏🙏 #ኦርቶዶክስ_የሆንኩት_መርጬ_ሳይሆን_ተመርጬ_ነው #ኦረቶዶክስ_ተዋህዶ_የነበረች_ያለችና_ለዘላለም_የምትኖር_ነች_ #እንኳን_አደረሳችሁ_ውድ_የተዋህዶ_ልጆች #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ለዘለዓለም_ፀንታ_ትኑር #ኢትዮጵያ_በክብር_ለዘለዓለም_ትኑር #ተዋህዶ_ሀይማኖቴ_የጥትንት_ነሽ_እናትና_አባቴ_ማህተቤን_አልበጥስም_ትኖራለች_ለዘላለም
@Eotc27
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ ተሰጠ ።

መግለጫውን ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) የሠጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት; ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ : በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።

ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለዳ በተሰማው ሕገ ወጥ "ሢመተ ጳጳሳት" ጉዳይ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገወጥነት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ
:-
1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።
2. መንግሥት ክስተቱ በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
3. ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት በሀሣብና በጸሎት እንዲጠብቁ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ: EOTCTV ══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @won21 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
ኢንተርኔት ቢዘጋ በደወል እንግባባ!
በቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ዓይነት ደወል አደዋወሎች አሉ። ከእነዚህም መካከል አንዱ የአደጋ ጊዜ ደወል ነው።
                ••●◉ ✞ ◉●••
የአደጋ ጊዜ ደወል ያለ ማቋረጥ በተደጋጋሚ የሚደወል ሲሆን፣ ይህ ያለማቋረጥ የሚደረግ የደወል ድምፅ ከተሰማ ቤተ ክርስቲያን አደጋ ውስጥ ናት ማለት ነው። በመሆኑም በማንኛውም ሰአት ደወል ያለ ማቋረጥ በፍጥነት ከተደወለ ቤተ ክርስቲያን ችግር ገጥሟት እየጠራቻችሁ መሆኑን አውቃችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገስግሱ

                ••●◉ ✞ ◉●••
በር ሰብሮ የሚገባው ሽፍታ እንጂ የቤተክርስቲያን አባት አይደለም። የንፁሀንን ደም እረግጦ ወንበር ላይ የሚቀመጥ ፓለቲከኛ እንጂ ጳጳስ አይደለም"
                ••●◉ ✞ ◉●••
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
     ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot  🔊  @efr21    ⛪️
💒 @Geb19bot  🔊 @won21  ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💁‍♀️እምዬ " ተዋሕዶን " ሮጦ የቀደማት ፣ ተከራክሮ የረታት ማንም የለም። አንዳንዶች በእሳት አቃጥለው ፣ አንድደው ፤ ዶግ አመድ አድርገው ፤ አንዳንዶች በሰይፍ እና በስለት ከፍ ብለው አንገቷን ዝቅ ብለው ባቷን መትረው ለማጥፈት ሞክረዋል።አሁን ድርቡሹ መንግስት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ እንደቃጣዉ ማለት ነዉ።
••●◉ ✞ ◉●••
✍️አቃጣዮቿ ተቃጥለው ፤ አሳዳጆቿ ድራሻቸዉ ጠፍቶ ገዳዮቿ ሞተው ስም አጠራራቸው እስኪጠፋ ድረስ ተረስተዋል ። እሷ ግን ይኸው የገዳዮቿን ሰይፍና ካባ በክብር አስቀምጣ ለትውልድ እያስጎበኘች እንዳለች አለች።
••●◉ ✞ ◉●••
📖ወደፊትም ሙሽራዋ ክርስቶስ በክብር መጥቶ እስኪቀበላት ወደ እቅፉም እስኪያስገባት ድረስ እንዲሁ እንዳማረባት ፣ እንደፈካች ፣ እንዳበበች ትኖራለች።ምክንያቱም የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም ምሳሌ የፈጣሪ መናገሻ ከተማዉ ናትና ተስፋ አላት።
••●◉ ✞ ◉●••
❗️ይህ የኳስም ድጋፍ አይደለም አንድ የፓለቲካ ግለሰብ ለመደገፍም አይደለም ይህ የነብሳችን ማረፊያ የሀይማኖት ጉዳይ ነው የማህተብ ጉዳይ ነው። ማንም የቤተክርስቲያኗ ጥቃት ይመለከተኛል ያለ የስላሴን ልጅነት ያገኘ ሁሉ ዘመችሃዉን ይቀላቀል ። እምዬ ተዋህዶ ዳግም ትንሳኤዋን ያሳየን።በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ትመር እንደሆነ ምረር
••●◉ ✞ ◉●••
💁ሼር በማድረግ ለጓደኛ በየግሩፑ በተለያዩ ሶሻል ሚዲያ #ሼር በማድረግ ዘመቻውን ይቀላቀሉ !!!
••●◉ ✞ ◉●••
✍️አንድ_መንበር
✍️አንድ_ፓትርያርክ!
ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት ።
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @ ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
ማቅ የለበሰች ከተማ
               ••●◉ ✞ ◉●••
ከተማው እጅግ ያስጨንቃል! ሆድ ያባባል! ያዘነ ከተማ እንዴት ያለ እንደሆነ በአይናችን አይተናል። እንደዚህ ያለው ነገርስ በየትኛው ዘመን በየትስ ሀገር ተከናውኖ ይሆን? ከሌላ ፕላኔት የመጡ ባእዳን እንግዳ ፍጡራን የሆንን እስኪመል ድረስ ግራ ያጋባል! ሁሉም በጸጥታ ይተማል ! ሾፌሮች፣ ረዳቾች ፣ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች፣ የካፌ አስተናጋጅዎች ፣ የመንግሥት ሰተኞች ሁሉም ጥቁር ለብሰዋል ፤ በእጦቱ ምክንያት ጥቁር ልብስ የሌለው ፊቱ ጠቁሮ የአንገት መስቀሉን አውጥቶ ይጓዛል ፣ ጥቁር ልብስ የሌላቸው እህቶችና እናቶች ደግሞ ጥቁር ሻሽ ጣል አድርገዋል።
               ••●◉ ✞ ◉●••
አበያተ ክርስቲያናት ጥቁር ለብሰዋልና አዛዎንት አባቶችና እናቶች ይኸንን ዘመን ለምን አሳኸን እያሉ እግዚአብሔርን እየወቀሱ ያለቅሳሉ ። ሕጻናት በሆነው ነገር ግራ ተጋብተዋል! አንዳንድ ሙስሊምና ፕሮቴስታንት ኢትዮጵያውያን ጥቁር ለብሰዋል፣ ታላላቅ የሀገሪቱ የፓለቲካ ሰዎች ሳይቀሩ በሆነው ነገር እጅግ አዝነው ጥቁር ለብሰዋል። ቅስም የሚሰብር በደል ተፈጽሞአልና ያዘነ ሕዝብ ተገልጧል። ይህንን የሀዘን ትእይንት በምልአት ለመዘገብ ጠቢባንን ይሻል። ግን የሆነው ነገር ምንድነው ?በዚህች ሀገር የተከሰተው አሳዛኝ ግፍ እንዴት ያለ ነው?
                ••●◉ ✞ ◉●••
ብዙ አሰቃቂ ጦርነትን አሳልፈን በመቶ ሺህ ወገኖቻችንን አጥተናል! በርካታ የረሀብ ዘመንንም አስተናግደን በጅምላ ሞተናል፣እርዛትና የበሽታ ወረርሽኝ ተለይቶን አያውቅም በነዚህ ሁሉ ስናዝን ኖረናል ግን እንደ አሁኑ ጊዜ መሪር ሀዘን አጋጥሞን አያወቅም፤ ከተማና አገር ማቅ ለብሰው ሲያዝኑ አልታየም።
               ••●◉ ✞ ◉●••
ግን የሆነው ነገር ምንድነው ? ለሺ ዓመታት አገር ስታዝን አብራ የምታዝን ፣ ሀገር ስትቆስል አብራ የምትቆስል ፣ ሀገር ስትሰደድ አብራ የምትሰደድ ፣ ሀገር ስትደሰት አብራ የምትደሰት የአፍሪካ የነጻነት አርማ በሆነችው በጥንታዊቷና በአንጋፋዋ ቤተ ክርስቲያንና ልጆቿ ላይ ያ ሁሉ ውለታ ተዘንግቶ በ21ኛው ዘመን ሊደረግ የማይችል የአካል ልየታ በራሷ የፖለቲካ ሰዎች መደረጉ ነው ። የሰማይ አምላክ ይኸንን መሪር ሀዘንና ተጋድሎ አይቶ ኢትዮጵያን በቃሽ ይበላት! የሀዘንም መጨረሻ ያድርግላት! አሜን!
                ••●◉ ✞ ◉●••
✍️አንድ_መንበር
✍️አንድ_ፓትርያርክ!
ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት ።
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
     ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot  🔊  @efr21    ⛪️
💒 @Geb19bot  🔊 @eotc27   ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
Forwarded from የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️ (༒ ₩ōňđĩ€ Zēfñōte-Hïwõt ፮ ༒ً)
📖በትንሣኤሁ ቅድስት አግብኦ ለብእሲ ዳግመ ውስተ ገነት/ልዩ በሆነች መነሳቱ ሰውን እንደገና ወደ ገነትአገባው::ቅ/ ኤፍሬም
••●◉ ✞ ◉●••
🗣ይግብሩ በዓለ ሰማያት ይግብሩ በዓለ ደመናት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሃጺባ በደመ ክርስቶስ።ቅ/ያሬድ
••●◉ ✞ ◉●••
📖ሞቱን በሚመስል ሞት ከርሱ ጋር ከተባበርን ትንሳኤዉን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፡፡ ሮሜ 6፥5
••●◉ ✞ ◉●••
🙏በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር የመተሳሰብ ይሁንልን ፡፡እግዚአብሔር በህመም የአልጋ ቁራኛ የሆኑትን ምህረትን ይላክላቸው፡፡የጎደለንን እግዚአብሔር ይሙላልን።እንደ ሰደድ እሳት በአለም ዙሪያ የሰው ነፍስ እያጠፋ ያለውን የጊዜውን ክፍ መንፈስ በእግዚአብሔር በበረታው ክንዱ ተመቶ ከእግራችን ስር ያድርግልን።ስንዱዋን አመቤት እምዬ ተዋህዶ ቤታችንን እግዚአብሔር ይጠብቅልን።ባለ ቀሰተ ደመነዋ ሀገር ኢትዮጵያን ክፍዋን አያሳየን🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን።ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን።ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን ❗️❗️
💒💒💒💒💒💒
💒 @Geb19bot 📖 @eotc27
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21
💒💒💒💒💒💒💒
Forwarded from የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️ (ወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉ ༒ً🏃)
✍️ደብረታቦር
══════◄✣••✥••✣►══════
ደብረታቦር ማለት በወይራ የተከበበ ተራራ ማለት ። ደብረታቦር ከጌታ ከዘጠኙ በዓላት አንዱ ነው። ወእምድኅረ ስሱ መዋዕል ነሥኦሙ እግዚእ ኢየሱስ ለጴጥሮስ ወለ ያዕቆብ ወለዮሐንስ እኍሁ ወአዕረጎሙ ደብረ ነዋኃ እንተ ባሕቲቶሙ ማቴ 17:-1 ከስድስተኛው ቀን በኃላ ወደ ጴጥሮስ፣ዮሐንስ፣ያዕቆብን ወደ ተራራ አወጣቸው ማለት በፍልጵስዩስ ከተማ የሰውን ልጅ ሰው ማን ይልዋል ብሎ ጠይቋቸው ዮሐንስ ነው የሚሉህ አሉዉ ኤልያስ ነው የሚሉህ አሉዉ እናተስ ማን ነው ትሉኛላችሁ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ የእግዚአብሔር አብ የባህይሪ ልጅ ነህ ቢለው በአንተ ቃል መሰረትነት ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን አንፃታለው።የሲኦል ደጆችም አይበረታቱባትም። ══════◄✣••✥••✣►══════
ነሐሴ 13 ከነቢያት መሴና ኤልያስን። ከሐዋርያት ያዕቆብ፣ጴጥሮስና ዮሐንስን ይዞዎ ካወጣቸው በኋላ ባህርየ መለኮቱን ቢገልጥባቸው ያዕቆብና ጴጥሮስ ወደቁዉ ሙሴም መቃብሬ ይሻለኛል አለ። ኤልያስም በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ተነጠቀ። ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ሲሆን ቢወድቁም አትፍሩ እኔ ነኝ አላቸው። ለምን ምስጥሩን በከተማ አላደረገውም ቢሉ በከተማ አድርጎት ቢሆን ምስጢር አፈሳ በሆነ ነበርና። ለምን በታቦር አደረገው ቢሉ ሐዋርያት በሲኖዶስ ታቦር ብለው አንስተውታል። ══════◄✣••✥••✣►══════
ትንቢት ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ ተብሎ ተነግሯል። ምሳሌም ባርቅ ሲሳራን ድል ነሥቶበታል። ጌታም በልበ ሐዋርያት ያደረውን ሰይጣን ድል ነስቶበታል። ከደናግል ኤልያስን ከመአስባን ሙሴ ማምጣቱ መንግሥተ ሰማያትን ማአስባንም ደናግልም እዲወርሳት ሲያጠይቅ ነው ። መልካም በዓል። ══════◄✣••✥••✣►══════
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
❗️❗️❗️
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @efr21 ⛪️
💒 @Geb19bot 🔊 @eotc27 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
Forwarded from የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️ (༒ً✮ًٍٜ۪۪͜͡ ₩ōňđĩ€ Zēfñōte-Hïwõt ፮✮ًٍٜ۪۪͜͡༒ً)
🔊ምስጢረ ሥላሴ በብሉይ ኪዳን📖
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙏እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር፡ እግዚአብሔርም አለ፡- ሰውን በመልካችን እንደምሳሌአችን እንፍጠር ዘፍ 1፥26 እዚህ ላይ እግዚአብሔርም አለ ሲል አንድነቱ፣ እንፍጠር ሲል ከአንድ በላይ መሆኑን ግሱ /ቃሉ/ ያመለክታል፡፡በዚህ ንባብ እግዚአብሔር የሚለው ሥመ አምላክ ከአንድ በላይ የሆኑ አካላትን የሚመለከት መሆኑን ከተረዳን ስለ ሥላሴ ኃልወት በሌሎች የቅዱሳት መጻሕፍት  ከተጻፉት ምንባባት ጋር በማገናዘብ ይህ ጥቅስ ፍጹም አንድነቱንና ልዩ ሦስትነቱን እንደሚመሰክር በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ በዚህ አንቀጽ እንፍጠር በመልካችን እንደምሳሌያችን የሚለው ንግግር የሦስት ተነጋጋሪዎች ነው እንጂ ያንድ ተናጋሪ ቃል አይደለም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር፤ ሰውን እንፍጠር በመልካችን እንደምሳሌያችን፤ ሲል ሦስትነቱን ማስተማሩ ነው፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ሙሴም ይህን የእግዚአብሔርን ነገር ሲጽፍልን ሰውን እንፍጠር በመልካችን እንደ ምሳሌያችን ያለውን የብዙውን አነጋገር ለአንድ ሰጥቶ፤ እግዚአብሔር አለ፤ ብሎ መጻፉ በአካል ሦስት ሲሆን በባሕርይ በህልውና አንድ ስለሆነ በአንድ ቃል መናገሩን ከእግዚአብሔር ተረድቶ ለእኛ ሲያስረዳን ነው፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣እግዚአብሔርም ለሰው ልጅ ቃል ኪዳን ሲሰጥ፡እግዚአብሔር አምላክ አለ፡- እነሆ አዳም መልካሙንና ክፉውን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ዘፍ 3፥22 በማለት ባለቤቱን አንቀጽን አንድ፣ አሳቡን ዝርዝሩን የብዙ አድርጐ ይናገራል፡፡ እግዚአብሔር አለ ሲል አንድነቱን፣ «ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ» ሲል ደግሞ ከአንድ በላይ መሆኑን ያመለክታል፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ በማለቱ ሦስትነቱን ያስረዳል፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ምንአልባትም እግዚአብሔር አለ፤ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ የሚለው ቃል ሦስት ተነጋጋሪዎች በአንድ ቦታ ቢኖሩ አንዱ ሁለቱን ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ብሎ ሲነገር ከአንድ የበዙ ተናጋሪዎች ቃል መሆኑን ነው የሦስትነት ተነጋጋሪዎች መሆኑን ስለሚያስረዳ እግዚአብሔር ሦስት አካል መሆኑ በዚህ አነጋገር ግልጽ ነው፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖በባቢሎን ግንብ ወቅት፡ እግዚአብሔርም አለ፡- «ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው፡፡» ዘፍ 11፥6-8፡፡ «እግዚአብሔር አለ» ብሎ አንድነቱን፣ «ኑ እንውረድ» ብሎ ደግሞ ከአንድ በላይ መሆኑን ያመለክታል፡፡በዚህ አንቀጽ እግዚአብሔር ኑ እንውረድ ብሎ በመናገሩ ከሁለትነት የተለየ ሦስትነቱን ያስረዳል፡፡ መረጃውም ሦስት ተነጋጋሪዎች በአንድ ቦታ ሁነው ሲነጋገሩ ሦስተኛው ሁለቱን ኑ እንውረድ ሊላቸው ይችላል፤ ምክንያቱም ሁለት ሆነው ግን አንዱ ሁለተኛውን ና እንውረድ ቢለው እንጂ ኑ እንውረድ ሊለው ስለማይችል ነው፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
👆ከዚህ በላይ የተጠቀሱት የእግዚአብሔር ቃላት ተገልጸው ሲተረጐሙ፤ አካላዊ ልባቸው አብ አካላዊ ቃሉ ወልድንና አካላዊ ሕይወቱ (እስትንፋሱ) መንፈስ ቅዱስን፤ ሰውን እንፍጠር በመልካችን እንደ ምሳሌያችን፤ እነሆ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ እንዲሁም ኑ እንውረድ፤ ብሎ እንዳነጋገራቸው ይታወቃል፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂ለአብርሃም በተገለጠለት ጊዜ የአንድነቱና የሦስትነቱ ማስረጃ ሁነው የታመኑ እነዚህ ሦስቱ ቃላት ከአንድ የበዙ የሁለት ተነጋጋሪዎች፤ ከሁለትም የበዙ ተነጋጋሪዎች ቃላት መሆናቸው ይታወቃል እንጂ ከሦስት ያልበለጡ የሦስት ብቻ ተነጋጋሪዎች ቃላት እንደ ሆኑ ቃላቶቹ በማያሻማ ሁኔታ ስለማያስረዱ፤ እግዚአብሔር በእነዚህ አነጋገሮች ከሦስት ያልበዛ ሦስት አካላት ብቻ መሆኑ አይታወቅም የሚል አሳብም ቢነሳ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህም በሌላ አንቀጽ ይመልሳል፡፡ «በቀትርም ጊዜ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት አብርሃም ሦስት ሰዎችን በፊቱ ቆመው አየ» ዘፍ 18፥1-15 በማለት እግዚአብሔር አንድ መሆኑንና ሦስት አካል ያለው መሆኑን ወስኖ ያስረዳናል፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣የነቢያት ምስክርነት፡ እግዚአብሔር ለሙሴ በተገለጠለት ጊዜ «እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ነኝ» ዘፀ 3፥6 ሲል «አምላክ፣ አምላክ፣ አምላክ» ብሎ ሦስትነቱን፣ «እኔ እግዚአብሔር ነኝ» ብሎ ደግሞ አንድነቱን ገልጾ ተናግሯል፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊትም «የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች፣ በእግዚአብሔርም ቃል ሰማዮች ጸኑ፣ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ» በማለት የሥላሴን ምስጢር ተናግሯል (መዝ 32፥6)፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ነቢዩ ኢሳይያስም «ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በልዑል ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ አየሁት… ሱራፌልም ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያሉ ይጨሁ ነበር፡፡» ኢሳ 6፥1-8 በማለት ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ብሎ ሦስትነቱን፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአበሔር ብሎ ደግሞ አንድነቱን አይቶ መስክሯል፡፡ እንዲሁም “የጌታንም ድምፅ ‘ማንን እልካለሁ? ማንስ ወደዚያ ሕዝብ ይሄድልናል’ ሲል ሰማሁ” (ኢሳ 6፥8) በማለት ፍጹም አንድነቱንና ልዩ ሦስትነቱን አመልክቷል፡፡  
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙏የእግዚአብሔር ቀራቢዎች አገልጋዮች ሱራፌል በምስጋናቸው ሦስት ጊዜ ብቻ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ማለታቸው የሦስትነቱን አካላት መጥራታቸው ነው፤ እግዚአብሔር የሠራዊት ጌታ በማለት በአንድ ስም ጠርተው ምድር ሁሉ ምስጋናህን መልታለች በማለት ያንድ ተመስጋኝ ምስጋናን መስጠታቸው ሦስቱ አካላት አንድ ሕያው እግዚአብሔር፤ አንድ ገዥ፤አንድ አምላክ፤ አንድ ተመስጋኝ አምላክ መሆኑን መመስከራቸው ነው፡፡ ሱራፌልም በዚህ ምስጋናቸው እግዚአብሔር በአካል ከሦስትነት ያልበዛ ሦስት ብቻ እንደ ሆነ በባሕርይ በህልውና ከአንድነት ያልበዛ ሦስት አካል አንድ አምላክ ብቻ መሆኑን ይመሰክሩልናል፡፡
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ሚስጢረ ስላሴ በሐዲስ ኪዳን ይቀጥላል
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒
💒 @efr21 📖 @Geb19
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19
💒 @efr21 🔔 @Geb19
💒💒💒💒💒💒💒
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
https://www.tiktok.com/@wondie12/video/7394058131342445830?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7386261005708314117
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🔊ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን 🙏
✝️✝️✝️✝️✝️✝️
══════◄✣••✥••✣►══════
🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
══════◄✣••✥••✣►══════
💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
💒 @efr21 📖 @Geb19 ⛪️
💒 @Geb19bot🔊 @Geb19 ⛪️
💒 @efr21 🔔 @Geb19 ⛪️
💒💒💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
2025/01/10 07:55:16
Back to Top
HTML Embed Code: